Best analytics service

Add your telegram channel for

  • get advanced analytics
  • get more advertisers
  • find out the gender of subscriber

audience statistics ||ጥበብ ኢስላም||™

📩 አስተያየት ካላቹ እንዲሁም እንድናስተዋውቅሎ የሚፈልጉት ነገር ካለ  @tibeb_bot  ላይ ጠቁሙን! ☟︎︎︎ወደ  #YouTube  ቻናላችን☟︎︎︎  https://www.youtube.com/channel/UCDcX9sbuS4bhYuv3mfygPEg  
39 3900
~0
~0
0
تقييم تيليجرام العام
عالميًا
24 643المكان
من 78 777
187المكان
من 396
في الفئة
627المكان
من 2 333

جنس المشتركين

تعرف على عدد كل من المُشتركين الذّكور والإناث على القناة.
?%
?%

لغة الجمهور

معرفة توزيع المشتركين في القناة حسب اللغة
الروسية?%الإنجليزية?%العربيّة?%
نمو القناة
رسم توضيحيجدول
ي
أ
ش
س
help

جار تحميل البيانات

فترة تواجد المستخدم على القناة

اعرف كم من الوقت قضى المُشتركون على القناة.
حتى أسبوع?%المؤقتات القديمة?%حتى شهر?%
الزيادة في المُشتركين
رسم توضيحيجدول
ي
أ
ش
س
help

جار تحميل البيانات

Since the beginning of the war, more than 2000 civilians have been killed by Russian missiles, according to official data. Help us protect Ukrainians from missiles - provide max military assisstance to Ukraine #Ukraine. #StandWithUkraine
...┏━┅┅┄┄⟞ 😞 ⟝┄┄┉┉━┓...              ". ".           ፀሀፊ | አብድልቃድር ኑር ...┗━┅┅┄┄⟞ 😔 ⟝┄┄┉┉━┛...            .┏─━─━─━∞🍂∞━─━─━─┓. .  በ የተዘጋጀ .     🍂. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.🍂 .┗─━─━─━∞🍂∞━─━─━─┛.        .┏━━━━ • 🥀 • ━━━━┓.           [◦22◦]        .┗━━━━ • 🥀 • ━━━━┛. የ<እብደት መጀመሪያ> . . በሆነ አንድ ቀን ያለውን ሕመም መቋቋም ያቃተው ሰልማን ላይገኝ ወደሩቅ ቦታ ተጓዘ። ከሕይወት ጋር ግብግብ ሳይሰለቸውም አልቀረ መሠለኝ ሰው ወደማያገኘው ርቀት ሔደ። የተፈጠሩትን ባለማመኑና የጌታውን ስራ አምኖ ባለመቀበሉ እጅጉን ተጎዳ፣ እናም ክረምት ወጥቶ በጋ በገባበት አንድ ቀን ራሱን ለማጥፋት አንድ ጫካ ገባ። የሔደበት ሩቅ መንደር ውስጥ ማንም አያውቀውም እሱም ማንንም አያውቅም ነበር። ገመዱን ዛፉ ላይ አንጠልጥሎ ራሱን ለመስቀል ሞከረ፤ ሞት ናፈቀኝ ብሎ እስትንፋሱን ሊገታው ናፈቀ፣ <ገመድን ማን ሐራም አረገ> ሰልሚ ጥሎ ከመጥፋቱ በፊት በተደጋጋሚ አፉ ላይ የማይለይ ቃል ነበር። ንግግሩ ቅኔ ቢሆንም ጆሮ የሰጠው አልነበረም። ነገር ግን ለሰልማን የመሞቱ ምክንያት ሊሆን የነበረ ሰበብ ነበር። ፍላጎቱን አሳክቶ በገመዱ ጠለቀ ነገር ግነሸ ብዙ ሳይቆይ ድንገት ሆኖ በአቅራቢያው ሲጓዙ የነበሩ ሁለት ሰዎች መጡ፣ የተሰቀለው ሰዉ የቆየ እንዳልሆነና ከአፉ ሲወጣ የነበረው አረፋና የደምስሮቹ መወጣጠር ነብሱ እንዳልወጣች በመጠራጠር ከገመዱ በማላቀቅ ወደሆስፒታል ይዘውት ሄዱ። ሆስፒታል እስኪደርስ ግን ምንም አይነት ትንፋሽ የለም። ቢሆንም የደምስሩ እንቅስቃሴ ብርታት ሆኗቸው ወሰዱት። ሆስፒታል ገብቶ ተኛ፣ ሶስት ሰአት ሙሉ ምንም ሳይነቃ በዶክተሮች ርብርብ ቆየ፣ አራተኛ ሰአት ሊሞላ ደቂቃዎች ሲቆጠሩ ግን እንደ እብድ ባንኖ ተነሳ። ከዛ በኋላ ግን በጥንቃቄ ታክሞ ድጋሚ ነፍስ ዘርቶ ቆመ። ከሕመሙ ከነቃ በኋላ ግን ሰው ሸሸው። ጤነኛው እብድ ብለው አሸሹት፣ አንድ ሰው ወደራሱ ቢያስጠጋውም ሰልማን ግን እብድ የሚሉትን ቃል ሰምቶ ሳያብድ እንደ እብድ ሆነ። ** ሰልማን ነኝ ሰልማንነቴን አልካድኩም አልክድምም፤ በሌላ አለም የመጣው ሰልማን፣ እኔ ግን በነሱ አልፈርድም። ፈራጁ ይፋረዳቸው! ከዚህ በፊት አይተውት የማያውቁትን ሰው ድንገት ተሰቅሎ መመልከት ከሰማይ የወረደ እብድ ከማለት ውጪ ሌላ ምን ይበሉ፤ እንዴትስ አምነው ጤነኛ ነው ይበሉ፣ጤንነቴንስ እንዴት ይረዱ? ግን አይችሉም በስተመጨረሻ እብደቴን ያለምንም ማረጋገጫ አምነው መቀበል ነበረባቸው። እኔ ግን መኖሬን እና ዳግም ነፍስ መሆኔን አልወደድኩትም፣ ዳግም ከሕይወት ጋር መገናኘቴ አላስደሰተኝም፣ እያንዳንዱን ትንፋሼ ጠላሁት፣ ነብሴን ጠላኋት፣ ሰው መሆን ከረፋኝ፣እብድ መባሌ ጥሞኛል ተስማምቶኛል ግን ከልባቸው እብድ ነው ብለው ማሰባቸውን አልወደውም። ምክንያቱም ጤነኛ እብድ ስለሆንኩ። ሰልማን አዲስ ሰፈሩን ተቀላቅሎ ሁሉንም ተላመደ፣ ዋና የመተላለፊያ መንገድ አስባልት ላይ መኖሪያውን አደረገ። እብድ እያለ የሚገፋው ቢበዛም የሚወዱትም ብዙ ናቸው። እብድነቱን ቢያምኑም ተግባሩ የሚያሳዝናቸው ብዙ አሉ። በአጠገቡ ሲያልፉ የሳንቲም ሽርፍራፊዎችን እየወረወሩ የሚቀልቡት መንገደኞች አሉ። እሱ ግን ብዕሩን ይዞ ፅሁፉን ትልቅ ካርቶን ላይ ከማስፈር ውጪ አንገቱን ቀና አድርጎ ሰው አይቶ አያውቅም። እንደው ሲጠናበት ሳንቲሙን ለቃቅሞ አንዳች ነገር ገዝቶ ይጎርሳል፣ አልያም የሰፈር ወዳጆቹ ሳህን ሞልተው የሚያመጡትን ምግብ በልቶ ይኖራል። ሰው አይጎዳም ውስጡ ፍቅር አለ፣ ግን ጤነኛ እብድ ነው እያወቀ ይጎዳል እየተባለ ይፈራል። አለማበዴን ለማሳወቅ የት መሔድ ነበረብኝ፣ ለማንስ መናገር፣ ምንስ ማድረግ  ነበረብኝ?ስለእውነት ያበዱ እብዶች ግን ታድለዋል እብድነታቸውን ሰው በመደብደብ፣ የሚያደርጉትን ባለማወቅ እብደታቸውን ያስመሰክራሉ። አንዴ እብድ የተባለ ጤነኛ ሰው ግን አለማበዱን ለማረጋገጥ ምንም እድል የለውም። ግን ቆይ እብደት ከየት ነው ሚመጣው፤ ሳያብዱ ወይም እውነት አብደው የሚያመጡት ከየት ነው፤ ያንን ትክክለኛ እብደት እኔ እፈልገዋለሁ፣ የማደርገውን ሳላውቅ ሰውም የመጥላት ጥሜን ተወጥቼ ራስ ወዳድ መሆንን እናፍቃለሁ። የልቤን አድርሼና ልቤን አርክቼ ከጨረስኩ በኋላ እብድ ነው ብለው እንዲያልፉኝ እፈልጋለሁ፣ ግን እንዴት አድርጌ ስለእውነት ልበድ፤ የት ማን ጋር ሔጄ ልፈልግ? ትክክለኛ እብዶችን ከኔ የውሸት እብደት ጋር ልቀይራቸው እፈልጋለሁ ግን ተራ ፍላጎት ነበር። እብደት የት ነው ሚሸጠው ማነው ሚጠቁመኝ? ምን አደከመኝ ብቻ ራሴን በማወቅ እብድ መባል ስላሰኘኝ ሰው መደብደብ ነበረበኝ እና አውቆ አበድ መባልን ፈልጌ ሰው ወደኔ እንዳይቀርበኝ በማድረግ የ <እብደት መጀመሪያ> እቅድን ለራሴ አወጣሁ። ⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊ .┏━━━━ • 🍂 • ━━━━┓.    [°23°] ይቀጥላል .┗━━━━ • 🍂 • ━━━━┛. ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን! ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴ ╔╦══• •😞•🍂•😔 • •══╦╗              🍁        🍁 ╚╩══• •😞•🍂•😔 • •══╩╝         .↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴.          የኛን ግሩፕ ለመቀላቀል👇            . . የ ዩቲዩብ ቻናላችንን 👇👇ሰብስክራይብ ያድርጉ ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴ ይቀላቀሉን⇊                     ይቀላቀሉን⇊                         . ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴.                  For any comment👇                       
عرض المزيد ...
2 834
9
ይህ የሼኽ መሀመድ ሀሰናት ትምህርቶች የሚለቀቅበት ቻናል ነው የሼኽ መሀመድ ሀሰናት ወዳጆች 😍
1 487
1
✅ይህ የዶክተር ዛኪር ናይክ ሐዲሶች በአማርኛ በዐልይ ፕሮዳክሽን በጥራት ተተርጉሞ የሚቀርብበት ቻናል ነው ተቀላቀሉ
794
0
#አዲስ_ልብ_አንጠልጣይ_ታሪክ_ዛሬ መለቀቅ ተጀምሯል።🎉 በእውነተኛ ታሪክ የተመሰረተ 🥰 🥰 ታሪኩን ለማግኘት በማለት ማግኘት ይቻላል😘 ➥ ወሊሂ የ ውሸት ማስተዋወቅያ አይደለም። 😌 ሙስሊም አይዋሽም😌 🥳ማየት ማመን ነው 🥳
466
1
#አዲስ_ልብ_አንጠልጣይ_ታሪክ_ዛሬ መለቀቅ ተጀምሯል።🎉 በእውነተኛ ታሪክ የተመሰረተ 🥰 🥰 ታሪኩን ለማግኘት በማለት ማግኘት ይቻላል😘 ➥ ወሊሂ የ ውሸት ማስተዋወቅያ አይደለም። 😌 ሙስሊም አይዋሽም😌 🥳ማየት ማመን ነው 🥳
918
1
#አዲስ_ልብ_አንጠልጣይ_ታሪክ_ዛሬ መለቀቅ ተጀምሯል።🎉 በእውነተኛ ታሪክ የተመሰረተ 🥰 🥰 ታሪኩን ለማግኘት በማለት ማግኘት ይቻላል😘 ➥ ወሊሂ የ ውሸት ማስተዋወቅያ አይደለም። 😌 ሙስሊም አይዋሽም😌 🥳ማየት ማመን ነው 🥳
383
0
✅ይህ የዶክተር ዛኪር ናይክ ሐዲሶች በአማርኛ በዐልይ ፕሮዳክሽን በጥራት ተተርጉሞ የሚቀርብበት ቻናል ነው ተቀላቀሉ
599
0
አስተማሪ ታሪክ📚 አንድ ሀብታም ሰው በመስኮቱ በኩል ሲመለከት አንድ ድሃ ሰው ከአቧራ ማስቀመጫው ውስጥ አንድ ነገር ሲመርጥ አየ ... ኻሊቁ ይመስገን እኔ ድሃ አይደለሁም አለ። ድሃው ሰው ዞር ብሎ ሲመለከት እርቃኑን ሰው በመንገድ ላይ ሲሄድ አየ ... ጀሊሉ አመሰግናለሁ አላበድኩም አለ። እብዱ ሰው ወደ ፊት ተመለከተና
60
0
✅ይህ የዶክተር ዛኪር ናይክ ሐዲሶች በአማርኛ በዐልይ ፕሮዳክሽን በጥራት ተተርጉሞ የሚቀርብበት ቻናል ነው ተቀላቀሉ
1 583
2
አስተማሪ ታሪክ📚 አንድ ሀብታም ሰው በመስኮቱ በኩል ሲመለከት አንድ ድሃ ሰው ከአቧራ ማስቀመጫው ውስጥ አንድ ነገር ሲመርጥ አየ ... ኻሊቁ ይመስገን እኔ ድሃ አይደለሁም አለ። ድሃው ሰው ዞር ብሎ ሲመለከት እርቃኑን ሰው በመንገድ ላይ ሲሄድ አየ ... ጀሊሉ አመሰግናለሁ አላበድኩም አለ። እብዱ ሰው ወደ ፊት ተመለከተና
1 484
1
...┏━┅┅┄┄⟞ 😞 ⟝┄┄┉┉━┓...              ". ".           ፀሀፊ | አብድልቃድር ኑር ...┗━┅┅┄┄⟞ 😔 ⟝┄┄┉┉━┛...            .┏─━─━─━∞🍂∞━─━─━─┓. .  በ የተዘጋጀ .     🍂. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.🍂 .┗─━─━─━∞🍂∞━─━─━─┛.        .┏━━━━ • 🥀 • ━━━━┓.           [◦21◦]        .┗━━━━ • 🥀 • ━━━━┛. <ጤነኛው እብድ> ... ስለምን ሲባል 2 አመታትን ተቀማው? . . . ሁለት አመታትን በብቸኝነት አለም፣ በእብደት ጎዳና፣ በስቃይና ሕመም ግርፋት እየተቀጣው አለፍኩ። <<ምፅ ተመልከቱት ያን ሚስኪን ይቺ ዱንያ አባቱንና ወንድሙን ከአፈር አስገብታ እናቱንና ሌላ ወንድሙን አልጋ ላይ አስተኛች ዛሬ ደግሞ እሱን አሳበደችው>> ተብሎ የሚወራለት እብድ ተባልኩ። ማበድ? የምን ማበድ ፤ ስለምን እብደት ነው ሚያወሩት ፤ እኮ እኔን እብድ? አአ እብድ እንኳን አይደለሁም! ነው ወይስ እብድ እብደቱን አይቀበልም እንደሚባለው እየዋሸሁ ነው? ሰልማን አላበደም፣ ሰልማን ጤነኛ ነው፣  እንደ ድሮው ነው ምንም የተቀየረ ነገር የለም፣ ሰልማን ራሱን አያቅም፤ አቅሉን የሳተና እብደቱን አምኖ ያልተቀበለ እብድ ነው፣ በእብደትና በጤንነት ውስጥ ያለ ራሱን ያላወቀ እብድ፤ አይደለም ለሰው ለራሱም መሆን ያቃተው የብዕር ምርኮኛ፤ እብድ እብድ እብድ <እብድ?> ስለእውነት ስላቹ እኔ ግን አላበድኩም። ሰልማን ንፁህ ሰው ነው፣ ጤነኛ ነው፣ ያስባል፣ ሰልማን አይተገብርም፤ ሰልማን ፀሐፊ ነው፣ የመፃፍ ትርጉሙ ለራሱ ነው፤ሰልማን ለሰው እብድ ግን ለራሱ ጤነኛ ነው፤ እሱ ለሰው እንደ እብድ የታየ ግን ራሱን የሚያውቅ አዋቂ፣ እጁ ላይ ብዕርን ይዞ ካርቶን አይሉት ወረቀት ላይ የሚከትብ ፀሐፊ፣ አንገቱን አቀርቅሮ ትርጉም አልባ ፅሁፍን የሚፅፍ ቢሆንም ግን ለሱ ከባድ ትርጉም ያለው ፅሁፍን የሚፅፍ፣ ልቡ የዋህ ለሰዎች ግን ሰውን የሚጎዳ እብድ መስሎ አለ። እውነት እብደት ምንድነው? እብድ ሚባለውስ ምን አይነት ሰው ነው፣ እብድ እብደት ማበድ አበደ ቆይ ምንድናቸው? እውነት ማበድ መቆሸሽ ነው፣ማበድ ማለት ራስን መጣል ነው፣እብደት ማለት ለብቻ መሆን ነው፣ ማበድ ማለት መንገድ ላይ ወጥቶ መቀመጥ ነው፣ ማበድ ማለት ከሰው መራቅ ነው፣ እኮ ማበድ ማለት ፀጉር አጨንባሮ መበላሸት ነው፤ የተቀደደ ልብስ ማድረግ ነው፣ በሐዘን ምርቃና ማንባት ነው፣ ጎዳና ጥግ ተቀምጦ ለብቻ ማውራት ነው፣ ማበድ ማለት ከቤት ወጥቶ ከታመመ ሰው ጋር መቀላቀል ነው? ግን እብድ ማለት እብድ ሆስፒታል መግባትም አይደለም፣ እብድ ተብሎ መርፌ መወጋት እብድ አያስብልም፤ ሰው ስለሸሸኝ ብቻ እብድ ነኝ ማለት አይደለም። እብድ ተብሎ እጅን መታሠር እብድ አያስብልም፣ እብድ ተብሎ ለብቻ ወህኒ ውስጥ መወርወርም እብድ አያስብልም ኸላስ! እብድን ሚያሳብደው በሰዎች እብድ መባል ነው፣ እብድ እብድ ሆኖ ሚያብደውም እብድ ተብሎ ከአሳባጆች ጋር ሲቀላቅሉት ነው። ሳያብድ አበደ መባሉ ያሳብደዋል፣ አላበደማ! ጤነኛ ሆኖ ማበዱን ባለማመኑ ብቻ እብድ መባል ነበረበት? በፍፁም! ግን አላበድኩም ብሎ ለሰዉ ቢናገርስ ማን ይሰማዋል፤ አላበድኩም ቢል አው አላበድክም ይሉታል? ግን አይሉትም! እብድ በሞላበት አለም ላይ እሱ ግን ስለየቱም ግድ የለውም። <እብድ?> ስለእውነት ስላቹ እኔ አላበድኩም። እጄ ላይ አመታትን ያልነጠፈ ብዕር በመያዜ እንደ እብድ ካስቆጠረኝ እብደቱ የኔ ሳይሆን የነሱ ነው፤ አዎን እኔ አላበድኩም። ልቤ ላይ የማውቀው እውነታ አለኝ፣እብድ ሳልሆን እብድ ያስባለኝ ምክንያት አለ። ቆይ ቆይ ለብቻ መሳቅ ወይም ማልቀስስ ነዉ እብደት? ጎዳና ጠንቶ የተንኳተተ ልብስ መልበስ ነው እብደት? አይገርማቸውም ያበዱት ግን እነሱ ናቸው። እብድነታቸውን ሳያምኑ ያበዱ ትልቅ እብዶች፣ እኔ ልቤ ነው ያበደው ልቤ የሚለኝን ነገር አልሰማም። እውነት ነው ልቤ አብዷል ምክንያቱም እሱ የሚለኝን አንዳችንም ነገር አልሰማም። ሰውነቴና ድርጊቴ ከልቤ ጋር አብረው አብደዋል፣  ልብሴ ተጨምሮባቸው ጨርቁን የጣለ እብድ ብለው እያሙ ያሳሙኛል፣ ግን ማበድ ማለት ይህ አይደለም፤ አእምሮዬ በደንብ ይሰራል የሚያስበውን ያውቃል፣ ምን ማድረግ እንዳለበት አጣርቶ ይረዳል። አስተውላለሁ አገናዝባለሁ፣ ሰው እንደሚያስበው አስባለሁ፣ ምናልባት ሳልሻላቸውም አልቀርም መሠለኝ። ሳያብድ አበደ የሚልን ሰው ከእብድ በታች አላየውም፣ ከዛ ሰው በላይ ራሱን የሚያውቅ የለም ግን እነሱ ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው እንዲሉ ከኔ በላይ እናውቅሀለን እያሉ ገሚሱ እብድ ነው ገሚሱ ጤነኛ ነው እያሉ የማይሆን ተረት ይተርታሉ፣ ከዛ በተለየ <ጤነኛው እብድ> የሚሉኝም ነበሩ ግን በዛ እስማማለሁ። ምክንያቱም ጤነኛ ሆኜ በተግባሬ ብቻ ያበድኩ እብድ ስለሆንኩ። ለምን እብድ ተባልኩ? ⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊ .┏━━━━ • 🍂 • ━━━━┓.    [°22°] ይቀጥላል .┗━━━━ • 🍂 • ━━━━┛. ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን! ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴ ╔╦══• •😞•🍂•😔 • •══╦╗              🍁        🍁 ╚╩══• •😞•🍂•😔 • •══╩╝         .↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴.          የኛን ግሩፕ ለመቀላቀል👇            . . የ ዩቲዩብ ቻናላችንን 👇👇ሰብስክራይብ ያድርጉ ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴ ይቀላቀሉን⇊                     ይቀላቀሉን⇊                         . ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴.                  For any comment👇                       
عرض المزيد ...
5 387
18
✅ይህ የዶክተር ዛኪር ናይክ ሐዲሶች በአማርኛ በዐልይ ፕሮዳክሽን በጥራት ተተርጉሞ የሚቀርብበት ቻናል ነው ተቀላቀሉ
1 516
2
አስተማሪ ታሪክ📚 አንድ ሀብታም ሰው በመስኮቱ በኩል ሲመለከት አንድ ድሃ ሰው ከአቧራ ማስቀመጫው ውስጥ አንድ ነገር ሲመርጥ አየ ... ኻሊቁ ይመስገን እኔ ድሃ አይደለሁም አለ። ድሃው ሰው ዞር ብሎ ሲመለከት እርቃኑን ሰው በመንገድ ላይ ሲሄድ አየ ... ጀሊሉ አመሰግናለሁ አላበድኩም አለ። እብዱ ሰው ወደ ፊት ተመለከተና
1 447
1
﷽ ቻናሉ የ ዶ/ር ዛኪር ናይክን ክሪክሮች እና ደዕወዎችን ለዑማዉ በቀላሉ ለማድረስ ታስቦ የተጀመረ ነው ኢን ሻ አላህ ግቡን ይመታል ቢኢዝኒላህ join us 👇👇👇👇👇
962
1
ደብዳቤዉም እንዲህ ይላል. ...============================ውዴ የኔ ፍቅር የአይኔ ብሌን የህይወቴ አለኝታ አንዋሬ እንዴት ነህ፡፡ የእኔነቴ ትርጉም ነህ ..በቅፅበት ተዋውቀን ...ብዙ ደስታን ሰጠህኝ ግን አንዋሬ ደስታየን ገና እንደጀመርኩት ሳታስጨርሰኝ ጠፋህኝ የት ብየ ወደየት ሂጄ ልፈልግህ??? አይኖቼ አንተን በመጠበቅ ተራቡ አቅሜም ከዳኝ፡ ተስፋህ ቃልህ ግን እረዳኝ ቅርስ አድርጌ ያስኩት ፡፡ግን ምንም አልጎዳኝ እንደውም በጣም ጠቀመኝ ህይወቴን አበራልኝ ትልቅ ማስታወሻም ሰጠህኝ ፡፡ግን አንዋሬ እንደ እንጀራ እርበህኝ እንደውሀም ጠማህኝ ....... እዚህ ላይ ስደርስ አይኔ እምባ....
1 786
3
...┏━┅┅┄┄⟞ 😞 ⟝┄┄┉┉━┓...              ". ".           ፀሀፊ | አብድልቃድር ኑር ...┗━┅┅┄┄⟞ 😔 ⟝┄┄┉┉━┛...            .┏─━─━─━∞🍂∞━─━─━─┓. .  በ የተዘጋጀ .     🍂. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.🍂 .┗─━─━─━∞🍂∞━─━─━─┛.        .┏━━━━ • 🥀 • ━━━━┓.                [◦⓴◦]        .┗━━━━ • 🥀 • ━━━━┛. <ሌላ ሕይወት> ... ቀናት በእሽቅድድም ይሸሻሉ፤ ኡሚ በተፈጠረባት የጭንቀትና ድንጋጤ መአት እንዲሁም ሐዘን ምክንያት ታማ አልጋ ላይ ተኛች፣ ለወራት ኮማ ውስጥ ስለገባች በጣሙን ተጎዳች። ባባን ለመቅበርና ለመሸኘትም ሳትታደል ቀረች። የሕይወቷ ትርጉም የሆነውን የአመታት ባሏን ለመሸኘት አሻፈረኝ አለች፤ ውስጧ ላይ ከባድ ሕመም ይነበባል፣ ያላወጣችውና ያልተነፈሰችው የእሳት ነበልባል አለ ግን እንዴት አድርጋ ታውጣው፤ እንዴትስ ይርጋላት? ግን አትችልም አንድም ምክንያት የባባ አደራ አለ፣ ቢሆንም ግን እኛም ብንሆን አላስቻለንም ፊት ለፊታችን ላይ ስለተጋረጠው ከባድ የሕይወት ድቁሻ መላ ጠፍቶን እጅ አስረክበናል። ሰው መጥቶ ቢያፅናናንም የኛን ሕመም ግን የሚመልስ አንድም አብሽር አልነበረም። በዚህ አመት ብቻ በወራት ልዩነት ሁለት ሰዎችን ከምድር በታች መክተት እና ሁለት ሰዎችን አልጋ ላይ ማየት ከምንም በላይ መናገር የማይችሉት ህመም ነው። ከጉድም ቅጥ አልባ ጉድ፣ . . . ሁሉም ተበታተኖ ቤታችን ባዶ ሆኗል። <ሌላ ሕይወት> ተጀመረ። ሰው ወደቤት ቤቱ ሔደ፣ጭርታው አስፈራ፣ያኔ እኔ ጋር የነበረውን ሕመም ወላሂ በቃል ለመግለፅ አልችልም፣ሲመሽ ይቅርና ደንገዝገዝ ሲል ያመኝ ጀምሯል፣እሮሮዬን በምን መልኩ እንኳን ማውጣት እንዳለብኝ አላውቅም። ውስጤ የተቀጣጠለ ነገር ያለ ይመስል ታፍኗል። የታፈነውን እንዴት ማርጋት እንዳለብኝ ስለማላውቅ እዛው እነዳለሁ። የኔም የእህቶቼም ሕይወት ድብልቅልቁ ወጥቷል፣የማሒር ሕመም ከፍቷል፣ እንደውም ወርሐዊ ክፍያው አቅቶናል፣ ዶክተሮቹ ወደውጭ ሐገር መሔድ አለበት ብለዋል አልያ ግን እሱም የወንድሙና አባቱ እጣ እንደሚደርሰው ተነግሮናል፤ ግን ደግሞ ያለው ወጪ ከምንም በላይ ከባድ ነበረሰ፣ለኡሚ ሆስፒታል ለአልጋ የምንከፍለው በራሱ አንድ ችግር ሆኖብናል ግን ግዴታ ማሒር መሔድ ነበረበት። የሰው እጅን ከማየት በላይ ከባድ ነገር የትም የለም። በባባ እና ሰሚር መሞት ምክንያት ማሒርን ችላ ብንለውም ለዚህ ሁሉ ወራት ግን ምንም አዲስ የተቀየረ ነገር አልነበረም። እንዲህ የተለመደ የሕይወት አካል የሆነ ክስተት በእኛም ላይ ሲደርስ መረጋጋት እንዳለብን በፊት ሰሚር እንዲሁም ባባም ሲሞት አስረድቶናል። ማዕበል ይመጣል ልክ እንደመጣ ደግሞ ይሄዳል፤ ነፋስ ከየት እንደመጣ ሳናውቀው ወደ እኛ ይነፍሳል፣ ወደየት እንደሚሄድ ሳናውቀው ደግሞ ወደሌላ ቦታ ይነፍሳል። ምንአልባት የኛ ፈተና ነብስ መነጠቅ ቢሆንም ሌላው ሳይጨመርብን ገለል እንዲል ተማፀንን። አላህን አማረዋለሁ መኖር አይሉት መሞት ይሄን ያህል ስቃይ ለምን እያልኩ እጠይቀዋለሁ፣ሕመምም ሞትም ለምን ለኔ አልሆኑም እያልኩ እመኛለሁ፣ ከምንም በላይ ሰው አስጠላኝ፣ከዛ በላይ ራሴን ጠላሁ፣ከነዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ የሕይወትና የዱንያ ፈተና አንገሸገሸኝ። ገመድን ማን ሐራም አደረገው?! ማነው እንደወንጀል የቆጠረውው?! ለምን እንድሞት አይፈቀደልኝም? መብቴ አ እንዴ? መኖርን በቃኝ ብዬ ከጌታዬ ጋር መገናኘት አልችልም እንዴ? ተው ተይ እየተባባልን ከሕይወት ጋር መነታረክ ይብቃኝ ማለት ስህተት ነው እንዴ? የዱንያን ፈተና በዚሁ እዚሁ ልቋጨው ማለት ጥፋት ነው እንዴ? ግን ለኔ አይደለም ምክንያቱም ከዚህ በኋላ ማንም አያስቆመኝም፣ አልቻልኩም አቅቶኛል የቤተሰቤን ሲቃ በየቀኑ ማየት ደብሮኛል፣ ይህ ራስ ወዳድ ካስባለኝ አው ራስ ወዳድ ነኝ፤ ራስ ወዳዱማ ሰሚር ነው፣ ያ ሁሉ እንባ  እንደቅጠል ሲረግፍ ጥሎን የሔደ ክፉ፤ ራስ ወዳድማ ባባ ነው፣ በቁስል ላይ ቁስል ጨምሮብን አድምቶን የሔደው፤ ራስ ወዳዱማ ማሒር ነው፣ ለአመት ተጨነቁ ብሎ በድን የሆነው፤ ራስ ወዳድማ ኡሚ ናት፣ ስቃያችንን አይታ እንዳላየ አይኗን የከደነች፤ ሰብስባ ያላፅናናች፤ ታዲያ እኔ ከነሱ አንፃር ራስ ወዳድ ልባል እችላለሁ እንዴ? አይችልም። . . ጌታዬ ፈቅዶ በሰራው ስራ ለምን እያልኩ ከተኳረፍኩ ደቂቃና ሴኮንድ፤ሰአትና ወቅት፤ጊዜና ቀናት፤ወራቶችና አመታት ረገፉ፤ ብቸኝነቴንስ መምረጤ አንዴ መርጫለሁ ያየኝ ሰው በሙሉ ከንፈር የሚመጥለት አሳዛኝ፣ የነሱ ከንፈር መምጠጥ ለኔ ምን ሊበጀኝ? እዉነት ካዘኑልኝ ለምን ከአፈር የገቡትን ሰዎች መልሰውልኝ አያስደስቱኝም? እኮ ለምን ከአልጋ የሆኑትን ሰዎች አያስነሱልኝም? ካልሆነ ግን የነሱ ከንፈር መምጠጥ ኢምንት ከሟሽሟጠጥ በታች አልቆጥረውም። ⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊ .┏━━━━ • 🍂 • ━━━━┓.    [°21°] ይቀጥላል .┗━━━━ • 🍂 • ━━━━┛. ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን! ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴ ╔╦══• •😞•🍂•😔 • •══╦╗              🍁        🍁 ╚╩══• •😞•🍂•😔 • •══╩╝         .↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴.          የኛን ግሩፕ ለመቀላቀል👇            . . የ ዩቲዩብ ቻናላችንን 👇👇ሰብስክራይብ ያድርጉ ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴ ይቀላቀሉን⇊                     ይቀላቀሉን⇊                         . ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴.                  For any comment👇                       
عرض المزيد ...
5 973
19
﷽ ቻናሉ የ ዶ/ር ዛኪር ናይክን ክሪክሮች እና ደዕወዎችን ለዑማዉ በቀላሉ ለማድረስ ታስቦ የተጀመረ ነው ኢን ሻ አላህ ግቡን ይመታል ቢኢዝኒላህ join us 👇👇👇👇👇
355
0
ደብዳቤዉም እንዲህ ይላል. ...============================ውዴ የኔ ፍቅር የአይኔ ብሌን የህይወቴ አለኝታ አንዋሬ እንዴት ነህ፡፡ የእኔነቴ ትርጉም ነህ ..በቅፅበት ተዋውቀን ...ብዙ ደስታን ሰጠህኝ ግን አንዋሬ ደስታየን ገና እንደጀመርኩት ሳታስጨርሰኝ ጠፋህኝ የት ብየ ወደየት ሂጄ ልፈልግህ??? አይኖቼ አንተን በመጠበቅ ተራቡ አቅሜም ከዳኝ፡ ተስፋህ ቃልህ ግን እረዳኝ ቅርስ አድርጌ ያስኩት ፡፡ግን ምንም አልጎዳኝ እንደውም በጣም ጠቀመኝ ህይወቴን አበራልኝ ትልቅ ማስታወሻም ሰጠህኝ ፡፡ግን አንዋሬ እንደ እንጀራ እርበህኝ እንደውሀም ጠማህኝ ....... እዚህ ላይ ስደርስ አይኔ እምባ....
977
1
﷽ ቻናሉ የ ዶ/ር ዛኪር ናይክን ክሪክሮች እና ደዕወዎችን ለዑማዉ በቀላሉ ለማድረስ ታስቦ የተጀመረ ነው ኢን ሻ አላህ ግቡን ይመታል ቢኢዝኒላህ join us 👇👇👇👇👇
1 331
1
🚫ሀ ቂ ቃ ገ ራ ሚ ቻ ና ል🚫 ብዙዎች የመሰከሩለት💯 👌በአጭር ጊዜ ውስጥ ተወዳጅነትን ያፈራ ምርጥ ኢስላሚክ ቻናል ሙስሊም አይዋሽም ገብተው ይመስክሩ‼️ 👉ቁም ነገርና ቀልድ,ገራሚ ንግግሮች,ሀዲስ ና ትረካዎች✌️
2 309
0
﷽ ቻናሉ የ ዶ/ር ዛኪር ናይክን ክሪክሮች እና ደዕወዎችን ለዑማዉ በቀላሉ ለማድረስ ታስቦ የተጀመረ ነው ኢን ሻ አላህ ግቡን ይመታል ቢኢዝኒላህ join us 👇👇👇👇👇
1 526
2
...┏━┅┅┄┄⟞ 😞 ⟝┄┄┉┉━┓...              ". ".           ፀሀፊ | አብድልቃድር ኑር ...┗━┅┅┄┄⟞ 😔 ⟝┄┄┉┉━┛...            .┏─━─━─━∞🍂∞━─━─━─┓. .  በ የተዘጋጀ .     🍂. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.🍂 .┗─━─━─━∞🍂∞━─━─━─┛.        .┏━━━━ • 🥀 • ━━━━┓.           [◦⓳◦]        .┗━━━━ • 🥀 • ━━━━┛. <በእንቅርት ላይ. .> ... አንድ ሳምንት ደቂቃን መስሎ አለፈ፣ ዛሬ ዛሬን መስሎ ትናንት ሆነ። ሰሚር አፈር ከዋጠው 5 ወር ሞላ፣ ከውሸተኛው አለም ለቆ ከወጣ ወራቶች በራሪ ሆኑ። ባባና ማሒርም ሕይወት ያለዉ በድን ከሆኑ እነሆ አንድ አመት ከወራቶች ተቆጠሩ። አንዳንድ ጊዜ ሕይወት እንደ ማዕበል ነው፤ በሰላም ይሄዱ የነበሩ ነገሮች ልክ የተመካከሩ ይመስል በአንድ ላይ ይናጋሉ፣ የሁኔታዎች አልሳካ ማለት፣ ድንገተኛ ወጪዎች፣ የገንዘብ እጥረት፣ የጉዳዮች መጥመም፣ ድንገተኛ ሞት፤ የሰዎች ክህደት፣ ስጋትን የሚፈጥሩ ሁኔታዎች መከሰት፣ የጤንነት መቃወስ የሚጠቁሙ ምልክቶች ልክ እንደ ማዕበል በአንድ ላይ ይመጣሉ፡፡ . . . . .. በወራቶች ልዩነት ባባም ሰሚርን ተከትሎ ሔደ፣ የልጁን እድል ወስዶ ያለምንም እረፍት እንዲሁ ሔዶ እሱም ቀረብን። አንድ እንኳን ቃል ሳይሰጠን እሱም እንደሰሚር አያገባኝም የራሳቹ ጉዳይ ያለ ይመስል ሐዘናችንን ባልሰማ አለፎ ሄደ፤ <በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ> እንዲሉ በሰሚር ሐዘን የልባችን ሕመምና ቁስል ሳይሽር ባባ አመረቀዘብን፤ እሱ መጥቶ በሱ እንረፍ ስንል አላህ ሳይፈቅድ የሱንም ሩሕ እንዲወጣ ፈለገ። የቤቶች ምሰሶ ባንዴ ተናዱ፣ ሰሚር ቤተሰቦቼ እያለ ባባም ቤተሰቤ እያለ ሁለቱም በቅፅበታት የጎማ እራት ሆነው አረፉት። የሰሚር ቅፅበታዊ ሞት በመሆኑ ለቃሎቹና ማለት ስለፈለገው ነገር እድሉን አላገኘም፣ እንዲህ እንዲያ ብሎ የተናዘዘው አንድም ነገር የለም፤ ያ ነገር ቤተሰቤን አንገብግቦታል፣መመለስ የማይቻል ሆኖ አሳረረን፣ቃላትና አንደበትን ዘግቶ የማይወራ ቁስልን ፈጠረብን፣ ቢያንስ የመጨረሻ ቃሉንና ንግግሩን በሰማን ብለን ተመኘን፣ ከአንደበቱ የሚወጡት እያንዳንዷ ቃላቶችን መስማት ፈለግን፣ ድምፁን አልፎም ስስ ቁጣውን ናፈቅን ግን በጭራሽ የማይቻል ነገር ነውና እንዲሁ በሕይወት ያሉ ሟቾች እንደሆንን ተቀበልን። ስለባባ ሞት ምንም ማለት አልችልም በቃ ከትልቅ አፋፍ ላይ የተወረወሩ ቤተሰቦች ነው የሆንነው፤ ግን አንድ ነገር ትዝ ይለኛል፣ አእምሮዬ ውስጥ ተቀርፆ የተቀመጠ አንድ ትዉስታ አለ፣ መቼም የማይወጣ አንድ ነገር አለ፤ ላውጣው ብል እንኳን የማልችለውና መቃብሬ ድረስ አብሮኝ የሚወርድ አንድ የማልረሳው ትውስታ አለ። ባባ ወደአኼራ የመሔጃው ቀን የደረሰ ሰሞን እንዲሁ በትንሹ ነቅቶ ያወራ ነበር እናም ማውራት ሲያቅተዉና አፉ ሲተሳሰር በአይኑ እንባ ነበር የሚገልፅልን፣ ትንሽ መለስ ሲል ያወራናል እናም አብሽር አለን <<ምንም አትዘኑ ምንም እንዳልተፈጠረ ለማስመሰል ቢከብድም ከባድ ጊዜ ለኛ አዲስ አይደለም፣ግን ከዚህ በኋላም ፈተና እናንተ ላይ ብርቱ ነው፣ያን በጥበብ የማለፍ ግዴታ አለባቹ ከስራችን የሚመጡ ብዙ የኛ ዘሮች ይኖራሉ፣ዛሬ በእኔ መሞት የሐዘን ድንኳን ቢጣልም ነገ ደግሞ የደስታ ድንኳን ይጣላል፣ዛሬ እኔ ብሰናበትም ነገ አዲስ ልጅ ሰላምታ ሰጥቶ ይመጣል፣ዛሬ በኔ ሐዘን አይናቹ ቢያነባም አላህ ብሎ ነገ የደስታን እንባ ታነባላቹ። ከችግር በኋላ ድሎት አለ ተብለንም የለ ይህ ቀን ትዉስታ ሆኖ የሚያልፍበትና ያ ቀን ብላቹ የምታወሱበት ቀን ይመጣል። ይህን ቀን ትናንት የምትሉት ነገ ይሆናል፣ባባ ወይም ሰሚር ብላቹ አንዲት ዘለላ እንባን እንድታነቡ አልፈልግም አልያ ግን አላህ ምስክሬ ነው አዝንባቹዋለው። ሞት ሐቅ ያለና ለማንም የማይቀር ነገር ነው ሞት ለመልዕክተኛውም አልቀረላቸውምና ይህን ክስተት አማና አታክብዱት!። ሁሉንም ነገር በስርዐቱ እንዲሁም ሐዘናችሁን በልክ አድርጉት፣ባለፉ ትውስታዎችም በጭራሽ ራሳችሁን እንዳታሳዝኑ፣እኔ ከእናንተ አልተለየሁም አለሁ ያለሁትም በልባቹና በዱአቹ ውስጥ ነው። ነገ በጀነቱ አላህ ይሰበስበን ዘንድ ጠንካራ ሁኑ፣ይህ ለኛ ገና መለያየት አይደለም እውነተኛ መለያየት ማለት የጀነትና የጀሐነም ተብለን የተለያየን ቀን ነው፣ያ እንዳይሆን የናንተ ትእግስት ያስፈልጋል፣ሁሌም እንደ ድሮአችን ነገሮችን በሶብር አሳልፉ። ትዝ ባልናችሁ ሰአት ከዱአ ዉጪ ምንም አታድርጉ>> ብሎን ባባ ላይ ጣዕረ ሞት መጣ፤ አይኖቹ ሊከደኑ፣ምላሶቹ ተሳስረው ከአንደበቱ ሚወጡት ቃላቶች ሊገቱ ሰአቱ ተቆረጠ፤ ዱንያ ላይ የተሰጠው የቆይታ ጊዜ ዛሬና አሁን ሆኖ ከች አለ፤ የሆስፒታሉ ክፍል በሐዘን ሲቃ አስተጋባ፣ የአይኖቻችን እንባ ሳይደርቁ ሌላ እንባ ያዘሉ አይኖች ሆነው መጡ። ባባ ሰከራተል መውት ላይ መሆኑን ያወቅኩት ለኔ በኔ ደረጃ የመጀመሪያዬ ነበር፤ ያን እውነታ ባውቀውም ግን ባባ ሊሔድ እንደሆነ ሳስብ ውስጤ ተበጠበጠ፣ ከራሴ ጋር አይ አይሆንም እያልኩ ከሱ ጋር አወራለሁ፣ አይኖቹ ማየት ተስኗቸው ተከድነው እና ልሳኖቹ ተዘግተው ባባ እያልኩ እንደማይሰማኝ በመጠራጠር ባባ በአንደበትህ እንኳን ባይሆን በልብህ ሸሐዳን በል እያልኩት ላይመለስ ጥሎኝ ተሰናበተ። ⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊ .┏━━━━ • 🍂 • ━━━━┓.     [°⓴°] ይቀጥላል .┗━━━━ • 🍂 • ━━━━┛. ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን! ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴ ╔╦══• •😞•🍂•😔 • •══╦╗              🍁        🍁 ╚╩══• •😞•🍂•😔 • •══╩╝         .↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴.          የኛን ግሩፕ ለመቀላቀል👇            . . የ ዩቲዩብ ቻናላችንን 👇👇ሰብስክራይብ ያድርጉ ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴ ይቀላቀሉን⇊                     ይቀላቀሉን⇊                         . ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴.                  For any comment👇                       
عرض المزيد ...
7 610
21
﷽ ቻናሉ የ ዶ/ር ዛኪር ናይክን ክሪክሮች እና ደዕወዎችን ለዑማዉ በቀላሉ ለማድረስ ታስቦ የተጀመረ ነው ኢን ሻ አላህ ግቡን ይመታል ቢኢዝኒላህ join us 👇👇👇👇👇
428
2
እናቴ ሶላት ቁማ ሰው ገድሏታል ብሎ አለቀሰ ደነገጥኩኝ እናቴን ብቻ መሰለህ የገደለዉ? .እኔም ሌላ ማንን ገድሏል ??አልኩት .......ሌሎች ቤተሰቦችንም ገድሎ ከአገር ጠፋ .....ገዳዩን ስንከታተል ....ሳውዲ ገብቷል ብለውኝ ነዉ ወደ እዚህ የመጣሁት ወንድሜም ሪያድ አለ እሱም እኔም ገዳዩን እየፈለግነው ነው ብሎ ስቅስቅ ብሎ እያለቀሰ ነገረኝ ......እኔም አፅናናሁት ..ነገሩ ገባኝ ሰልሀዲን የእናቱን እና የዘመዶቹን ገዳይ ለመበቀል ሳዉዲ እንደመጣ ከንግግሩ ተረዳሁኝ ፡፡ ከዛም ሰልሀዲን ሰውየውን ለአላህ ተወው እሱ የስራውን ይሰጠዋል አንተ እሱን ብትበቀለዉ ሌላ ወንጀል ይሆንብሀል አልኩት ....ሰልሀዲንም ከዚህ ቡሀላ አልከታተለውም በአንተ የተነሳ ዲነል ኢስላምን አዉቂያለሁ ... ግን እሱን ለመበቀል ያለበትን ቦታ አልከታተልም ነገር ግን ፊትለፊት ካገኝሁት እጋደለዋለሁ አለኝ። እኔም እምባዉን እየጠረኩ አፅናናሁት በጣም የሚያሳዝን ነገር ነዉ የነገረኝ ... ሰልሀዲን በጣም የዋህም ነው፡፡
عرض المزيد ...
1 079
0
የሚሸጥ የYouTube Channel የሚፈልግ 4.340(4.3k) Subscriber ያለው (6k) እውነተኛ ገዢ ብቻ ከስር ባለው አድራሻ ያናግረኝ።👇                      
1 949
2
﷽ ቻናሉ የ ዶ/ር ዛኪር ናይክን ክሪክሮች እና ደዕወዎችን ለዑማዉ በቀላሉ ለማድረስ ታስቦ የተጀመረ ነው ኢን ሻ አላህ ግቡን ይመታል ቢኢዝኒላህ join us 👇👇👇👇👇
959
1
...┏━┅┅┄┄⟞ 😞 ⟝┄┄┉┉━┓...              ". ".           ፀሀፊ | አብድልቃድር ኑር ...┗━┅┅┄┄⟞ 😔 ⟝┄┄┉┉━┛...            .┏─━─━─━∞🍂∞━─━─━─┓. .  በ የተዘጋጀ .     🍂. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.🍂 .┗─━─━─━∞🍂∞━─━─━─┛.        .┏━━━━ • 🥀 • ━━━━┓.           [◦⓲◦]        .┗━━━━ • 🥀 • ━━━━┛. <ጥቅም አልባ እውነት> ... የሰውን ትርምስ በቃል መግለፅ ይከብዳል። ከደቂቃዎች በኋላ ለሚሸኘው ሰሚር ሁሉም እየተሯሯጠ ነው፣ ድጋሚ ላይታይ እየሔደ ነው፣አይን ያልከፈቱ ልጆቹን በጌታው ትዕዛዝ መሠረት ጆሮ ዳባ ብሏቸው ሊጓዝ ነው።የአይኑን ብሌን እናቱ ያለምንም መሠናበቻ እስከዘላለም ሊሠናበታት ነው፣ሳቁንና ደስታውን ብቻ የሚፈልገውን አባቱን ከድቶት ሊሔድ ነው። ኡሚ ራሷን መቆጣጠር አልቻለችም። ባለቤቱ አስያ የምትይዘውና የምትጨብጠው ጠፍቷት የሐዘን ሲቃ ታሰማለች፣ እህቶቼ እንዲሁም የነበረው ኸልቅ ያለማቋረጥ  እያነባ ነው። ግን እኔስ? ለምን እንደሆነ ባላውቅም ዝምታን መርጫለሁ፣ እጅጉን ጠልቄ አስባለሁ። ከሔድኩበት ስነቃ ከሰው ጋር እንደተቀላቀልኩ ብቻ ነው ትዝ የሚለኝ። የማይቆዩ አመታት፣እድሜ ልክ የማይኖሩ ብዙ ዘመናት፣ከተሰጠን ጊዜ በላይ አንዲትም ማለፍ የማንችልበት ክስተት፣ በሕይወታችን ላይ መጨረስና ማዝለቅ የማንችላቸው ጥቂት ጊዜያቶች ናቸው ያሉን። ማድረግ ልንሻቸው የምንፈልጋቸው እጅግ በጣም ብዙ ብዙ ውጥኖችና ሐሳቦችን መሸሽ፣አገባደን ሳንጨርስ የሕይወት ማገባደጃ ጊዜው መጥቶ ትንቅንቅ ፈጥሮ ከምድር የሚለየን ዱብዳ፣ ገና ጀመርን ብለን ስናስብ የጅማሮ እይታ እንኳን ሳይኖረው የሚያበቃበት፣የሕይወት እና የሞት ግብግብ፣የኔ ነው የኔ እያሉ ጠብ የሚፈጥሩበት፣ጠቡ ለኛ አንዲትም ጥቅም ሳይሰጥ የሚቀርበት፣ ከተባለበት ቀን ግን ፍንክች ሳይል ሳይወላወል ከች ብሎ ስጋችንን ከአጥንታችን የሚለያይበት ብርቱ ቀን አለ! ዋ ነብሴ ያን ቀን ፈራሁልሽ። . . . ዋይ ሰሚር ከቀብር ስር ወርዷል፣ ዱንያን ተሸጋግሮ አፈርን ተቀላቅሏል፣ የዱንያን ፈተና አልፎ ወደዋና ማለፊያው ተሸጋግሯል፣ የሞቀና የተደላደለውን ሕይወት ትቶ ከአፈር በታች ተገኝቷል። እስከመቼም መመለስ በማይችልበት መልኩ ለቆ ወጥቷል፣ ወደዛ አስፈሪ ወደሆነው ጨለማ አዘንብሏል፣ እነሆ ሰሚር ከናፈቀው ጌታው ጋር ተገናኝቷል። ሰውን ደም እንባ አስለቅሶና ልብን አቁስሎ ተሸኝቷል። ጉድ ነው እንዲሉ የተገኘው ኸልቅና እሱን የሸኘው ፍጡር ብዛት ለቁጥር ይከብዳል።የሉም ተብለው የነበሩ፣አይመጡም ተብለው የመጡና ጠፉ ተብለው የተገኙ ብዙ ሰዎች መጡ። ማነው ምንድነው ሳይል መጥቶ የሸኘውና እንባውን ዘርቶ የሔደው ሰው ብዛት ያስደነግጣል፣ ሕመሙ ከልጅ እስከሽማግሌ ዉስጥ ገብቶ እንባን አራጨ፣ ልብ ላይ ቁስል ጥሎ አለፈ። እሱ አፈር ውስጥ ከገባ በኋላ የወደደውን ሰው ብዛት ለመግለፅ ቃላት ይሰንፋሉ። ዱንያ ላይ በነበረበት ወቅት ያልነበሩ ብዙዎች ተገኙ። ግን እሱ በሕይወት እያለ የት ነህ ሳይሉ፣ሰው ሲርበው የሰውን ገፀባህሪ ተላብሰው ቀርበው ሰው እንዲጠግብ ማድረግ ሳይችሉ፣ አሞኛል ሲላቸው አስታማሚ ሆነው መቅረብ ሲያቅታቸው፣ቸገረኝ ሲል ንፁህ ልብ ሳይሰጡት፣ከበደኝ ሲል ወደጌታህ ተዋደቅ ብለው ያልሞሉት ሰዎች፣ትናንት ከፋኝ ሲላቸውና ብዙ ውጣውረዶች ላይ ሲባዝን አይተው ባላየ ያለፉት ሰዎች ዛሬ የመገኘታቸው ትርጉም ምንድነዉ? ዛሬ ከሱ ኋላ ኋላ የመሔዳቸው ጥቅም ምንድነው፣ ዛሬ ሰሚር በሌለበት ሰሚር ብለው መምጣታቸው ለሰሚር ምን ሊበጀው? ድሮስ የረፈደ ተውበት ምን ሊበጅ!? ለኔስ <ጥቅም አልባ እውነት>ነው የሆነብኝ። ከቀብር በኋላ የምናውቀውም የማናውቀውም የሰፈር ሰዉ በሙሉ እየመጣ አብሽር ይሉናል፣ ብዙ ቁምነገር አዘል ድንቅ ንግግሮችንም እንሰማለን። አንድ አባት ያሉት ንግግር ስሬን ነካው፣ ልቤ ደርሶ ከነከነኝ፣ <ሁሉም ነፍስ ሞትን ቀማሽ ናት> ብለዉ ነበር ያሉት ሰውየው፣ይህን ቃል የማውቀው ነገር ቢሆንም ዛሬ ግን እንደ አዲስ ቃል ሆኖብኝ እንደማብሰልሰል በሐሳብ ጠልቄ ገባሁበት። <<ሁሉም ነፍስ ሞትን ቀማሽ እንደሆነች ካመንን ታዲያ ለምን ሁሌ ለሞት አዲስ እንሆናለን፣ ለምን እንደነግጣለን? ስለምንረሳዎ ብቻ ነው! ምክንያቱ ግን እኛ ላይ እስኪመጣ እየጠበቅን ነው። አጠገቦቻችን ባሉ ሰዎች ላይ ካላየን በቀር አናስተውለውም። ኧረ እንደውም ጭራሽ ትዝ አይለን፤ ግን ያንን የመሞት እውነታ ካረጋገጥን ለምን አንዘጋጅም? የትም መሔጃ የሌላት ሚዳቋ ፊት ለፊቷ እየመጣ ካለው ግዙፍ አንበሳ ማምለጥ እንደማትችል አውቃ ስለመበላቷ ኢምንት ሳትጠረጥር አምና ተቀብላ እንዳረጋገጠችው ለምን እኛም የትም ማምለጫ እንደሌለን አንገነዘብም? በአይን ብቻ እስክናይ ለምን እንጠብቃለን፣ ጊዜያችን ሲደርስ ሩሃችንን ከነብሳችን ጎትተው የሚያወጡበት ቀን እንዳለ ለምን አናምንም፣ ለዛስ ለምን አንዘጋጅም፣ ሁሌ አዲስ ክስተት አድርገን የምናስበው ለምንድነው? የዱንያ ጊዜያችን አብቅቶ አዝራኢል ወደኛ መጥቶ ትንፋሻችንን ፀጥ የሚያደርግበት የሆነ ጊዜ እንዳለ ለምን አንረዳም?>> እያልኩ ከራሴ ጋር ሆኜ ራሴን እጠይቀዋለሁ ግን የሚያሳዝነው የሚመልስ ማንም አልነበረም። ⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊ .┏━━━━ • 🍂 • ━━━━┓. [°⓳°] ይቀጥላል .┗━━━━ • 🍂 • ━━━━┛. ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን! ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴ ╔╦══• •😞•🍂•😔 • •══╦╗              🍁        🍁 ╚╩══• •😞•🍂•😔 • •══╩╝         .↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴.          የኛን ግሩፕ ለመቀላቀል👇            . . የ ዩቲዩብ ቻናላችንን 👇👇ሰብስክራይብ ያድርጉ ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴ ይቀላቀሉን⇊                     ይቀላቀሉን⇊                         . ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴.                  For any comment👇                       
عرض المزيد ...
6 614
21
﷽ ቻናሉ የ ዶ/ር ዛኪር ናይክን ክሪክሮች እና ደዕወዎችን ለዑማዉ በቀላሉ ለማድረስ ታስቦ የተጀመረ ነው ኢን ሻ አላህ ግቡን ይመታል ቢኢዝኒላህ join us 👇👇👇👇👇
2
0
የሚሸጥ የYouTube Channel የሚፈልግ 4.340(4.3k) Subscriber ያለው (6k) እውነተኛ ገዢ ብቻ ከስር ባለው አድራሻ ያናግረኝ።👇                      
1
0
...┏━┅┅┄┄⟞ 😞 ⟝┄┄┉┉━┓...              ". ".           ፀሀፊ | አብድልቃድር ኑር ...┗━┅┅┄┄⟞ 😔 ⟝┄┄┉┉━┛...            .┏─━─━─━∞🍂∞━─━─━─┓. .  በ የተዘጋጀ .     🍂. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.🍂 .┗─━─━─━∞🍂∞━─━─━─┛.        .┏━━━━ • 🥀 • ━━━━┓.           [◦⓱◦]        .┗━━━━ • 🥀 • ━━━━┛. <የጠፋው ደም> ... ዶክተሩ ገና በሩን ከፍቶ ከመውጣቱ ኡሚ እግሩ ላይ ወድቃ ማልቀስ ጀመረች፤ <<አደራህን ዶክተር መጥፎ ዜና አታሰማን>> ብላ ለመነችው። እሷን በማንሳት ፈንታ እኛም አብረናት አለቀስን፣ የምሬት እንባዎች የኛ ይለያሉ። ከኛ አልፎ ብዙ ዶክተሮች ከኛ ጋር ሲያለቅሱ ነበር። ፈተናዎች ቢበረቱም አንድ ላይ ተያይዘን እናልፈዋለን ስንል ሌላ ከባድ ፈተናዎች ፊታችን ላይ ተደቀኑ። ይኖራል የተባለው ሞቶ፣ ይሞታል የተባለው ኖረ። የአላህ ስራ ድንቅ ነው፣ የሕይወት ገፅታ ድንቅ ነው፣ ትናንት ከሰሚር ጋር ሆነን ለባባና ማሒር እንዳላዘንን ዛሬ ግን ሕይወት ተቀይራ ለራሱ ለሰሚር እንድናዝን አደረገችን። <<ደም ያስፈልገናል>> ዶክተሩ ነበር ለባባ ደም እንደሚያስፈልገው ያሳወቀን፤ የባባ አይነት ደም ያለዉ እኛ ቤት ሰሚር ቢሆንም እሱ ግን የዘላለም እንቅልፍ ተኝቷል። ቢሆንም እኔም የባባ አይነት ደም ነበረኝ። <> አለ ዶክተሩ.. ሁላችንም እርስ በርስ ተያየን እኔ ብዬ ለዶክተሩ አሳወቅኩት ግን ያየኝ አስተያየት ግራ አጋባኝ። ትንሽ ቀጠን ያልኩና ደም ለመስጠት ባልሆንም ለአባቴ ደም መስጠት ካለብኝ ግን ሞቼም እንደምሰጥና ደም ስሬን ቀድጄ እንደማደርገው በምሬትና ለቅሶ  ነገርኳቸው ግን አይሆንም ተባለ። ካለኝ የሰውነት አቋም ጋር ደም ለመስጠት እንደማልችል ነገሩን። ቢሆንም ሌላ ሰው ማግኘት አልቻልንም፣  ከቤተሰባችን የኛ ቢመሳሰልም የሌሎቹም ተለያየ። ሆስፒታል የነበርነው ሁላችንም ተመረመርን ከመሐላችን O የደም አይነት ያለው ግን አንድ ሰው ብቻ ነበር። እሱም ተከራያችች አሕመድ ነው። <የጠፋው ደም> አሕመድ ጋር ተገኘ፤ የኛን ቤት ተከራይቶ ብዙ አመታት ኖሯል፣ አግብቶም የሞሸሩት እነኡሚ እንዲሁም እትዬ ዘምዘም ናቸው። ለኛ ከቤተሰባችንም በላይ ባለውለታችን ነው። እሱም ያለምንም ማመንታት እና ማንገራገር ደሙን ለባባ ሰጠ። . . ባባ ደም ከተሰጠው በኋላም ያለበት ሁኔታ እጅጉን አሳሳቢና ዳግም ሕይወት ዘርቶ ለመነሳት አዳጋች እንደሆነ ተነግሮናል። ነቅቷል ድኗል ብለን ደስታችንን ጠግበን ሳንጨርስ በሰአታት ውስጥ  ከባድ አደጋዎች ተፈጠሩብን። ቢሆንም ግን አላህ ሚፈትነው የሚወደውን ነውና በአላህ ላይ ብቻ ተስፋ አደረግን። ሰሚር ወንድሙንና አባቱን እንዲሁም ሙሉ ቤተሰቡን ለመታደግ ተንከራቷል፣ እኔ እስካለሁ ከአላህ እገዛ ጋር  ማንም ምንም አይሆንም ቢለንም ሕይወት ግን ከዛ በላይ እንዲቆይ አልፈለገችም። አላህ ቀኑን የፃፈው ለዛሬ ነውና ወደሱ ጠራው። ብዙ ሕልምና ሐሳቦቹን ሳያሳካ የዱንያ ጊዜዎችህ አብቅቷል ተባለ። የሰሚርን ጀናዛ ይዘን ወደቤት ሔድን። ሕዝቡ በእንባ ተራጨ፣ይይዝ ይጨብጠውን አጣ፣ ማመን አቅቷቸው ካላየነው አሉ፣ ያ ትንስ ልጅ .. ያ በብዙዎች ልብ ላይ የነበረው ሰሚር ዛሬ እስከመጨረሻ መሔዱ ሁሉንም አሳመመ። መመለስና መስማት ለማይችለው ሰሚር ጥያቄ፣መናገርና መንቀሳቀስ ለማይችል አካል የተግባር ጥያቄ ወደሰሚር ይሰነዘራሉ። መላ የሰፈሩ ሰው ቤታችንን እና ጊቢያችንን እንዲሁም አካባቢውን ሞልተውታል። 24 ሰአት ባልሞላ ሰአት ነገራቶች መቀያየራቸውና የነበሩት ነገሮች ሁሉ ወዳልነበረ ቦታ ሲዘበራረቁ የሕይወት ገፅታ ተንፀባረቀብኝ፤ ሳቅ እና ሐዘን፣ ሕመም እና ቁስል፣መሰበር፣ ሩቅ እና አሁን፣ጥያቄዎቹ እንዲሁም መልሶቹ፣ ያልተመለሱና መልስ ያጡ ጥያቄዎች እኮ ለምን በሰአታት ይሔ ሁሉ አደጋ? የማይመለሱ ቢሆኑም መልሱና ምክንያቱ ግን አላህ ነውና እንደገና በሕመም አለፍነው። በአንድም በኩል የሕይወት ትወና ነውና አምነን ለመቀበል ተገደድን። ** ህይወት እውነተኛ ጭንብሏ “ጀምሮ መጨረስ” ነው፡፡ ከእናታችን ማሕጸን ተወልደን የጀመርነው ይህ ሕይወታችን በትክክል ኖርነውም አልኖርነው አንድ ቀን ማብቃቱና መፈጸሙ አይቀርም፡፡ በዚህ የሕይወት ዘመናችን የሚገኙ ማናቸውም ነገሮች ለዚህ ሕግ ተገዢዎች ናቸው፡፡ የግል፣ የቤተሰብ፣ የጓደኝነት፣ የትምህርት፣ የፍቅር፣ የትዳር፣ የስራ፣ የንግድና የተለያዩ የሕይወት ዘርፎች ይጀመራሉ! ይጨረሳሉ! (ዶ/ር እዮብ ማሞ) የሚለው ንግግር ትዝ አለኝ። ሰሚር ግን ገና ጀምሮት እንደሔደ እንጂ ጨርሶት እንደሔደ አላስብም፤ ጀምሮ ሳይጨርስ ለቆ ሔዷል። ሁሉም ቦታ ቦታውን የያዘ ቢመስልም ገና የኛ ሕይወት ግን ምን ያህል አቀበት እንደሚጠበቀው ለመገመት አይከብድም። ⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊ .┏━━━━ • 🍂 • ━━━━┓. [°⓲°] ይቀጥላል .┗━━━━ • 🍂 • ━━━━┛. ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን! ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴ ╔╦══• •😞•🍂•😔 • •══╦╗              🍁        🍁 ╚╩══• •😞•🍂•😔 • •══╩╝         .↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴.          የኛን ግሩፕ ለመቀላቀል👇            . . የ ዩቲዩብ ቻናላችንን 👇👇ሰብስክራይብ ያድርጉ ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴ ይቀላቀሉን⇊                     ይቀላቀሉን⇊                         . ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴.                  For any comment👇                       
عرض المزيد ...
4 972
20
آخر تحديث بتاريخ: ١١.٠٧.٢٣
سياسة الخصوصية Telemetrio