Best analytics service

Add your telegram channel for

  • get advanced analytics
  • get more advertisers
  • find out the gender of subscriber
Channel location and language

audience statistics Ethio telecom

The first Telecom operator in Ethiopia  https://t.me/EthiotelecomChatBot  
367 164-138
~33 371
~5
11.62%
Telegram general rating
Globally
2 596place
of 78 777
6place
of 396
In category
49place
of 1 396

Subscribers gender

Find out how many male and female subscibers you have on the channel.
?%
?%

Audience language

Find out the distribution of channel subscribers by language
Russian?%English?%Arabic?%
Subscribers count
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

User lifetime on the channel

Find out how long subscribers stay on the channel.
Up to a week?%Old Timers?%Up to a month?%
Subscribers gain
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

Since the beginning of the war, more than 2000 civilians have been killed by Russian missiles, according to official data. Help us protect Ukrainians from missiles - provide max military assisstance to Ukraine #Ukraine. #StandWithUkraine
ኩባንያችን አዲስና አካታች የዲጂታል ስነምህዳር ለመገንባት በሚያደርገው ጥረት ምርትና አገልግሎታቸውን በአጭር ጊዜ Time To Market (TTM) ተደራሽ ለማድረግ የሚፈልጉ አጋር ድርጅቶች ከቴሌብር ሱፐርአፕ ጋር ሲስተሞቻቸውን በፍጥነት ለማስተሳሰር (to integrate) የሲስተም ሙከራ የሚያከናውኑበት የዴቨሎፐርስ ፖርታል አዘጋጅቶ በይፋ አስጀመረ፡፡ የዴቨሎፐርስ ፖርታሉ በዋነኛነት የአጋር ድርጅቶች ሲስተም ወደ ዋናው ቴሌብር ሲስተም ከመተሳሰሩ በፊት በተለየ የሙከራ ቦታ ላይ (sandbox environment) የኢንተግሬሽን ሙከራ ለማከናወን ያስችላል፡፡ አገልግሎቱ ከሶፍትዌር ዴቨሎፕመንት፣ የሲስተም መፈተሻ እና የትግበራ ቦታ በተጨማሪ ለዴቨሎፐሮች ዶክመንቴሽኖች፣ መመሪያዎች፣ የቪዲዮ ቱቶሪያሎች፣ የኮድ ናሙናዎች፣ የኤፒአይ ማጣቀሻዎች እና ሌሎች አጋዥ መርጃ መሳሪያዎች ያካተተ ነው፡፡ ፖርታሉ ዴቨሎፐሮች ከኩባንያችን ሲስተሞች ጋር በፍጥነት እንዲላመዱ እና ክህሎት በመጋራት ደረጃቸውን የጠበቁ በርካታ ችግር ፈቺ የፈጠራ ስራዎች እንዲያፈልቁ ከማስቻሉ በተጨማሪ የኦንላይን ማህበረሰብ በመፍጠር የስነምህዳሩን ተደራሽነት ይጨምራል ብለን እናምናለን፡፡ የዴቨሎፐርስ ፖርታሉን ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጠቀሙ!
Show more ...
1
0
ኩባንያችን በዛሬው ዕለት የዲጂታል ሕይወትን በማቅለል እልፍ ጉዳይ በአንድ መተግበሪያ መከወን በሚያስችለው ቴሌብር ሱፐርአፕ ደንበኞች ከመገበያየት እና ገንዘብ ከማስተላለፍ ባሻገር መረጃን በነጻ በመለዋወጥ ማህበራዊ ግንኙነታቸውን እና ቢዝነሳቸውን የሚያጠናክሩበት ቴሌብር ኢንጌጅ የተሰኘ አገልግሎት አስጀመረ፡፡ አዲሱ ቴሌብር ኢንጌጅ የቢዝነስ እና ግለሰብ ደንበኞች ያለምንም ተጨማሪ የኢንተርኔት ክፍያ ለተናጠል ወይም ለጋራ የጽሁፍ፣ የፎቶ፣ ድምጽ፣ ቪዲዮ እና ፋይሎችን ለማጋራት የሚያስችል ሲሆን ከዚህም ባሻገር ለበዓል ወይም ለተለያዩ ማህበራዊ ሁነቶች የተናጠል ወይም የቡድን መልካም ምኞት መልእክት ከገንዘብ ስጦታ ጋር መላክ የሚያስችላቸውን አዲስ ገጽታ አካቷል፡፡ በተጨማሪም በጭውውቶች ወቅት ገንዘብ ለመጠየቅ፣ ለመላክ እና ለመቀበል፣ ቢል ለማጋራት እንዲሁም ጥቅል ወይም የአየር ሰዓት መግዛትን ጨምሮ በርካታ የዲጂታል አገልግሎቶችን በአንድ መተግበሪያ እንዲያከናውኑ ያስችላል፡፡ ኩባንያችን ለክቡራን ደንበኞቹ አዳዲስ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አማራጮችን በማስተዋወቅ የቢዝነስ ተሞክሮአቸው እና የዕለት ተዕለት ኑሮአቸው ላይ ተጨማሪ ምቾት እና ቅልጥፍና በመጨመር ለዲጂታል ኢትዮጵያ እውን መሆን ሁሉን አቀፍ ጥረት ማድረጉን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ለተጨማሪ ማስፈንጠሪያውን ይጠቀሙ፡፡
Show more ...
1
0
በኦክሽን ኢትዮጵያ ድረገጽ የሚቀርቡ ጨረታዎችን ለመጫረት ወይም ማጫረት ሲያሻዎ ክፍያዎን በቴሌብር በቀላሉ ይፈጽሙ! ቴሌብር - ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
11 585
15
መልካም የሥራ ሳምንት !
6 734
2
መልካም የእረፍት ቀን! ወዳጅ ዘመድዎን በ 35 ሳንቲም ብቻ ሃሎ ይበሉ !
13 651
10
የቴክኖሎጂ አጋራችን ሁዋዌ ቴክኖሎጂስ የአፍሪካ ክፍለ አህጉር ኃላፊዎች ልኡካን ቡድን በዛሬው ዕለት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚገኘውን የኩባንያችንን የኤክስፒሪየንስ ማዕከል ጎበኘ፡፡ ልዑካን ቡድኑ በማዕከሉ የሀገራችንን የቴሌኮም ታሪካዊ ጉዞ አሁን እስከደረሰበት የእድገት ደረጃ የሚያመላክቱ ቴክኖሎጂዎችን የጎበኙ ሲሆን፣ የስማርት ግብርና፣ ትምህርት፣ ማዕድን ልማትን እና ቱሪዝም የመሳሰሉት የስማርት ሶሉሽኖች ለሀገራችን ዲጂታል ኢኮኖሚ ይዞት የሚመጣው ትሩፋት ላይ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡ የልዑካን ቡድኑ በኤክስፒሪየንስ ማዕከሉ በቀረቡት የዲጂታል ሶሉሽኖች እና በአመራሩ ብቃት መደነቃቸውን የገለጹ ሲሆን ኩባንያችን ለዲጂታል ኢትዮጵያ እውን መሆን እየተጫወተ ያለው ሚና ለሌሎች አፍሪካ ሀገራት አርአያ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡
Show more ...
5 359
0
ሚያዝያን ለመቄዶንያ! በዚህ ወር በማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችን በሚቀላቀሉ አዲስ ተከታዮች (Followers) ብዛት ልክ 30 ብር እንዲሁም በሚጋሩ ልጥፎች (Share) ልክ 10 ብር ለመቄዶንያ አረጋዊያን እና ህሙማን መርጃ ማዕከል እንለግሳለን! እርስዎም ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይከተሉ፤ ፖስቶቻችንን ያጋሩ፤ ለወገን ድጋፍ ይተባበሩ! | | | | | | ዘላቂ የጋራ ማኅበራዊ ኃላፊነት ለወገን ብሩህ ተስፋ!
6 240
3
በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ አብዱራህማን ኢድ ጣሂር የተመራ የከፍተኛ ኃላፊዎች ልኡካን ቡድን በዛሬው ዕለት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚገኘውን የኩባንያችንን የኤክስፒሪየንስ ማዕከል ጎበኘ፡፡ ለልዑካን ቡድኑ በማዕከሉ በቀረበው ዓውደ-ርዕይ የሀገራችንን የቴሌኮም አገልግሎት ጉዞ እንዲሁም ኩባንያችን ለማህበረሰባችን፣ ለቢዝነሱ እና ለተቋማት የሚያቀርባቸው ዲጂታል ሶሉሽኖችን ላይ በተግባር የተደገፈ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡ በመጨረሻም ኩባንያችን በገነባው ሰፊ መሰረተ ልማት በመጠቀም የዲጂታል ሶሉሽኖችን በስፋት በማቅረብ በማሕበረሰባችን ሕይወት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲያመጣ እንዲሁም የተቋማት እና ቢዝነሶች አሰራር በማዘመን ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን የማድረጉን ጉዞ ለማፋጠን የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንደሚያስፈልግ በአጽንኦት ተገልጿል፡፡
Show more ...
14 683
3
የሶስተኛ ወገን ኢንሹራንስ ክፍያዎን በቴሌብር ! አስደሳች ዜና ለሶስተኛ ወገን ኢንሹራንስ ከፋይ ግለሰቦችና ድርጅቶች፤ ከዚህ በኋላ ለሁሉም የኢንሹራንስ ተቋማት የሶስተኛ ወገን ክፍያዎን በቴሌብር መፈጸም ይችላሉ! ቴሌብር ሱፐርአፕን ማስፈንጠሪያውን በመጠቀም ይጫኑ፤ የዲጂታሉን ዓለም ይቀላቀሉ! ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
19 528
12
ባህር ማዶ ከሚኖር ወዳጅ ዘመድ በአጋሮቻችን በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በቴሌብር ዓለም አቀፍ ሃዋላ በኩል እስከ ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ሲቀበሉ 20% የገንዘብ ስጦታ ያገኛሉ፤ የዕድል ጨዋታ በመጫወት የአየር ሰዓት ይሸለማሉ! ለተጨማሪ መረጃ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ
19 823
10
ቀጣዩ ሚሊየነር እርስዎ ሊሆኑ ይችላሉ! በ22 ኛው ዙር አድማስ ዲጂታል ሎተሪ የ4 ሚሊየን ብር እና ሌሎችም ሽልማቶች እድለኛ ለመሆን በቴሌብር ወይም ወደ 605 A ብለው በመላክ በ 10 ብር አሁኑኑ ይቁረጡ! እድል ከእርስዎ ጋር ትሁን! የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር እና ኢትዮ ቴሌኮም በአጋርነት
24 091
17
በኩባንያችን የቀድሞ ዋና ስራ አስኪያጅ (በስተግራ) የተመራ የከፍተኛ አመራር ልኡክ በስፔን የአይ.ቲ.ዩ ስብሰባ ላይ ሃገራችንን ወክለው በታደሙበት ወቅት የተወሰደ ምስል ለትውስታ አጋራናችሁ ዘንድ ወደድን!
25 872
7
አስደሳች ዜና ለዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ! በዩኒቨርሲቲው የኦንላይን መመዝገቢያ ድረ-ገፅ አስፈላጊውን መረጃ ከሞሉ በኋላ ክፍያውን ደግሞ ባሉበት ሆነው በፈጣን እና አስተማማኙ ቴሌብር መክፈል ይችላሉ! ቴሌብር ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹና አስተማማኝ
26 064
44
እጥፍ ድርብ የበዓል ስጦታ! ዒድ አል-ፊጥርን አስመልክቶ ባህርማዶ ከሚኖሩ ወዳጅ ዘመድዎ ከብር 99 ጀምሮ የሞባይል አየር ሰዓት ወይም ጥቅል በአጋሮቻችን በኩል ሲላክልዎ ለ15 ቀናት የሚያገለግል የ200% ስጦታ ይበረከትልዎታል! ዒድ ሙባረክ! ደንብና ሁኔታዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ። ለተጨማሪ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ
28 454
7
በዓሉን ከቤተሰብዎ ጋር ተሰባስበው በደመቀ ድባብ እያከበሩ ሩቅ ካለ ወዳጅ ዘመድ ጋር ደግሞ እየተደዋወሉ ዒድ ሙባረክ ሲባባሉ ለመልካም ምኞትዎ መግለጫ እስከ 25% ቅናሽ የተደረገበትን ልዩ የዒድ አል-ፊጥር የሞባይል ጥቅል በቴሌብር ሱፐርአፕ ከተጨማሪ 10% ስጦታ ጋር እንዲሁም በማይ ኢትዮቴል፣ አርዲ ቻትቦት ወይም *999# ገዝተው በስጦታ ያበርክቱ! ዒድ ሙባረክ!
24 467
3
እንኳን ለዒድ አል-ፊጥር በዓል በሰላም አደረሰዎ!

IMG_9256.MP4

27 373
14

Eid contest winners day 2.pdf

28 440
6
መልስ - ሐ. የደስታ ምሽት አሸናፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ! ትክክለኛውን ምላሽ ከሰጡ ተሳታፊዎች ውስጥ በእጣ ለ 300 ዕድለኞች 10 ጊ.ባ ወርኃዊ የኢንተርኔት ጥቅል ሽልማት እናበረክታለን! አሸናፊዎች በ 24 ሰዓት ውስጥ እየሰራ ያለ የስልክ ቁጥር ባሸነፋችሁበት ማህበራዊ ገጽ በውስጥ መልዕክት ላኩልን። ከ 24 ሰዓት በኋላ የሚላኩ ቁጥሮች ተቀባይነት የላቸውም። ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ! አብራችሁን ስለነበራችሁ እናመሰግናለን ! ዒድ ሙባረክ! የአሸናፊዎችን ዝርዝር ለመመልከት 👇🏼
29 156
2
With only a few hours remaining, our exclusive Eid Al-Fitr mobile package is approaching its conclusion, offering a generous 25% discount as a token of appreciation for our valued customers! Spread the joy of the holiday season by sharing these packages with your loved ones through telebirr SuperApp and receive an additional 10% discount. Alternatively, indulge yourself in this offer via My Ethiotel, Ardi Chatbot, or by dialing *999#.
Show more ...
23 782
4
Last updated: 11.07.23
Privacy Policy Telemetrio