El servicio también está disponible en tu idioma. Para cambiar el idioma, pulseEnglish
Best analytics service

Add your telegram channel for

  • get advanced analytics
  • get more advertisers
  • find out the gender of subscriber
Ubicación del canal e idioma

all posts Ethio Construction

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም 👷‍♂እናማክራለን 🏢ዲዛይን እናደርጋለን 📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን 🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን 📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም tiktok  https://www.tiktok.com/@ethiocons  ለሃሳብ እና ኣስተያየት  @Ethiocon143bot  ይጠቀሙ 
Mostrar más
26 667+57
~3 574
~88
14.55%
Calificación general de Telegram
Globalmente
34 213lugar
de 78 777
252lugar
de 396
En categoría
266lugar
de 546
Archivo de publicaciones
"በሕንጻ ግንባታ ሥራ selective material ከመጠቅጠቁ (ከመረምረሙ) በፊት ውኃ የሚጠጣው ለምንድነው? የጎንዮሽ ተጽእኖስ አለው ይላሉ?" 🏷የአፈር መጠቅጠቅ ሂደት ቅንጣቶች በመካከላቸው ያለውን ክፍተት ለመቀነስ የሚደረግ የመጫን ጉልበት (compaction) ትግበራ ነው። 💫በጣም የታመቀ፣ የተጠቀጠቀ አፈር የቅንጣቶችን ክፍተት በመቀነስ አፈሩ በጣም ጥቂት ቦታን (ስፋትን) እንዲይዝ ያግዘዋል። ⭐️ነገር ግን ይህንን የመጠቅጠቅ (ጥግግት) ደረጃ  የምናገኘው ጥሩ የእርጥበት መጠን ካለው  ነው። አፈሩ በጣም ጥሩ እርጥበት የሌለው ከሆነ የአፈር ቅንጣት ጥግግት በሚፈለገው ልክ ሊከናወን ስለማይችል ውስጥ ውስጥ  ያሉትን ክፍተቶች በሙሉ ለመሙላት አስቸጋሪ ይሆናል።  የተደፋው አፈር (Back filled or selective material) ሁሉም አካሉ በቂ እርጥበት እንዲኖረው ቢያንስ ከአንድ ሌሊት በፊት ቀደም ብሎ  ውኃ መጠጣት አለበት። 🌟የተወሰነ ጊዜ ቀድሞ ማጠጣት (አንደኛ) በሰዓቱ መርዘም የተነሳ የውኃውን የስርገት ሂደት በመጨመር እና ሁሉንም አካል የማግኘት (የማዳረስ) ዕድሉን በማስፋት ሁሉም የአፈር ቅንጣት በቂ እርጥበት እንዲያገኝ ያደርገዋል። 🌟(ሁለተኛ) የአፈሩ የመጠቅጠቅ ሂደት አስቀድሞ በውኃው ስርገት የተነሳ እየተከናወነ እንዲቆይ ያድርጋል። ያ ማለት የመጠቅጠቂያ ጉልበትን ይቀንሳል። ⚡️ሆኖም ግን የተመረጠው አፈር በቂ የሆነ የኮረት፣ የጓል እና የደቃቅ አፈር መዋጮ የሌለበት ከሆነ ውኃ ሲጠጣ የባሰ የላመ አፈር (silty) የመሆን እድሉን ስለሚጨምር ከሚፈለገው አገልግሎት አንጻር ጉዳት እንዳይደርስበት የውኃውን መጠን እና የሚጠጣበትን የጊዜ ርዝማኔ እንደአፈሩ አይነት እና እንደአካባቢው አየር የመመጠን ሥራ ከአንድ መሐንዲስ የሚጠበቅ የውሳኔ አካል ነው።
Mostrar más ...
3 468
22
የዓለማችን ድንቅ እስላማዊ የ ኮንስትራክሽን ስትራክቸሮች እንሆ 1. መስጂድ አል-ሀራም፡- መካ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ የሚገኝ መስጂድ አል-ሀራም የአለማችን ትልቁ መስጂድ ሲሆን በእስልምና እጅግ የተቀደሰ ቦታ የሆነውን ካባንን ይከብባል።  መስጂዱ በሀጅ ወቅት እስከ 4 ሚሊዮን ሰጋጆችን ማስተናገድ ይችላል። 2. መስጂድ አል-ነበዊ፡- በመዲና፣ ሳውዲ አረቢያ፣ መስጂድ አል-ነበዊ በእስልምና ሁለተኛው ቅዱስ መስጂድ ነው። የነብዩ መሐመድ መቃብር የሚገኝበት ሲሆን በግሩም አረንጓዴ ጉልላት እና በዓይነቱ ልዩ የሆነ የስነ-ህንፃ ጥበብ ይታወቃል። 3.ቡርጅ ካሊፋ፡ 828 ሜትር ላይ የቆመው ቡርጅ ካሊፋ በዱባይ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ በአለማችን ረጅሙ ህንፃ ነው ኢስላማዊ እና ዘመናዊ ኪነ-ህንፃዎች ቅልቅል ያለው እና ተወዳጅ የቱሪስት መስህብ ነው። 4. ሱልጣን አህመድ መስጂድ፡- በተለምዶ ሰማያዊ መስጂድ በመባል የሚታወቀው በቱርክ ኢስታንቡል የሚገኘው ሱልጣን አህመድ መስጂድ የውስጥ ግድግዳውን እና ስድስቱን ሚናራዎችን በሚያጌጡ ሰማያዊ ሰቆች ይታወቃል።  etconp የኦቶማን አርክቴክቸር ድንቅ ስራ ነው። 5. ሀሰን II መስጂድ፡ በሞሮኮ ካዛብላንካ ውስጥ የሚገኝ፣ ሀሰን 2 መስጂድ በአለም ላይ ካሉት ትልቁ መስጊዶች አንዱ ነው እና አስደናቂ የእብነበረድ ውስጠኛ ክፍል፣ ውስብስብ የጣር ስራ እና አስደናቂ የባህር ዳርቻ አቀማመጥ አለው። 6. አልሀምብራ፡ በግራናዳ፣ ስፔን ውስጥ የምትገኝ፣ አልሀምብራ መጎብኘት ያለበት የእስልምና አርክቴክቸር ድንቅ ነው። ይህ ቤተ መንግስት እና ምሽግ ውስብስብ የስቱኮ ማስዋቢያዎች፣ የፈረስ ጫማ ቅስቶች እና የተረጋጋ የአትክልት ስፍራዎችን ያሳያል። 7. የሼክ ዛይድ ታላቁ መስጊድ፡ በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አቡ ዳቢ የሚገኘው የሼክ ዛይድ ታላቁ መስጂድ የዘመናዊ ኢስላማዊ ኪነ-ህንፃ ድንቅ ስራ ነው።  etconp ነጭ የእብነበረድ ጉልላቶች፣ ውስብስብ ቅርጻ ቅርጾች እና አስደናቂ የአበባ ንድፎችን ይዟል። 8. ታላቁ የኮርዶባ መስጊድ፡ በ8ኛው ክፍለ ዘመን በኮርዶባ፣ ስፔን ውስጥ የተገነባው ታላቁ የኮርዶባ መስጊድ የሞሪሽ፣ የጎቲክ እና የህዳሴ ስነ-ህንፃ ቅጦች ድብልቅልቅ የሚያሳይ የባህል ሀብት ነው።  ውስጣዊ ክፍሎቹ ከ 850 በላይ አምዶች እና ውስብስብ ቢሞች ኣሉት። ❤️መልካም ዒድ😇
Mostrar más ...
4 042
10
✅ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን እንኳን ለመውሊድ በዓል አደረሳችሁ፣ መልካም በዓል!
3 595
2
የቻይና መሃንዲሶች ለትራንስፖርት ተስማሚ የሆነ የመንገድ መሠረተ ልማት ለመገንባት የሚያግዳቸው ተራራማ፣ ኮረብታማ እና ጎበርባጣ መልከዓ ምድር የለም ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል።
4 651
7
🌼🌼🌼እንኳን አደረሳችሁ!🌼🌼🌼 🌻አዲሱ አመት የሰላም ፣ የደስታ ፣የፍቅር ፣ የመተሳሰብ፣ የስኬት አመት ይሁንላችሁ!!! 🌼🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት!🌼🌼🌼
6 192
21
ኮንስትራክሽን ክሌም           የኮንስትራክሽን ክሌም ለመስራት የውሉ የክፍያ መንገድ ላምፕ ሰም ወይስ አድሜዠርመንት የሚለውን መለየት ግድ ነው። የውሉ አይነትም ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(DBB) ወይም ዲዛይን ቢዩልድ(DB) ስለመሆኑ  መለየት ይገባል። DBB እና DB የተለያየ ጀኔራል ኮንዲሽን ይጠቀማሉ።ለምሳሌ FIDIC 2017 Red Book ለDBB እና Yellow Book ለDB መጠቀም ይቻላል። የክፍያ መንገዱ ላምፕ ሰም ወይም አድሜዠርመንት መሆኑ ግን የጀኔራል ኮንዲሽን እንድትቀይር አያስገድድም። ለምሳሌ ፒፒኤ 2011 ቨርሽን ለሁለቱም የክፍያ መንገዶች ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። ስፔሻል ኮንዲሽን ላይ የተለወጠ የጀኔራል ኮንዲሽን ክሎስ ያለ እንደሆነ ማረጋገጥም ቀዳሚ ተግባር መሆን አለበት። ከዚህ በኋላ ለክሌሙ አግባብነት ያለውን የውል ድንጋጌ፣የህግ ድንጋጌ እና የጀኔራልና ስፔሻል ኮንዲሽን ድንጋጌ መለየትና መስፈርቱን የሚያሟላ ክሌም ማዘጋጀት ይቻላል። ከዚያም ክሌሙ ለአማካሪ፣ለዲስፒውት ሪቪው ቦርድ፣ለአርቢትሬሽን ወይስ ለፍርድ ቤት መቅረብ እንደሚገባው ለመለየት ጀኔራል ኮንዲሽኑን እና በዋናነት ስፔሻል ኮንዲሽኑን ማየት ይገባል። በጉባዔ አሰፋ
Mostrar más ...
7 348
21
ጥያቄ ✅በአንድ ተቋራጭ ሥር የሚሠሩ ምክትል ሥራ ተቋራጮች (Sub Contractors) የሠሩበትን የሥራ ክፍያ ዋናው ተቋራጭ አልከፍል ቢላቸው ክስ መስርተው በዋናው ተቋራጭ ውል ላይ የተመለከተውን የሥራ ዋጋ የማግኘት መብት አላቸው? መልስ በኢትዮጵያ የሕንጻ ነክ ሕጎች መሰረት በአንድ የሕንጻ ተቋራጭ ሥር የሚሰሩ ምክትል /ንዑስ/ ሥራ ተቋራጮች (Sub contractors) ወይም ሠራተኞች (labours) ዋናው ተቋራጭ ለሠሩበት ሥራ ሳይከፍላቸው ከቀረ እና ለሠሩበት ሥራ ዋጋ እንዲከፈላቸው ክስ ካቀረቡ ክሳቸውን ባቀረቡበት ጊዜ አሠሪው ለሥራ ተቋራጩ ሊከፍል በሚገባው ገንዘብ መጠን በቀጥታ ገንዘባቸውን የመጠየቅ መብት ስላላቸው ያንን ክፍያ የማግኘት መብት አላቸው። ለምሳሌ፦ አንድ ተቋራጭ በውል ሰነዱ ውስጥ የአንድ ካሬሜትር የፎርምወርክ ሥራን በ500 ብር ሂሳብ ተዋውሎ ለምክትል ሥራ ተቋራጮች  (Sub contractors) በ300 ብር ተነጋግሮ ካሠራቸው በኋላ ክፍያ ሳይከፍላቸው ቢቀር (ቢያዘገይባቸው) ክስ ማቅረብ ይችላሉ። ክስ ሲያቀርቡ ሥራውን ለመሥራታቸው ማረጋገጫ ካቀረቡ እና የሥራው ጥራት ታይቶ ተቀባይነት ካገኘ ዋናው ተቋራጭ የተዋዋለበትን 500ብር ሊከፈላቸው የሚችልበት አግባብ አለ ማለት ነው።
Mostrar más ...
6 531
31
ይህ ግዙፍ የአፓርትመንት ኮምፕሌክስ መጠሪያ ስሙ Novy Okkervil ይባላል፤ በሩሲያ ነው የሚገኘው። 🏷እ.ኤ.አ በ2015 የተገነባው የመኖሪያ መንደር ከአለማችን ከሚገኙ ተመሳሳይ ግንባታዎች በቀዳሚነት እንደሚገኝ ይነግርለታል። 💫በዚህ መንደር ውስጥ ወደ 18 ሺህ የሚጠጋ ህዝብ ይኖርበታል። ⭐️እያንዳንዱ ሕንፃ ባለ 25 ወለል ሲሆን፣ በጠቅላላው ወደ ሕንፃው ለመግባትም ሆነ ለመውጣት 35 በሮች አሉት።
7 672
6
🌟Training (With Discount)           🌟Online Class (With Certificate) 1. ETABS Price = 2000birr 2. Ms Project Price = 2500birr 3. Quantity Survey Price = 2000birr 4. Civil 3D Price =2500birr 5. Etabs With Safe Price = 3000birr 6. Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000 7. Structural Design in ProtaStructure Software 8. Autocad Price = 2500birr 9. Sap2000 Price = 2500birr 10. Autodesk Revit Architecture 11. WatrGems 🫵 If u take More than 2 Course u will have Big Discount 🚧Prepared by Engineering Solution Abel Muluken 🫵For Registration - 0948552002 Or 0933575753 or 🚧Telegram Channel - 🚧YouTube Channel -
Mostrar más ...
Engineering Solution
Youtube link - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2BA
6 071
10
5 085
15
አንድ ሰው ግንባታ እያከናወነ የጎረቤት ቤት ቢፈርስበት የጎረቤቱን ቤት እንዲያሰራ ይገደዳል ወይስ ሌላ የህግ እይታ አለ? አንድ ሰው ግንባታውን ሲያከናውን የጎረቤቱን ቤት ቢናድበት ወይም በግንባታ ሥራው የተነሳ የጎረቤቱን ቤት ቢያፈርስ ተጠያቂ ነው። 💫የመፍረስ አደጋ ባይገጥምም እንኳን በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2077 (1) እና (2) መሰረት  አንድ ሕንጻ በሌላው ይዞታ ላይ ያልታሰበ ድንገተኛ ሌላ አደጋ ቢያደርስ የሕንጻው ባለቤት ተጠያቂ (ካሳ ከፋይ) ይሆናል። ▶️ይህም ማለት እንዲፈርስ ያደረገውን ቤት በእራሱ ወጪ እንዲጠግን/እንዲሰራ ይገደዳል። ⏺ቢሆንም ግን በቁጥር 2079 መሰረት በግንባታ ወቅት (በተለይ ከቁፋሮ ጀምሮ ባሉት የመሰረት ሥራዎች ጊዜ) በሌላ የጎረቤት ሕንጻ ላይ የመፍረስ አደጋ ከመድረሱ በፊት አስቀድሞ ሥጋት ላይ ያለው ክፍል አስፈላጊውን ድጋፍ ወይም ጥንቃቄ እንዲደረግለት ማድረግ ይችላል። ▶️“ጎረቤት” የተባለው አካልም ይህ ስጋት ከተሰማው አስቀድሞ ጥንቃቄ እንዲደረግለት የመጠየቅ ሕጋዊ መብት አለው። 🚧ጠቅለል ሲደረግ፦ አንድ የሕንጻ ባለይዞታ በግንባታ ወቅት በጎረቤት ይዞታ ላይ የተገነባን ሕንጻ የመፍረስ ወይም የመሰንጠቅ ጉዳት ቢያደርስ እንዲሁም ሕንጻው በሚገነባበት ወቅትም ይሁን ከተጠናቀቀ በኋላ ከዚያ ሕንጻ ላይ እየወደቁ በሌላው ሕንጻ ወይም ይዞታ ላይ ለሚያደርሱት ጉዳት ተጠያቂ ነው (ፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2080)። ❇️የጎረቤት ሕንጻ ቢፈርስ ተጠያቂ የማይሆንበት አግባብ ▶️በጎረቤት ይዞታ ወይም ሕንጻ ላይ ጉዳት ቢደርስ የማይጠየቀው በሁለት ምክንያት ነው። 📜[አንደኛው] በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2078 (1)  መሰረት ጎረቤት የተባለው ባለይዞታ ይዞታውን ግንባታ ለሚያከናውነው ሰው የለቀቀለት እንደሆነ ወይም ግንባታ የሚያከናውነት አካል የራሱን ሕንጻ ለፈረሰበት ጎረቤቱ የሚለቅለት ከሆነ ነው። 📜[ሁለተኛው] “ጎረቤት” የተባለው አካል ሕንጻው የመፍረስ አደጋ እንዳይገጥመው ጥንቃቄ እንዲደረግለት የመጠየቅ መብት የሚኖረው ግን አስቀድሞ የገነባው ሕንጻ በመሬት ውስጥ፣ በመሬት ላይም ይሁን በአየር ላይ አዲስ የሚገነባውን ባለይዞታ የካርታ መስመር ያላለፈ ከሆነ ብቻ ነው። 🗂ለምሳሌ፦ አስቀድሞ የገነባው ጎረቤት የመሰረት ግንባታው ወይም ተንጠልጣይ የባልኮኒ ወለል ወደሰው ይዞታ አንድ ሳንቲሜትርም ቢሆን ካለፈ እንዲያስተካክል ወይም እንዲያፈርስ ይገደዳል። ⏹አዲስ ግንባታ የሚገነባውም ሰው ጎረቤቱ ወደይዞታው ገብቶ የሰራውን የሕንጻ አካል እንዲያፈርስና እንዲያስተካክል ሳያስጠነቅቅ ማፍረስ የለበትም፣ በፍርድ ቤት በተቆረጠ ቀነ ገደብ እንዲያስተካክል ማሳሰብ ሲኖርበት በዚያ ቀነገደብ ካላስተካከለ ግን ትእዛዝ አስወጥቶ ማስፈረስ/ማፍረስ/ ይችላል።
Mostrar más ...
7 337
34
የግንባታ ውል ሰነድ በግልጽ ማስቀመጥ ያለበት ነጥቦች:- የፕሮጀክቱን ዲዛይን እና ዝርዝሮች: ➢የፕሮጀክት ባለድርሻ አካላትን ድርሻ፣ መብትና ግዴታ፣ ➢የሚጠበቀውን የግንባታ ጥራት የሚገልጹ ትንታኔዎች፣ ➢የፕሮጀክቱን ተጠባቂ የጊዜ ሰሌዳዎች፣ ➢የፕሮጀክቱን ዋጋ እና አከፋፈል ሁኔታዎች፣ ➢የደህንነት እና የጤና አጠባበቅ፣ መመሪያዎች፣ ➢ፕሮጀክቱን የሚመለከቱ የሕግ ማእቀፎች ➢የፕሮጀክቱ ባለድርሻ አካላትን ፊርማ እና ማኅተም ➢ፕሮጀክቱ የሚፈልገውን የሰው ኃይል ብቃትና ብዛት ➢ፕሮጀክቱ የሚፈልገው ማሺነሪ አይነትና ብዛት ➢የእያንዳንዱን የሥራ አይነት ዝርዝርና የግንባታ ስነዘዴ ➢የፕሮጀክቱን ባለድርሻ አካላት ዝርዝር መረጃ አንድ የግንባታ ውል ሰነድ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ዋና ዋና ጭብጥ ጉዳዮች በግልጽ እና በዝርዝር ማስቀመጥ ይኖርበታል። የተወሳሰበ፣ ያልተብራራ እና እርስ በእርሱ የሚጋጭ ሀሳብ ቢኖርበት ግን በሚኖረው የፍርድ ቤት ክርክር ባለድርሻ አካላትን በተናጠል አልያም በጋራ ኪሳራ ላይ ሊጥል ይችላል። ይህ ሁኔታ ደግሞ ፕሮጀክቱን በጤናማ ግንኝነት ለመፈጸም እክል ሊፈጥር ስለሚችል ለጥራት ችግር እና ለጊዜ ብክነት እንዲጋለጥ ያደርገዋል። 
Mostrar más ...
7 164
34
🌟Training (With Discount)           🌟Online Class (With Certificate) 1. ETABS Price = 2000birr 2. Ms Project Price = 2500birr 3. Quantity Survey Price = 2000birr 4. Civil 3D Price =2500birr 5. Etabs With Safe Price = 3000birr 6. Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000 7. Structural Design in ProtaStructure Software 8. Autocad Price = 2500birr 9. Sap2000 Price = 2500birr 10. Autodesk Revit Architecture 11. WatrGems 🫵 If u take More than 2 Course u will have Big Discount 🚧Prepared by Engineering Solution Abel Muluken 🫵For Registration - 0948552002 Or 0933575753 or 🚧Telegram Channel - 🚧YouTube Channel -
Mostrar más ...
Engineering Solution
Youtube link - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2BA
3 379
1
✅የግንባታ ቦታን ማስረከብ 🚧🏗 የግንባታ ባለቤት (Client) ለግንባታ ሥራ መሰናክል ከሆኑ ነገሮች (ለምሳሌ፦ የካሳ ጥያቄ ከሚያነሱ ሰዎች ቁጥጥር፣ ከመብራት፣ ከውሃ፣ ከቴሌ ግንባታዎችና መሣሪያዎች) በማጽዳት ወይም ነጻ በማድረግ ዝግጁ የሆነ የግንባታ ቦታን ለሥራ ተቋራጩ (Contractor) የማስረከብ ሕጋዊ ኃላፊነት አለበት። ባለቤቱ የግንባታ ቦታውን ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ውስጥ ለሥራ ተቋራጩ ካላስረከበ የግንባታ ማስረከቢያ ጊዜ መራዘም/መዘግየት/ ላይ ለሚያስከትለው ኪሳራ ወይም ወጪ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ የሕንጻ ግንባታ ደንቦች (Standard Building Contract with quantities) በአንቀጽ 2.4 እና 2.24 ስር የሰፈረ ድንጋጌ ነው።
5 405
17
5 964
3
🌟Training (With Discount)           🌟Online Class (With Certificate) 1. ETABS Price = 2000birr 2. Ms Project Price = 2500birr 3. Quantity Survey Price = 2000birr 4. Civil 3D Price =2500birr 5. Etabs With Safe Price = 3000birr 6. Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000 7. Structural Design in ProtaStructure Software 8. Autocad Price = 2500birr 9. Sap2000 Price = 2500birr 10. Autodesk Revit Architecture 11. WatrGems 🫵 If u take More than 2 Course u will have Big Discount 🚧Prepared by Engineering Solution Abel Muluken 🫵For Registration - NaN Or NaN or 🚧Telegram Channel - 🚧YouTube Channel -
Mostrar más ...
Engineering Solution
Youtube link - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2BA
3 261
8
https://t.me/major/start?startapp=371415119 👑 Join me in game and earn $MAJOR token soon! ⭐️ 750 rating bonus for you. ⭐️ 1000 rating bonus if you are Premium.
Major
Welcome to @Major bot. Boost your rating by stars and completing tasks. Convert rating to $MAJOR token soon.
1 468
0
በሀገራችን ኢትዮጵያ በግንባታው ዘርፍ የሚታዩ ዋና ዋና ችግሮች:- ⚡️በኮንስትራክሽንፈ ኢንዱስትሪ የማጭበርበር አመለካከትና ተግባር የሚስተዋልበት ነባራዊ ሁኔታ መኖሩ ⚡️በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሰለጠነና የሙያ ብቃቱ የተረጋገጠ የሰው ኃይል እጥረት ያለ መሆኑ ⚡️የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ስራ አመራር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር የተሳለጠ ያለመሆኑ ⚡️በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሚሠማሩ አማካሪዎችና ተቋራጮች መካከል ተወዳዳሪነት በሚፈለገው ደረጃ ማድረስ ያልተቻለ መሆኑ ⚡️ለኮንስትክሽን ኢንዱስትሪ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ቀጣይነት ያለው የአቅርቦት ሠንሠለት ያልተዘረጋ መሆኑ 🌟ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ መስፋፋትና መጠናከር የተመቻቸ ሁኔታ የሚፈጥር የፋይናንስና የማሽነሪ አቅርቦት ሥርዓት የተጠናከረ ያለመሆን 🌟የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዋና ዋና ባለሚናዎች በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ ለዘርፉ የተፋጠነ ዕድገት በጋራ የሚሰሩበት ሁኔታ ያለመፈጠሩ 🌟የህንፃ ግንባታና መጠቀሚያ ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር አገልግሎት የተጠናከረ ያለመሆን 🌟ፈርጀ ብዙ ሥራዎች ከኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ሥራዎች ጋር ተጣጥመው የሚታቀዱበትና የሚተገበሩበት ሥርዓት ያለመዘርጋቱ 🌟የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት ፕሮግራም ወይም ፓኬጅ አዘጋጅቶ በተሟላና በቀጣይነት ያለመተግበር 🌟ለባለሞያዎችና ስራተቋራጮች የሚደረግ የአቅም ግንባታ ድጋፍ እጅግ አናሳ መሆን
Mostrar más ...
10 791
24
🌟Training (With Discount)           🌟Online Class (With Certificate) 1. ETABS Price = 2000birr 2. Ms Project Price = 2500birr 3. Quantity Survey Price = 2000birr 4. Civil 3D Price =2500birr 5. Etabs With Safe Price = 3000birr 6. Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000 7. Structural Design in ProtaStructure Software 8. Autocad Price = 2500birr 9. Sap2000 Price = 2500birr 10. Autodesk Revit Architecture 11. WatrGems 🫵 If u take More than 2 Course u will have Big Discount 🚧Prepared by Engineering Solution Abel Muluken 🫵For Registration - NaN Or NaN or 🚧Telegram Channel - 🚧YouTube Channel -
Mostrar más ...
Engineering Solution
Youtube link - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2BA
6 026
26
የግንባታ ላይ ደህንነት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ትኩረት አንዱና ዋነኛው ትኩረት ማድረግ የሚገባው በሰው ልጆች ደህንነት ላይ መሆን ይኖርበታል፡፡ ግንባታዎች በሚገነቡበት በዋናነት ለሰውልጆች አገልግሎት ለመስጠት በመሆኑ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ስራዎች የስራ ላይ ደህንነት ሥጋት የሌለባቸው እንዲሁም ለአገልግሎት በሚውሉበት ጊዜ ለአካባቢ የተመቹ እና ደህንነታቸው  የተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል፡፡ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ትኩረት ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ውስጥ የደህንነት ጉዳይ አንዱ ነው፡፡ ደህንነቱ የተረጋገጠ የኮንስትራክሽን ስራ እንዲኖር ቁጥጥር በማድረግ ሂደት ትኩረት እንደሚሰጥ ቢነገርም ደህንነት በቁጥጥር ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ሁሉም የግንባታው ዘርፍ አካላት በየራሳቸው ትኩረት ሊያደርጉበት የሚገባ ነጥብ  ነው፡፡ 👷‍♀የግንባታ ሂደት ውስጥ የሰራተኞች ደህንነት እንዲጠበቅ በግንባታ ስራው ላይ የሚሰማሩት የመስክ ሰራተኞች በሙሉ ደህንነታቸው የተጠበቀ ሆኖ እንዲሰሩ የሚያስፈልጋቸውን የግል የአደጋ መከላከያዎችን  በማቅረብ ሰራተኞቹም የስራ ላይ ትጥቃቸውን በመጠቀም በስራ ወቅት የሚደርሱ አደጋዎችን መቀነስ ይቻላል፡፡ በህንጻ ግንባታ ሆነ በሌሎች ግንባታዎች ደህንነቱ የተጠበቀ በማድረግ በሰውም ሆነ በንብረት ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን መቀነስ ይቻላል፡፡ የህንጻ ግንባታዎች ላይ በተለይም የግንባታ ስራ የእቃ መስቀያ፣ መወጣጫዎች እንዲሁም ወደ መንገድ እና ወደ አጎራባች ህንጻዎች፤ መኖሪያዎች፣መተላለፊያዎች የሚወርዱ የግንባታ ተረፈ ምርቶች የግንባታ ግብዓቶች በሰው እና በንብረት ላይ ቀላል የማይባል አደጋ ያደርሳሉ፡፡ ሆኖም በእነዚህ አደጋዎች የሚፈጥሩትን ኪሳራ የግንባታ ጊዜ ማስታወቂያዎች መከላከያዎች በማድረግ እንዲቀነሱ ማድረግ ይቻላል፡፡ 🚧በግንባታ ስራ ላይ የተሰማሩ ሙያተኞች ወደስራ ቦታቸው ሲገቡ አስፈላጊውን የደህንነት መጠበቂያ ባለማድረጋቸው የሚደርሱ የአካል እና የመንፈስ ስብራቶች ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ የራስ (የአናት) መከላከያ ቆብ፣ ጓንት፣ አስፈላጊ የደህንነት ጫማዎች፣ የመለያ አልባሳት ወ.ዘ.ተ ለደህንነት ዓላማ የተዘጋጁ ቁሶች እንደመሆናቸው ቅድሚያ ለደህንነት በመስጠት መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ በቀላል የሚቀረፉ እና የሚስተካከሉ ጉዳዮች በብዙ ዋጋ የሚያስከፍሉ እንዳይሆኑ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ግንባታ ዘርፈ ብዙ የሆኑ ጥቅሞች ቢኖሩትም በግንባታ ወቅት የሚደርሱ ኪሳራዎች ደግሞ በግለሰብ በማህበረሰብና በሀገር ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ ቀላል የሚባል ባለመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ ታሳቢ ቢያደርገውና ቅድሚያ ለደህንነት በማለት የመጀመሪያውን እርምጃ ለደህንነት ማድረግ ይኖርበታል፡፡                                            (ኢኮባ)
Mostrar más ...
11 680
12
የግንባታ ላይ አረንጓዴ ስፍራ ህግ በ100 ሜትር ካሬ ይዞታ ላይ 2 በ2 ሜትር ስፋት ያለው ከግንባታ ነጻ መሬት እንዲኖር የሚደነግገው ህግ ጽሁፍ ተያይዟል።
11 360
44
Ads❗❗ አንድ ቀን ብቻ ቀረው‼️ ቴሌግራም ወደ Business app እየተቀየረ ነው፣Dogs mining ሊያበቃ አንድ ቀን ብቻ ቀረው፣መጪው August 14 ቴሌግራም የተመሰረተበት እለት ነው፣ስለ Dogs airdrop አዲስ ነገር አለ ተብሏል፣ ከስር ባለው ሊንክ task ስሩ👇👇👇
3 955
2
👉August 14 የቴሌግራምን birthday ምክንያት በማድረግ ትልቅ ነገር እንዳለ በ official ገፃቸው ተናግረዋል። 🚨 በብዙ መረጃዎች ላይ 100,000 dogs እየተገመተ ያለው ከ300$ እስከ 500$ ነው 🥶 እንስካሁን ያልጀመራችሁ ጥቂት ቀናት አላቹ task ስሩ።
2 536
6
አስደሳች ዜና በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ ለተሰማራችሁ ባለሙያዎች፡፡ አዲስ ኮስት ኤስቲሜተር ይባላል፡፡ ዌብ ሳይቱ ይግንባታዎትን መረጃ ከእርስዎ በመዉሰድ ጥንቅቅ BOQ በኤክሴል አዘጋጅቶ ይሠጥዎታል፡፡ አጠቃቀሙ በጣም ቀላል ሲሆን አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጋችሁ፣ የኢሜል አድራሻ ብቻ ነዉ፡፡ አሁኑኑ በነጻ ይሞክሩት፡፡ ✨ጥቅሞቹ 📌የተሟላ የዋጋ ዝርዝር 📌ፈጣን እና ቀላል 📌ቶሎ ቶሎ የሚሻሻል የገበያ ዋጋ 💥ስራዎትን በጥራት እና በፍጥነት በማጠናቀቅ ደንበኛዎትን ያስደስቱ፡፡ For more information call NaN
8 693
48
Did you know? 💫The reasons for honeycomb in concrete: 1. Inappropriate workability of concrete. 2. Use of stiff concrete mix or the concrete is already set before placing. 3. Improper vibration of concrete in formwork. 4. Over reinforcement. 5. Use of larger size aggregates in excessive amounts. 6. Formwork is not rigid and watertight. 7. Concrete is poured from more than allowable height. 8. Congestion of steel is preventing the concrete to flow over all corners.
Mostrar más ...
11 155
32
Watering the concrete with water after pouring: 👉 increases the strength of concrete and the durability of the building. 👉 reduces the permeability of concrete due to water evaporation. 👉 completes the cohesion and reaction of cement that continues for a period after pouring. ⚡️Watering the concrete with water after pouring is very important. It must be done for a period of at least one week, twice a day, to reach 70% of its resistance in a week.
8 393
26
አስደሳች ዜና በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ ለተሰማራችሁ ባለሙያዎች፡፡ አዲስ ኮስት ኤስቲሜተር ይባላል፡፡ ዌብ ሳይቱ ይግንባታዎትን መረጃ ከእርስዎ በመዉሰድ ጥንቅቅ BOQ በኤክሴል አዘጋጅቶ ይሠጥዎታል፡፡ አጠቃቀሙ በጣም ቀላል ሲሆን አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጋችሁ፣ የኢሜል አድራሻ ብቻ ነዉ፡፡ አሁኑኑ በነጻ ይሞክሩት፡፡ ✨ጥቅሞቹ 📌የተሟላ የዋጋ ዝርዝር 📌ፈጣን እና ቀላል 📌ቶሎ ቶሎ የሚሻሻል የገበያ ዋጋ 💥ስራዎትን በጥራት እና በፍጥነት በማጠናቀቅ ደንበኛዎትን ያስደስቱ፡፡ For more information call NaN
14 561
113
8 289
3
ዜና ዕረፍት! የዝነኛው ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ባለቤት ሲሞን ፔትሮ ሳሊኒ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ በአገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ብሔራዊ እና ግዙፍ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በማከናወን ዝናን ያተረፈው ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ባለቤት በ92 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። እኚህ ግለሰብ 1.5 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሀብት እንዳላቸው የፎርብስ መጽሔት መረጃ ያሳያል።
10 043
14
የቤት ዋጋ እንዴት ሊቀንስ ይችላል? "ቤት አትግዙ " የሚል የሶሻል ሚዲያ ቻሌንጅ የማከብረው ወዳጄ ልኮልኝ ተመለከትኩ። አላማው በደምሳሳው ቤት ውድ ስለሆነ እስኪቀንስ ድረስ አትግዙ የሚል ነው...ይሄ ብዙም ውጤታማ ሊሆን የማይችል ቻሌንጅ እንደሆነ ቢታወቅም ሀሳቡ ግን የሚበረታታ  አይደለም ምክንያቱም ስሁት ነው። የሪል እስቴት ዘርፍን በቅጡ ካለመገንዘብ የመጣ ቤት ተወዷል ብሎ ለውድነቱም አልሚዎችን ብቻ ተወቃሽና ተከሳሽ ለማድረግ የታሰበ የችግሩን መሰረት ያልተረዳ ነው።  እስኪ የዘርፉን አሰራርና ችግሩን እንድንረዳ ስለ ሪል እስቴት ኢንቨስትመንት ዋና ተዋናዮችና አስተዋጽኦዋቸው ጥቂት እንበል።  ሀ) ባለድርሻ አካላትና ድርሻዎቻቸው የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት አምስት ዋና ዋና ባለድርሻ አካላት አሉት። የሀገራችንን ሁኔታ ታሳቢ አድርገን ስናቀርበው ከዚህ በታች የተገለጸውን ሊመስል ይችላል:- ፩) አልሚ (Developer) :- ስራ ፈጣሪ ነው፣ መሬትን ወደ ውጤታማ የሆነ ተፈላጊ የመኖሪያ ስፍራ በመቀየር ትርፍን የሚያገኝ መላ ፈጣሪ ነው፣ የገንዘብ አምጪ፣ የኪሳራሃላፊነት ወሳጅ፣ ቀጣሪ ሲሆን ዓላማው የገንዘብ ትርፍ ማግኘት፣ የቤት ችግር መቅረፍ ቢዝነሱ ያደረገ፣ ዘላቂ ንብረት ማፍራት፣ ጥሩ ስም መገንባት ... ፪) መንግስት(public organization):- መንግስት ዜጎች ቤት እንዲያገኙ የተለያዩ ፖሊሲዎችንና መመሪያዎችን ያወጣል፣ ለቤት ልማት የሚሆን መሬት ያቀርባል፣ የግንባታ ሂደቱን ይከታተላል፣ የግብይት ሂደቱን ይቆጣጠራል.... በሪል እስቴት ልማት ውስጥ የመንግስት ዋና ፍላጎት  የልማቱ ሂደት በስኬት ተከናውኖ   ዜጎች ቤት እንዲያገኙ ማድረግ፣  የህዝብ ሃብት የሆነው መሬት በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ .... ፫) ካፒታል ማርኬት:- ይህ ለግንባታም ሆነ ለቤት ገዢዎች ብድር የሚሆን የገንዘብ አቅርቦትን የሚያቀርቡ ባንኮችንና ሌሎች ወደፊት የሚመጡ የገንዘብ አቅርቦት የሚሰሩ ተቋማት ሲሆኑ ተሳትፏቸውም ለልማቱና ለቤት ገዢዎች ገንዘብ ማቅረብና ከልማት ሂደቱ ማትረፍ ነው። ፍላጎታቸው ኢንቨስትመንቱ አዋጭ መሆኑን ማረጋገጥ ነው። ፬) የቤት ገዢዎች (ተከራዮች) (ደንበኞች):- ዋና ፍላጎታቸው ለመኖር በቂ የሆነ ፣ በጊዜው ተጠናቅቆ መረከብ፣ በቂ ስፋት ያላቸው መገልገያ ክፍሎች ፣ በተመጣጣኝ ዋጋ ቤት ማግኘት ሲሆን። የቤት አልሚው ይህንን የቤት ገዢዎችን አቅምና ፍላጎት በገበያ ጥናት አጥንቶ መገንባት ይጠበቅበታል። ፭) የተለያዩ ባለሙያዎች (Development Team ) :- የሪል እስቴት ዘርፍ ብዙ ሙያዎችን የሚጠቀም ዘርፍ ነው። ለምሳሌ አርክቴክቶች፣ መሃንዲሶች፣ ገንቢዎች፣ የግብይት ሂደት ውስጥ ያሉ ባለሙያዎች፣ የፋይናንስ፣ የባንኪንግ ፣ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ባለሙያዎች፣ IT ባለሙያዎች፣ የህግ ባለሙያዎች ወዘተ.... ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው ። ባለሙያዎቹ በግልም በህብረትም በየሙያቸው ያለውን ከፍተኛና ፈጠራ የተካተተበት የደንበኞችን  ፍላጎት መሰረት ያደረገ ውጤት እንዲመጣ የማድረግ ሃላፊነት አለባቸው። ለ) ቤት ዋጋ እንዲቀንስ የሚጠበቅባቸው አስተዋጽኦ የሪል እስቴት ልማትና ግብይት የተሳካ እንዲሆን ከላይ የተዘረዘሩት ባለድርሻ አካላት የሚጠብቃቸውን ያለማጓደል ሊያበረክቱ ይገባል። ለምሳሌ :- ፩) መንግስት ለአልሚዎች መሬት በቅናሽና በብዛት ካቀረበ፣  የዲዛይን ማጽደቅና ክትትል ስራውን ካሳለጠ፣ ግብይቱ የሚመራበት መመሪያና ግብይቱን የሚመራ  አካል ሰይሞ በስርዓት እንዲመራ ካደረገ፣ በርካታ ቤቶችን ለሚገነቡ አልሚዎች የግንባታ  ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ  ካደረገ። ፪) የገንዘብ አቅራቢ ተቋማት ለአልሚዎችና ለቤት ገዢዎች በቂ የሆነ የገንዘብ አቅርቦት ካደረጉ ፫) ቤት ገዢዎች ጠንክረው ሰርተው ቁጠባን ባህላቸው ቢያደርጉና እቅም ከፈጠሩ ፬) ባለሙያዎች ገበያውንና የቤት ገዢዎችን አቅምና ፍላጎት ያገናዘቡ ቤቶች የሚገነቡበትን ዲዛይን፣ ወጪ ቀናሽ የግንባታ ቴክኖሎጂ ፣ የአከፋፈል ስርዓት በጥናት ላይ በተመሰረተ ሁኔታ ካዘጋጁ ፭) አልሚዎች ዘርፉን በእውቀት በባለሙያዎች እንዲመራ ካደረጉ ሐ) መውጫ በምሳሌ ነገር ግን ከአምስቱ  አንዱ ሲያጎድል ዘርፉ ውጤታማ እንዳይሆን ሊያደርግ ይችላል በሌሎቹ አካላት ላይም ተጽዕኖን ያሳድራል ። ለምሳሌ :- ባለሙያዎች ገበያውን ያላገናዘበ ውድ ቤቶች ንድፍ ቢሰሩና የሰሩትም ቢገነባ  ቤት ገዢዎች ሊገዙት አይችሉም፣ ካልተሸጠ ባንኮች ያበደሩት ብር በወቅቱ አይመለሰም፣ የቤት ችግርን ስለማይቀረፍ መንግስት ላይ ተጽዕኖ ይፈጥራል ከልማቱ ማግኘት የነበረበትን ገቢ ያሳጣል፣ አልሚውም ይከስራል... ስናጠቃልለው የቤት ዋጋ ሊቀንስ የሚችለው በአልሚዎች ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ከላይ የተጠቀሱት አካላት የተናበበ የጋራ ተሳትፎ ሲኖር ብቻ ነው። በ ደሳለኝ ከበደ (አቶ ደሳለኝ ከበደ ሲቪል መሀንዲስ፣ ስራ ተቋራጭ፣ አሰልጣኝ እና ጸሀፊ ሲሆኑ በግንባታው ዘርፍ ላይ ሰፊ ተሞክሮ ያላቸው ባለሙያ ናቸው)
Mostrar más ...
11 338
23
5 Steps Of Load Pathway For Concrete Structures The load pathway for a concrete structure involves the transfer of loads from the point of application to the ground. Here are the typical five steps in this pathway: 1. Load Application: - Loads such as gravity loads (dead and live loads), environmental loads (wind, earthquake), and other imposed loads are applied to the structure. 2. Load Distribution: - These loads are distributed across the surface or point of application (e.g., floors, roofs) and transferred to structural elements like beams and slabs. 3. Load Transfer to Vertical Elements: - The distributed loads are transferred from beams and slabs to vertical structural elements such as columns and walls. 4. Load Transfer to Foundation: - The vertical elements, in turn, transfer the loads to the foundation of the structure. This can include footings, pile foundations, or mat foundations. 5. Load Transfer to the Ground: - Finally, the foundation transfers the loads to the ground, where they are dispersed into the soil, ensuring the stability of the entire structure. Each of these steps is crucial for maintaining the structural integrity and ensuring that the loads are safely transferred to the ground without causing failure or excessive deformation in any part of the structure.
Mostrar más ...
9 331
34
Structural behavior of cantilever beams A famous photograph by Benjamin Baker, in which through a living model the cantilever structural principle on which the solution to the Firth Bridge over the Forth was based. To illustrate the structural theory of a cantilever beam (Gerber), a human demonstration was carried out. The loads were represented by the person sitting in the middle of the span of the suspended span. The arms of the persons seated on both sides represented the traction at the joints; the wooden bars, the compression at the lower elements, and the bricks, the anchor points located at the pylons. The chairs represent the granite piles. Imagine the chairs 500 m apart and the men's heads as high as St. Paul's cross (London church, 104 m) their arms are represented by steel beams and the canes by 3.5 m diameter tubes at the base you get a good notion of the structure. Heinrich Gerber applied in 1866 a theory that consisted in subdividing the continuous beam through ball-and-socket joints "which define a point of zero bending moment". This type of beam with intermediate joints is what is now known as a Gerber beam. The position where these hinges are located allows for influencing the behavior of the beam; therefore, it is not only used directly in some structures but in some projects, a real beam can be idealized by assimilating it to a Gerber beam, whose isostatic allows a simple approximate calculation.
Mostrar más ...
8 091
12
#ተዓምረ_Dog 🐕🚀🐕🚀🐕🚀🐕 😵 በሁለት ቀናት ውስጥ 9.4 ሚሊዮን ህዝብ ተቀላቅሏል:: 🙀 Varified ነው 😳 ማድረግና የለውም (ጊዜ አይወስድም) 😻 ስትጀምሩ ቴሌግራም ላይ የቆያችሁበት ዓመት አስልቶ ይሰጣችኋል (የእኔ አካውንት ስለሆነ ከእኔ ስትጀምሩ እጥፍ ይሰጣችኋል:: የተያያዙትን እጥፍ ያገኙ Screenshot ተመልከቱ) 🙀 "Who are you dawg?" የሚል ጽሁፍ ከመጣላችሁ አካውንታችሁ የለውም ማለቱ ነው - አስገቡበት:: 🙀 ብዙ ተከታይ ያላችሁ የራሳችሁን link በማጋራት ራሳችሁንም ሌሎችንም ጥቅሙ:: 😻 ያልጀመራችሁ - ጊዜ አትውሰዱ:: በአቃራጭ የመጣ የማይደገም እድል ነው:: 👇👇👇 Who let the DOGS out?
Mostrar más ...
6 240
8
https://t.me/dogshouse_bot/join?startapp=cfb5cSz1TdO8TWlQQe0jTw Who let the DOGS out?
Join DOGS
Get rewarded with the most Telegram-native memecoin
1 406
1
የአዲስ አበባ ከተማ ሪል ስቴት ገበያ በዋጋ ደረጃ ለመስከኑ የኦቪድ ግሩፕ አስተዋፅዎ ቀላል አይደለም ። ኦቪድ ግሩፕ በሪል ስቴት ልማት ክንፉ ፣ የገነባቸው ቤቶችን በብዛት ለገበያ ማቅረቡ የሪል ስቴት ገበያው እንዲሰክን አድርጓል - ወይም ሰብሯል ። ቀደም ባሉት ወራት በዋጋ ሽቅብ ይጎን የነበረው የሪል ስቴት ገበያ የዋጋ ቅናሽ እየታየበት ነው - ዋጋውን ጣሪያ የሰቀሉ ጭራሽኑ ጠያቂ አጥተዋል ። ግዙፉ የሪል ስቴት ዘርፍ ዘገር ነቅናቂ ሆኖ የቀረበው ኦቪድ - በታሪክ ተመዝግቧል ...... ብራቮ ዮናስ ታደሰ ! በአዲስ አበባ ከተማ የሪል ስቴት የካሬ ሜትር ዋጋ ወቅታዊ ነፀብራቅ ምን መልክ ይዟል ተብሎ ቢታይ - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ባስጠናው ጥናት የአንድ ካሬ ሜትር የሪል ስቴት መገንቢያ ዋጋ ከ 30,000 ብር እስከ 40,000 ብር - አለፍ ብሎም እስከ 50,000 ብር ነው ። ነገር ግን ይህንን ዋጋ ብዙዎቹ የሪልስቴት አልሚዎች በፍፁም አይቀበሉትም ። ይልቁኑ እንደየ ሪልስቴት ግንባታው ደረጃ የሚለያይ ቢሆንም በአልሚዎች ጥናት የሪል ስቴት የግንባታ ዋጋ በካሬ ሜትር ከ 63,000 ብር እስከ 70,000 ብር ይደርሳል። የሪል ስቴት መገንቢያ ቦታ በሁለት መንገድ ይገኛል ። አንድም ከአስተዳደሩ ሁለትም ከግለሰቦች በግዥ ። ከግለሰቦች በግዥ የሚገኘው ውድ እንደመሆኑ በግንባታው ላይ የመሬት ዋጋ ፣ የሠራተኛ እና የመሳሰሉ ወጪዎች ሲጨመሩበት ዋጋውን ማናሩ አይቀርም ። ኦቪድ ግሩፕ ገበያውን ከመቀላቀሉ በፊት አብዛኛዎቹ አልሚዎች ለገበያ ያቀረቡትን ሪል ስቴት በካሬ ከ 80,000 ብር እስከ 120,000 ብር ይጠሩ ነበር - በውጭ ምንዛሪ ደግሞ በካሬ ሜትር ከ 3,000 እስከ 4,000 ዶላር ድረስ ይጠራሉ - ከዚህም በላይ ዋጋ የሚጠራላቸው ቅንጡ ሪልስቴቶች እዚህም እዚያም እንዳሉ አሉ! በአሁኑ ገበያ ግን በካሬ ሜትር 70,000 ብር እና ዙሪያውን ፣ በውጭ ምንዛሪም 2,000 እና ዙሪያውን እየተጠራ ይገኛል ። ከዚህ ባለፈም ከ10 እስከ 20 በመቶ ቅናሽ ማማለያ እየተሰጠ ነው ። በዚህ መሀል ማን ሰንጥቆ መጣ !? ለሦስት አስርት ከግንባታ ተገልሎ የቆየው የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በለውጡ ዳግም አንሰራራ - ረሻድ ከማል የሚባል ዶዘር መጣለት - ፌቤኮ ተገማች ባልሆነ መንገድ በዋና ዋና ግንባር ቦታዎች ሁነኛ ህንፃዎችን ገንብቶ ባልተጠበቀ ዋጋ ቤቶችን ገንብቶ ለገበያ ሲያቀርብ - ገበያው ከኢኮኖሚ ማንሰራሪያ ባሻገር ለብዙሃኑ ሃብት ሆነ ... ግን ግን የግልና መንግስት አጋርነት ( PPP ) ከመንግስት በ 70/30 ቀመር መሬት የወሰዱ ሪል ስቴት አልሚዎች በስንት ብር ቢሸጡት ያዋጣቸው ይሆን !? በ70 ሽህ ? መንግስት ከተገነባው ሪል ስቴት ድርሻውን ሲወስድ አልሚዎቹ የመገንቢያ ዋጋውን እንዴት አብቃቅተው አትራፊ ይሆኑ ይሆን - ልናይ ኋላ! በልዩ ሁኔታ የሚታይ ቢሆንም የፐርፐዝ ብላክ ዋጋ ሳያስደምም የሚቀር አይደለም - የፐርፐዝ ብላክ ነገር እስካሁን መጨረሻው ባይለይም አምስት ቢሊየን ብር ቦታ ገዝቶ ፤ በ 60 ቢሊዮን ብር 113 ወለል ህንፃ ከነ አጀቡ ገንብቶ - ከአክሲዮን ድርሻ ጋር ፣ መቶ ካሬ ሜትር ቤት በ 1.5 ሚሊዮን ብር ፤ ቆየት ብሎም በ3.5 ሚሊዮን ብር ሂሳብ ( በካሬ ሜትር 15,000 ብር እና 35,000 ብር መሆኑ ነው ) መዋዋሉ ከትርፋማነት ቀመር ውጭ ነው ። የአዲስ አበባ ከተማ ሪል ስቴት ዘርፍ ለመኖሪያ ፈላጊው ጥሩ አማራጭ ገበያ እንዲሆን ካስፈለገ የመሬት አቅርቦት ፣ የፋይናንስ አማራጭ ፣ የሸማች መብት ጥበቃ ወሳኝነት አላቸው - በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ቢሊየነሮች የገቡበት ዘርፍ መሆኑ ልብ ይሏል - የዚያኑ ያህልም የተካኑ ባለካልኩሌተሮችም ዘርፉን ተቀላቅለዋልና መፍዘዝ ጥሩ አይደለም !
Mostrar más ...
7 888
42
5 712
7
https://t.me/major/start?startapp=371415119 👑Help me to become best of the best in and get some Stars! 15⭐️ invite bonus for you 50⭐️ if you are Premium Major
Major
Hello, future major! Welcome to @Major⭐️ Your task is to become the best of the best in the player rating. Vote for others by stars and collect stars yourself⭐️ The coolest majors will receive a valuable token in the future!
8 487
10
የአዲስ አበባ ከተማ ኮሪደር ልማት 33 ቢሊዮን ብር እንደወጣበት ተገለፀ የአዲስ አበባ ከተማ ኮሪደር ልማት 33 ቢሊዮን ብር እንደወጣበት ተገለፀ። የኮሪደር ልማቱን ተግባራዊ ለማድረግ በተደረገ ጥናት መሰረት ከ40 ቢሊዮን ብር በላይ የበጀት እቅድ ተይዞለት የነበረ ሲሆን፤ ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ በመሰራቱ በ33 ቢሊዮን ብር እየተገባደደ እንደሆነ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግበዋል።
10 308
9
ለመሬት ረገጥ ሀብት ግዢ አንዳንድ ጥንቃቄዎች (Precautions in Real Estate Purchase) መሬት ረገጥ ሀብትን (Real Estate) ስንገዛ ማሰብና መከወን ያሉብን ቴክኒካዊ ጉዳዮች በ22 ዝርዝሮች ተቀምጠዋል።  በብዙ ሚሊዮን ብር ኢንቨስትመንት ስናደርግ እንደዚህ በጥልቀት ማየት የሚኖርብን ሲሆን፣ እነዚህ ዝርዝሮች ከአሻሻጮቹም ሆነ ከነጋዴዎቹ እውቀት በላይ በመሆናቸው ልፋት አከል ሥራዎች ሊሆኑ ይችላሉ። በተጨማሪም አብዛኞቹ መሬት ረገጥ ሀብቶች የሚሸጡት በአካል በአገር ውስጥ ለሌሉ ደንበኞች ሲሆን፣ ባለሀብቶቹ ከማከራየት ባለፈ እንደ ኢንቨስትመንት ስለሚያዩዋቸው እንደተዘረዘሩት የሚጨነቅ ገዢም ሆነ ገንቢ እንዲሁም ተከራይ አይገጥሙንም። (ያከራየኝ ሰው ቤቱንም አይቶት አያቅም ሲባል አልሰማችሁም) በቅርቡ ግን ሁላችንም በሰማይ ላይ ተንጠልጥለን መኖራችን ስለማይቀር ሁሉም ቴክኒካዊ ዝርዝሮች ሁላችንንም አንድ በአንድ እንደሚያገቡን እሙን ነው። ስለዚህ እነዚህን ጥያቄዎች ለማወቅ አልሚዎችን ስንጠይቅ እንደደፋር ተቆጥረን  "ትገዛ እንደሆነ ግዛ አንተ ምን ስለሆንክ ነው የምትጠይቀው?" አይነት መልስ ልናገኝ እንደምንችል ይገመታል። ወደ ዝርዝሩ፦ 1. የአልሚ እና የገዢ ውሉን ህግ፣ ለህግ አዋቂ ከፍሎ ማስመርመር፤ 2. የአልሚውን የበፊት የማልማት ዝናን መፈተሽ፤ 3. ከተቻለ የተገነባን  ሀብት መግዛት፤ 4. የተገነባም ሆነ ሊገነባ ያለ ከሆነ የቤቱን ፕላን በህንጻ ነዳፊ ማስመርመር፤ ( የእሳት ማጥፍያ የውሀ ስርአት ፣ የእሳት አደጋ ግዜ ማንቅያ፣ በእሳት አደጋ ጊዜ የአደጋ ማምለጫ ደረጃ እሳትና ጭስ የመቋቋም ስርዓት፣ የምግብ ማብሰያ እና መታጠብያ ቤት ሽታ ማስወገጃ፣ በቂ ተሽከርካሪ ማቆሚያ፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረግያ ወዘተርፈ መኖሩን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።) 5. የህንጻ አስተዳደር (facility management) ተገማች ወርሀዊ ወጪ ስንት እንደሆነ መጠየቅ፤ 6. የመነሻ አፈር ምርመራን፣ የግንባታ ወቅት ተከታታይ የብረት እና አርማታ ምርመራ ምስክር ወረቀትን ጠይቆ ማየት፤ 7. የኤሌክትሪክ ገመዶችና ስርዓቶችን በባለሙያ ማስመርመር፣ ተጠባባቂ ኃይል አመንጪ መኖሩን እና አቅሙን መጠየቅ፤ ቁመተ ረጅም ህንጻ ከሆነ ስለመብረቅ መከላከያ ስርአት መጠየቅ፤ 8. የፍሳሽ መስመር ላይ በተጓዳኝ የሚዘረጋ የማስተንፈሻ ቱቦ እና ስርዓት መኖሩን ማረጋገጥ (የፍሳሽ ሽታ ማስወገጃ ዘዴ) 9. ህንጻው የከተማ የፍሳሽ መስመር አጠገቡ መኖሩን ማጣራት (አለበለዝያ በየወቅቱ የፍሳሽ ማስመጠጫ ተሽከርካሪ አዋኪነትን መቀበል) 10. በቂ የውሀ ማከማቻ እና አቅርቦት ስርአት እንዳለው በባለሙያ ማጣራት። 11. የፍሳሽ ማስወገጃ የቁመት ትቦዎች የሚያልፉበት ድምጽ በማያሳልፍ  በተከለለ ቀዳዳ እንደሚያልፍ ማረጋገጥ፤ (እነዚህ ቱቦዎች በድምጽ ስለሚረብሹ በየመታጠብያ ክፍሉ ተጋልጠው መገኘት የለባቸውም) 12. ለተሽከርካሪ መንገድ ቀረቤታ ካለው የድምጽ መከላከያ እርምጃዎች ምን እንደሆኑ ማጣራት፤ 13. ለሳተላይት ርቀት ማያ (TV) ወይም ለበይነመረብ ፕሮቶኮል ርቀት ማያ (IPTV) የተዘጋጀ መስመር እንዳለው ማረጋገጥ (አለበለዝያ ሁሉም ሰው የሳተላይት ሰሃኑን ሰገነት ላይ ሰቅሎ የህንጻው መልክ እንደሚበላሽ መቀበል) 14. የተጣራ እና ያልተጣራ የሚሸጥ የቤት ስፋትን ማጣራት፣ (መተላለፍያ፣ ደረጃ፣ ተሽከርካሪ ማቆምያ ወዘተርፈ.... በነዚህ ስፋቶች መካተት አለመካተታቸውን ማጣራት) 15. የከፍታ ተሽከርካሪን (lift) የሰው የመጫን አቅምን፣  ብዛትን  እና ፍጥነትን ማጣራት። 16. የጥያራ  ማረፍያ (airport) በአካባቢው ካለ ጥያራው የሚያስነሳውን አዋኪ ድምጽ ዴሲቤል በተንቀሰቃሽ ስልክ መለካት፤ 17. አካባቢው ከቤተ እምነቶች በድምጽ ማጉልያ የሚወጡ ድምጾች እንዳሉ ማረጋገጥ፤ 18. የሚገዛው ቤት ዋና ዋና ክፍሎች አቅጣጫን ማወቅ (ለምሳሌ ወደ ሰሜን የሚከፈት ክፍል በፍጹም ፀሐይ የማያገኝ ከመሆኑ የተነሳ በአርማታ በተሰራ ህንጻ ውስጥ፣ በአዲስአበባ ከተማ አውድ እጅግ ቀዝቃዛና የሚደብት መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል) 19. የሚቻል ከሆነ አልሚው የመስኮቶች ክፍተት ላይ ትንኝ-ከላ ወንፊትን ከመስታወቶች አዳብሎ እንዲሰራ ማመላከት፤ 20. አካባቢው በቋሚነት ከሚከሰት መጥፎ ሽታ ነፃ እንደሆነ ማረጋገጥ፤ 21. ልማቱ ላይ እጅግ የበዛ አባወራ እንዲኖርበት የተነደፈ ከሆነ ወደልማቱ የሚወስዱ ተመጣጣኝ ስፋት ያላቸው መጋቢ መንገዶች እንዳሉ ማረጋገጥ፤ 22. በመጨረሻም ባለብዙ ወለል ባለብዙ መኖርያ  የጋራ መኖርያ ቤት የሚሰራ ከሆነ እና እንደ ባህላችን በቀስታ ተቁላልተው የሚሰሩ ምግቦች የሚበስሉባቸው ማብሰያ ክፍሎች የሚኖሩ ከሆነ ማብሰያ ክፍሎች ውስጥ ያለውን የሽታ ማስወገጃ ስርአት በጥልቅ መመርመር ያስፈልጋል። አንደኛ ካንዱ ቤት ወደ አንዱ ቡና እና ወጥ ሽታ እንዳንቀባበል፣ ሁለተኛው ደግሞ ሽታዎች  ከምግብ ማብሰያ ወደ መኝታ እና እንግዳ መቀበያ እንዳይገቡ ሲባል ነው። (ዳዊት በንቲ፣ መምህር እና ሕንፃ ነዳፊ)
Mostrar más ...
12 051
69
🛎 These 3 Packages will Start Tomorrow ( June 23) Morning @ 3:00 LT. 1. Advanced Structural Design 2. Bridge Design 3. Project Planning & Contract Administration 🔸Every Sunday Morning 3:00-8:00 LT. 📲 NaN / NaN 📌 Megenagna,Marathon Bldg, No. 614
10 122
5
አርኖ ሩሱቩዎሪ (Aarno Ruusuvuori 1925-1992 እኤአ) 💥የልማት ባንክ ህንጻ ነዳፊ ⚡️አርኖ ሩሱቩዎሪ ፊንላንዳዊ ህንጻ ነዳፊ፣ ፕሮፌሰር እና የፊንላንድ የኪነህንጻ ቤተመዘክር ስራአስኪያጅ ነበር። ⚡️ሩሱቩዎሪ በፊንላንድ እኤአ  በ1960ዎቹ ስመጥር ህንጻ ነዳፊ የነበረ ሲሆን ዘወትር በጥሬ ኪነህንጻ ዘይቤ (brutalism) የተጋለጡ የአርማታ ንድፎችን በዘመናዊው ፍልስፍና በመንደፍ   የሚታወቅ ነዳፊ ነበር። ⚡️አዲስ አበባ በተለምዶ ሱፐር ማርኬት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በ1960ዎቹ አጋማሽ ልማት ባንክ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሚገኙበትን በተጋለጠ አርማታ፣ በድግግሞሽ መርህ (modularization) እንዲሁም በሰፋፊ የአእማድ ርቀት የተገነባውን አስገራሚ ህንጻ ሩሱቩዎሪ ነበር የነደፈው።
10 411
2
የአዲስ አበባ ካቢኔ 3ኛ ዓመት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ካፀደቃቸው ጉዳዮች አንዱ የመንገድ ሴት ባክ (Set Back) አጠቃቀምን በተመለከተ ከላይ ያለው ይመልከቱ
11 568
46
በበአሉ ምክንያት ለነገ ሰኔ 9/2016 ሊጀመሩ ታቅደው የነበሩ የትምህርት ኘሮግራሞች ለ ቀጣይ ሳምንት ሰኔ 16/2016 ተዛውረዋል። Due to the holiday , New class schedules starting June 16/2024 are postponed to June 23/2024. Thank you all.
11 831
1
እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ኢድ ሙባረክ! Happy Eid Al-Adeha (Arefa) to all Muslims! Eid Mubarak!
11 453
0
አንድ መዋቅር ከመገንባቱ (design ከመደረጉ) በፊት የአፈርን ተፈጥሮ (አይነት) ግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው ::
11 310
11
Did you know that efflorescence and dampness in buildings usually leads to unhealthy conditions and is unsafe from structural point of view. One of the essential requirements is that the building should be dry as far as practicable. However, inorder to check the entry of water in a building, damp proof membrane be placed at various levels.
9 813
8
ይህንን ድርጊት ከsite እንዴት መከላከል ይቻላል? በህንፃው ላይ ምን ተጽእኖ ይኖረዋል? ለምንስ bend ይደረጋል? ➡️መልሱን በtiktok accountችን ይጠብቁ❗️
9 693
11
በአለም ውስጥ የመጀመሪያው የፍሬም ግንባታ በአለም የመጀመሪያው በብረት የተሰራ ህንፃ በአጠቃላይ በቺካጎ ፣ ዩኤስኤ ውስጥ "የቤት ኢንሹራንስ ህንፃ" ተብሎ ይታሰባል። 📌በመሐንዲስ እና አርክቴክት ዊልያም ለ ባሮን ጄኒ የተነደፈው በ1885 ተጠናቀቀ። 🔰የቤት ኢንሹራንስ ህንፃ የዘመናዊው ሰማይ ጠቀስ ህንፃ መወለድን የሚያመለክተው በብረት ቅርጽ የተሰራ የግንባታ ፈር ቀዳጅ ምሳሌ ነው። ❇️ይህ ፈጠራ ረጃጅም ህንጻዎችን ለማልማት መሰረት ጥሏል እና በዓለም ዙሪያ የከተማ መልክዓ ምድሮችን ቀይሯል። #ConstructionHistory
8 633
4
https://t.me/hAmster_kombat_bot/start?startapp=kentId371415119 Play with me, become cryptoexchange CEO and get a token airdrop! 💸 2k Coins as a first-time gift 🔥 25k Coins if you have Telegram Premium
Hamster Kombat
Just for you, we have developed an unrealistically cool application in the clicker genre, and no hamster was harmed! Perform simple tasks that take very little time and get the opportunity to earn money!
1 382
0
join our tiktok channel
9 895
3
https://vm.tiktok.com/ZMre3pNM9/
619
0
Plastering ➡️is coating which may apply by thin successive layers on a vertical supports of masonry or concrete with a decorative and/or protection aim or to standardize a surface need to support another coating (paint for example). And plastering worker is a worker who works the mortar covering on walls and usually builds work where the cement or the lime is one of the main constituent. Before starting plastering the structure which is required for plastering should chiseled used for surface to holding the mortar but in the case of ribbed slab no need of chiseling because HCB can trap the mortar easily. Plastering work has three coats (layers):- 1,First coat “berarigirf” 🔸Mix proportion, 1:4 (cement sand by volume with sufficient water) of mortar 🔸Spread by trowel & allowed to cure for 24 hrs before applying second coat. 🔸Has thickness of 0.5 – 1 cm , which is plastered by mortar 2,Second coat “mulet” 🔸This layer is about 1.5cm-2.5cm which is done by mortar 🔸Mix ratio is 1:4 (cement: sand by volume) 🔸Set for 21days, before third coat started. 3,Third coat (fine coat) “feno” 🔸Mix ratio is 1:1 (one bag cement and one box of sand) 🔸Which is done to make the slab, wall & column smooth 🔸The sand for this task should be sieved to make smooth Plastering of slab was started after leveled by” gomawuhalik” then make align by string with the needed thickness this is called locally “fasha”. Thickness for fashais take from10 up to 15-cm. In case of quantifying the plastering work all works except the gutter measured in meter square (m2) and the gutter is in meter linear ✅Requirements of good plastering 🔸It should provide smooth, non-absorb ante and washable surface. 🔸It should not contract in volume while drying and setting. 🔸It should adhere firmly to the surface and resist the effect of weather.
Mostrar más ...
9 042
57
1
0
New 2 Months Package Class Schedule : 1. Advanced Structural Design 2. Bridge Design 3. Project Planning & contract Administration 🔸Every Sunday Morning 3:00-8:00 LT.Registration is active Class starts on June 16/2024 📲 0911890392 / 0920933016 📌 Megenagna,Marathon Bldg, No. 614 Course outlines are here👇
8 800
8
Please fill this mini form(3 questions )to show your interest areas. 👇
BeGet Eng. June 16/2024 Starting Class Registration Form
BeGet Engineering Solutions PLC Students Registration Form:
8 278
1
ታሪካዊ የከተማ ቦታ እድሳት ✅ታሪካዊው 70 ደረጃ እየታደሰ ነው በአፄ ምኒልክ ዘመን በአርመኖች አርክቴክቶች የተገነባው በራስ መኮንን ድልድይ ዙሪያ የሚታየው የ70 ደረጃ ደረጃዎች እድሳት እየተደረገላቸው ነው።
10 397
5
የቱ ጋር ነው የተሸወድነው? የመጀመሪያው በአውስትራሊያ ሲድኒ ከተማ፣ ሁለተኛው ደግሞ በሎስ አንጀለስ ከተማ ሦስተኛው አድስ አበባ ውስጥ ለመንገደኞች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የኤሌክትሪክ ባቡሮች ናቸው። አንዳንዴ በውጪ ሀገራት ቀለል ብለው የተገነቡ የከተማ ባቡሮችን ስንመለከት እዚህ በአዲስ አበባ በተካበደ ሁኔታ ተገንብቶ ከጥቅሙ ባሻገር ብዙ መዘዝ ያመጣ እንዲሁም ቅሬታ የሚቀርብበት ባቡራችን ግርምትን ነው የሚፈጥረው
7 050
8
What is Fibre-reinforced concrete Fibre-reinforced concrete (FRC) is concrete that has fibrous materials mixed in to increase the concrete's durability and structural integrity. FRC has small, short, and discreet fibres that are randomly oriented yet uniformly distributed throughout the concrete. The fibres can be circular or flat, and often makeup one to three per cent of the concrete mix's total volume. Common fibres used in reinforced concrete include steel, glass, synthetic, and natural fibres. Why fibres are used? On its own, concrete lacks tensile strength and is prone to cracking. But fibre-reinforced concrete can improve tensile strength and control cracking in concrete structures that are often caused by plastic shrinkage and drying shrinkage. Fibres in concrete can also reduce the permeability of concrete, which limits the amount of water that bleeds out, further reducing shrinkage cracking during curing. The necessity of Fiber Reinforced Concrete 1- It increases the tensile strength of the concrete. 2- It reduces the air voids and water voids the inherent porosity of gel. 3- It increases the durability of the concrete. 4- Fibers such as graphite and glass have excellent resistance to creep, while the same is not true for most resins. Therefore, the orientation and volume of fibres have a significant influence on the creep performance of rebars/tendons. 5- Reinforced concrete itself is a composite material, where the reinforcement acts as the strengthening fibre and the concrete as the matrix. It is therefore imperative that the behaviour under thermal stresses for the two materials be similar so that the differential deformations of concrete and the reinforcement are minimized. 6- It has been recognized that the addition of small, closely spaced and uniformly dispersed fibres to concrete would act as crack arrester and would substantially improve its static and dynamic properties. Types of Fibers : 1- Steel fibres 2- Glass fibres 3- Carbon Fibers 4- Cellulose Fibers 5- Synthetic Fibers 6- Natural Fibers Advantages Of Fibre Reinforced Concrete : 1- High modulus of elasticity for effective long-term reinforcement, even in the hardened concrete. Does not rust nor corrode and requires no minimum cover. 2- Ideal aspect ratio (i.e. the relationship between Fiber diameter and length) which makes them excellent for early-age performance. 3- Easily placed, Cast, Sprayed and less labour intensive than placing rebar. 4- Greater retained toughness in conventional concrete mixes. 5- Higher flexural strength, depending on the addition rate. 6- Can be made into thin sheets or irregular shapes. 7- FRC possesses enough plasticity to go under large deformation once the peak load has been reached. 8- Increased durability and high flexural rigidity. 9- Reduced permeability, bleeding, and formation of microcracks. 10- Minimum weathering effect. 11. Reduces deflection. 12. Minimum corrosion. Disadvantages Of Fibre Reinforced Concrete: 1- Fibres are costly. 2- The fibres should be uniformly distributed in concrete because they may not mix well and form lumps. 3- The size of the coarse aggregate is restricted to 10 mm. 4- Mixing of fibres in large volume could be tedious. 5- Construction with FRC skilled labours.
Mostrar más ...
8 083
35
6 923
3
ፅድት_ያለች_ካድ_app ካድ_ፋይል_በስልካችሁ_ለመክፈት ለተቸገራችሁ አንድ ፅድት ያለች ይዠላችሁ መጥቻለሁ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን በማውረድ ሳይት ላይ ለምትሰሩም እሱን መጠቀም ትችላላችሁ❗️ Check out "DWG FastView-CAD Viewer&Editor"
DWG FastView-CAD Viewer&Editor - Apps on Google Play
* Convert any drawing to PDF/JPG file offline, Fully compatible with AutoCAD!
10 490
35
በሲሚንቶ ኮንክሪት የሚገነቡ መንገዶች በመላው አለም ተመራጭነታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። ኢትዮጵያን ለመሳሰሉ ከፍተኛ የመንገድ መሠረተ ልማት ለሚያካሂዱ ሀገሮች ደግሞ በሲሚንቶ ኮንክሪት የሚገነቡ መንገዶች አዋጪ መሆናቸው ሳይታለም የተፈታ ነው። በተለይ ኢትዮጵያ በከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ ለአስፋልት ኮንክሪት የሚሆን ቢቱሜን (ሬንጅ) ከውጪ ከማስመጣት፣ ሲሚንቶን በስፋት አምርታ ተጠቃሚ መሆን ትችላለች። በመጪዎቹ ወራትም በኢትዮጵያ በቀን 10 ሺህ ቶን ሲሚንቶ የሚያመርት ግዙፍ ሲሚንቶ ማምረቻ ፋብሪካ ወደ ሥራ ይገባል። አሁን በቅርቡ ህንድ እንኳን፣ ከሙምባይ እስከ ናግፑር ከተማ 700 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ስድስት ሌን ያለው የፈጣን መንገድ ግንባታን በሲሚንቶ ኮንክሪት ገንብታ ለምርቃት ዝግጁ ማድረጓ እየተሰማ ነው። በህንድ በ2018 የመሠረት ድንጋይ ተቀምጦለት የነበረው የዚህ መንገድ ጅምሮ በመጪው ሰኔ ይመረቃል። ይህ በሲሚንቶ ኮንክሪት የተገነባው መንገድ ላይ 33 ትላልቅ ድልድዮች፣ 274 አነስተኛ ድልድዮች እና 6 የዋሻ ውስጥ መተላለፊያዎች እና ሌሎች 65 ተሻጋሪ መንገዶችን ያቀፈ ነው። በሲሚንቶ ኮንክሪት የሚገነቡ መንገዶች፣ በአስፋልት ኮንክሪት ከሚገነቡ መንገዶች ይልቅ ተመራጭ እየሆኑ የመጡት፣ በሲሚንቶ የሚገነቡ መንገዶች ረጅም አመት ስለሚቆዩ ነው። በዚያም ላይ በሲሚንቶ ኮንክሪት የሚገነባ መንገድ የጥገና ወጪም የለበትም።
Mostrar más ...
8 724
11
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ተስፋዬ ወፍጮ ቤት እየተባለ በሚጠራ አካባቢ እየተገነባ ባለ ህንጻ የአፈር ናዳ መከሰቱ ተነገረ፡፡ 🚧ህንጻ ለመገንባት የአፍር ቁፋሮ እያደረጉ የነበሩ በርካታ ሰራተኞች የአፍር ናዳው እንደተናደባቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ለጣበያችን ተናግረዋል፡፡ ✳️ከአፈር ናዳው እስካሁን ድረስ አንድ ሰው ብቻ ማውጣት እንደተቻለ የገለጹት ነዋሪዎቹ በቦታው ያለው ነገር የሚያሳዝን ነው ብለዋል፡፡ 🔰የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ሰራተኞች ባሁኑ ሰአት በቦታው መገኝታቸቀው የተነገረ ሲሆን ሰራተኞቹን ለማዳን ብርቱ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ⏺የአፈር ናዳው የደረሰው ህንጻው ከህንጻው አጠገብ ባሉ መኖርያ ቤቶች መሆኑ ነው የተነገረው፡፡ #FirstSafety
8 712
3
በአፍሪካ ረጅሙ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ነው።  ✨ Iconic Tower ይባላል፤ ቁመት 400 ሜትር ሲሆን፣ 77 ወለሎች አሉት።  ጠቅላላ የወለሎቹ ስፋት ደግሞ 250 ሺህ ስኩዌር ሜትር ነው። ይህ ሕንፃ በግብጽ ከዋና ከተማዋ ካይሮ ወጣ ብሎ ከተገነባው አዲሱ የአስተዳደር ዋና ከተማ ውስጥ ከተገነቡ 20 ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን፣ በአመዛኙ የቢሮ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ታውቋል።
7 738
8
ፕሪ እስትረስድ ኮንክሪት ኮንክሪቱ ላይ ሎድ ከመጫኑ በፊት Axial Compressive Stress አፕላይ ይደረግባቸል። ✨ለምሳሌ አንድን ቢም ከጎንና ከጎን Compressive ፎርስ ስናደርግበት የ ‹‹ በ ›› ፊደል አይነት ቅርፅ ይኖረዋል (ሲጋነን) ኢሄ የታጠፈው ቢም እላዩ ላይ ሎድ ሲጫንበት ቢሙ ወደ ነበረበት ቦታው ይመለሳል:: እንደዛ ነው pre-stressed ኮንክሪቶች act የሚያደርጉት PSC Vs RC RC beam ላይ ለዲዛይን assume ስናደርግ ኮንክሪቱ ምንም አይነት tensile stress አይሸከምም - tensile እስትረሱን የሚሸከመው ፌሮው ነው ብለን ነው ሌላው assumption ፌሮው ቴንሽኑን ይሸከማል ብንልም የፌሮውን አቅም fully utilize አናደርገውም ወይም ደሞ ሙሉ ለሙሉ አንጠቀምበትም የዚህም ምክንያቱ ኮንክሪቱ ቴንሽን ዞን ውስጥ የሚከሰተውን Crack width ለመገደብ ወይም limit ለማድረግ ነው። ከላይ በተገለፁት ሁለት ምክንያቶች ማለትም የኮንክሪቱንም የፌሮውንም አቅም ሙሉ ለሙሉ ባለመጠቀማችን የተነሳ ለትልልቅ ሎዶች RC ከ PSC አንፃር ኢኮኖሚካል አይደለም። የዚህም ምክንያቱ የ RCን አቅም ሙሉ ለሙሉ ስለማንጠቀምበት ነው በተጨማሪም RC ላይ ትልልቅ Grade ያላቸው ኮንክሪትና ፌሮ መጠቀማችን ብዙም ዋጋ የለውም ከ RC ድክመት ለመዳን Pre-Stressed ኮንክሪቶች ተፈጠሩ ከRC በተሻለ መልኩ የኮንክሪቱንና የብረቱን እስትሬንግዝ ይጠቀማሉና። ✨Methods of Prestressing 1) Pre tensioning👇 A, ቢሙን ካስት ማድረጊያ mold እናዘጋጃለን። B, ሞልድ ውስጥም PSC ኬብሎች ወይም tendon እናስቀምጣለን C, እነዚህ ኬብሎችም ላይ Tensile ፎርስ apply እናደርጋለን D,አፕላይ እንደተደረገ ኮንክሪቱን ሞልድ ውስጥ አስገብተን ኮንክሪቱን ካስት እናደርጋለን E, ኮንክሪቱ ሲደርቅ ፎርሶቹን remove እናደርጋለን ቢሙም ዝግጁ ሆነ ማለት ነው:: 2) Post tensioning እዚህ ላይ ኮንክሪቱ ከደረቀ በኋላ ነው Compressive force አፕላይ የምናደርገው Apply የሚደረጉት ፎርሶች ኮንክሪቱ ላይ compressive stress ሲፈጥሩ ብረቱ ላይ ደሞ tensile stress ይፈጥራሉ ማለት ነው:: 😱Join our TikTok channel 👇
Mostrar más ...
8 408
39
https://t.me/tapswap_mirror_1_bot?start=r_371415119 🎁 +2.5k Shares as a first-time gift
2 686
4
6 688
5
5 914
2
አዲሱ የአባይ ወንዝ ድልድይ የድልድዩ_ግንባታ_ስራ፡- 📌ከድልድዩ ግንባታ ጎን ለጎን  ተያያዥ የኮንክሪት ስትራክቸር ስራዎችና፣ የተሽከርካሪ መወጣጫ /ramp/ ፣ የትራፊክ ምልክቶች፣ የድልድይ ላይ መብራቶች ስራም ያካተተ ነው ፡፡ ይህ ድልድይ ኤክስትራ ዶዝድ የሚባል ስያሜ የተሰጠው ተንጠልጣይ ድልድዮች (ሰስፔንሽን) ከሚባሉት ድልድዮች የተለየና ይልቁን የመኪና ተሸካሚው ዴክ ከፊትና ከሁዋላ ከግራና ከቀኝ በ18 ኬብሎች በአጠቃላይ በ72 ኬብሎች (በገመዶች የተወጠረ) ሆኖ ጠቅላላ ክብደቱ በገመዶቹ አማካይነት ወደ ቋሚው ምሰሶ የሚተላለፍና ከምሰሶውም ወደ መሰረቱ የሚዘልቅ ነው፡፡ ☄ይህ አይነቱ ድልድይ የረጃጅም ኬብል ስቴይድ (በገመድ የተወጠረ) ድልድዮችና  የረጃጅም ቦክስ ገርደር አይነት ድልድዮች ውሁድ ሆኖ ስፋታቸው ከ 250 ሜትር እከ 500 ሜትር በሚደርሱ ወንዞች ላይ አመቺና ወጪ ቆጣቢ ሆነው እንዲሰሩ በመጀመሪያ በፈረንሳይ ሀገር የተፈለሰፈ በቀጣይ ግን በብዛት ጃፓን ሀገር ስራ ላይ የዋለ የድልድይ አይነት ነው፡፡ ☄የተጠናቀቀው የድልድዩ የምህንድስና ሰነዶች እንደሚያመለክቱት የቋሚው ምሰሶ ከመሰረት በላይ (piers) 7 ሜትር  ከፍታ እና ታወሩ 27 ሜትር ከፍታ ሲኖረው ከውሀና ከመሬት በታች እስከ 24 ሜትር ጥልቀት ባላቸው በርካታ ፓይሎች የተዋቀረ ነው፡፡ ✅ለድልድይ ግንባታው ጥቅም ላይ የዋሉ ✳️የተለያዩ የጥንካሬ ደረጃ (Grade C-30, C-40, C-50, and C-55) ያላቸው አርማታ 54,138.68 ሜ.ኩ ✳️የተለያዩ ስፋት እና የጥራት ደረጃ ያላቸው የአርማታ ብረት 9,241.45 ቶን ✳️የተለያዩ ስፋት እና የጥራት ደረጃ ያላቸው የማንጠልጠያ  እና መወጠሪያ 474.37 ቶን   👍የድልድይ ግንባታ ሥራውን ከዚህ ቀደም በሀገራችን ከተሠሩት 🔰የወንዙን አቅጣጫ የማስቀየስ ሳይከናወን በሀገራችን ብዙም ያልተለመደ እና አዲስ ቴክኖሎጅ (ማለትም ተንሸራታች የሆነ ብረት የድልድይ አቃፊ) ግብዓት በመጠቀም መሠራቱ 🔰ድልድዩ በከተማ ውስጥ እንደመሠራቱ የትራፊክ ፍሰቱን ከማሳለጥ ባሻገር የቱሪሰት መስህብ እንዲሆን ታሳቢ ተደርጎ የአካባቢውን ማህበራዊ፣ ተፈጥሮአዊ እሴቶችን በማገናዘብ ቅንጡ ተደርጎ መሠራቱ 🔰በድልድዩ መወጠሪያ ገመዶች ላይ የተለየ መስተጋብር መስጠት የሚችሉ መብራት የተገጠመ መሆኑ ይገኙበታል፡፡ ❇️ ⏺በአሁኑ ወቅት ከአቅሙ በላይ አገልግሎት  በመስጠት ላይ የሚገኘውን  ነባሩ የአባይ ወንዝ ድልድይ ላይ ይደርስ የነበረውን  የትራፊክ መጨናነቅ እና ጫና ያስቀራል፡፡ ⏺ለሀገሪቱ የገቢ ወጪ የንግድ እንቅስቃሴም የበኩሉን አስተዋጽዖ ያበረክታል። ⏺ድልድዩን ለሚያቋርጡ እግረኞች የትራፊክ አደጋ ሳያሰጋቸው በተዘጋጀላቸው 5 ሜትር ስፋት ባለው መሄጃ ላይ በመጠቀም  ከስጋት ነጻ  ያደርጋቸዋል፡፡ ⏺ብስክሌት ለሚጠቀሙ የአካባቢው ነዋሪዎችም ሆኑ ቱሪስቶች  ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። ⏺በተጨማሪም በባህርዳር ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቅረፍ የበኩሉን ሚና ይጫወታል፡፡ ☄ብዙ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች ላላት ባህርዳር እና አካባቢዋ  አዲሱ ድልድይ እራሱን የቻለ የቱሪስት መስህብ በመሆን አዎንታዊ ሚናውን ይወጣል፡፡ 📌አንዱን አካባቢ ከሌላው ጋር በማስተሳሰር የምርትና የሸቀጥ ልውውጥን ያለእንግልት በቀላሉ እንዲያከናወኑም ይረዳል ፡፡
Mostrar más ...
Ethio Construction
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም 👷‍♂እናማክራለን 🏢ዲዛይን እናደርጋለን 📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን 🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን 📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም tiktok https://www.tiktok.com/@ethiocons ለሃሳብ እና ኣስተያየት @Ethiocon143bot ይጠቀሙ
8 344
12
6 257
16
ትኩረት ለአካል ጉዳተኞች
5 779
3
በጥቂት ቀናት ውስጥ በጃፓን አሮጌውን መንገድ ለመጠገን አዲስ ድልድይ ለመገንባት ተችሏል። 🏗ይህ ሊሆን የቻለው በጃፓን ውስጥ ብቻ ነው ! Via:- infera Ethiopia
6 265
6
አሳዛኝ_ዜና ኢዩኤል ታዬወርቅ ሸዋታጠቅ ይባላል ተወልዶ ያደገው አዲስአበባ ኬንያ ኢምባሲ ከፍ ብሎ ልደታ ቤተክርስቲያን አካባቢ ነው። እዩኤል (አቢቲ) በጎንደር ዩኒቨርስቲ የኪነህንፃ ኢንጅነሪንግ 5ኛ ዓመት ተማሪ ነበር። የፋሲካ በዓልን አያቱ ጋር አክብሮና እዛው ሲጫወት አድሮ በማግስቱ ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ከመጣ ታናሽ ወንድሙ ጋር ወደቤተሰቦቹ ቤት ሲመለስ ኬንያ ኢምባሲ አካባቢ እየተሰራ ከሚገኝና 14 ፎቅ እርዝመት ካለው ፎቅ ላይ ተወርውሮ የወረደ ብረት ጭንቅላቱ ላይ መቶት በአበባነት እድሜው በአሳዛኝ ሁኔታ ተቀጥፏል። #FirstSafety
6 841
13
✅አዳማ‼ በአዳማ ከተማ ለሕንፃ ግንባታ ጉድጓድ በመቆፈር ላይ በነበሩ ሰራተኞች ላይ አፈር ተደርምሶ የሁለት ሰራተኞች ህይወት ማለፉን የከተማው ዋና ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡ በመምሪያው የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ እንደገለጹት አደጋው ትናንት በከተማው ደጋጋ ወረዳ ልዩ ቦታው ቀጠና አራት አካባቢ የደረሰ ነው፡፡ በአደጋው ህይወታቸው ካለፉት በተጨማሪም ሌሎች ሁለት የጉልበት ሰራተኞች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው የሕክምና እርዳታ  እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ሀላፊው ተናግረዋል፡፡ ሕንፃ አሰሪዎች ለሚያሰሯቸው ሰራተኞች የስራ ደህንነት ሊጠብቁና  ዋስትና ሊሰጡ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
6 004
16
4 906
12
✅እንኳን ለትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ! በዓሉ የደስታ እና የሰላም እንዲሆንላችሁ እንመኛለን:: መልካም በዓል!
2 515
3
L- connection of tie beam 1- Rebars must cross like the fingers of a hand. 2- Put an additional rebar around the outer corner. 3- Extend hooked bars from the inside to the outside.
7 451
12
Advance payment ለምን ይከፈላል? ✨በውል ላይ ካልተቀመጠ advance መከፈል ግዴታ አይደለም ነገር ግን FIDIC አንቀጽ 14.2 ላይ Advance ለስራ ተቋራጭ የሚከፈል ከወለድ ነፃ የሆነ ብድር መሆኑን ይገልፃል:: ይህም ማለት  ተቋራጭ advance ካልተከፈለው በራሱ ገንዘብ ስርቶ payment ሲጠይቅ ግን ወለዱን የመጠየቅ መብት ይኖረዋል::
Ethio Construction
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም 👷‍♂እናማክራለን 🏢ዲዛይን እናደርጋለን 📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን 🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን 📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም tiktok https://www.tiktok.com/@ethiocons ለሃሳብ እና ኣስተያየት @Ethiocon143bot ይጠቀሙ
6 701
16
Última actualización: 11.07.23
Política de privacidad Telemetrio