አርሰናል ከ ቶተንሃም !
አርሰናል እና ቶተንሃም ሁለቱም በፕሪሚየር ሊጉ ቶፕ 4 ውስጥ ሆነው አራት ጊዜ ብቻ የተገናኙ ሲሆን አርሰናል 2ቱን ሲያሸንፍ 2ቱን አቻ ወጥተዋል።
አርሰናል ከቶተንሃም ጋር በሜዳው ካደረጋቸው ካለፉት 9 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ጎል ሳያስተናግድ መውጣት የቻለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።
አርሰናል በሁሉም ውድድሮች ከቶተንሃም ጋር በሜዳው ካደረገው ካለፉት 29 ጨዋታዎች በ27ቱ አልተሸነፈም።
ቶተንሃም ባደረጋቸው ያለፉት 6 ጨዋታዎች ላይ ቢያንስ 2 ጎሎችን ያስቆጠረ ሲሆን በፕሪምየር ሊጉ ያደረጋቸውን ያለፉትን 4 ጨዋታዎች ደግሞ ማሸነፍ ችሏል።
ሶን ሄንግ ሚን ከአርሰናል ጋር ባደረጋቸው ያለፉት ሰባት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ አራት ግቦችን አስቆጥሮ ሁለት ተጨማሪ ጎሎችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።
"Share"
@dynamicsport
@dynamicsportMostrar más ...