Xizmat sizning tilingizda ham mavjud. Tarjima qilish uchun bosingO'zbek
Best analytics service

Add your telegram channel for

  • get advanced analytics
  • get more advertisers
  • find out the gender of subscriber

всі пости ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች፣ ስንክሳር፣ መዝሙራትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም አስተያየት  @Zimaredawitmessanger  ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል። ስለሚሰጡን ገንቢ ሃሳብ እናመሰግናለን። YouTube Page -  https://bit.ly/2O1Z3d8  Facebook Page -  https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR  
Показати весь опис
140 875+9
~19 498
~3
14.38%
Загальний рейтинг Telegram
В світі
7 650місце
із 78 777
У країні, Ефіопія 
47місце
із 396
У категорії
152місце
із 2 333
Архів постів

[object Object]

[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
0
Анонімне голосування
5 063
20
ሰላም ውድ የዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች እንደምን ዋላችሁ? እግዚአብሔር ይመስገን። መንፈሳዊ የዜማ መስሪያ ወይም ስቱዲዮ ያላችሁ ወንድሞች በውስጥ በኩል መልዕክት ይላኩልን። የምታውቁም ካለችሁ ጠቁሙልን
5 185
3
ይላል አንደበቴ ይላል አንደበቴ እግዚአብሔር ቅዱስ ነው አይተወኝምና ወላጅ እንደሌለው ትናንት የጠበቀኝ የነገም ተስፋዬ ትልሃለች ነፍሴ ፍቅር ነህ ጌታዬ አዝ የትናንት ሕይወቴን ዞር ብዬ ሳየው ማምለጫ የሌለው አጥሩም እሾህ ነው ወደ እረፍቴ ወጣሁ ይድረስ ምስጋናዬ ደጆች ቢዘጉብኝ በር ሆኖኝ ጌታዬ (2) አዝ በጥልቁ በረሃ ምግብ መጠጥ ሆኖኝ መንገዴን አቀናው እጄን በአፌ አስጫነኝ በእሳትና ውሃ መካከል አልፌ ተመስገን እላለሁ ቅኔ ሞልቶት አፌ (2) አዝ የብቸኝነቴን ማዕበል ገስጿል ለእኔ ብርሃን ሆኖ ለከሳሽ ጨልሟል ቀስቱን እያጠፈ ታደገኝ ከስቃይ የጌታዬ ሃሳብ ፍቅር ነው በእኔ ላይ (2) አዝ ትናንት ዛሬ ነገ ዘላለም ጠባቂ የልቤን ፍላጎት ሳልነግረው አዋቂ በባሕርይው ቅዱስ የሌለው አምሳያ ስሙ ወደቤ ነው መልህቄን መጣያ ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

ይላል_አንደበቴ_Yilal_Andebete_ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ.m4a

9 036
129
መስከረም ፲፩ በዚህችም ቀን በእስክንድርያ አገር ትህትናን ገንዘብ ያደረገች ቅድስት ታዖድራ አረፈች። ቅድስት ታዖድራ እድሜዋ በደረሰ ግዜ ወላጆቿ ያመጡላትን ባል እሺ ብላ አገባች። በሥጋ ወደሙም ተወስነው ኖሩ። አንድ ቀን ግን ከቤተክርስቲያን ስትመለስ፤ በመልኳ ምክንያት ለኃጢአት ይፈልጋት የነበር አንድ ጎረምሳ ያዛት። በአቅምም አልቻለችውም፤ የሚፈልገውንም አድርጎ ከክብር አሳነሳት። ታላቅ ኀዘን አዘነች፤ መሪር የሆነ ልቅሶንም አለቀሰች። የወንዶችንም ልብስ ለብሳ ወንድ መስላ ስሟንም ቴዎድሮስ በማለት በወቅቱ የሴቶች ገዳም አልነበረምና የወንዶች ገዳም ገባች። የምንኩስና ልብስንም ለበሰች። ሰይጣን ግን ፈተናውን አጸናባት። በአንድ ወቅትም አንድ ወንድ ከአንዲት ብላቴና ጋር አመነዘረ፤ እርሷም ወንድ ልጅ ወለደች። ወላጆቿም ድንግልናሽን ያጠፋው ማነው ብለው ጠየቋት። ሰይጣንም በእርሷ አድሮ፤ በገዳም ውስጥ የሚኖር አባ ቴዎድሮስ የሚባል ነው አለች። ወላጆቿም የተወለደውን ልጅ ወስደው ለገዳሙ አበምኔት የአባ ቴዎድሮስ ልጅ ነው ብለው ሰጡት። አበምኔቱም ቅድስት ታዖድራን ልጁን አስይዘው ከገዳም አባረሯት። በበረሀም በብዙ ፈተና ሰባት አመት ኖረች። በኋላም ዳግመኛ ተቀብለው ወደ ገዳም አስገቧት። ጥቂት ቀንም ኖረች፤ መልካም ተጋድሎዋንም ፈጽማ በዚህች እለት አረፈች። በረከቷ ይደርብን! አሜን ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
11 016
42
በብርሃን ፀዳል በብርሃን ፀዳል ተከባ እመቤቴ በደመና ዙፋን ተቀምጣ ከፊቴ የፅጌውን ዜማ ስንዘምር በደስታ በምስጋናሽ መጠጥ ሲሰማኝ እርካታ/2/ አዝ እንባዬ ሲቀዳ ናፍቆትሽ መስጦኝ ከደስታ በላይ አንቺን ስላየሁኝ ምኞቴ ተሳክቶ ፊትሽን አይቼው የሌሊቱ ሕልሜ የቀን ምኞቴ ነው/2/ አዝ እሩሩህ ነሽና ይህ ህልሜ ተሳክቶ አመስግኜሽ ድንግል ህሊናዬ እረክቶ ልጅሽ ልሁን ድንግል ከስርሽ አልጥፋ አንቺን በማመስገን ሕሊናዬ ይትጋ/2/ አዝ ልጅሽ ልሁን ድንግል ከስርሽ አልጥፋ አንቺን በማመስገን ህሊናዬ ይርካ የምስጋናሽ ብዕር ብራናሽ ልሁን ስምሽ ይጻፍብኝ በልዩ ሕብር/2/ ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️

በብርሃን_ፀዳል_Be_Berhan_Tsedal_ሊቀ_መዘምራን_ይልማ_ኃይሉ.m4a

9 943
117
​​ንስሐ ንስሐ ማለት ሐዘን፣ፀፀት፣ ቁጭት፣ ቀኖና፣ የኃጢአት ካሣ ማለት ነው፡፡ ንስሐ አንድ ሰው በሠራው ጥፋት፣ ባደረገው ስህተት፣ በፈጸመው ኃጢአት ማዘኑና መፀፀቱን ዳግመኛም ያንን የመሰለ ኃጢአት ላለማድረግ የሚወስነው ውሳኔ ነው፡ ንስሐ የመንግሥተ ሰማያት መግቢያ በር ነው፡፡ በሌላ አገላለፅ ደግሞ ንስሐ ማለት  ወደ እግዚአብሔር መመለስ፣ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ፣ ከኃጢአት መራቅ፣ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት መመለስ ነው።   ንስሐ ለመግባት ስናሳብ ከታች የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ማሟላት አለብን፦ 1. በአጥቢያችን ከሚገኝ ቤ/ክ  ክህነት ያላቸው በአገልግሎት ላይ ያሉ መልካም መንፈሳዊ ምግባር ያለቸውን አባቶች የንስሐ አባት መያዝ፤ 2. የሰራነውን ኃጢአት ማመንእና በሰራነው ኃጢአት ከልብ አብዝተን መፀፀት፣ማዘንና ማልቀስ፤ 3. እግዚአብሔር ይቅር እንዲለን በፍጹም ትህትና ራስን በማዋረድ መጠየቅ፤ 4. ከእኛ ኃጢአት ይልቅ የእግዚአብሔር ቸርነትና ይቅር ባይነት እንደሚበልጥ እና ይቅር እንደሚለን ያለጥርጥር ፍጹም ማመን፤ 5. ወደ ንስሐ አባታችን ሄደን ንስሐ ለመግባት እና ቀኖናችንን ለመቀበል ማሰብ እና መወሰን፤ 6. ከልጅነት እስከ ዕውቀት የሰራናቸውን ኃጢአቶች ለማስታወስ መሞከር ከተቻለም ለማስታወስ ይረዳን ዘንድ በጽሑፍ መያዝ፤ 7. ዳግም ወደ ሰራነው ኃጢአት እንደማንመለስ ለራሳችን ቃል መግባትና መወሰን፣ኃጢአትን መጸየፍ፤ 8. ወደ ንስሐ አባታችን ሄደን የሰራነውን ኃጢአት ሳንደብቅ በግልፅ መናዘዝ። 9.የሚሰጠንን ቀኖና በትክክል መተግበር፤ 10. ዳግም ወደ ኃጢአት እንዳንመለስ ራሳችንን በቃለ እግዚአብሔር ማነጽ፤ 11. ዳግመኛ ለንስሐ መዘጋጀት። ንስሐ ከሚደገሙ ምስጢራት መካከል አንዱ ነው። ሰዎች እንደመሆናችን በተደጋጋሚ በኃጢአት እንወድቃለን ስለዚህ በተደጋጋሚ ንስሐ ልንገባ ይገባናል ማለት ነው። ኃጢአት ለንስሐ አባት መናዘዝ ለምን አስፈለገ? ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያዘዘው ትዕዛዝ ስለሆነ ነው። ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፡ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለመንጻትህ ሙሴ እንዳዘዘ መሥዋዕት አቅርብ አለው። ሉቃ.፭፥፲፬ ንስሐ ከገባን ቀኖናችንን በስርዓቱ ከፈፀምን በኋላ ንስሐችንን ፍፁም የሚያደርገው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል ነው። ዮሐ 6፥33 ብዙዎቻችን መቁረብን እንደ ትርፍ ነገርና በዕድሜ የተገደበ ለአዛውንቶች ብቻ አድርገን ስለምንቆጥር ለመቀበል ዝግጁ አይደለንም። ነገር ግን ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ቅዱስ ቁርባን የግድ ያስፈልገዋል። ቀኖና የተቀበልንበት በደላችን የሚሰረየው ሥጋውን ስንበላ፣ ደሙንም ስንጠጣ ነውና። ንስሐ ገብተን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ለመቀበል ያብቃን። አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
image
12 227
186

[object Object]

[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
0
Анонімне голосування
12 102
18
ሰባቱ መንጦላይት ሰባቱ መንጦላይት ወዴት ተጋረዱ ሰባቱ መብራቶች ወዴት ተሰናዱ ታናሽ ሙሽራ ነሽ የአሥራ አምስት ዓመት በአንቺ ላይ ሲፈጸም እንግዳ ሥርዓት አዝ አንዴ እየታጠቀ አንዴም እየፈታ ገብርኤል ሲያበስርሽ በፍጹም ሰላምታ ይኩነኒ ብለሽ ስትቀበይው መለኮት እንዴት ነው የተዋሐደው ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል    አዝ ሁሉን የሚወስን ባንቺ ተወሰነ ከሦስቱ አካል አንዱ ቃልም ሥጋ ሆነ ስፋት እና ጥበት ሰማይ እና ምድር ባንቺ ተገናኙ ገባሪና ግብር ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል አዝ እንዴት ቢመርጥሽ ነው እንዴት ቢያከብርሽ ትናንት እና ዛሬን ያገናኘብሽ ምልዐትና ወሰን ግዝፈትና ርቀት ባንቺ ተዋሐዱ ፈጣሪና ፍጥረት ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል      አዝ ምስጢር ሊመረምር ይወጣል ኀሊና ያልፋል ይሻገራል ከሰማይ ደመና ነገር ግን አይችልም ምንም ቢገሠግሥ ከመሰወሪያው ዘንድ ከልጅሽም ሊደርስ ስለዚህ አቅቶት ደክሞት ይመለሳል መልክዐ ውዳሴሽን በአድናቆት ያደርሳል ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

ሰባቱ_መንጦላይት_ዘማሪ_ቀሲስ_ምንዳዬ_ብርሃኑ.m4a

13 673
181
መስከረም ፲ በዚህች ዕለት ጼዴንያ በምትባል አገር ሥጋ የለበሰች ከምትመስል፤ ከሠሌዳዋም ቅባት የሚንጠፈጠፍባት የእመቤታችን የድንግል ማርያም ሥዕል ተዐምር ተገለጠ። ይህችን ሥዕል የሳላት ቅዱስ ሉቃስ ነው። ወደ ጸዴንያ እንዴት መጣች ቢሉ፤ አንዲት ማርታ የምትባል ሴት ነበረች በቤቷም እንግዳ ትቀበል ነበር። ድንግል ማርያምንም አብዝታ ትወዳት ነበር። በአንዲት ቀንም ስሙ ቴዎድሮስ የሚባል መነኩሴ በእንግድነት መጣ። በማግስቱ ስትሸኘው ወዴት ነህ ብላ ጠየቀችው። እርሱም ወደ ኢየሩሳሌም እንደሆነ ነገራት። እርሷም ሲመለስ የእመቤታችንን ሥዕል አምጣልኝ አለችው። ከዚህም በኋላ ከቦታው ደርሶ ሥዕሏን ሳይገዛ ተመለሰ፤ በመንገድም ሥዕሏን ለምን አልገዛህም? የሚል ድምጽ ሰምቶ ተመልሶ ገዛ። በጎዳናው እየተመለሰ ሳለም የሚያስፈሩ ወንበዴዎች፤ ኋላም አንበሳ ገጠመው፤ የያዛት ሥዕልም ቃል አውጥታ አዳነችው። አባ ቴዎድሮስም ይህን ድንቅ ተአምር ባየ ግዜ ሥዕሏን ወደ ሀገሩ ሊወስዳት ወደደ። በሌላ ከተማም አድርጎ ሊሄድ መርከብ ተሳፈረ። በመርከቧ ሳለም ታላቅ ነፋስ ተነስቶ አቅጣጫውን አስቀይሮ ወደ ጸዴንያ ወሰደው። ኋላም ቢመሽበት ማርታ ቤት ሄደ እራሱን ግን አልገለጠም። በማግስቱም ተሰውሮ ከከተማው ሊወጣ ቢሞክር መውጫው ጠፍቶት ሲዞር ውሎ ተመለሰ። እንዲህም እያለ ሶስት ቀን ሆነው። ማርታም ይህን ተመልክታ ምን እንደሆነ ጠየቀችው። እርሱም ሁሉንም ነገራት። በኋላም የመነኩሴውን እጅና እግር ስማ ሥዕሏን ተቀበለች። በታላቅ ክብርም አስቀመጠቻት። ያም መነኩሴ እስከሚሞትበት ቀን ድረስ የእመቤታችን ድንግል ማርያምን ሥዕል እያገለገለ ኖረ። የእመቤታችን በረከት ይደርብን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
15 057
121
እግዚአብሔርን አመስግኑት እግዚአብሔርን አመስግኑት ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት/2/ አዝ ሰማይን ያለምሰሶ ምድርንም ያለ መሠረት ያጸናው እርሱ ነው ሥራህ ድንቅ ነው በሉት አዝ የባሕርን ጥልቀት የመጠነ ዳርቻዋን የወሰነ እግዚአብሔርን አመስግኑት ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት አዝ ማዕበል ነፋስ የሚገስጽ ፍጥረቱ ለስሙ የሚታዘዝ ትጉህ እረኛ ድካም የሌለበት እግዚአብሔርን ሥራህ ድንቅ ነው በሉት አዝ ንጹሀ ባሕርይ ነው ሁሉን የሚገዛ የነገስታት ንጉሥ አልፋና ኦሜጋ  ዘላለም እርሱ የማይለወጥ እግዚአብሔርን ሥራህ ድንቅ ነው በሉት አዝ  ጥበብን የሚገልጥ ጥበበኛ ፍርድን የሚያደርግ እውነተኛ ዳኛ  እንደ እርሱ ያለ ከቶ አይገኝም  እግዚአብሔር ግሩም ነው ዘለዓለም ዘማሪት ፀዳለ ጎበዜ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

እግዚአብሔርን_አመስግኑት_ዘማሪት_ፀዳለ_ጎበዜ.m4a

13 416
142
ውድ የዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች እንደምን ዋላችሁ? እግዚአብሔር ይመስገን። ቪድዮ ኤዲት እና ግራፊክስ የተማራችሁ እና እንዲሁም ተሰጥኦ ያላችሁ ካላችሁ ወይም የምታውቁት ሰው ካለ በ ይላኩልን።
2 625
23

[object Object]

[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
0
Анонімне голосування
14 629
36
ምክንያት ስላለኝ ነው ምክንያት ስላለኝ ነው የምዘምርልሽ ምክንያት ስላለኝ ነው ቅኔ እምቀኝልሽ አሁንም ይብዛልኝ ፍቅርሽ/2/ ከዚህ በላይ እንዳመሰግንሽ አዝ አውቃለሁ ከደጅሽ ምን እንዳገኘሁኝ አስታውሰዋለሁ ሸክሜን እንደጣልኩኝ የለመንኩሽ ሁሉ መቼ ከንቱ ቀረ ሰይጣን ተመለሰ እያቀረቀረ ጠላት ቢከፋውም ለአንቺ በመቆሜ  አደገድጋለው ደግሜ ደግሜ/2/ አዝ ልቤ አርፏል በአንቺ በእናቴ አማላጄ እንቅፋት እሾሁ አይበቅልም በደጄ በሚጣፍጥ ዜማ በኤፍሬም ውዳሴ ሳሸበሽብልሽ ትረካለች ነፍሴ ጠላት ቢከፋውም ለአንቺ በመቆሜ  አደገድጋለው ደግሜ ደግሜ/2/ አዝ ውለታ ያለበት የማይከፈል ሲመሽም ሲነጋ ያመሰግናል ማርያም ማርያም ይላል ምድርና ሰማዩ በልጅሽ መከራ ሞቶለት ገዳዩ ጠላት ቢከፋውም ለአንቺ በመቆሜ አደገድጋለው ደግሜ ደግሜ/2/ ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

ምክንያት_ስላለኝ_ዘማሪት_ምርትነሽ_ጥላሁን_Official_Audio.m4a

15 624
193
መስከረም ፱ በዚህች ቀን መጺል በምትባል አገር ኤጲስ ቆጶስ የነበረ፤ ቅዱስ አባት አባ ቢሶራ በሰማዕትነት አረፈ። በወቅቱ ዲዮቅልጥያኖስ የተባለ ክፉ ሰው በንግስና ላይ የነበረበት ግዜ ነበር። በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሰይጣን ቀጥሎ እንደዚህ የከፋ ስም የለም። የዓለም ክርስቲያኖችን የጨፈጨፈ ሰው ነው። መከራውም እየገፋ ሲመጣ ቅዱሱ በመፍራት ፈንታ የሰማዕትነት ፍቅር አደረበት። በክርስቶስ ስም ደሙን ያፈስ ዘንድ ወደደ። ሕዝቡንም ሰብስቦ አቆማቸው፤ ሊጠብቁት የሚገባውን ለጽድቅ የሚያበቃቸውን ትዕዛዝ ሁሉ አዘዛቸው። ከዚህም በኋላ ለሰማዕትነት እንደተዘጋጀ ነገራቸው። ይህንንም በሰሙ ግዜ ሁሉም አለቀሱ። የሙት ልጆች እንሆን ዘንድ ለምን ትተወናለህ፤ እንድትሄድ አንለቅህም አሉት ሊይዙትም ቃጡ። ቅዱሱም ሰላምታ ሰጥቷቸው ከእነርሱ ዘንድ ወጥቶ ተጓዘ። አንዳንድ አባቶችም አብረን እንሞታለን ብለው አብረውት ሄዱ። በኋላም መኰንኑ ጽኑ የሆነ መከራ አደረሰባቸው ፤አባቶች ግን በታላቅ ትዕግስት ጸኑ። ከዚህም በኋላ ራሶቻቸውንም በሰይፍ ይቆርጧቸው ዘንድ  አዘዘ። በዚህች ዕለትም የሕይወት አክሊልን በመንግስተ ሰማያት ተቀበሉ። በረከታቸው ይደርብን ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
16 193
43
በበጎ ፍቃዱ በበጎ ፍቃዱ ሁሉ በእርሱ ሆነ (2) ነገር ሁሉ በርሱ ተከናወነ   (2) አዝ ሰማይና ምድር ግብሩን ተናገሩ ፈጥሯቸዋልና እንዲገለጥ ክብሩ በፈጠረው ፍጥረት የሚታወቅ እሱ እግዚአብሔር ይመስገን ስሙን አወድሱ አዝ አልሆነም ያለእርሱ ፍፁም አንዳች ነገር ብንመረምረው በሰማይ በምድር ፍቃዱ ነውና መልካምና በጎ ሰርቶ አሳይቶናል ሁሉን ውብ አድርጎ አዝ ክረምትና በጋ ሌሊትና ቀን ሁሉን አሳይቶ ጌታ አስተማረን ያደረገው ሁሉ እንከን የሌለው ለዚህ ቅዱስ አምላክ ምሳሌም የለው አዝ ያዘነውን ያውቃል ደስም ያለውን ሁሉ በእርሱ ፍቃድ ስለ ሚከወን ችግርና ደስታም ለበጎ ነውና ይህን ያስተማረን ይድረሰው ምሥጋና ዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️

በበጎ_ፍቃዱ_ሁሉ_በርሱ_ሆነ_ዘመን_የማይሽረው_ዝማሬ_ቀሲስ_ዘማሪ_አሸናፊ_zemari_Ashenaf.m4a

14 591
109
ስግደት ስግደት ማለት መዋረድ፣ ማጎንበስ፣ መንበርከክ፣ በግንባር መውደቅ፣ ግንባርን ምድርን አስንክቶ መሬት ስሞ መመለስ ማለት ነው። ስግደት ለምን ይጠቅማል? ስግደት ከአምላካችን ፀጋ እና በረከትን እንድናገኝ እንዲሁም ክፉ መንፈስ ከእኛ እንዲርቅ ይረዳል። በቤተ ክርስቲያን ሁለት አይነት ስግደቶች አሉ፦እነሱም ፩.የአምልኮ (የባህሪይ) ስግደት ይህ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ብቻ አንተ አምላኬ ነህ በማለት የምንሠግደው ስግደት ነው። ማቴ 4፥10 ፪.የአክብሮት (ጸጋ) ስግደት6 ለመላእክት ለቅዱሳን ለፃድቃን ለሰማዕታት የሚሰገድ ስግደት ነው። በፀሎት ጊዜ በተለይም ስግደትን የሚያነሳ አንቀፅ ሲገኝ ህሊና ተሰብስቦ የአንክሮ፣ የተደሞ፣ የትህትና ስግደት ይሰገዳል። ስግደት በቤተክርስቲያን እንዲሰገድ መጽሐፍ ቅዱስ ያዝዛል። ቤተክርስቲያን በሌለበት ቦታ ደግሞ በስተምስራቅ አቅጣጫ እንሰግዳለን። ስርዓተ ቤተክርስቲያን በወር ውስጥ አምስት ቀናት ስግደት እንዳይሰገዱባቸው ያዛል፦ 1. የበዓለ ወልድ እለት (በየወሩ በ29) እና በጌታችን አበይት በአላት 2. የእመቤታችን ወርሃዊ መታስቢያ (በየወሩ በ21) እና በእመቤታችን በዓላት   3. የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል መታሰቢያ (በየወሩ በ12) 4. ቀዳሚት ሰንበት (ቅዳሜ) 5. ሰንበተ ክርስቲያን (እሁድ) እና በዓለ ሀምሳ። በእነዚህ ቀናት የማይሰገድበት ምክንያት 📌 ዕለተ ቅዳሜ ጌታችን ፍጥረታትን ሁሉ ፈጥሮ ከስራው ያረፈበት ቀን ስለሆነ። 📌 ዕለተ እሁድ ጌታ ከሙታን መካከል ተለይቶ የተነሳበት ቀን ስለሆነ። 📌 በ12 በዓለ ቅዱስ ሚካኤል ራዕ᎐፲፪ኀ ሰይጣን የወደቀበት ቀን ስለሆነ። 📌 በ21 በዓለ ማርያም የነፍሳችን ዕረፍት ነጻ የወጣንባት ስለሆነ። 📌 በ29 በዓለ እግዚአብሔር የነጻነት ቀን ጌታ የተወለደበት ቀን ስለሆነ። የአምልኮት ስግደት ሦስት ደረጃዎች አሉት እነርሱም;- ፩᎐ ሰው አድርገህ ከመሬት ፈጥረኸኛልና ስንል ወደ ምድር ጉልበትና ግንባራችንን እናስነካለን። ፪᎐ በኃጢአት ወድቄ በንስሐ እነሳለሁ ስንል ከሰገድንበት ብድግ እንላለን። ፫᎐ ብሞት በትንሣኤ እነሳለሁ ስንል ከሰገድንበት ቦታ በሁለት እግሮቻችን እንቆማለን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
image
16 462
235

[object Object]

[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
419
Анонімне голосування
15 772
61
ቸሪቱ አማላጅቱ ሆይ ቸሪቱ አማላጅቱ ሆይ እናቱ ነሽና ለአዶናይ በሥላሴ ፊት ስልጣን ያለሽ የባህሪያችን መመኪያ ነሽ (2) አዝ ተጥሎ አዝኖ የኖረው በልጅሽ ነው ቀናቀና ያለው ንጉሱን ስትወልጂ በበረት ተፈታ አዳም ከእስራት ዘጸውዓ ስምኪ ወዘገብረ ተስካርኪ ብሎ ቃልኪዳን ሰጠሽ ፍጥረትን እንዲምርብሽ አዝ ከሚያስብ ከማይዘነጋ ፍጥረቱን ከሚያረጋጋ ስላለሽ በእግዚአብሔር ቀኝ ለኃጥአን ድንግል ለምኝ ዘጸውዓ ስምኪ ወዘገብረ ተስካርኪ ብሎ ቃልኪዳን ሰጠሽ ፍጥረትን እንዲምርብሽ አዝ ከሰማይ ሰማያት ወርዶ መለኮት ሥጋን ተዋህዶ አየነው በጠባብ ደረት ወሰንሽው በአጭር ቁመት ዘጸውዓ ስምኪ ወዘገብረ ተስካርኪ ብሎ ቃልኪዳን ሰጠሽ ፍጥረትን እንዲምርብሽ አዝ ሰነድ ነሽ መታረቂያችን ከተማም መማፀኛችን በሰማይ በምድርም ያሉ ለክብርሽ ቅኔ ይቀኛሉ ዘጸውዓ ስምኪ ወዘገብረ ተስካርኪ ብሎ ቃልኪዳን ሰጠሽ ፍጥረትን እንዲምርብሽ ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ማርያም 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

ቸሪቱ_አማላጅቱ_ዘማሪ_ገብረዮሐንስ_ገብረፃድቅ_ቤተ_ቅኔ_Beta_Qene.m4a

16 899
168
ኦ እንዳንተ ያለ ወዳጅ ኦ እንዳንተ ያለ ወዳጅ አላገኘሁም እኔ ኦ ውለታህን ሳስበው በእንባ ይመላል አይኔ/2/ አዝ ከእናቴም ልጆች በላይ አንተ ውድ ነህ ለኔ ወዳጅ እና ዘመዴ ጌታ የክፉ ቀኔ ምን አለኝ እና ልስጥህ የሚነገር የሚወራ እኔስ ተሸንፌያለሁ በእንባ ስምህን ልጥራ አዝ ተሰድጄ ብወጣ ወተሃል ከኔ ጋራ ትናንትናን አለፍኩት ጠላቴን እያራራ ደግሞ የነገውን ቀን አንተ ታውቃለህ ጌታ ወጥመዴን ስበር እና አፌን ሙላው በእልልታ አዝ በእስረኞች መሃል ሆኜ ሰንሰለት ለብሻለሁ አለም እውነት የላትም ፍትህ ካንተ እሻለሁ መቼ ታጽናናኛለህ ወዳጅ እና ዘመዴ አውጣኝ አውጣኝ ለሚልህ አንተ አታጣም ዘዴ አዝ መመላለስ አይደክምህ እኔን ማስታመም አንተ ደክመህ አልፈህልኛል እጆቼን አበርትተህ ሁሌ በሬ ላይ ቆመህ ደጃፌን የምትመታ ግባ የክብር ንጉስ ብያለሁ ማራናታ ብያለሁ ማራናታ/4/ ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

ቸሪቱ_አማላጅቱ_ዘማሪ_ገብረዮሐንስ_ገብረፃድቅ_ቤተ_ቅኔ_Beta_Qene.m4a

1
0
መስከረም ፰ በዚህች ቀን ደግሞ የእግዚአብሔር ሰው የሆነ፤ ቅን፤ የዋህ፤ ጻድቅ፤ የነቢያት አለቃ የቅዱስ ሙሴ ዕረፍቱ ነው። ከኮከብም ኮከብ እንደሚበልጥ ከነቢያት ሁሉ ደግሞ ቅዱስ ሙሴ ይበልጣል። የቅዱስ ሙሴ አባት እንበረም እናቱ ደግሞ ዮካብድ ይባላሉ። ቅዱስ ሙሴ በተወለደ ወቅትም የእስራኤል ወንድ ልጆች ይገደሉ ነበር። ወላጆቹም እርሱን ለማሸሽ ሲሉ ገና በ3ወሩ በግብጽ /ዓባይ/ ወንዝ ውስጥ ጣሉት። የፈርዖን ልጅም ከወንዝ ላይ ባገኘችው ግዜ ለእርሷ ልጅ ይሆናት ዘንድ ወስዳ በመልካም አስተዳደግ አሳደገችው። ስሙንም ሙሴ ያለችው እርሷ ናት፤ ትርጉሙም ከውሃ የተገኘ ማለት ነው። ወላጆቹ ግን በተወለደ ወቅት ፊቱ ያበራ ነበርና ምልክአም ብለው ስም አውጥተውለት ነበር። እናቱ ዮካብድም በሞግዚትነት ገብታ ልጇን ማንም ሳያውቅ አሳድጋዋለች። በቅዱስ መጽሐፍ እንደምናነበው ቅዱስ ሙሴ ኮልታፋ ነው፤ ይህም ገና በ5 አመቱ ፈርኦንን በጥፊ በመምታቱ እሳት አበሉት በዚህም ኮልታፋ ሆኖ ቀርቷል። 40 አመት በሞላው ግዜም አንድ የግብጽ ሰው አንዱን ዕብራዊ ሲያጠቃው ተመልክቶ ለዕብራዊው ተበቅሎ ግብጻዊውን ገደለው ከዚያም ወደ ምድያም ሸሽቷል። ቅዱስ ሙሴ በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ግብጻውያን ላይ ዘጠኝ መቅሰፍት በአስረኛውም ሞተ በኩር መታ። እሥራኤልንም ነጻ አወጣ። መልካም ተጋድሎንም ፈጽሞ በዚህች ዕለት ዐረፈ። በረከቱ ይደርብን! አሜን ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
17 812
81
ኦ እንዳንተ ያለ ወዳጅ ኦ እንዳንተ ያለ ወዳጅ አላገኘሁም እኔ ኦ ውለታህን ሳስበው በእንባ ይመላል አይኔ/2/ አዝ ከእናቴም ልጆች በላይ አንተ ውድ ነህ ለኔ ወዳጅ እና ዘመዴ ጌታ የክፉ ቀኔ ምን አለኝ እና ልስጥህ የሚነገር የሚወራ እኔስ ተሸንፌያለሁ በእንባ ስምህን ልጥራ አዝ ተሰድጄ ብወጣ ወተሃል ከኔ ጋራ ትናንትናን አለፍኩት ጠላቴን እያራራ ደግሞ የነገውን ቀን አንተ ታውቃለህ ጌታ ወጥመዴን ስበር እና አፌን ሙላው በእልልታ አዝ በእስረኞች መሃል ሆኜ ሰንሰለት ለብሻለሁ አለም እውነት የላትም ፍትህ ካንተ እሻለሁ መቼ ታጽናናኛለህ ወዳጅ እና ዘመዴ አውጣኝ አውጣኝ ለሚልህ አንተ አታጣም ዘዴ አዝ መመላለስ አይደክምህ እኔን ማስታመም አንተ ደክመህ አልፈህልኛል እጆቼን አበርትተህ ሁሌ በሬ ላይ ቆመህ ደጃፌን የምትመታ ግባ የክብር ንጉስ ብያለሁ ማራናታ ብያለሁ ማራናታ/4/ ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

ኦ_እንዳንተ_ያለ_ወዳጅ_ዘማሪት_ምርትነሽ_ጥላሁን_Official_Audio1.m4a

16 512
183

[object Object]

[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
0
Анонімне голосування
17 914
65
ድንቅ አድርጎልኛል ድንቅ አድርጎልኛል የሠራዊት ጌታ 2 አልረሳኝም አምላክ አነሳኝ ከትቢያ 2 አዝ ድንቅ አድርጎልኛል በደሌን ሳይቆጥር ድንቅ አድርጎልኛል ወደቤቱ ጠራኝ ድንቅ አድርጎልኛል እረክሼ ሳለሁ ድንቅ አድርጎልኛል ልጄ ሆይ ና አለኝ ድንቅ አድርጎልኛል በዳግም ምጻቱ ድንቅ አድርጎልኛል መንግስቱን ሊያወርሰኝ አዝ ድንቅ አድርጎልኛል ከአንበሳ መንጋጋ ድንቅ አድርጎልኛል ከጉድጓድ አወጣኝ ድንቅ አድርጎልኛል በጠላቶቼ ፊት ድንቅ አድርጎልኛል ግርማ ሞገስ ሰጠኝ ድንቅ አድርጎልኛል ምን እመልሳለሁ ድንቅ አድርጎልኛል እንዲህ ለወደደኝ አዝ ድንቅ አድርጎልኛል ጠላቶቼ ሁሉ ድንቅ አድርጎልኛል ሲጓደዱብኝ ድንቅ አድርጎልኛል ማን ይደርስለታል ድንቅ አድርጎልኛል እያሉ ሲሉኝ ድንቅ አድርጎልኛል ፈጥነህ ደረስክልኝ ድንቅ አድርጎልኛል ከሞት አዳንከኝ ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

ዘማሪ_ቀሲስ_ምንዳዬ_ብርሃኑ_Mendaye_Birhanu_ድንቅ_አድርጎልኛል_Denk_Adrgolgna.m4a

19 125
368
መስከረም ፯ በዚህች ቀን የመጥምቁ ዮሐንስ እናት፤ የከበረች ኤልሳቤጥ አረፈች። ቅድስት ኤልሳቤጥ እድሜዋ በደረሰ ግዜ ካህን ለሆነው ለቅዱስ ዘካርያስ አጋቧት። ነገር ግን እስከ እርጅና ዘመናቸው ልጅ መውለድ አልቻሉም ነበር። የኤልሳቤጥ እድሜ 90 የዘካርያስም 100 ደርሶ ነበር። እግዚአብሔርም ትዕግስታቸውን እና ጽድቃቸውን ተመልክቶ በመልዐኩ ገብርኤል አብሳሪነት ታላቅ የሆነ ነቢይን ሰጣቸው። የኤልሳቤጥ የስድስት ወር ጽንስም የድንግል ማርያምን ድምጽ በሰማ ግዜ በደስታ ዘሏል። ቅዱስ ዮሐንስም 2 ዓመት ከ6 ወር በሞላው ግዜም ንጉስ ሔሮድስ የተወለደውን ንጉስ /ኢየሱስ ክርስቶስን/ ለማጥፋት ተነሳ። አይሁዶችም ለንጉስ ሔሮድስ ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ ሲወለድ ደግሞ የከፈተ ዮሐንስ የሚባል አለና እርሱን ግደል አሉት። ቅድስት ኤልሳቤጥም ቅዱስ ዮሐንስን ይዛው ሸሸች። አባቱ ካህኑ ዘካርያስን ግን በቤተመቅደስ ውስጥ ገደሉት። ቅድስት ኤልሳቤጥም ዮሐንስን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 ዓመታት ቆየች። ቅዱስ ዮሐንስም 5 ዓመት በሞላው ግዜ በዚህች ዕለት ቅድስት ኤልሳቤጥ በዚያው በበርሃ አረፈች። በረከቷ ይደርብን ወስብሐት ለእግዚአብሔር 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
20 607
75
የሥላሴን መንበር የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት ኪሩቤል በደመና ዙፋኑን ይዘውት ድንግልን ከመሃል ሚካኤልን ከፊት አእላፍ መላዕክት ሲሰግዱ በፍራት እዩት ተመልከቱት የሰማዩን ድምቀት እዩት ተመልከቱት የሰማዩን አባት አዝ የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት እያሸበሸቡ የሰማይ መላዕክት ካህናተ ሰማይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሲሉ ይህን ልዩ ተ0ምር ሊያዩ የታደሉ በጽድቅ ስራቸው በምድር ይታያሉ/ 2/ አዝ የቅዱሳን ህብረት የቅዱሳን ሀገር ሲያወድስ ይኖራል የሥላሴን ክብር ጽድቅና ርህራሄ የተሞላ ሰማይ እግዚአብሔር ያድለን በትንሳኤ እንድናይ/2/ አዝ የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት እያሸበሸቡ በሰማይ መላዕክት ካህናተ ሰማይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሲሉ ይህን ልዩ ተዐምር ሊያዩ የታደሉ በጽድቅ ስራቸው በምድር ይታያሉ/ 2/ ሊቀ መዘምራን ይልማ ሀይሉ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

የስላሴን_መንበር_ቅዱሳን_ከበውት_ሊቀ_መዘምራን_ይልማ_ሀይሉ.m4a

18 137
189

[object Object]

[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
0
Анонімне голосування
18 909
52
​​ አሥራት ሰው እግዚአብሔር ከሰጠው ላይ አሥራትን ካልከፈለ እግዚአብሔር አምላክ ሰርቃችሁኛል ይላል። አሥራት የሚለው ቃል ዐሠረ (ዓሥር) አደረገ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ፍቺውም ከአሥር (10) አንድ ማለት ሲሆን ይህንንም ለእግዚአብሔር መስጠት ማለት ነው።አሥራት ሰው ጥሮ ግሮ ሠርቶ ከሚያገኘው ከላቡ ገቢ ለእግዚአብሔር ከአሥር አንድ እጁን ወይንም ከመቶ አሥር ክፍሉን ለእግዚአብሔር መሥጠት ማለት ነው። አሥራት በሕገ ልቦናና በሕገ ኦሪትም ይሠጥ ነበረ።ለምሳሌ በሕገ ልቦና አብርሃም አባታችን ለካሕኑ ለመልከጼዲቅ አሥራትን እንደከፈለ በቅዱስ መጽሐፍ  ተገልጧል። አብርሃምም ከሁሉ አሥራት ሠጠው።ዘፍ ፲፬÷፳ አባታችን ያዕቆብም ቤቴል ብሎ በሰየማት በሎዛ ምድር እግዚአብሔር ቢገለጥለት በሥፍራው የእግዚአብሔር ቤት እንደሚታነጽና እርሱም አሥራት እንደሚያደርግ ቃልኪዳን አደረገ። ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከአሥር እጅ አንዱን እሰጥሃለሁ። ዘፍ፳፰÷፳፪ እግዚአብሔር አምላካችን ሙሴን በሲና ተራራ ካዘዘው ትእዛዝ አንዱ አሥራትን ስለመክፈል ነው።ይሕም በዘሌ ፳፯÷፴፡፴፫ ተጽፎ ያለው ነው።ስለዚህ አሥራትን ማውጣት የአምላክን ሕግ መጠበቅና መፈጸም ነው። ሰው እግዚአብሔር ከሰጠው ላይ አሥራትን ካልከፈለ እግዚአብሔር አምላክ ሰርቃችሁኛል ይላል። ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም። የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው። ትን ሚል 3:8 አሥራት የሚከፈለው ለካሕናት መገልገያ በአጠቃላይ ለእግዚአብሔር መንግስት ማስፋፊያ ነው። ካሕናት ሙሉ በሙሉ ጊዜያቸውን ሁሉ አምላካቸውን እንዲያገለግሉ ሕዝቡንም እንዲጠብቁ ነው። አሥራትን በዘመነ ወንጌልም በዘመነ ክርስትናም እንደሚፈጸም ክብር ይግባውና ጌታችን እንዲህ ብሎ አዟል። የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጡ የማቴ ፳፪÷፳፩ እግዚአብሔር አምላክ ዘጠኙን ሊባርክልን አንዷን ብቻ ለኔ ሥጡኝ ሲለን ገንዘብ አምላኪዎች እንዳንሆን ከእርሱም ይልቅ ገንዘብን እንዳንወድ ወይም ለእርሱ ያለንን ፍቅር ያይበት ዘንድ ስለሚፈልግ  አሥራትን በኩራትን ምፅዋትንና ለጋስነትን አስተማረን አንድም ቸር ለጋስ መሆን እርሱን መምሰል ነውና። ስለዚህ እኛም ይህን በመረዳት ከምናገኛት ገቢያችን ላይ አነሰም በዛም ሳንል አስራታችንን በስርአቱና በጊዜው እናውጣ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! ምንጭ:- መጽሐፈ አሚን ወሥርዓት 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
image
17 868
112
መስከረም ፮ በዚህች ዕለት ታላቅ ነቢይ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ አረፈ። ታላቁ ነቢይ ኢሳይያስ ከተናገራቸው ትንቢቶችም አንዱ በትንቢተ ኢሳይያስ 7፥14 "ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች" የሚል ነበር ።በወቅቱ የነበሩ አንዳንድ ክፉ ሰዎች ግን ለንጉስ ሕዝቅያስ "ይህ ትንቢት ላንተ ነው ድንግል የተባለችዋ ኢየሩሳሌም ስትሆን ወንድ ልጅ የተባለው ደግሞ አንተ ነህ" አሉት። ንጉሱም ይህን ሰምቶ አልገሰጻቸውምና። እግዚአብሔርም በንጉሱ ተቆጥቶ ኢሳይያስን ላከው። እንዲህም አለው ትሞታለህ እንጂ አትተርፍምና ቤትህን ሥራ። መጽ ነገ ካልዕ 20:1 ይህ እንደሆነ ንጉሱ በጽኑ ታመመ ደከመ። ንጉሡም በልቡ ተጸጽቶ ጌታ ሆይ ይቅር በለኝ ሲል ተማጸነ። እግዚአብሔርም ንስሐውን እንደተቀበለው እና በዘመኑም ላይ 15 ዓመታትን እንደጨመረለት ነቢዩ ነገረው። በኋላ ዘመንም ንጉስ ምናሴ ጣዖትን ያመልክ ነበር። ነቢዩም በአደባባይ ገሰጸው። ምናሴም በዚህ ተበሳጭቶ ነቢዩ ኢሳያስን በዚህች ዕለት በእንጨት መጋዝ ለሁለት አሰነጠቀው። ቅዱሱም ተጋድሎውን ፈጸመ። በረከቱ ይደርብን ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
1
0
የተወደደ ቀን የተወደደ ቀን የተወደደ ዓመት ወደ አባቴ መቅደስ የተመለስኩበት አንባር ቀለበትን የተሸለምኩበት የተወደደ ዓመት አዝ አምሽቶ የመጣ አይገባም አትበሉ(2) አባክኖ የመጣ አይገባም አትበሉ(2) ፍቅር ስለሆነ እግዚአብሔር ለሁሉ(2) ልጅ ቤቱን ይወርሳል እንደተስፋ ቃሉ(2) አዝ ከናዝሬት መልካም ሰው አይወጣም እያሉ(2) ፊልጶስ ናትናኤል ይነጋገራሉ(2) አድርጎታልና ውሀውን ወይን(2) ዛሬም ለውጦኛል ወስዶታል ልቤን(2) አዝ እኔ ነኝ አላማው እኔ ነኝ ሀሳቡ(2) አባቴ ደግ ነው የሚራራ ልቡ(2) ዘጠና ዘጠኙ ታምነውት እያለ(2) አንዱን ይፈልጋል ወዴት ነህ እያለ(2) አዝ ሁሉን አይቻለሁ ሁሉን መርምሬአለሁ(2) አለም ካንተ ሌላ እንደሌለ አውቃለሁ(2) እንደማይለወጥ አባትነትህ ወዳጅነትህ ጠፍቼ ስመጣ አየሁት ልጅህ(2) ዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

የተወደደ_ቀን_ቀሲስ_አሸናፊ_ቁ_7_Yetewedede_ken_Kesis_Ashenafi_7_ethiop.m4a

17 062
203
እንደ ዝማሬ ዳዊት ገጽ ከሁለት አመት በፊት በቅዱስ ጊዮርጊስ ስዕል እና ቢራ ዙሪያ ትልቅ የሆነ የሚድያ ንቅናቄ ቢያደርግም ግቡን ሳይመታ ቀርቶ ነበር። አሁንም የተጀመረው የግዜ ጩኸት ብቻ ሆኖ እንዳይቀር ነገሩን ከኛ በዘለለ ከላይ ባሉ አባቶቻችን ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። በሕግ ዕውቀት ያላችሁ የተዋህዶ ልጆችም ቤተ ክርስቲያናችሁ ትፈልጋቹሀለች። የኛን ክብር ማስጠበቅ እምንችለው እኛው ነን። እንደ ማሳሰብያ ማስተላለፍ የምንፈልገው መልዕክት ግን በተለያዩ ሶሺያል ሚድያ ይህን ድርጊት በመቃወም የተለያየ ቪድዮ በምትሰሩ ግዜ የቅዱስ ጊዮርጊስን ስዕለ አድኅኖ ክብር በማያወርድ እና ኦርቶዶክሳዊ ሥነምግባርን በተላበሰ መልኩ ሊሆን ይገባል። በአንዳንድ ቦታ ያልተገባ ድርጊት ስላስተዋልን ነው።
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
ቅዱስ ጊዮርጊስ - ቢራ ወይስ ሰማዕት? የቅዱሳን ስዕል አድህኖ በክብር መቀመጥ ሲገባው የቅዱስ ገዮርጊስ ስዕል ግን 1/ በየጠርሙሱ ተለጥፎ የሰካራም እጅ ያለ ንጽህና በድፍረት ይጨብጠዋል። 2/ ስዕል አድህኖው በየመጠጥ ቤቱ እየወደቀ ይረገጣል። ከቆሻሻ ጋር ተጠርጎ ይጣላል። 3/ በስሙ ታቦት መቀረጽ ሲገባው የሚያሰክር መጠጥ ሆኖ ስሙን ለማርከስ ተሰርቷል 4/ ኢትዮጵያ ከሰማዕቱ የምታገኘውን ክብርና ጥበቃ ለማሳጣት በ1915 ዓ.ም ጣሊያኖች አቅድው አቋቋሙት። የሚገርመው መጠጡን የሚጠጣው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታዩ ነው። አንዳዴ እንደቀላል የምናያቸው ነገሮች ከፍተኛ የሆነ ጥፋቶች ናቸውና እንንቃ። ይህን ጽሁፍ ያነበበ ለነፍሱ ይወስን!
18 195
12
መስከረም ፮ በዚህች ዕለት ታላቅ ነቢይ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ አረፈ። ታላቁ ነቢይ ኢሳይያስ ከተናገራቸው ትንቢቶችም አንዱ በትንቢተ ኢሳይያስ 7፥14 "ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች" የሚል ነበር ።በወቅቱ የነበሩ አንዳንድ ክፉ ሰዎች ግን ለንጉስ ሕዝቅያስ "ይህ ትንቢት ላንተ ነው ድንግል የተባለችዋ ኢየሩሳሌም ስትሆን ወንድ ልጅ የተባለው ደግሞ አንተ ነህ" አሉት። ንጉሱም ይህን ሰምቶ አልገሰጻቸውምና። እግዚአብሔርም በንጉሱ ተቆጥቶ ኢሳይያስን ላከው። እንዲህም አለው ትሞታለህ እንጂ አትተርፍምና ቤትህን ሥራ። መጽ ነገ ካልዕ 20:1 ይህ እንደሆነ ንጉሱ በጽኑ ታመመ ደከመ። ንጉሡም በልቡ ተጸጽቶ ጌታ ሆይ ይቅር በለኝ ሲል ተማጸነ። እግዚአብሔርም ንስሐውን እንደተቀበለው እና በዘመኑም ላይ 15 ዓመታትን እንደጨመረለት ነቢዩ ነገረው። በኋላ ዘመንም ንጉስ ምናሴ ጣዖትን ያመልክ ነበር። ነቢዩም በአደባባይ ገሰጸው። ምናሴም በዚህ ተበሳጭቶ ነቢዩ ኢሳያስን በዚህች ዕለት በእንጨት መጋዝ ለሁለት አሰነጠቀው። ቅዱሱም ተጋድሎውን ፈጸመ። በረከቱ ይደርብን ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
21 826
60
ታላቅ በሆነው    ታላቅ በሆነው እምነትሽ ታመንኩኝ     ካለሽበት ገስግሼ መጣሁኝ     እናቴ ክብርሽን አንግሼ     ቆምኩኝ እንደ ህፃን ታድሼ     እናቴ ቅድስት አርሴማ     ዝናሽ ለአለም ተሰማ   አዝ ስመጣ ባልጋ ነበረ     ተስፋዬም የተሰበረ     በእምነትሽ በጠበልሽ     ሰው ሆኜ ቆምኩኝ ደጅሽ    ልናገር ዝናሽን ላውራ     ይደነቅ የአምላክሽ ስራ     ተጋድሎሽ የእምነትሽ ፅናት     ሆኖኛል የእምነቴ መብራት     አዝ ደምግባት ከንቱ ብለሽ     ለሰማይ ክብር የታጨሽ     የእምነቴ ሐሰረ ፍኖት     በምልጃሽ አለሁኝ በህይወት  የልቡን ለነገረሽ     ፈጥኖ ይደርሳል መልስሽ     ዘንባባሽ ህይወት ይዘራል     የጠራሽ ማን አፍሮ ያውቃል     አዝ እርዳታሽ የደረሰለት     ያመጣል የልቡን ስለት     ላመኑሽ ፈውስሽ ቅርብ ነው     ባንቺ አፍሮ የሄደ ማነው የልቡን ለነገረሽ     ፈጥኖ ይደርሳል መልስሽ     ዘንባባሽ ህይወት ይዘራል     የጠራሽ ማን አፍሮ ያውቃል       አዝ ስመጣ ባልጋ ነበረ     ተስፋዬም የተሰበረ     በእምነትሽ በፀበልሽ     ሰው ሆኜ ቆምኩኝ ደጅሽ     ልናገር ዝናሽን ላውራ     ይደነቅ የአምላክሽ ስራ     ተጋድሎሽ የእምነትሽ ፅናት     ሆኖኛል የእምነቴ መብራት።       ዘማሪት ሲስተር ሊድያ ታደሠ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

ታላቅ_በሆነው_እምነትሽ_ታመንኩኝ_ዘማሪት_ሲስተር_ልድያ_ታደሰ.m4a

17 614
159
የዕለቱን ስንክሳር በአጭሩ ማንበብ ይፈልጋሉ፤ ጠዋት እና ማታ የምንለቃቸውንም ዝማሬዎች ማዳመጥ ይፈልጋሉ፤ በተጨማሪም የምንለቃቸውን ትምህርቶች ማግኘት እና ማንበብ ይፈልጋሉ። ነገር ግን ዝንጉ አይምሮ ነውና ያለን ማስታወስ አቅቶን የዝማሬ ዳዊት ቻናልን ከፍተን ሳናይ ከቴሌግራም እንወጣለን። ይህም የሚሆንበት አንዱ ምክንያት ቴሌግራም ላይ ካሉ ብዙ ቻናሎች መሀከል ስለሚደበቅ ነው። በመሆኑም ቻናላችንን ከላይ Pin በማድረግ ወደ ቴሌግራም በሚገብ ግዜ ሁሉ ከፊት ለፊት ስለሚያገኙት የምንለቃቸው ነገሮች በሙሉ አያመልጧችሁም። Pin ለማድረግ ይህን ቅደም ተከተል ይከተሉ። 1. የዝማሬ ዳዊት ገጽን ለትንሽ ግዜ ጫን ብለው ይቆዩ። 2. ከላይ ምስሉ ላይ እንደሚታየው ቻናሉን Mark ካደረገላችሁ በኃላ Pin የሚል ጽሁፍ ካያችሁ እርሱን መንካት ወይም በቀይ ሰንጠረዥ የጠቆምናትን ምልክት መንካት። በዚህ መልኩ ቻናላችንን PIN ማድረግ ትችላላችሁ። ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን።
Показати повністю ...
18 960
11

[object Object]

[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
0
Анонімне голосування
18 770
43
በዘባነ ኪሩብ በዘባነ ኪሩብ ለሚቀመጠው በእሳት ድንጋዮች ቅጥሩን ላጠረው ዘምሩ ለእግዚአብሔር ለጌታ ዘምሩ የተከበረ ነው በሰማይ በምድሩ 2 አዝ ኢሳይያስ ሲያየው እጅግ አፈረ የተፈራ ነው የተከበረ የሰማይ ደጆች ተንቀጠቀጡ ለቅዱስ ስሙ ክብርን ሲሰጡ አዝ ያልተቀደሰ ለምጽ ያነደደው እንዴት ይችላል ሊያመሰግነው በል ፍቀድልኝ ፍቅር ነህና ልግባ መቅደስህ ላቅርብ ምስጋና አዝ ዙፋንህ ታየኝ ትምክህቴ ሆይ ስትመሰገን በሰማይ ላይ ሲያመሰግንህ ያልተደሰተ  ባይተዋር አልሁን አልውጣ ካንተ አዝ ቅኔ የሞላበት ያን ሰገነት ልቀላቀለው ተመኘው በእውነት ልዘምርልህ ባይገባኝም ዝም የሚል ልሳን አልሰጠኸኝም ሊቀ መዘምራን ቴድሮስ ዮሴፍ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️

በዘባነ_ኪሩብ_Bezebane_Kirub_ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ.m4a

17 663
163
መስከረም ፭ በዚህች ቀን የከበረች ሶፊያ ከሁለት ልጆቿ አክሶስ እና በርናባ ጋር በሰማዕትነት አረፈች። ቅድስት ሶፍያ አስቀድማ አረማዊት ነበረች ወላጆቿም ጣዖታትን የሚያመልኩ ነበሩ። እርሷም በልቧ የወላጇቿ ሃይማኖት ከንቱ እንደሆነ ከመረመረች በኋላ ወደ መኖፌ ኤጲስቆጶስም ሄዳ ክብር ይግባውና በጌታችን በክርስቶስ ታመነች። እርሱም ሃይማኖትን የቤተክርስቲያንን ሕግ አስተማራት። ከዚሕም በኋላ ከልጆቿ ጋር በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም አጠመቃት። የሀገሩ ገዢ ለጣዖት መስገድን ትታ ክርስቲያን እንደሆነች በሰማ ጊዜ ከልጇቿ ጋር ብዙ ስቃይን አሰቃያት። ገዢውም ልጇቿ አይተው ይፈሩ ዘንድ በጅራፍ ይገርፏት ዘንድ አዘዘ። ያን ጊዜም የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ ወርዶ እናታቸውን ከግርፋት ሲሰውራት አዩ። ከዚህም በኋላ ወደ እስር ቤት ወስደው አሰሯት እራሷንም በሰይፍ ይቆርጡት ዘንድ አዘዘ የድል አክሊልንም ተቀበለች። ከዚህም በኋላ ልጆቿን ወደርሱ ይመለሱ ዘንድ አስፈራራቸው እንቢ ባሉት ጊዜም እያከታተለ አንገታቸውን አስቆረጠ። ምስክርነታቸውንና ተጋድሏቸውን ፈጸሙ። ከመቃብራቸውም፤ በሽታውንና ደዌውን ሁሉ የሚፈውሱ ብዙ የሆኑ ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። በረከታቸው ይደርብን ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
21 333
87
አምላኬ መቅደስህን እወደዋለሁ አምላኬ መቅደስህን እወደዋለሁ በውስጡ ለመኖር እናፍቃለሁ ሰላም እንድሆን በቤት በደጄ ወደ ማደርያህ ልምጣ ማልጄ እንድሰለጥን በመላእክት ዜማ የሕወትን ቃል ከአፍህ ልስማ እንዲቀል ሸክሜ ከትክሻዬ ወደ ዙፋንህ ልቅረብ ጌታዬ መልካም በሚልዋት በመቅደስህ ሳመልክህ ልኑር ስማጸንህ አዝ ተመለሰልኝ ደስታ ሰላሜ ቤትህ መጥቼ በመሳለሜ ስጋዬም ዳነ ታደሰች ነፍሴ ወደ ማደርያህ በመግስገሴ መልካም በሚልዋት በመቅደስህ ሳመልክህ ልኑር ስማጸንህ አዝ የተማርኩባት የሰላም ቅኔ የተባረከው እድሜ ዘመኔ የተለወጠው ሞቴ በሕይወት እኔ እናፍቃለሁ የእግዚያብሔርን ቤት መልካም በሚልዋት በመቅደስህ ሳመልክህ ልኑር ስማጸንህ አዝ የሰማይ ዜማ የሚሰማባት ሰዎች ከሀዘን የሚጽናኑባት የጸሎት ስፍራ የአምልኮት ቦታ ቤተክርስትያን ውድዋ ስጦታ ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ማርያም 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

አምላኬ_መቅደስህን_ዘማሪ_ገብረዮሐንስ_ገብረፃድቅ_ቤተ_ቅኔ_Beta_Qene.m4a

18 292
148

[object Object]

[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
0
Анонімне голосування
19 348
58
ለውዳሴሽ ልትጋ ለውዳሴሽ ልትጋ ስምሽ ግርማ አለው 2 እመቤተ ኧኸ እመቤተ ስልሽ እውላለው ከልቤ አቀርባለው ምስጋናን ለስምሽ ተመስክሮልሻል ብፅዕት ተብለሽ የሰላምታ ድምፅሽ ያልነካው ማን አለ ጽንሱ በማህፀን በደስታ ዘለለ አዝ ማርና ወተት ነው የስምሽ ስያሜ እመቤተ ስልሽ ይቀላል ሸክሜ ቅኔ ማህሌቱ ሰአታት መዝሙሩ ያመሰግኑሻል ምድርና ጠፈሩ አዝ እናቱ ነሽና አንቺ ለኢየሱስ አድሮብሽ ይኖራል እግዚአብሔር መንፈስ ሰዓሊ ለነ ብዬ ቀኑን ጀምራለው ልጅሽን አምኜ ነገም እኖራለው አዝ ነይ ነይ እልሻለው እንደት ካህናቱ በሰዓታት ጸሎት ቆሜ በሌሊቱ ዝም አልልም እኔ አወድስሻለው ያለምን መከራ እረሳብሻለው ዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️

የዘመናት_ተወዳጅ_መዝሙር_ለውዳሴሽ_ልትጋ_ዘማሪ_ቀሲስ_አሸናፊ_ቁ_2_Lewdasesh_Kesis_A.m4a

19 316
210
መስከረም ፬ በዚህች ዕለት የእስክንድርያ ሊቀጳጳሳት አባ መቃርስ አረፈ። አባ መቃርስ ከታናሽነቱ ጀምሮ በገድል የተጠመደ ነበር የምንኩስናንም ልብስ ሊለብስ ወዶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ወጣ።በዚያም መነኮሰ በምንኩስናም ያለውን ታላቅ ተጋድሎ ተጋደለ። ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀጳጳስ አባ ሚካኤል በአረፈ ጊዜም ኤጲስቆጶሳቱ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሂደው አባ መቃርስን ሊሾሙት ተስማሙ። አባታችን ግን ለዚች ሹመት የተገባው አይደለሁም ብሎ ሹመቱን እንቢ አለ ቢሆንም ግን በገመድ አስረው ሾሙት። በሹመቱ ወራትም ከራሱ ከሚገባውን ግብር ለቤተክርስቲያን ይሰጣል ለድኖችና ለችግረኞችም ይመጸውታል እንጅ ከቤተክርስቲያን ገንዘብ ምንም ምን አልወሰደም። በሹመቱም ሃያ ሰባት ዓመት ኖረ እግዚአብሔርንም በአገልግሎት ደስ አሰኝቶ በዚህች ዕለት አረፈ። በረከቱ ይደርብን! አሜን ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
20 434
65
አጥቷል ጎሎበታል አጥቷል ጎሎበታል ብለህ ሳትንቀኝ ለዚህ ያደረስከኝ ጌታዬ እኔ ማነኝ ይሞላል አይቀርም ባንተ ሸለቆዬ ጠብቃለሁና ቀንህን ጌታዬ አዝ ሀዘን ፅልመት ክፉ ዘመን ቢገጥመኝም እንኴን ያልፋል ሁሉም ታሪክ ሆኖ በፊትህ ሲለካ ማን ጎደለ ማን አፈረ አንተን የጠበቀ ፀና ልቤ በእግዚአብሔር ይሄን እያወቀ አዝ ባለም ስፍራ ባይኖረኝም ብሆንም ጎስቇላ አምላኬ ሆይ ካንተ በቀር አልሄድ ወደ ሌላ ጌታዬ ሆይ በፍለጋ ወጣሁ ከመቃብር ስመሰክር እኖራለሁ ስራህን ስናገር አዝ ቀን ለክተህ ጊዜን አይተህ ሰውን የማትከዳ ያለ ወረት ትመጣለህ እኔን ልትረዳ ከእነ ኤልያስ ወንድሞቼ ባልስተካከልም ማማ ሆነህ ከፍአረከኝ አንተ ሰው አጥልም አዝ እንደ እናት ልጅ እንዳልቆጥርህ ከዚህም ትበልጣለህ ካንተ በቀር ያፈቀረኝ በምድር ስለሌለ ስለ ስምህ መነቀፌ ክብሬ ነው ማረጌ በምን መንገድ ላስደስትህ እንደምን አድርጌ ዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

አጥቷል_ጎድሎበታል_ብለህ_ሳትንቀኝ_በቀሲስ_ዘማሪ_አሸናፊ_ገ_ማርያም_Atetowal_godelobe.m4a

18 039
158
​​​​የከበሮ ክፍል ምሳሌያዊ ትርጉም የከበሮ ክፍል ምሳሌያዊ ትርጉም አለው። ምሳሌውን ግልጽ ለማድረግ ከታች ያለውን ስዕላዊ  መግለጫ እንመለከት እና ወደ ትንታኔው እንሂድ። ከበሮ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው። ግራና ቀኝ ሲመታ ስንመለከልት  ጌታችን በአይሁድ እጅ በጥፊ መመታቱን ያስታዉሰናል። ፩. ሰፊው የከበሮው አፍ የመለኮት ምሳሌ ነው። ይህ  የከበሮ አፍ የጌታችንን የባህሪ  አምላክነት  ምሉዕ በኵለሄ መሆኑን ስልጣኑ ወሰን ድንበር  እንደሌለው የሚያስታውሰን ነው። የአፉን መስፋት ስንመለከት በአጭር  ቁመት  በጠባብ ደረት ተወስኖ  የተገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ  በህልውና በመለኮት  ባሕርይ አባቱ ከአ ባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተስተካከለ ሁሉን የያዘ ሁሉን የሚገዛ መሆኑን እናስባለን። ፪. ጠባቡ የከበሮው አፍ የትስብእት ምሳሌ ነው በመዝሙር ጊዜ  እየተቆረቆረ ድምጽ የሚሰጠው ጠባቡ  የከበሮ አፍ የወልድ እግዚአብሔርን በጠባብ ደረት በአጭር ቁመት ተወስኖ መገለጥ የሚያመለክተን ነው። ፍጥረታትን ሁሉ የሚገዛ እሱ በስልጣኑ ሽረት በመለኮቱ ኅልፈት የሌለበት ቢሆንም ስጋን ተዋህዶ ተገልጧል። ይህንን ጠባብ የከበሮ  አፍ  ስንመለከት ሁሉን የሚገዛ እሱ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት መወሰኑን እናስባለን። ዩሐ፤፩፡፩-፩፬ ፫. ከበሮው የሚለብሰው ጨርቅ    ከበሮ የጌታችን ምሳሌ እንደሆነ ከላይ  አይተናል። ከዚህ አንጻር የለበሰው ጨርቅደግሞ በዕለተ ዓርብ አይሁድ ጌታችንን ያለበሱት ጨርቅ (ቀይ ከለሜዳ) ምሳሌ ነው።  ''ልብሱንም ገፈው ቀይ ልብስ አለበሱት'' ማቴ 26:28 ፬. በከበሮው ላይ የተለጠፈው ጠፍር   በጌታችን ጀርባ ላይ የታየው የግርፋት ሰንበር ምሳሌ ነው። ጠፍሩን በከበሮው ላይስንመለከት በጌታችን ጀርባ ላይ የታየውን ሰንበር እናስታውሳለን። ''እጆቼን እና እግሮቼን ቸነከሩኝ አጥንቶቼ ሁሉ ተቆጠሩ'' መዝ 21(22):16 እንዲል ጌታችን አጥንቱ እስኪቆጠር ጀርባው እስኪቆስል ተገርፏልና የዚያ ምሳሌ ነው። ፭. የከበሮው ማንገቻ የከበሮውን መምታት ስናስብ በአንገታችን የምናስገባው ማንገቻ ጌታችንን አስረው  የጎተቱበት ገመድ ምሳሌነው። አይሁድ ጌታችንን ወደ ቀራኒዮ ሲወስዱት የእጁ መጋፊያና መጋፊያ እስኪገጥም ድረስ በገመድ የእንግርግሪት አስረው ጎትተውታል ማንገቻውን ከበሮው ላይ ስናይ ይኽንን ጌታችን የታሰረበትን ገመድ እናስታውሳለን። በተጨማሪም በከበሮ ውስጥ የሚገኙት አምስት ጠጠሮች የአምስቱ አእማደ ሚስጥራት ምሳሌዎች ናቸው።
Показати повністю ...
image
19 850
273

[object Object]

[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
0
Анонімне голосування
17 749
36
የያሬድ ውብ ዜማ የያሬድ ውብ ዜማ ድንግል እመቤቴ ስጦታዬ ነሽ 2 በምን አንደበቴ እንዴትስ ባለ ቃል ማርያም ልበልሽ 2 ምድርና ሰማዩ ተዓምርሽን ይንገሩ ፍጥረታት በሙሉ ስላንቺ ይመስከሩ ተነግሮ የማያልቅ ድንቅ ነው ስራሽ ድንግል ሆይ እናቴ አምሳያም የለሽ ማርያም ድንግል እረዳቴ የምትደርሺልኝ ነይ ስልሽ በጭንቀቴ ተአምርሽንም በአይኔ አይቻለሁ ፅዮን ሆይ ስልሽ ድንግል ሆይ እጠግባለ አዝ የእግዚብሔር ጥበቡ በአንቺ ተገለጠ የአዳም ዘር በሙሉ ከሞት አመለጠ የመዳን ምክንያት ማርያም አንቺ ነሽ ለፍጥረቱ ሁሉ መሠላል የሆንሽ ነገን ባላውቅ እኔንም ቢያስፈራኝ አንቺ ካለሽኝ በፍፁም አልወድቅም በፊትሽ እንድቆም ለምስጋን ማርያም ልበልሽ በትህትና አዝ ትውልዱ በሙሉ ለምስጋና ይቁም በአንቺ ስለሆነ የቀረለት መርገም አዳም ከነ ልጁ በሰማይ በምድር ማርያም ማርያም ይበል ተዓምርሽን ይናገር ጨለማውም ከፊቴ ተገፈ ማርያም በምልጃሽ ልቤ አረፈ ከጎኔ ነሽ ስልሽ እፅናናለሁ እሳት ገደሉን ሁሉንም አልፈዋለሁ ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

የያሬድ_ውብ_ዜማ_Ye_Yared_Wub_Zema_ዘማሪ_ቀሲስ_ምንዳዬ_ብርሃኑ.m4a

18 210
144
ሰላም ውድ የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮች ትላንት ምሽት በጠየቅነው ጥያቄ መሰረት አጠቃላይ እስከ አሁን ድረስ 2,060 የሚሆኑ የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮች የተሳተፉ ሲሆን ትክክለኛውን መልስ ያገኙት ግን 1,526 ሰዎች ብቻ ናቸው። ይህም የሚያሳየው ከ500 በላይ የሚሆኑት ጥያቄውን በግምት ወይም ጠዋት የተለቀቀውን አጭር የስንክሳር ታሪክ ሳያነቡ ነው። ስለዚህ እባካችሁ የሚለቀቁት ለእናንተ ስለሆነ በሚገባ አንብቡት ከቀናችሁ ላይ ከ5 ደቂቃ በላይ አይወስድም ጥቅሙ ግን በቁጥር የሚለካ አይደለም። ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን! አሜን
18 068
6
በቸርነት በይቅርታው አሰበን በቸርነት በይቅርታው አሰበን በፍቅሩና በምሕረቱ ጎበኘን አምላካችን በሞቱ ወደደን አምላካችን በሞቱ ወደደን ተነጥቆ ሰላም እረፍታችን ላያድን ላይፈውስ ጽድቃችን ተጥለን ስንኖር በሞት በደምህ ወጣን አርነት በደምህ ወጣን ነጻነት አዝ የጭንቀት የመከራ ዓመት ተረሳ በኢየሱስ ሞት በፍጹም ፍቅሩ ወደደን በሞቱ ከሞት አዳነን በሞቱ ከሞት አዳነን አዝ ህዝቡን ሲያስጨንቅ የነበረ የጠላት ቅጥሩ ተሰበረ ማልቀስ ቀረልን መቅበዝበዝ ገነት ገብተናል በእርሱ ወዝ ገነትን ወረስን በእርሱ ወዝ አዝ ሰማይና ምድር ተስማሙ ታጥበዋልና በደሙ ነፃነት አዋጅ ተሰማ አዜምን የጽድቅን ዜማ ዘመርን የጽድቅ ዜማ አዝ ህዝቡን ሲያስጨንቅ የነበረ የጠላት ቅጥሩ ተሰበረ ማልቀስ ቀረልን መቅበዝበዝ ገነት ገብተናል በእርሱ ወዝ ገነትን ወረስን በእርሱ ወዝ ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

Ethiopian_Orthodox_Church_song_የዘማሪ_ዲ_ን_አቤል_መክብብ_በቸርነት_በይቅርታ.m4a

19 392
263
መስከረም ፫ አባ ዲዮናስዮስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ይኸውም የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት ሲሆን እርሱም የትንሣኤ ሙታንን ድርሳን የደረሰው ነው፡፡ ይኸውም ነፍስ ከሥጋ ጋር ትሞታለች፣ በትንሣኤም ከሥጋ ጋር  አብራ ትነሣለች የሚሉ መናፍቃን ከዐረቢያ አገር በመነሳታቸው ቅዱስ ዲዮናስዮስ በግብጽ የአንድነት ገባዔ አድርጎ ቢያስተምራቸው እምቢ ቢሉት ዛሬ በቤተ ክርስቲያን ስለ ትንሣኤ ሙታን የሚነገረውንና የነፍስን ረቂቅነት፣ ዘላለማዊና ሕያዊት መሆኗን የሚናገር ድርሳን ደረሰ፡፡ ከደረሳቸው ድርሰቶች መካከልም፦ በዚህ በቸርነቱ ስጦታ ውስጥ የእግዚአብሔር ፍቅር የጎላ የተረዳ ሆነ ነፍስ ረቂቅ ስለሆነች እንደ መላእክት በሕይወት እንድትኖር እንጂ እንዳትሞት እንዳትጠፋም ማድረጉ ነው። ከሥጋዋ በምትወጣ ጊዜ ስለ በጎ ሥራዋ እንደሚገባት መጠን ወደ ሕይወት ቦታዋ ይወስዷታል ወይም እንደ ሥራዋ ክፉነት ወደ ሥቃይ ይወስዷታል። በትንሣኤ ቀንም ንቃሕ መዋቲ ተብሎ አዋጅ ሲነገር በፈጣሪያቸው ትዕዛዝ የሙታን በድኖች ሲነሡ ነፍሳት እንዲህ ይሆናሉ እያንዳንዲቱ ነፍስ ከሥጋዋ ተዋሕዳ አብራ ትነሳለች። እግዚአብሔርንም ሲያገለግል ኖሮ በዛሬዋ ዕለት በሰላም አርፎ ወደ ሚወደው አምላክ ሄደ። በረከቱ ይደርብን! አሜን ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
17 791
24

[object Object]

[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
0
Анонімне голосування
17 970
44
በዝማሬ ዳዊት ቻናል የምትለቋቸው መልዕክቶች እኛ ጋር Not supported ነው የሚለን ብላችሁ መልዕክት ለላካችሁልን ተከታታዮች በሙሉ፤ እባክዎ ከስር ባስቀመጥነው ሊንክ የቴሌግራም መተግበሪያዎን ያዘምኑት /Update/ ያድርጉት።
Telegram - Apps on Google Play
Telegram is a messaging app with a focus on speed and security.
17 027
2
🌼አዲስ አመት አዲስ ዘመን🌼 አዲስ አመት አዲስ ዘመን  የሰጠኸን ጌታ ክበር ተመስገን ምድርን በአበባ አጊጠህ አሳምረህ ክረምትና በጋን ታፈራርቃለህ የማታንቀላፋ ሳተፍ እንኳ ለአፍታ ተመስገን አዲስ ቀን በሰጠኸን ጌታ 2 እንኳን ለዚህ ቀን አደረሳችሁ እንኳን እግዚአብሔር አብሮ አደረሰን 2 አዝ የመከራ ዘመን ታለፈና ዛሬ ለአዲስ አመት በቃን ይኸውና ዛሬ ዘመን ለፍስሃ ሰተኸናልና የዘመናት ጌታ ይድረስህ ምስጋና 2 እንኳን ለዚህ ቀን አደረሳችሁ እንኳን እግዚአብሔር አብሮ አደረሰን 2 አዝ በአመቱ ያድርሰን ብለን ተመራርቀን የዓመታት ባለቤት ይኸው አደረሰን እድሜ ጤና ሰጥተህ ለዚህ ቀን ደርሰናል የጊዜ ባለቤት በብዙ ረድቶናል 2 እንኳን ለዚህ ቀን አደረሳችሁ እንኳን እግዚአብሔር አብሮ አደረሰን 2 አዝ ከሩቅ ሀገር ያለው ላገሩ አብቃውና የአባቶች ምርቃት ያግኝ እንደገና ውዳሴ ምስጋና ለአንተ እናቀረባለን 2 እንኳን ለዚህ ቀን አደረሳችሁ እንኳን እግዚአብሔር አብሮ አደረሰን 2 አዝ የመከራ ዘመን ታለፈና ዛሬ ለአዲስ አመት በቃን ይኸውና ዛሬ ዘመን ለፍስሃ ሰተኸናልና የዘመናት ጌታ ይድረስህ ምስጋና 2 እንኳን ለዚህ ቀን አደረሳችሁ እንኳን እግዚአብሔር አብሮ አደረሰን 2 ዘማሪ ዳግማዊ ደርቤ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

አዲስ_ዓመት_አዲስ_ዘመን_በዘማሪ_ዳግማዊ_ደርቤ_አዲስ_ዝማሬ_ለአዲስ_ዓመት_እነሆ_Zemari_Da.m4a

16 649
49
🌼ተሰጥቶናል አዲስ አመት🌼 የአህዛብን  ፈቃድ ያረጋችሁበት ጣዖትን በማምለክ ይኖራችሁበት በምኞት በስካር በዘፈን ያሳለፋችሁት ይብቃ ያለፈው ዘመነ ያለ ልክ በመብላት በመጠጣት በመስረቅ በመግደል በመዋሸት የተመላለስ ነው በቂም በበቀል የተተከለ አረም ከኛ ይነቀል ተሰቶናል አዲስ ዘመን ተሰቶናል አዲስ አመት ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንኑርበት አዝ በከንቱ አንድከም በብዙ አንልፋ ይህ የዓለም ጤዛ ነው ታይቶ የሚጠፋ  በመንፈስ ቅዱስ ሃይል እንድንታደስ በፍጹም ንስሐ አሁን እንመለስ ተሰቶናል አዲስ ዘመን ተሰቶናል አዲስ አመት ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንኑርበት አዝ በድካም አይለቅ ዘመናችን ቸርነቱ በዝቶ የተሰጠን ብርሃናችንም በሰው ፊት ይብራ ቅጠል ብቻ እንሁን ፍሬንም እናፍራ ተሰቶናል አዲስ ዘመን ተሰቶናል አዲስ አመት ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንኑርበት አዝ ያለ ልክ በመብላት በመጠጣት በመስረቅ በመግደል በመዋሸት የተመላለስ ነው በቂም በበቀል የተተከለ አረም ከኛ ይነቀል ተሰቶናል አዲስ ዘመን ተሰቶናል አዲስ አመት ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንኑርበት ዘማሪ በአቤል በገና ተማሪዎች 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

በገና_መዝሙር_ናጌን_ቁጥር_1_ተሰጥቶናል_አዲስ_ዘመን.m4a

16 587
67

[object Object]

[object Object]
[object Object]
[object Object]
[object Object]
0
Анонімне голосування
16 360
10
🌼ያለፈው ዘመኔ ይበቃኛል🌼 ያለፈው ዘመኔ ይበቃኛል 2 በአምላክ መታመኔ ይሻለኛል 2 እውነት በሌለበት በውሸቱ ኑሮ ነፍሴ እየባዘነች በኃጢአት ቀጠሮ አሁን ግን ተረዳሁ ይበቃኛል እግዚአብሔር አምላኬ ይሻለኛል አዝ ካራን ተሰሎንቄ ባቢሎንና ግብፅ አይኔን ቢጋርዱኝ በእግዚአብሔር እንዳምፅ ዛሬ ግን ማዳኑን አየሁት ያዳነኝን አምላክ ወደድኩት አዝ ጌታን ባለማወቅ የተጓዝኩትጉዞ በሀጢያት በእርኩሰት ህሊናዬ ናውዞ ሰማሁት አወኩት ቃልህን በእርሱ ላይ አቀናሁ መንገዴን አዝ እረፍት ያጣሁበት ያለፈው ዘመኔ ዛሬ ጠፍቶልኛል ተወግዷ ከአይኔ ህግህ ለመንገዴ ብርሀን ነው አዲስ ሰው የሆንኩት በአንተው ነው ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️

ያለፈው ዘመኔ ይበቃኛል.mp3

16 250
110
መስከረም ፪ በዚህች ዕለት የካህኑ የዘካርያስ ልጅ መጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዕረፍቱ ሆነ። መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ንጉሥ ሄሮድስን የወንድምህን ሚስት ልታገባ አልተፈቀደልህም እያለ ይዘልፈው ነበር። ዳግመኛም ሌላ ያደርገው ስለነበረው ክፉ ነገር ይገሥጸው ነበር። ቅዱስ ዮሐንስም በተግሣጽ ላይ ተግሣጽን በጨመረ ጊዜ ንጉሡ ቅዱስ ዮሐንስን ተቀየመውና በግዞት ቤት አኖረው። በመጨረሻም ንጉሱ በዚህች ቀን ልደቱን ባከበረ ግዜ የሄሮድያዳ ልጅ በዘፈን አጥምዳ ቃል አስገባችው እርሱም የከበረች የቅዱስ ዮሐንስን አንገት ቆርጦ ሰጣት። አንገቱ ግን ክንፍ አውጥታ ትሰብክ ነበረ። አበውም እንዲህ አሉ ;- እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር። ደቀ መዛሙርቱም ይህን በሰሙ ጊዜ መጥተው በድኑን ወስደው ቀበሩት። በረከቱ ይደርብን! አሜን ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
17 123
57
መስከረም ፪ በዚህች ዕለት የካህኑ የዘካርያስ ልጅ መጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዕረፍቱ ሆነ። መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ንጉሥ ሄሮድስን የወንድምህን ሚስት ልታገባ አልተፈቀደልህም እያለ ይዘልፈው ነበር። ዳግመኛም ሌላ ያደርገው ስለነበረው ክፉ ነገር ይገሥጸው ነበር። ቅዱስ ዮሐንስም በተግሣጽ ላይ ተግሣጽን በጨመረ ጊዜ ንጉሡ ቅዱስ ዮሐንስን ተቀየመውና በግዞት ቤት አኖረው። በመጨረሻም ንጉሱ በዚህች ቀን ልደቱን ባከበረ ግዜ የሄሮድያዳ ልጅ በዘፈን አጥምዳ ቃል አስገባችው እርሱም የከበረች የቅዱስ ዮሐንስን አንገት ቆርጦ ሰጣት። አንገቱ ግን ክንፍ አውጥታ ትሰብክ ነበረ። አበውም እንዲህ አሉ ;- እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር። ደቀ መዛሙርቱም ይህን በሰሙ ጊዜ መጥተው በድኑን ወስደው ቀበሩት። በረከቱ ይደርብን! አሜን ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
1
0
🌼የአዋጅ ነጋሪ ቃል🌼 የአዋጅ ነጋሪው ቃል በበረሃ አየለ የእግዚአብሔርን መንገድ አስተካክሉ እያለ ምስክርነቱን ዮሐንስ ካስረዳ ልባችን ለጌታ መልካም መንገድ ይሁን የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም አውደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም ሀገራችንን ባርኪልን ድንግል ማርያም ተራራው ዝቅ ይበል ጠማማውም ይቅና ካልተስተካከለ መንገድ የለምና የእግዚአብሔርን መንግስት እንመስርት ሁላችን ማረፊያ እንዲሆነን ለመጪው ሃብታችን የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም አውደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም ቤተክርስቲያን ጠብቂ ድንግል ማርያም ክፋትና ተንኮል ከልባችን ይጥፋ ጽድቅና ርህራሄ በኛ ላይ ይስፋፋ ሥጋና ደምህን በክብር አግኝተናል ህይወት እንዲሆነን አምላክ ተማጽነናል የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም አውደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም ሀገራችንን ጠብቂ ድንግል ማርያም ሁለት ልብሶች ያሉት ከማብዛት ልብስን ለሌለው ያድለው  ሁለተኛውን ከበደላችንም አንጻን አደራህን በክፉ እንዳንጠፋ እኛ ባህሮችህ የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም አውደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም ሀገራችንን ጠብቂ ድንግል ማርያም ክፋትና ተንኮል ከልባችን ይጥፋ ጽድቅና ርህራሄ በኛ ላይ ይስፋፋ ሥጋና ደምህን በክብር አግኝተናል ህይወት እንዲሆነን አምላክ ተማጽነናል የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም ቤተክርስቲያንን ጠብቂ ድንግል ማርያም የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም አውደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም ዘማሪት ፀዳለ ጎበዜ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

የአዋጅ_ነጋሪው_ቃል_ዘማሪት_ፀዳለ_ጎበዜ.m4a

15 632
157
ይህን ማድረግ ቀናችሁን ቀና ያደርጋል። በ2017 ዓ.ም ሕይወታችሁን የሚለውጥ አንድ ልማድ ላጋራችሁ! ሁልግዜ ጠዋት ስራም ሆነ ትምህርት ከመጀመራችሁ በፊት በዕለቱ የሚታሰበውን የአንድ ቅዱስ ታሪክ ከስንክሳር አንብባችሁ ጀምሩ። እንደው ግዜ አጥሮአችሁ ስንክሳር ማየት ካልቻላችሁ ወይም ስንክሳር ከሌላችሁ ግን ሁልግዜ ጠዋት ጠዋት አንድ ሰዓት ላይ በዝማሬ ዳዊት የቴሌግራም እና የፌስቡክ ገጽ የአንድ ቅዱስ ታሪክ ከስንክሳር በአጭሩ ስለምንለቅ እርሱን ሳያነቡ በፍጹም እንዳይውሉ። እንዲሁም ጠዋት የምንለቃቸውን ዝማሬዎችም በማድመጥ ቀናችሁን በመንፈሳዊነት ጀምሩ። መልካም አዲስ አመት የዝማሬ ዳዊት ገጽ አስተዳዳሪዎች 👉
17 266
31
🌼 እንደምን በረታች 🌼 እንደምን በረታች ዳነች ሰውነቴ ብትወደኝ እኮ ነው አቤት መድኃኒቴ ይቺን ዓመት ደግሞ አንተ ብትተወኝ ወዳጄ  መውደድህ ፍቅርህ አስለቀሰኝ ×2 የአህዛብን ፈቃድ ያደረኩበት ቀን እንደምን ይቆጠር ገብቶ በእኔ ዘመን ካየሁ ጀምሮ ይቆጠር እድሜ ሳላውቀህ የኖርኩት እኔ አይደል ጌታዬ ×2 አዝ የትግስት መጠን ስፋቱ ጥልቅ ነው ሁሌም እያጠፋሁ ቃልህ የፍቅር ነው ረቡኒ ተናገር ላድመጥ በዝምታ እስራቴ ይውለቅ ስትናገር ጌታ ×2 አዝ በእኔ ውስጥ ምሰሶ እያለ ተጋርዶ አይኔ ያያል የሰው የበደልን ነዶ አልታዘዝ ብዬ ልቤን ሳትታዘብ ሰው እየከሰስኩም አደረከኝ ገንዘብ ×2 አዝ ሰው ፊትን እያየ ሞገስን ሲያበዛ ሚዛንህ ልብ ነው የዓለሙ ቤዛ ከአገር የሰፋውን የእኔን እዳ ምህረ ለትንሽ ስጨክን ይቅር አለኝ ፍቅር ከአገር የሰፋውን የእኔን እዳ ምህረ ለትንሽ ስጨክን ይቅር አለኝ ልብህ ስላልተውከኝ ክበር ስላልተውኝ ንገስ የልቤ መድኃኒት ተስፋዬ ኢየሱስ ×2 ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

344337857.mp3

16 418
172
እግዚአብሔር የሚወዳችሁ እናንተም የምትወዱት ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የእውነት አዲስ ዓመት እንዲኾንላችሁ ካሻችሁ ነፍሳችሁን ከኀጢአት ቀንበር አላቋት እንጂ ድጋሜ በኀጢአት ሸክም አትጫኗት፡፡ አሮጌው ዓመት እንዳለቀ ስታዩ እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡ ወደሌላ ዘመን አሸጋግሯቸዋልና እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡ ልቡናችሁንም ውቀሱት፡፡ በዕሜአችሁ ስንት ጊዜ እያለፈ እንደ ኾነ እያሰባችሁም ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁት፡- ቀናት እየሮጡ ነው፡፡ ዓመታቱም እየነጐዱ ነው፡፡ የዕድሜዬ መንገድም እየተጋመሰ ነው፡፡ ታዲያ ምን በጐ ምግባር ያዝኩ? ከዚህ ምድር የማልፍበት ቀን እየቀረበ ነው፡፡ ታዲያ ምን የጽድቅ ሥራ ሠራሁ? በዚህ ዕድሜዬ መሥራት የነበረብኝ ምግባር ትሩፋት ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ አልችልም፡፡ ታዲያ ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ የማልችላቸውም የጽድቅ ሥራዎች (ፆም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ አገልግሎት፣… ዕድሜ ሲገፋ ይከብዳሉና) እንዳቅሜ እያደረግኩ ነውን? በማለት ልቡናችሁን ጠይቁት፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
16 169
43
🌼 አዲስ ዘመን አየን🌼 ኧኸ በጽድቃችን አይደል ኧኸ በመልካም ስራችን ኧኸ በቸርነቱ ነው ኧኸ ለዚህ የደረስን መውጣት መግባታችን እርሱ ሲፈቅድ ነው አዲስ አመት አየን ከሞት የተረፍነው ሜዳው ምድረ በዳው ደምቆ በአበባ አዲስ ቀን ተሰጠን ይሄው ዘመን ጠባ የሰማይ ጠል ወርዶ ምድር ረሰረሰ ዝማሬን ይሰዋ ለዚህ የደረሰ አ/ዝ ዘመን አክሊል ሆነ የክብር ሽልማት ባርኮ ሲለግሰን የምሕረትን ዓመት የሚያስፈልገንን ስለሚያውቅ ቀድሞ ለንስሐ ሰጠን ዛሬን እንደከርሞ አ/ዝ መልካሞች ቀኖችን ማየት የሚፈልግ ከክፋ እርቆ መልካም ነገር ያድርግ ዘመን የሚከፋው መልካም የሚያደርገው የሰው ልጅ ሕይወት ነው ሁሉን የሚያበጀው አ/ዝ ጆሮ ስንቱን ሰማ ስንቱን አየ አይናችን ባሳለፍነው አመት ባሳለፍነው ዘመን ዳግመኛ ከቸርከን ፈቅደህ እንድንኖር የእርቅ አድርግልን የሰላም የፍቅር አ/ዝ ሰዓታትን በቀን ቀንን በሳምንታት እያፈራረቀ ወራትን በአመታት በበዛው ምህረቱ ጨመረልን እድሜ ለመንግስቱ ግዛት የለውም ፍጻሜ ዘማሪ:- ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

NEW_አዲስ_ዝማሬ_አዲሰ_ዘመን_አየን_ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ_mahtot.m4a

16 208
102
🌼አምላክ ሆይ ባርክልን🌼 ውድ የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮች እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አሸጋገራችሁ። የዝማሬ ዳዊት ቻናል ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን መልካም አዲስ ዓመትን ይመኛል። መልካም በዓል🌼🌼🌼 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️

ዝማሬ_ዳዊት_አምላክ_ሆይ_ባርክልን_በዓሉን_16k.m4a

16 973
60
🌼 አምላክ ሆይ ባርክልን በዓሉን 🌼                                             አምላክ ሆይ ባርክልን በዓሉን /2/       ባርክልን ኧኸ በዓሉን ለዛሬ ዓመት ኧኸ አድርሰን ሠላም ፍቅር ኧኸ አድለን በዕምነታችን ኧኸ አበርታን በአንድነት ኧኸ አቁመን                              አምላክ ሆይ ባርክልን በዓሉን /2/                  ጽኑ ሠላም ኧኸ ለሐገሪቱ እንዲጦሩ ኧኸ አዛውንቱ ወጣቱ እና ኧኸ ሕጻናቱ ያለ ጊዜ ኧኸ እንዳይሞቱ አንድም ሳይጎድል ኧኸ በመሃላችን ለዓመት ያብቃን ኧኸ አምላካችን                                   አምላክ ሆይ ባርክልን በዓሉን /2/                አገልጋዩን ኧኸ ከመቅደሱ እንዲኖሩ ኧኸ ሲያወድሱ ታቦቱንም ኧኸ ከመንበሩ አታናውጠው ኧኸ ከደብሩ ወታደሩን ኧኸ በድንበሩ ጠብቅልን ኧኸ በበረከት ቸሩ ጌታ ኧኸ የፍቅር አባት        ድንግል ሆይ ባርኪልን በዓሉን /2/                   ለባርኮ ኧኸ አውደ ዓመት ንዒ ማርያም ኧኸ በምሕረት ያዘነው ኧኸ እንዲጽናና የተከዘው ኧኸ እንዲል ቀና በሐገር ውስጥ ኧኸ ውጭም ላለው በበረከት ኧኸ አትለይው                              ድንግል ሆይ ባርኪልን በዓሉን                    የናቁሽም ኧኸ ጽዮን ብለው ይሠግዳሉ ኧኸ ፊትሽ ወድቀው ካኅናቱ ኧኸ በማሕሌቱ በቅዳሴው ኧኸ በሠዓታቱ ከልጅሽ ጋር ኧኸ ከዓለም ጌታ ዘመሩልሽ ኧኸ በዕልልታ                             ድንግል ሆይ ባርኪልን በዓሉን                ባርኪልን  ኧኸ /4/ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
17 103
67
"...ያክለ ክሙ ዘሐለፈ መዋዕል" "...ያለፈው ዘመን ይበቃችኋል" ፩ኛ ጴጥ ፬ ÷ ፫ ውድ የዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አሸጋገራችሁ። የዝማሬ ዳዊት ቻናል ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን መልካም አዲስ ዓመትን ይመኛል። 👉
16 042
20
መስከረም 1  በዚህች ቀን ከአስራሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የሆነው በርተሎሜዎስ ምስክር ሆኖ አረፈ። ወንጌልን እዲሰብክ የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ተመርጦ ወደ ተለያዩ ሀገሮችና እግዚአብሔርን ወደማያውቁ ሰዎች እየተላከ  ወንጌልን እየሰበከ፣ እያስተማረና፣ ተአምራትን እያደረገ ሕዝቡን ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር እየመለሰ ኖረ። ሙታንን እያስነሳ፣ የተቆረጡ በሰው እጅ ላይ ያሉ የወይን ቅርንጫፎችን ፍሬ እንዲያፈሩ እያደረገና ብዙ ድንቅ ተአምራትን እየሰራ ሕዝቡን ይመልስ ነበር። በአንድ ሀገር የነበረ ንጉስ አግሪጳም ስለርሱ በሰማ ጊዜ በከበረ ሐዋርያ በርተሎሜዎስ ላይ እጅግ ተቆጣ በማቅ ከረጢት ውስጥ እንዲያደርጉትና አሸዋ ሞልተው ከባሕር እንዲጥሉት አዘዘ እንዲሁም ይህን አደረጉበት። ምስክርነቱንና ተጋድሎውንም በዚች ዕለት ፈጸመ። በረከቱ ይደርብን! አሜን ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
16 695
29
መስከረም  1 ሐዋርያው በርተሎሜዎስ ሐዋርያው በርተሎሜዎስ በጌታችን ከተመረጡ ከአስራሁለቱ ሐዋርያት አንዱ  ነው። ወንጌልን እዲሰብክ የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ተለያዩ ሀገሮች ና እግዚአብሔርን ወደማያውቁ ሰዎች እየተላከ  ወንጌልን እየሰበከ፣ እያስተማረና፣ ተአምራትን እያደረገ ሕዝቡን ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር መለሰ። ሙታንን እያስነሳ፣ የተቆረጡ በሰው እጅ ላይ ያሉ የወይን ቅርንጫፎችን ፍሬ እንዲያፈሩ እያደረገና ብዙ ድንቅ ተአምራትን እየሰራ ሕዝቡን ይመልስ ነበር። ሐዋርያው በርተሎሜዎስም ከዝሙት ርቀው ንጹሐን እንዲሆኑ ሰዎችን የሚያዝ ሆነ። በአንድ ሀገር የነበረ ንጉስ አግሪጳም ስለርሱ በሰማ ጊዜ በከበረ ሐዋርያ በርተሎሜዎስ ላይ እጅግ ተቆጣ በማቅ ከረጢት ውስጥ እንዲያደርጉትና አሸዋ ሞልተው ከባሕር እንዲጥሉት አዘዘ እንዲሁም ይህን አደረጉበት። ምስክርነቱንና ተጋድሎውንም በዚች ዕለት ፈጸመ።     በረከቱ ይደርብን! አሜን   ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
1
0
🌼ዘመንን ሰጠኝ እንዳመሰግን🌼 ሳይቆጥር ለዚህ ያደረሰኝ     ማነው እንደ እርሱ ሳይተሳሰብ በደሌን ትቶ      ጸጋ ሞገሱ      ዘመንን ሰጠኝ እንዳመሰግን በመቅደሱ ይደንቀኛል ምህረቱ ርኅራኄው ውበቱ ገደብ አልባ ከፍታ ፍቅር ልቡ የጌታ           አዲሱን ቀን እንዳየው          ጨለማዬን ሊያበራው          ከዘመናት ስፋት ላይ          አስጌጠልኝ በፀሐይ አ/ዝ ሲመግበው አለሙን ሲያረሰርስ ቃዴስን በፍቅር ዜማ ማራኪ ወንዙን ውኃውን ባራኪ             እስከ ልኩ እየሞላ            ወይንን ጨምርኩ ዘለላ            ባወድሰው ቀን በቀን           አይገልጸውም ምሕረቱን አ/ዝ እያጠራው ሰማዩን እየራሰ ምድርቱን በከዋክብት አስውቦ ጸጋ ምሕረት ደርቦ         ተራራውን  ነቅሶታል          ልምላሜ ኩሎታል          ከዘመናት እፍታ         ባርኮ ሰጠኝ ይቅርታ አ/ዝ አየዋለሁ ሲሰራ ዘወትር ለኔ ሲራራ ያስነባኛል ዘወትር አዲሱን ቀን ሲቀምር         አላፍርበት በስሙ         ስለ ዳንኩኝ በደሙ         የመውደዱን ፍለጋ        ገዝቶ አሳየኝ በዋጋ አ/ዝ እያጠራው ሰማዩን እየራሰ ምድርቱን በከዋክብት አስውቦ ጸጋ ምሕረት ደርቦ          ተራራውን  ነቅሶታል          ልምላሜ ኩሎታል          ከዘመናት እፍታ         ባርኮ ሰጠኝ ይቅርታ ዘማሪ፦ ዲያቆን አቤል መክብብ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

NEW_አዲስ_ዝማሬ_ዘመንን_ሰጠኝ_እንዳመሰግን_ዘማሪ_ዲያቆን_አቤል_መክብብ_mahtot.m4a

16 978
102
🌼ዘመንን ሰጠኝ እንዳመሰግን🌼 ሳይቆጥር ለዚህ ያደረሰኝ     ማነው እንደ እርሱ ሳይተሳሰብ በደሌን ትቶ      ጸጋ ሞገሱ      ዘመንን ሰጠኝ እንዳመሰግን በመቅደሱ ይደንቀኛል ምህረቱ ርኅራኄው ውበቱ ገደብ አልባ ከፍታ ፍቅር ልቡ የጌታ           አዲሱን ቀን እንዳየው          ጨለማዬን ሊያበራው          ከዘመናት ስፋት ላይ          አስጌጠልኝ በፀሐይ አ/ዝ ሲመግበው አለሙን ሲያረሰርስ ቃዴስን በፍቅር ዜማ ማራኪ ወንዙን ውኃውን ባራኪ             እስከ ልኩ እየሞላ            ወይንን ጨምርኩ ዘለላ            ባወድሰው ቀን በቀን           አይገልጸውም ምሕረቱን አ/ዝ እያጠራው ሰማዩን እየራሰ ምድርቱን በከዋክብት አስውቦ ጸጋ ምሕረት ደርቦ         ተራራውን  ነቅሶታል          ልምላሜ ኩሎታል          ከዘመናት እፍታ         ባርኮ ሰጠኝ ይቅርታ አ/ዝ አየዋለሁ ሲሰራ ዘወትር ለኔ ሲራራ ያስነባኛል ዘወትር አዲሱን ቀን ሲቀምር         አላፍርበት በስሙ         ስለ ዳንኩኝ በደሙ         የመውደዱን ፍለጋ        ገዝቶ አሳየኝ በዋጋ አ/ዝ እያጠራው ሰማዩን እየራሰ ምድርቱን በከዋክብት አስውቦ ጸጋ ምሕረት ደርቦ          ተራራውን  ነቅሶታል          ልምላሜ ኩሎታል          ከዘመናት እፍታ         ባርኮ ሰጠኝ ይቅርታ ዘማሪ፦ ዲያቆን አቤል መክብብ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
1
0
"...ያክለ ክሙ ዘሐለፈ መዋዕል" "...ያለፈው ዘመን ይበቃችኋል"                               ፩ኛ ጴጥ ፬ ÷ ፫ 👉
16 286
21
​​🌼 ልጄ ሆይ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ ልጄ ሆይ....... ወጣትነት ፈትኖህ፤ለስጋህ አድልተህ፤ነፍስህን አቀጭጨኻት ከአለም የኖርክበትን ዓመትህን ጥለኸው በንሰሐ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ። ልጄ ሆይ ..... በአዲስ አመት ለአምላክህ የሚገባህን ግብር ትፈፅም ዘንድ በፍቅሩ አፀድ እንድትገኝ ካለመታዘዘ ተለወጥ። ልጄ ሆይ ....... በአፈር ከሚሸነፈው ስጋዊ ዘርህ ወጥተህ ሰማያዊነትን ከሚያለብስህ ከማይጠፋው ሰማያዊ ዘር ክብረት ታደርግ ዘንድ ሰውን ካለመውደድ ጥላቻ ተለወጥ። ልጄ ሆይ ...... በምክንያቶች ተደልለህ አፅዋማትን ዘለህ፤ምስጋናን ነፍገህ፥አገልግሎትን ንቀህ ከአለም ጫጫታ ውስጥ የዘፈቀውን ማንነትህ እንዳያጠፋህ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ። ልጄ ሆይ ...... ዲያቢሎስ በቃል እንዳያስትህ፤በማማለል እንዳይጠልፍህ የመንጋውን ጠባቂ ቃልን ስማ፤ የመታዘዝን በረከት ታገኝ ዘንድ ከትምህክትህ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ። ልጄ ሆይ .....ቀናት ሳይሆን መንፈስህ ይለወጥ፤ፀሐይ ሳትሆን የህይወት ጀንበርህ ይለወጥ። ልጄ ሆይ ......ዕለታት አይሰልጥኑብህ፤ ዘመናት እስከ ሞትህ ጥግ ድረስ እስኪገፉህ ሳትጠብቅ አንተም እንደ ዘመንህ ተለወጥ ልጄ ሆይ .....የእግዚአብሔር ፍቅር ለተከፈተ ልብ ቸር ነው ። ርህራሄው ጥልቅ ነው ። በአምሳሉ ፈጥሮሃል እና እንዳትጠፋ አንድያ ልጁን ለሞት አሳልፎ እስከመስጠት የደረስ ጥልቅ ፍቅር አሳይቷል ። ስለዚህ ከዘመንህ ቀድመህ ተለወጥ። ልጄ ሆይ ...አዛኝቷን ተለማመን፤መላአኩን ተማለደው ፤ቀደምት ቅዱሳን አባቶችህን ጥራ፤ ፃድቃንን ዘክር እንጅ ላለመለወጥ ተማምለው ቀናት ብቻ ከሚለወጥባቸው ሰልፈኞች ተርታ አትገኝ ። በንስሐ ወደ በረቱ የምንመለስበት ዘመን ይሁንልን! አሜን 🌻 መልካም አዲስ አመት ይሁንልን ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ! 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
image
21 395
317
🌼ምስባክ መስከረም 1/1/2014 ዓ.ም 🌼በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ። ዲያቆን፦ 2 ቆሮ 6÷1-11 ንፍቅ ዲያቆን፦ ያዕ 5÷8-13 ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 5÷12-17 ፦ መዝ 141÷ 6-8 አድኅነኒ እምእለ ሮዱኒ እስመ ይኄይሉኒ። ወአውጽኣ እሞቅሕ ለነፍስየ። ከመ እግነይ ለስምከ እግዚኦ። ፦ እጅግ ተቸግሬያለኹና ወደ ልመናዬ አድምጥ በርትተውብኛልና ከሚያሳድዱኝ አድነኝ። አቤቱ ስምክን አመሰግን ዘንድ። ፦ ማቴ 11÷1-20 ፦ ዘወልደ ነጎድጓድ 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼

ነይ ነይ ማርያም ዝማሬ ዳዊት

16 368
47
🌼ምስባክ መስከረም 1/1/2014 ዓ.ም 🌼የዐውደ አመት ምስባክ🌼 ፦ መዝ 64 ÷ 11-13 ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ ። ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም ። ወይረውዩ አድባረ በድው ። ፦ በቸርነትኽ አመትን ታቀዳጃለኽ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል። የምድረ በዳ ተራራዎች ይረካሉ ኮረብታዎችም በደስታ ይታጠቃሉ። 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼

ነይ ነይ ማርያም ዝማሬ ዳዊት

15 888
43
​​🌼 "የዕንቁጣጣሽ" ሥያሜ አመጣጥ? ዓመታት ተፈጽመው አዲስ ዓመት ስንጀምር ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዓውደ ዓመት፣ አዲስ ዓመት ፣ ዕንቁጣጣሽ እየተባለ ይጠራል፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንደሚያስረዱት ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜው አመጣጥ ወይም ጥንተ ታሪክ በመጀመሪያ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በዕጣ ሲያካፍላቸው አፍሪቃ ለካም ደረሰችው፡፡ በአፍሪቃ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኃ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት «ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ» ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የሀገራችን ንግሥት ንግሥተ ሳባ የንጉሥ ሰሎሞንን ዜና ጥበብ እየሰማች ስታደንቅ ትኖር ነበር፡፡ በጆሮዋ የሰማችውን በዓይኗ ዓይታ ለመረዳት ስለፈለገች በግመሎች ላይ ሽቱና እጅግ ብዙ ወርቅ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኝ በኢየሩሳሌም የማይገኝ ልዩ ልዩ ገጸ በረከት አስጭና ከብዙ ሠራዊት ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፡፡ ከንጉሡ ሰሎሞንም ጋር ተገናኝታ የያዘችውን ገጸ በረከት ከሰጠችው በኋላ ብዙ ነገሮችን ጠየቀችው፡፡ እርሱም አንድ ነገር ላይ ሰውሮ ሁሉንም ገለጸላት፡፡ ቤተ መንግሥቱንም፣ በቤተ መንግሥቱ የሚገኙ እጅግ በጣም የከበሩ ዕቃዎችን ሁሉ አስጎበኛት፡፡ ሲያበቃ «ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ» ሲል እጅግ በጣም የከበረ ዕንቁ አበረከተላት/ሰጣት/፡፡ ወሩም ወረኃ መስከረም ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው መጥቷል፡፡ አሁን ከሚፈጸመው ሥነ ሥርዓት ደርሶ በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ የሚከበረውም መስከረም አንድ ቀን ነው፡፡ አንድም «ዕንቁ ዕፅ አወጣሸ» ብሎ የአበባውን መፈንዳትን ያስረዳናል፡፡ መልካም አዲስ አመት ይሁንልን ወስብሐት ለእግዚአብሔር 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
image
17 083
127
​​🌼 ዘመን መለወጫ አስቀድመን ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ማንነትና የዘመን መለወጫ መግቢያው ላይ በስሙ ስለመጠራቱ ተመልክተናል፡፡ ዘመን መለወጫ ደግሞ ለምን እንደተባለና ለምን መስከረም ወር ላይ እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንዲህ በማለት ያትታሉ፡፡ ሲያትቱም ብርሃናት/ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት/ የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው፡፡ ያን ጊዜ ሌሊቱም ከቀኑ ጋር ይተካከላል፡፡ ዓመቱንም ጠንቀቀው ቢቆጥሩት ፫፻፷፬ ቀናት ይሆናል፡፡ ለዘመን መታወቂያ ይሆን ዘንድ ፀሐይና ጨረቃ ከዋክብትን ፈጠረ ይላልና /መጽሐፈ ሔኖክ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፵፱፡፡ በሌላ በኩልም በዘመነ ኖኅ ዓለምን ውኃ አጥለቅልቋት ከቆየ በኋላ ዳግመኛ ከነበረው ውኃ የተገለጠችበት ወር «በመጀመሪያም ወር በምድር ታየች የንፍር ውኃው ከምድር ደረቀ» የሚለውን መሠረት አድረገው የአቡሻኽር ሊቃውንት የዘመን መለወጫን ታሪካዊ አመጣጥ ያስረዳሉ፡፡ /መጽሐፈ ኩፋሌ፡ ምዕ ፯ ቁጥር ፩/ በመሠረቱ ዘመን ተለወጠ ሲባል የሚለወጡት ወራቱ ብቻ አይደሉም፡፡ በወቅቱ የሚከሰቱት/የተከሰቱት/ መልካምም ሆነ ክፉ ነገር /ገጠመኝ ሲሆን ወራቶቹ ግን ያው በየዓመቱ እየተፈራረቁ ይመጣሉ፡፡ ዘመን መለወጫ ላይ የሰው ልጆች ሕይወት ሊለወጥ ይገባል፡፡ ተማሪው ተምሮ ወደቀጣዩ ክፍል /ደረጃ/ የሚለወጥበት፣ ገበሬው የክረምትን ወራት በሚገባ ተጠቅሞ የሚቀጥለውን የበጋወራት የሚቀበልበት፣ ሠራተኛው የክረምቱን ዝናብ ታግሶ የፀሐይን ወራት የሚቀበልበት ሌላውም እንደዚያ ሆነው ወራቶቹ በዚያ ዘመን ያለው የተፈጥሮ ክስተቶች የሚለወጥበት ዘመን ተለወጠ እየተባለ ይነገራል፡፡ 👉 በቀጣይ የዕንቁጣጣሽ ስያሜ አመጣጥ? ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ! 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
image
17 036
64
🌼🌼ዘመን ተሰጠን ለምስጋና🌼🌼 ዘመን ተሰጠን ለምስጋና ዘመን ተሰጠን ለውዳሴ ተመስገን ሥላሴ ቸርነትን ሰጠን ዘመን ለፍስሐ ይቺም እድሜ ለእርቅነች ለንስሀ ጥበባችን መቼ ሆነ እውቀታችን ምሕረትህ በዝቶልን ነው መቆማችን ከሰጠኸን አዲስ ዓመት ከሰጠኸን አዲስ እለት እንዘምራለን በደስታ በአኮቴት                    አ/ዝ🌼🌼🌼🌼 የለውም ጫፍ የለው ድንበር ያንተ ምህረት በእድሜያችን ጨመርክልን ይህቺን እለት ተደነቅን ተገረምን በአንተ ፀጋ ቀንና ሌት ሲፈራረቅ ክረምት በጋ ከሰጠኸን አዲስ ዓመት ከሰጠኸን አዲስ እለት እንዘምራለን በደስታ በአኮቴት              አ/ዝ🌼🌼🌼🌼 ምድር ረክታ በዝናቡ በሰማይ ጠል በአበባ ደምቃ ታየች በሐመልማል በእድሜያችን ላይ ከጨመርከው ይህን ዓመት የንስሀ ይሁንልን የመጸጸት ከሰጠኸን አዲስ ዓመት ከሰጠኸን አዲስ እለት እንዘምራለን በደስታ በአኮቴት           አ/ዝ🌼🌼🌼🌼 የእርቅ ይሁን ዘመናችን የይቅርታ ሰላም ትሁን ሀገራችን ፍቅር ተመልታ መለያየት መጠላላት የሌለበት አድርግልን ጌታችን ሆይ ይህን ዓመት ከሰጠኸን አዲስ ዓመት ከሰጠኸን አዲስ እለት እንዘምራለን በደስታ በአኮቴት 🌼ዘማሪ ዲ/ን አብኤል መክብብ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

ዘመን ተሰጠን ለምስጋና.mp3

1
0
ይችን አመት ተወኝ እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አሸጋገራችሁ። 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️

ይቺን ዓመት ተወኝ.mp3

17 952
165
ይቺን ዓመት ተወኝ ከአመት እስከ አመት ፍሬን ሳላፈራ ደረቅ እንደሆንኩኝ በራድ ወይም ትኩስ ሁለቱንም ሳልሆን እንዲያው ለብ እንዳልኩኝ አለሁኝ በቤትህ ለሙን መሬትህን እንዳጎሳቆልኲኝ አውቃለሁ አምላኬ ፍሬን ለመቀበል እንዳመላለስኩሁህ ዛሬም ሳላፈራ እሾህን አብቅዬ ደርቄ ጠበኩህ ያልተደረገልኝ ያላፈሰስክብኝ ያልሰጠኸኝ የለም ነገር ግን ይህ ሁሉ አላርምህ አለኝ አለየኝም ከዓለም አዝ የማትሰለቸኝ ሆይ ተነስቼ እስክቆም እባክህ ታገሰኝ የኔን ክፋት ተወው መላክህን ሰምተህ ይቺን ዓመት ተወኝ አዝ አውቃለሁ ታውቃለህ ቀጠሮን ሰጥቼ እንደማላከብር ብዙ ጊዜ አቅጄ ብዙ ጊዜ ዝቼ በወሬ እንደምቀር ዘንድሮስ እንዳልኩኝ አምና ይሔን ጊዜ ሰምተኸኝ ነበር ምንም ሳልለወጥ ዘንድሮዬ አልፎ በአዲስ ተቀየረ አዝ ፍሬ የማይወጣኝ እኔን በመኮትኮት እጆችህ ደከሙ እኔ ግን አለሁኝ ዛሬም አልበቃኝም በኃጢአት መታመሙ የቃልህን ውሃ በድንጋይ ልጅህ ላይ ሳታክት ስታፈስ ዘመን ተቆጠረ ወደ ልቤ ሳይሰርግ ሕይወቴን ሳይለውጥ እንዲያው ፈሶ ቀረ አዝ ቃልህን ጠግቤ እያገሳሁት ነው ሌሎች እስኪሰሙ በቃልህ መኖር ግን አልያዝህ አለኝ ከበደኝ ቀለሙ ብዙ ጥቅስ አገኘው ከቅዱስ መጽሐፍህ ገልጬ አይቼ ከራሴ ላይ ብቻ አንድ ጥቅስ አጣሁኝ በበደል ተኝቼ አዝ ውጤቴ ደካማ ትምህርት የማይሰርፀኝ ተማሪ ብሆንም ይቺን ዓመት ተወኝ ደግሞ ትንሽ ልማር ታገሰኝ አሁንም እባክህ አልቆረጥ በቅዱስ መሬትህ ልቆይ ፍቀድልኝ ያፈሩት ቅዱሳን የፍሬያቸው ሽታ መዓዛ እንዲደርሰኝ አዝ የተሸከምከኝ ሆይ ዛሬም ተሽከመኝ አትሰልቸኝ አደራ ማን ይታገሰኛል ጠላት እየሆንኩት አይሰሩ ስሰራ አታውጣኝ ከቤትህ ብዙ ቦታ አልይዝም ፍሬ ስለሌለኝ ስፍራ የማያሻኝ ቤት የማላጣብብ ፍሬ አልባ በለስ ነኝ አዝ ቦታስ የሚይዙ ባለምግባሮቹ ቅዱሳንህ ናቸዉ ልክ እንደ ዘንባባ የተንዥረገገ ተጋድሎ ፅድቃቸው ከሊባኖስ ዝግባ እጅጉን የበዛ ገድል ትሩፋታቸው አዝ እኔ አይደለሁም ቦታስ የሞትይዘው ያንተው እናት ናት ስሮቿ በምድር ጫፎቿ በሰማይ ሲደርሱ ያየናት ይቺን ዓመት ተወኝ ከስሯ ሆናለው ባፈራ ምናልባት አዝ ይቺን ዓመት ተወኝ እባክህ አምላኬ አንድ ዓመት ምንህ ናት ሺ ዓመት አንድ ቀን አይደለም ወይ ላንተ ዓመት ኢምንት ናት ይሔ ዓመት አልፎ ዳግም ዓመት ስጠኝ እስከምልህ ድረስ እባክህን ጌታ ይቺን ዓመት ተወኝ የወጉን እንዳደርስ ዘማሪ ዲያቆን ቀዳሚ ጸጋ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
19 138
158
ይቺን ዓመት ተወኝ ከአመት እስከ አመት ፍሬን ሳላፈራ ደረቅ እንደሆንኩኝ በራድ ወይም ትኩስ ሁለቱንም ሳልሆን እንዲያው ለብ እንዳልኩኝ አለሁኝ በቤትህ ለሙን መሬትህን እንዳጎሳቆልኲኝ አውቃለሁ አምላኬ ፍሬን ለመቀበል እንዳመላለስኩሁህ ዛሬም ሳላፈራ እሾህን አብቅዬ ደርቄ ጠበኩህ ያልተደረገልኝ ያላፈሰስክብኝ ያልሰጠኸኝ የለም ነገር ግን ይህ ሁሉ አላርምህ አለኝ አለየኝም ከዓለም አዝ የማትሰለቸኝ ሆይ ተነስቼ እስክቆም እባክህ ታገሰኝ የኔን ክፋት ተወው መላክህን ሰምተህ ይቺን ዓመት ተወኝ አዝ አውቃለሁ ታውቃለህ ቀጠሮን ሰጥቼ እንደማላከብር ብዙ ጊዜ አቅጄ ብዙ ጊዜ ዝቼ በወሬ እንደምቀር ዘንድሮስ እንዳልኩኝ አምና ይሔን ጊዜ ሰምተኸኝ ነበር ምንም ሳልለወጥ ዘንድሮዬ አልፎ በአዲስ ተቀየረ አዝ ፍሬ የማይወጣኝ እኔን በመኮትኮት እጆችህ ደከሙ እኔ ግን አለሁኝ ዛሬም አልበቃኝም በኃጢአት መታመሙ የቃልህን ውሃ በድንጋይ ልጅህ ላይ ሳታክት ስታፈስ ዘመን ተቆጠረ ወደ ልቤ ሳይሰርግ ሕይወቴን ሳይለውጥ እንዲያው ፈሶ ቀረ አዝ ቃልህን ጠግቤ እያገሳሁት ነው ሌሎች እስኪሰሙ በቃልህ መኖር ግን አልያዝህ አለኝ ከበደኝ ቀለሙ ብዙ ጥቅስ አገኘው ከቅዱስ መጽሐፍህ ገልጬ አይቼ ከራሴ ላይ ብቻ አንድ ጥቅስ አጣሁኝ በበደል ተኝቼ አዝ ውጤቴ ደካማ ትምህርት የማይሰርፀኝ ተማሪ ብሆንም ይቺን ዓመት ተወኝ ደግሞ ትንሽ ልማር ታገሰኝ አሁንም እባክህ አልቆረጥ በቅዱስ መሬትህ ልቆይ ፍቀድልኝ ያፈሩት ቅዱሳን የፍሬያቸው ሽታ መዓዛ እንዲደርሰኝ አዝ የተሸከምከኝ ሆይ ዛሬም ተሽከመኝ አትሰልቸኝ አደራ ማን ይታገሰኛል ጠላት እየሆንኩት አይሰሩ ስሰራ አታውጣኝ ከቤትህ ብዙ ቦታ አልይዝም ፍሬ ስለሌለኝ ስፍራ የማያሻኝ ቤት የማላጣብብ ፍሬ አልባ በለስ ነኝ አዝ ቦታስ የሚይዙ ባለምግባሮቹ ቅዱሳንህ ናቸዉ ልክ እንደ ዘንባባ የተንዥረገገ ተጋድሎ ፅድቃቸው ከሊባኖስ ዝግባ እጅጉን የበዛ ገድል ትሩፋታቸው አዝ እኔ አይደለሁም ቦታስ የሞትይዘው ያንተው እናት ናት ስሮቿ በምድር ጫፎቿ በሰማይ ሲደርሱ ያየናት ይቺን ዓመት ተወኝ ከስሯ ሆናለው ባፈራ ምናልባት አዝ ይቺን ዓመት ተወኝ እባክህ አምላኬ አንድ ዓመት ምንህ ናት ሺ ዓመት አንድ ቀን አይደለም ወይ ላንተ ዓመት ኢምንት ናት ይሔ ዓመት አልፎ ዳግም ዓመት ስጠኝ እስከምልህ ድረስ እባክህን ጌታ ይቺን ዓመት ተወኝ የወጉን እንዳደርስ ዘማሪ ዲያቆን ቀዳሚ ጸጋ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
1
0
🌼ዘመን ተሰጠን🌼 ዘመን ተሰጠን ለምስጋና ዘመን ተሰጠን ለውዳሴ ተመስገን ሥላሴ ቸርነትን ሰጠን ዘመን ለፍስሐ ይቺም እድሜ ለእርቅነች ለንስሀ ጥበባችን መቼ ሆነ እውቀታችን ምሕረትህ በዝቶልን ነው መቆማችን ከሰጠኸን አዲስ ዓመት ከሰጠኸን አዲስ እለት እንዘምራለን በደስታ በአኮቴት አዝ🌼 የለውም ጫፍ የለው ድንበር ያንተ ምህረት በእድሜያችን ጨመርክልን ይህቺን እለት ተደነቅን ተገረምን በአንተ ፀጋ ቀንና ለሊት ሲፈራረቅ ክረምት በጋ ከሰጠኸን አዲስ ዓመት ከሰጠኸን አዲስ እለት እንዘምራለን በደስታ በአኮቴት አዝ🌼 ምድር ረክታ በዝናቡ በሰማይ ጠል በአበባ ደምቃ ታየች በሐመልማል በእድሜያችን ላይ ከጨመርከው ይህን ዓመት የንስሀ ይሁንልን የመጸጸት ከሰጠኸን አዲስ ዓመት ከሰጠኸን አዲስ እለት እንዘምራለን በደስታ በአኮቴት አዝ🌼 የእርቅ ይሁን ዘመናችን የይቅርታ ሰላም ትሁን ሀገራችን ፍቅር ተመልታ መለያየት መጠላላት የሌለበት አድርግልን ጌታችን ሆይ ይህን ዓመት ከሰጠኸን አዲስ ዓመት ከሰጠኸን አዲስ እለት እንዘምራለን በደስታ በአኮቴት ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

ዘመን ተሰጠን.mp3

16 149
147
ጷጉሜ 5 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም ጷጉሜ አምስት በዚች ቀን ንፁሕ ድንግል አባት፤ የምስር ሀገር ኤጲስቆጶስ አባ ያዕቆብ አረፈ። አባታችን ገና በታናሽነቱ የምንኩስናን ልብስ ይለብስ ዘንድ ነፍሱ ወደደች ከሀገሩም ወጥቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደና በአባ ዮሐንስ ሐጺር በዓት ውስጥ በጽኑ ተጋድሎ ኖረ። የደግነቱ የትሩፋቱና የቅድስናውም ዜና ተሰማ በእግዚአብሔር ፈቃድ በምስር ሀገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት። በሹመቱ ወንበርም በተቀመጠ ጊዜ ጾምን ጸሎትን ተጋድሎውንም ጨመረ። ስለ ሹመቱም ተጋድሎውንና አገልግሎቱን አበዛ እንጂ ቸልም አላለም። ሕዝቡንም ሁልጊዜ ያስተምራቸዋል ኃጢያትን በመስራት የሚኖሩትን ይገስጻቸዋል። በንስሐ እስኪመለሱም ሥጋውና ደሙን ከመቀበል ያግዳቸዋል። በጎ ተጋድሎንም በፈጸመ ጊዜ ጥቂት ታመመ መንጋዎቹንም ጠርቶ በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ አዘዛቸው። ካህናቱንም ጠርቶ በጸሎትና በአገልግሎት ጊዜ ቸል እንዳይሉ አዘዛቸው። በዚህች ዕለትም አረፈ። በረከቱ ይደርብን! አሜን ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
16 103
26

እሰይ ደስ ደስ ይበለን.mp3

15 198
111
​​🌼 አበባዮሽ 🌼 እሰይ /ደስ ደስ ይበለን/(2) አዲሱ አመት መጣልን ደስ ደስ ይበለን ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2) ጌቶች አሉ ብለን ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2) እሜቴ አሉ ብለን ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2) ዘመን መጣ ብለን አበባዮሽ                    ለምለም(2) ባልንጀሮቼ                        " ግቡ በተራ                       " በእግዚአብሔር መቅደስ     "   በዚያች ተራራ                   "    እንድታደንቁ                      "           የአምላክን ሥራ                  "     ህይወት ያገኛል                  "   እርሱን የጠራ                    "       አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2) አበባዮሽ                   ለምለም (2) ክረምት አለፈ                   " ጨለማው ጠፋ                 "    የመስቀሉ ቃል                  " ሆነልን ደስታ                    "    እናገልግለው                    "   ቤቱ ገብተን                      "      ትንሽ ትልቁ                      "   ተሰልፈን                         "         አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2) አበባዮሽ               ለምለም(2) ያንን ኩነኔ                    " ዘመነ ፍዳ                    "  የሞቱ በራፍ                 " ያ ምድረበዳ                  " ልክ አንደ ክረምት          " ሄደ ተገፎ                     " ፀሐይ ወጣልን              " ጨለማው አልፎ             " አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2) አበባዮሽ                ለምለም(2) ይኸው መስከረም           " ይኸው ፀሐይ                 "     ንጉሡ ወርዶ                  "        ከላይ ሰማይ                  "         አውደ ዓመት ሆነ            " ደስታ ሰላም                   " ፍቅር ሲገለጥ                "    በአርያም                       "        አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2) አበባዮሽ                ለምለም(2) ይኸው አበባ                  " ለምለም ቄጤማ             " አዲሱ ዘመን                  " አምጥቷልና                   "     በሩን ክፈቱ                    "        መኳንንቶቹ                    "        የክብር ንጉሥ                "     ይግባ ቤታችሁ              "  አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2) አበባዮሽ                ለምለም(2) ቤታችሁ ይሙላ             " ሰላም ደስታ                  " ሰጥቷችሁ እርሱ            " የሁሉ ጌታ                     "       ከዘመን ዘመን                "      ያሸጋግራችሁ                 "       የሽበትን ዘር                  "    ይሸልማችሁ                 "       አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ ይሸታል ዶሮ ዶሮ የእማምዬ ጓሮ ይሸታል ጠጅ ጠጅ የአባብዬ ደጅ አብዬ ኧኸ ደግሞም እማምዬ መጣሁ ለሰላምታ ከቤት አሉ ብዬ እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰዎት ብዬ ከብረው ይቆዩን ከብረው የክብርን ወንጌል ሰምተው የበጉን ሥጋ በልተው የአምላክን ፊቱን አይተው ከብረው ይቆዩን ከብረው 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
17 691
178
​​🌼 አበባዮሽ 🌼 እሰይ /ደስ ደስ ይበለን/(2) አዲሱ አመት መጣልን ደስ ደስ ይበለን ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2) ጌቶች አሉ ብለን ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2) እሜቴ አሉ ብለን ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2) ዘመን መጣ ብለን አበባዮሽ                    ለምለም(2) ባልንጀሮቼ                   " ግቡ በተራ                   " በእግዚአብሔር መቅደስ     "   በዚያች ተራራ           "    እንድታደንቁ      "           የአምላክን ሥራ        "    ህይወት ያገኛል       "   እርሱን የጠራ       "       አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2) አበባዮሽ                   ለምለም (2) ክረምት አለፈ             " ጨለማው ጠፋ      "    የመስቀሉ ቃል          " ሆነልን ደስታ       "    እናገልግለው         "   ቤቱ ገብተን       "      ትንሽ ትልቁ        "   ተሰልፈን        "         አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2) አበባዮሽ               ለምለም(2) ያንን ኩነኔ               " ዘመነ ፍዳ             "  የሞቱ በራፍ            " ያ ምድረበዳ            " ልክ አንደ ክረምት     " ሄደ ተገፎ               " ፀሐይ ወጣልን        " ጨለማው አልፎ      " አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2) አበባዮሽ                ለምለም(2) ይኸው መስከረም    " ይኸው ፀሐይ     "     ንጉሡ ወርዶ    "        ከላይ ሰማይ   "         አውደ ዓመት ሆነ      " ደስታ ሰላም     " ፍቅር ሲገለጥ     "    በአርያም         "        አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2) አበባዮሽ                ለምለም(2) ይኸው አበባ            " ለምለም ቄጤማ       " አዲሱ ዘመን            " አምጥቷልና        "     በሩን ክፈቱ       "        መኳንንቶቹ       "        የክብር ንጉሥ      "     ይግባ ቤታችሁ       "  አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2) አበባዮሽ                ለምለም(2) ቤታችሁ ይሙላ      " ሰላም ደስታ            " ሰጥቷችሁ እርሱ     " የሁሉ ጌታ        "       ከዘመን ዘመን    "      ያሸጋግራችሁ    "       የሽበትን ዘር         "    ይሸልማችሁ      "       አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ ይሸታል ዶሮ ዶሮ የእማምዬ ጓሮ ይሸታል ጠጅ ጠጅ የአባብዬ ደጅ አብዬ ኧኸ ደግሞም እማምዬ መጣሁ ለሰላምታ ከቤት አሉ ብዬ እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰዎት ብዬ ከብረው ይቆዩን ከብረው የክብርን ወንጌል ሰምተው የበጉን ሥጋ በልተው የአምላክን ፊቱን አይተው ከብረው ይቆዩን ከብረው 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
852
13

እሰይ ደስ ደስ ይበለን.mp3

1 089
10
​​🌼 መስከረም 1 ሃይማኖታዊ መሠረት ቅዱስ ማርቆስ ወንጌሉን ሲጽፍ «የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ እነሆ መንገድህን የሚጠርግ መልእከተኛዬን በፊትህ እልካለሁ የጌታን መንገድ አዘጋጅ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ» ተብሎ በኢሳይያስ እንደ ተነገረ የነቢዩ ዘካርያስ  ልጅ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በዘመነ ብሉይ መጨረሻና በዘመነ ሐዲስ መጀመሪያ ላይ ተነሥቶ «መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ» እያለ ስለ ክርስቶስ አዳኝነት እየመሰከረ በምድረ በዳ የንስሐን ጥምቀት እያጠመቀ ለኃጢአት ሥርየት እየሰበከ መጣ ብሎ በዘመነ ወንጌል የመጀመሪያ ምዕራፍ ገልጾታል። /የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፵፤ ትንቢተ ኢሳይያስምዕ ፵ ቁ ፫ - ፬/። የመጥምቁ ዮሐንስ ተግባር ለዘመነ ወንጌል በር ወይም መነሻ ሆኖ መገኘቱን በመረዳት የቤተክርስቲያን አበው የበዓላቱን ድንጋጌ በወሰኑበት ጊዜ የመጥምቁ ዮሐንስ መታሰቢያ በዓል የኢትዮጵያ ርዕሰ ዓውደ ዓመት በሚሆን መስከረም ፩ ቀን እንዲከበር በየዓመቱ የዘመኑ መጀመሪያ በእርሱ ስም እንዲጠራ አባቶች ደንግገዋል፡፡ / ድርሳነ ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 1ጠ 3/ ይህንንም በዓል አባቶቻችን በርእሰ ዓውደ ዓመት ማክበር እንደሚገባ አስበው ያደረጉት ነው፡፡ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በሰማዕትነት ያረፈበት ቀን ሆኖ አይደለም፡፡ ለአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ወይም ርእሰ ዓውደ ዓመት «ቅዱስ ዮሐንስ» ይባላል፡፡  መጽሐፈ ስንክሳር የዓመቱን መጀመሪያ /መስከረምን/ ሲያትት «ይህ የመስከረም ወር የተባረከ ነው እርሱም የግብጽና የኢትዮጵያ ዓመቶች መጀመሪያ ነው በማለት ያስረዳል፡፡ የዚህ ወር ቀኑና ሌሊቱ እኩል ፲፪ ሰዓት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ከመስከረም አንድ ቀን ጀምሮ ቀኑ እየጎደለ ይሔዳል፡፡ 👉 ከዚህ በመቀጠል በዓሉ በተለያየ ስያሜ ስለመጠራቱና ትርጓሜያቸውን እንመለከታለን፡፡ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ! 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
image
17 796
86
✝ጎሳ ልብየ ✝    ጎሳ ልብየ ቃለ ሰናየ/2/    ወአነ አይድ ቅዳሴሃ ለማርያም/2/ አ.ዝ እኔስ የማርያምን ውዳሴዋን እናገራለሁ እንደ አባቴ ዳዊት በበገና እዘምራለሁ ቀን ከሌሊት ሳልል ለምስጋና እተጋለሁ የኃጢአቴ ቁስል እንዲፈወስ እጮሃለሁ ምርኩዜ ነሽና እመቤቴ በአንቺ እመካለሁ አ.ዝ ኦ...እመቤቴ በእውነት እንወድሻለን የእውነተኛ መብል ክርስቶስን ወለድሽልን ምክንያተ ድሂን ሆይ ድንግል ማርያም የአምላክ መገኛ በአማላጅነትሽ በመታመን እንጮሃን እኛ ምሕረትን አድይን ኪዳነምህረት የዓለም መዳኛ አ.ዝ ስለ ቸርነትሽ እመቤቴ ለእኔ እናቴ ነሽ ስለ ንግሥትነትሽ እመቤቴ ነሽ ዝናባት ሳያጠጡት አየራት ሳያሳድጉት ሰማያዊ እንጀራ የሰጠሸን ቤተልሔማዊት ቅድስተ ቅዱሳን የኖህ መርከብ የአምላክ እናት አ.ዝ ቃና ዘገሊላ በሰርጉ ቤት በዚያ ተገኝተሽ ሳለሽ ውኃውን ወደ ወይን ባንቺ ምልጃ እዳስለወጥሽ ዛሬም የእኔ ሕይወት ወይኑ አልቆ ባዶ ሆኖአልና አንቺየአምላክ እናት ንጽሂትቅድስት ርኅሪሂተ ህሊና ሕይወቴን አድሰሽ ቀድሰሽ ሙይው በምስጋና ዘማሪ፦ እንግዳወርቅ በቀለ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

ጎሳ ልብየ (2).mp3

16 666
203
የሰማይም የምድርም ጌታ✝ የሰማይም የምድርም ጌታ በዝቶልናል እጅግ ስጦታ በጎነትህ ቸርነትህ እረድቶናል ክቡር ስምህ። (2*) አዝ በማይዝሉ ጽኑ ክንዶችህ ተደገፍን በቸርነትህ የፍቅር አባት ላመኑህ ጥላ ክርስቶስ ነህ የእኛ ከለላ። አዝ ፍፁም ቆምን በንጹህ ደምህ ተፈወስን በቅዱስ ቃልህ መዛል ድካም ከቶ አይነካንም ኃይላችን ነው ሁሌም የአንተ ስም። አዝ ያጣው ሲጮኽ ፊትህ ተደፍቶ ሲያማክርህ ምስጢሩን ገልጦ አባት ለልጁ እንደሚራራ አወጣህን ከሙታን ሥፍራ፡፡ አዝ ምስክር ነን ለዓለም ሁሉ ስላዳነን በሕያው ቃሉ ለውለታው ምላሽ ባይኖርም ከምስጋና ከቶ አንቦዝንም    ዘማሪ፦ ቸርነት ሰናይ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️

የሰማይም የምድርም ጌታ.mp3

17 420
132
ጷጉሜ 4 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም፤ ጷጉሜ አራት በዚች ቀን ተጋዳይ አባ ባይሞን አረፈ። አባ ባይሞን የተባረኩ ስድስት ታላላቅ መነኮሳት ወንድሞች ያሉት ሲሆን ከኮከብም ኮከብ ይበልጣልና ከስድስቱ ቅዱሳን እርሱ የተለየ ነበር። መንፈስ ቅዱስ አነሳስቷቸው ሁሉም በአንድ ቀን መነኮሱ። ለእናታቸውም እንዳይቸግራት የሚያስፈልጋትን ሁሉ ካዘጋጁ በኋላ ይህን ዓለም ንቀው ወደ ገዳም ተጉዘው በአንዲት በዓት አረፉ። አባ ባይሞን በአስቄጥስ ገዳም ፈተና፣ የሃይማኖት ጥርጥርና ደዌ ያገኘውን ሁሉ ይፈውስ፣ያረጋጋም ነበር። ስለ ምንኩስና ሕግ፣ስለ መጋደል እና ስለ አምልኮም ብዙ ድርሳናትን ደረሰ። ዕድሜውንም በተጋድሎና በትሩፋት ሥራ ከፈጸመ በኋላ ወደ መልካም ዕርግና ደርሶ እግዚአብሔርን አገልግሎ አረፈ። አባታችን እንዲም ይሉናል እኛ የወንድማችንን በደል ብንሰውር እግዚአብሔርም በደላችንን ይሠውርልናል። በረከቱ ይደርብን! አሜን ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
18 545
31
✞ ቅዱስ ሩፋኤል ✞ ምስጢረ መለኮት አድራሽ ነህ ለእስራኤል መድኃኒት ነው ስምህ ቅዱስ ሩፋኤል (፪) የሱሳኑ ነቢይ በእጆችህ ተዳስሶ አይኖቹ በርተዋል ምህረትን ለብሶ እኔ ራሴን ማየት ተስኖኛልና ከኔ አልፎ አምላኬን ልየው በጽሞና አዝ እረፍትህ ምስጋና ነውና አታርፍም ችግር የምትጋርድ በያዝከው በእሳት ፍም በሳት ሰረገላ በሚፋጠን እግርህ ፈጥነህ ድረስልኝ የልቤን ስነግርህ አዝ ከአህዛብ እርሾ ደግሜ እንዳልበላ እንደ ጦቢት ጋርደኝ በክንፎችህ ጥላ እግዚአብሔርን ላስብ በፍፁም ልቦና አንተን እንደሚልክ አምነዋለሁና አዝ ሰናክሬም በክፋት ቆሞብኝ ከፊቴ ናልኝ እልሃለሁ ሩፋኤል አባቴ የሰራብኝን ግፍ በአንተ ረስቻለሁ በመድኃኒት እጅህ ደስታን አግኝቻለሁ ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ። ጦቢት፲፪፥፲፭ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

ቅዱስ ሩፋኤል.mp3

18 072
86
✞ ሩፋኤል ብዬ ✞ ሩፋኤል ብዬ ስጠራው ምስጢሬን ሁሉ ሳወራው ትላንት የረዳኝ ጸሎትህ ዛሬም ይድረሰኝ ለልጅህ ሩፋኤል ብዬ  አንደበቴ ለምዶት ስምህን ሩፋኤል ብዬ  ልጅነቴ  ቀምሶት ፍቅርህን ሩፋኤል ብዬ የህይወቴ ቅጥር ሲላላ ነፍሴ ትጮሀለች ሩፋኤል ሩፋኤል ብላ አዝ ሩፋኤል ብዬ ከአምላኬ ስትላክ ለምህረት ሩፋኤል ብዬ ስትጠብቀኝ ቀንና ለሊት ሩፋኤል ብዬ ባስከፋህ በትግስት እለፈኝ ምልጃህ እረድኤት ያግዘኝ እኔን ይደግፈኝ አዝ ሩፋኤል ብዬ ህመሜ እንዳይጸና ክፋቱ ሩፋኤል ብዬ መድሐኒት እንዲሆን ሀሞቱ ሩፋኤል ብዬ  ካጠገቤ እንዳትርቅ ከጎኔ ትዳሬ እንዲጸና ሩፋኤል እንዲበራ አይኔ አዝ ሩፋኤል ብዬ ከአምላኬ ስትላክ ለምህረት ሩፋኤል ብዬ ስትጠብቀኝ ቀንና ለሊት ሩፋኤል ብዬ ባስከፋህ በትግስት እለፈኝ ምልጃህ እረድኤት ያግዘኝ እኔን ይደግፈኝ ዘማሪ ሚኪያስ መንገሻ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...

ሩፋኤል ብዬ.mp3

17 494
194
​​ሩፋኤል ይቅር በለኝ አሳድገኝ ብዬህ ሮጬ ከልጆች ጋር ተሯሩጬ በጠበልህ እየታጠብኩ የውኃ ጨው እየቀመስኩ ሩፋኤል አሳድገኝ እንደ ታላቆቼ አድርገኝ ብዬ እየጮህኩኝ ስጣራ ሰምተኸኛል ከልጅ ተራ ዘንድሮን ግን ተጠለልኩኝ ጠበል ሲወርድ  ተሸሸግሁኝ ከበረከትህ ሸሸሁኝ ከቡራኬህ አመለጥኩኝ ሩፋኤል ሆይ ይቅር በለኝ ስላበቃ ልጅነቴ በቆሸሸ ሰውነቴ በረከሰ ማንነቴ እንዳላረክስ ጠበልህን ተጠለልኩት ጥምቀትህን ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
image
17 126
82
​​ፈታሔ ማሕፀን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ " የዘለዓለም ሕይወትን እንዲወርሱ ቅዱሳን መላእክት ምእመናን ለመርዳት ለማገልገል ከእግዚአብሔር የሚላኩ ረቂቃን ፍጥረታት አይደሉምን? ( ዕብ ፩÷፲፬) ብሏል። ቅዱስ ዮሐንስም "የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ"( ራእዩ ለዮሐንስ ፰÷፬) በማለት ተናግሯል። ቅዱሳን መላእክት ያለማያቋረጥ ለፈጣሪያቸው ምስጋና የሚያቀርቡ ረቂቃን ፍጥረታት ናቸው። በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ለተልእኮ ይፋጠናሉ። የሰውን ጸሎትና ልመና ወደ እግዚአብሔር ያደርሳሉ፤ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ምሕረት ወደ ሰው አድርሰው በእምነት ያጸናሉ። "በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፥ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው" (ራእ. ፰÷፪) የሚለው የሚያስረዳን ለተልእኮ መፋጠናቸውን ነው። ሄኖክም “በሰው ሰውነት ላይ የተሾሙ ከከበሩ ፯ቱ ሊቃነ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል አንዱ ነው” (ሄኖ.፮÷፩-፵፪) ብሏል። የሰዎችን ልመና ወደ እግዚአብሔር፣ የእግዚአብሔርን ምሕረት እና በረከት ወደ ሰው የሚወርድባት ዕለት"ርኅወተ ሰማይ” ትባላለች። ይህች ዕለት የሰዎች ሁሉ ጸሎት የሚያርግባት፣ አራተኛው መጋቢ ኮከብ የሚያልፍባት፣ ለሰው ልጆች ከፈጣሪያቸው ጸጋ በረከት የሚሰጥባት ስለሆነች "ርኅወተ ሰማይ-ሰማይ የሚከፈትባት ቀን" ትባላለች። እንዲህ የሚባለው በሰማይ መዘጋት መከፈት ኑሮበት አይደለም። የሰው ልጆችን ልመና ቅዱሳን መላእክት የሚያሳርጉበት፣ አንድም ቅዱስ ሩፋኤል የዓመቱን የጸሎት መዝገብ የሚከፍትበት ቀን ስለሆነ እንጂ። ቅዱስ ሩፋኤል ልቡናን ደስ የሚያሰኝ፣ ባለ መድኃኒት፣ የጸሎት መዝገብ መክፈቻ ቍልፍ የተሰጠው፣ የሴቶችን ማሕጸን የሚፈታና ሳይጨነቁ እንዲወልዱ ምጥን የሚያቀል መልአክ ነው። "ለሰብእ ወለእንሰ ፈታሔ ማሕጸኖሙ አንተ" እንዲል። የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ወደ ከበረና ወደ ገነነ ወደ እግዚአብሔር ጌትነትም ከሚያገቡ ከከበሩ መላእክት መካከል አንዱ እኔ ሩፋኤል ነኝ "(ጦቢያ ፲፪÷፲፭) የሚለው የሚያስገነዝበው ተራዳኢነታቸውን፣ ባለሟልነታቸውን፣ አማላጅነታቸውን ነው። ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን ዐረገ"(ሐዋ. ፲÷፬) የሚለው የመላእክትን አገልግሎት የሚገልጥ ነው። መላእክት ሰዎችን ይራዳሉ፣ የሰውን ጸሎት ያሳርጋሉ፣ ያማልዱሉ፣ ሰዎችን ከመከራ ነጥቀው ያወጣሉ። "የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ። አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ እነዚህን ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው? አለ፣ እግዚአብሔርም መልሶ ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረው መልአክ በመልካምና በሚያጽናና ቃል ተናገረው። ስለዚህም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ። ስበክ እንዲህም በል። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል (ዘካ፣ ፩÷፲፪÷፲፬) የሚለው አማላጅነታቸውን የሚገልጥ የማጽናኛ ቃል ነው። ጦቢያና መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ወደ ራጉኤል ቤት በደረሱ ጊዜ ሣራ ተቀብላ ደስ አሰኘቻቸው። መልአኩም ለጦቢያ አባትህ ከዘመዶችህ ወገን አግባ ያለህን ቃል አስብ አለው። ራጉኤልም ልጁ ሣራን ለጦቢያ አጋባት። ተመግበውም ከጨረሱ በኋላ ጦቢያን ወደ እርሷ አገቡት፤ ወደ እርሷም በገባ ጊዜ የመልአኩ የቅዱስ ሩፋኤልን ነገር አሰበ፤ የዕጣን እራሪ ወሰደ፤ ከዚያም ዓሣ ከልቡና ከጉበቱ ጨምሮ አጤሰው። ሽታውም ያን ጋኔን በሸተተው ጊዜ እስከ ላይኛው ግብፅ አውራጃ ድረስ ሸሸ። መልአኩም ጋኔኑን አሰረው( ጦቢ ፰÷፩) የተባለው የሚያስረዳን የመላእክትን ተራዳኢነት ነው። ጦቢያ የሰርጉን በዓል በጨረሰ ጊዜ ወደ አባቱ ቤት ከሚስቱ ከሣራና ከመልአኩ ከቅዱስ ሩፋኤል ጋር ተመለሱ። ሩፋኤልም አለው፥ "ያባትህ ዐይኖች እንዲበሩ አውቃለሁ፤ አንተ ግን ያን ሐሞት ያባትህ ዓይን ኳለው፤ በተኳለም ጊዜ ብልዙ ከአይኑ ይወጣል በደህናም ያያል። ጦቢያም የአባቱን አይን ኳለው ዓይኑም በራለት”( ጦቢ ፲፩÷፮) ተብሎ እንደተነገረው እግዚአብሔር ከዚህ ክፉ ወረርሽኝ ጠብቆን በሰላም በጤንነት ለሚመጣው ዓመት ያድርሰን። የጦቢትን ዓይን ያበራውን የቅዱስ ሩፋኤልን ዓመታዊ በዓል አክብረን በረከት ለማግኘት ያብቃን።አሜን!! ዲ/ን ተመስገን ዘገየ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ! 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
image
16 529
82
ጳጉሜ 3 ርኅወተ ሰማይ (ሰመይ የሚከፈትባት) ይህች ዕለት የሰዎች ሁሉ ጸሎት የሚያርግባት አራተኛው መጋቢ ኮከብ የሚያልፍባት: ለሰው ልጆች ከፈጣሪያቸው ጸጋ በረከት የሚሰጥባት ዕለት ስለሆነች ሰማይ የሚከፈትባት ቀን ትባላለች። ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት በመጽሐፈ ጦቢት ላይ ተጽፎ እንደምናገኘው ቅዱስ መልአክ ሰው(አዛርያን) መስሎ ጦብያን ለትዳር አብቅቶ ሣራን አስማንድዮስ ከሚባል ሰይጣን አድኖ የጦቢትን ዓይን አብርቷል። ዳግመኛም ይህች ቀን ለቅዱስ ሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱ ናት። ቅዱስ ሩፋኤል ልቦናን ደስ የሚያሰኝ: ባለ መድኃኒት ፈዋሽ: የጸሎት መዝገብ መክፈቻ የተሰጠው በዙፋን ለይ በክብር ለሚቀመጡ መላእክት መሪ: የሰውንም ሆነ የእንስሳትን ማኅጸን የሚፈታ: (አዋላጅ: ምጥን የሚያቀል) መላእክ ነው። በረከቱ ይደርብን! አሜን ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
16 385
45
​​ጳጉሜን ጳጉሜን የሚለው ስያሜዋ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ጭማሪ ማለት ነው፡፡ በግእዝ ተውሳክ ማለት ሲሆን ተውሳክ ማለት ተጨማሪ ማለት ነው፡፡ “ወሰከ - ጨመረ” ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ ሌሎች ሀገሮች ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ያደርጓታል፡፡ ይኸውም ይታወቅ ዘንድ እኛ የወርን ቁጠር 30 ስናደርግ እነርሱ 31 ብለው የሚቆጥሩት ወር አላቸው፡፡ ይኹን እንጂ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ሳያደርጉ የዓመት ተጨማሪ አድርገዋታል፡፡ ጳጉሜን በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን ትመጣለች፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ሉቃስ መጨረሻ በዘመነ ዮሐንስ መግቢያ ጳጉሜን ስድስት ቀን ትሆናለች፡፡ በዚህም ሀገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ /Thirty months of sunshine/ በመባል ትታወቃለች፡፡ ጳጉሜን ስድስት በምትሆንበትም ጊዜ ጾመ ነቢያት /የገና ጾም/ ህዳር 14 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈትቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡ በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜን ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው። ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙዎች ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ዮዲ 2፥2-7፡፡ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋት በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡ ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት፡፡ ዮዲ 8፥2፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡ ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ፡፡ የጳጉሜን ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብባትም ወር ነች፡፡ ይህም ጳጉሜን የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️
Показати повністю ...
image
17 313
34
#ቀዋምያን ቀዋምያን ለነፍሳት እሙንቱ ሊቃናት  ኡራኤል ወሩፋኤል/2/  ይትፌነዉ ለሣህል/2/ እምኀበ ልኡል/2/  ፦ ለነፍሳት የቆሙ እነዚህ መላእክት  ኡራኤልና ሩፋኤል/2/  ከልኡል ዘንድ ለይቅርታ/2/ ይላካሉ ከልኡል/2/ 💚 💚 💛 💛 ❤️ ❤️

ነይ ነይ ማርያም ዝማሬ ዳዊት

17 203
28

እመቤታችን አማላጅነቷ በቃና ዘገሊላ.m4a

17 061
23
ነገረ ማርያም ክፍል ፫ እነሆ🤲🤲🤲
19 045
3

ክርስቶስን_እስክትወልድ_ድረስ_አላወቃትም_ዮሴፍ.m4a

15 382
20

የክርስቶስ ወንድሞች እነማን ናቸው.m4a

14 957
19
ነገረ ማርያም ክፍል ፪ እነሆ🤲🤲🤲 ክፍል ፩ ያላዳመጣችሁ ካላችሁ በኮመንት አሳውቁን
16 964
2

አንቺ ሴት ለምን አላት ክርስቶስ.m4a

17 727
22
Останнє оновлення: 11.07.23
Політика конфіденційності Telemetrio