Xizmat sizning tilingizda ham mavjud. Tarjima qilish uchun bosingEnglish
Best analytics service

Add your telegram channel for

  • get advanced analytics
  • get more advertisers
  • find out the gender of subscriber
Kanal joylashuvi va tili

barcha postlar "ኡማ ቲቪ " Tv

መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ! የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇  https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf  
42 568-11
~9 396
~24
21.31%
Telegram umumiy reytingi
Dunyoda
22 541joy
ning 78 777
Davlatda, Efiopiya 
173joy
ning 396
da kategoriya
987joy
ning 2 793
Postlar arxivi
1 233
1
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የልማት ኤጀንሲ ለማጠናከር የአመራር ለውጥ ተካሄደ! የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የልማት ክንፍ የኾነው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲ (ኢሙልኤ) አዲስ ለተሾሙት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጁነዲን ሰይድ የኃላፊነት ርክክብ አካሄደ። በልማት ኤጀንሲው ቅጥረ ግቢ ዛሬ በተካሄደው መርኃ ግብር ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጂ ከማል ሐሩን ጠቅላይ ምክር ቤቱ በለውጥ ሂደት ላይ መኾኑን ጠቅሰው፣ ከለውጦቹ አንዱ የልማት ኤጀንሲውን በቀጣይ ለሕዝብ ተደራሽ ማድረግ መኾኑን ተናግረዋል። ጠቅላይ ምክር ቤቱ ላለፉት ዘጠኝ ወራት የተቋሙን የወደፊት አቅጣጫ ለመቅረጽ በባለሙያ ጥናት ሲያስደርግ መቆየቱን ሐጂ ከማል አስታውሰው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲ ቀደም ሲል በነበረበት የአቅም ውስንነት ሳቢያ ሰፊውን ሙስሊም ማኅበረሰብ ተጠቃሚ ማድረግ አለመቻሉን ገልፀዋል። የኢሙልኤ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አሕመድ ሑሴን ኤጀንሲው የሚሰጠውን አገልግሎት ለሕዝብ ተደራሽ ለማድረግና አቅሙን ለማሳደግ የተለያዩ ጥናቶች ሲያስጠና መቆየቱን ጠቅሰው፣ ጥናቱን ወደተግባር ለመለወጥ የተቋሙን ሥራ ወደ ከፍታ ሊያደርሱ የሚችሉ የሙያ ዘርፎች ላይ ቦርዱ ቅጥር መፈፀሙን ተናግረዋል። ኢሙልኤ ከተቋቋመበት ዓላማ አኳያ ሰፊ ሥራ መሥራት ይጠበቅበታል ያሉት የቦርድ ሰብሳቢው በቀጣይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተባብሮ በመሥራት አዲሱ  አመራር ለውጥ ማምጣት ይጠበቅበታል ብለዋል። አዲሱ የኢሙልኤ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጁደዲን ሰዒድ ኤጀንሲው የሚሰጠውን ሰብኣዊ አገልግሎት በማሳደግ እንደ አገር የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት አዲሱ አመራር ከመቼውም በላይ ዝግጁ መኾኑን ተናግረዋል። በቀጣይም ሰዎች ከተረጂነት ወጥተው ወደ ረጂነት እንዲቀየሩ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች እና የገቢ ማስገኛ ሥራዎች ላይ እንደሚሰማራና፣ "ከከጃይ እጅ የላይ እጅ ይበልጣል" የሚለውን የነቢያችን ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲስ አስታውሰዋል። የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈፃሚ አባልና የትምህርትና ማኅበራዊ ዘርፍ ተጠሪ ኢንጅነር አንዋር ሙስጠፋ በአንዳንድ የአገራችን ክፍሎች በደረሱት የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ  ችግሮች ሳቢያ የእርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ በመምጣቱ የዕለት ደራሽ ሥራዎች ላይ ኤጀንሲው ጥናት በማድረግ መሥራት ይጠበቅበታል ብለዋል።
Ko'proq ko'rsatish ...
2 855
1
2 554
0
ጥራታቸውን የጠበቁ፤ የውጪ አረቢያን መጅሊስ የሚያስንቁ ማራኪ የሀገር ውስጥ መጅሊሶችን በተመጣጣኝ ዋጋ፤ ከሀምዛ ዑመር  አረቢያን መጅሊስ እና መጋረጃ ያግኙ 🏬አድራሻ:   መርካቶ ዱባይ ተራ ፓርኪንግ መውጫ አጠገብ የሱቅ ቁጥር B33/1 ስልክ፦NaN          NaN ለበለጠ መረጃና የተለያዩ እቃወችን ለማገኘት የቴሌግራም አድራሻችንን ይቀላቀሉ  
645
0
"ህይወቱን ያለ ፍትህ የተነጠቀዉ"ኸሊፋ ዊሊያምስ (marseilles william) አንዲት ጋዜጠኛን 43 ጊዜ በመውጋት ገድለሃል ተብሎ በጥርጣሬ ተይዞ ለ 24 አመት ከታሰረ በሆላ ምንም አይነት መረጃ ሳይገኝበት በሞት ስለተቀጣዉ ንፁህ ሰው ሙሉ ፕሮግራሙን ከምሽቱ 03:00 ላይ በሀሩን ሚዲያ ይጠብቁን።
3 414
0
የሒዝቡላህ መሪ ሐሰን ነስረላህ በእስራኤል የአየር ድብደባ መገደላቸው ተረጋግጧል። ለ 32 ዓመታት ሒዝቡላህን በመምራት እስራኤልን ሲያስጨንቁ የኖሩት ነስረላህ ትላንት ሌሊት ላይ በተደረገ የአየር ድብደባ ከሌሎች ባልደረቦቻቸው ጋር መገደላቸውን ሒዝቡላህ እራሱ ይፋ አድርጎታል። የኢራን ቀኝ እጅ በመካከለኛው ምስራቅ የሚባሉት ነስረላህ በአካባቢው ላይ ለአሰርት ዓመታት ተፅዕኖ በመፍጠር አቻ ያልነበራቸው ሲሆን ደቡባዊ ሊባኖስ ነፃ ግዛታቸው ነበረች። የአካባቢው ውጥረት እየናረ ሲሆን በቀጣይ ሒዝቡላህ ምን እርምጃ እንደሚወስድና የኢራን ምላሽ ደግሞ ምን ሊሆን እንደሚችል ስጋት ያጫረ ሲሆን አካባቢው በሌላ የጦርነት እቶን ሊንቀለቀል እንደሚችል የብዙዎች ስጋት ነው።
4 382
8
ከሒዝቦላህ ባይረጋገጥም ወራሪዋ እስራኤል ሀሰን ነርሰላህን ትላንትና በቤሩት  የአየር ጥቃት መግደሏን ይፋ አድርጋ ነበር ግና አሁን ባወጣው መግለጫ ሀሰን ነስረላህ ወደማይቀረው ሞት መሸጋገሩን ይፋ አድርጓል። ይህን ተከትሎ የአልቀሳም ብርጌዶች ቃል አቀባይ አቡ ኡበይዳ፡- "ከታላቅ አክብሮትና ከጠልቅ ትዕግስት ጋር ሀሰን ነስረላህ በአል አቅሳ ዘመቻ መገደላቸው ቢያሳዝነንም አሻራቸውን ግን ሁሌም እንዘክራለን። የፍልስጤም ህዝብና ጀግኖች ሙጃሂዶቻችን ፍልስጤምንና መስጂደል አቅሳን ከወራሪዋ ነፃ ለማውጣት የምናደርገውን ተጋድሎ አጠናክረን እንቀጥላለን" በማለት ተናግሯል።
4 684
4
4 800
3
እስራኤል የሂዝቦሊን መሪ ሀሰን ነስረላህን ገደልኩ አለች የሄዝቦላ ዋና ጸኃፊ ሀሰን ነስረላህ የተገደለው የእስራኤል ጦር በትናንትናው እለት በቤሩት በፈጸመው የአየር ጥቃት ነው ተብሏል።
እስራኤል የሂዝቦሊን መሪ ሀሰን ነስረላህን ገደልኩ አለች
የሄዝቦላ ዋና ጸኃፊ ሀሰን ነስረላህ የተገደለው የእስራኤል ጦር በትናንትናው እለት በቤሩት በፈጸመው የአየር ድብደባ ነው ተብሏል
4 923
1
🍔🍕🧀 እንኳን ደህና መጡ🥘☕️🍴 🚶‍♂️‍➡️🚶‍➡️🏞ወደ ካፌያችን ጎራ ብለው ጣፋጭ ምግቦችን ምቹ በሆነ ሁኔታ  ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተቋድሰው እርካታዎን ያጣጥሙ።🥬🥦🌲🌿 🍮ሲና ካፌና ሬስቶራንት @አለም ባንክ፣ ሙስዐብ መስጅድ መግቢያ ኦሮሚያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ googl አድሬስም ስላዘጋጀን በቀላሉ እኛን ማገኘት ይቻላል ። Tik Tok ቴሌግራም Facebook

file

5 202
2
ታች ወርዶ መስራት! ኡስታዝ ማህሙድ ሀሰን የልብ ❤️ስንቅ -ዛሬ በተዉፊቅ ፍልዉሀ መስጂድ ━━━━━━━━ ━━━━━━━━ ━━━━ ታች ወርዶ መስራት! ግለሰብን በኢማን ማነፅ ለዘለቄታዊ ለውጥ ያለው አስተዋፅኦ እንመለከታለን።'ኢንሻአላህ የዙሁር ሶላት እንደተጠናቀቀ በተዉፊቅ ፍልዉሀ መስጂድ🕌 ━━━━━━━━ ━━━━━━━━ ━━━━
4 523
1
እስራኤል የሄዝቦላህ መሪ ሀሰን ናስራላህን ኢላማ ያደረገ ጥቃት መፈጸሟ ተነገረ ለሄዝቦላህ ቅርበት ያላቸውና የኢራን መገናኛ ብዙሃን ናስራላህ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰባቸው እየዘገቡ ነው   ኢራን፥ እስራኤል በቤሩት እየተፈጸመችው ያለው ድብደባ “ቀይ መስመሩን ያለፈ ነው” ብላለች እስራኤል በሊባኖስ መዲና በትናንትናው እለት የፈጸመችው ድብደባ በሄዝቦላህ መሪ ሀሰን ናስራላህ ላይ ያነጣጠረ ነበር ተባለ። ቴል አቪቭ የአየር ጥቃቱ ናስራላህ ላይ ኢላማ ስለማድረጉ እስካሁን ማረጋገጫ ባትሰጥም ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የእስራኤል ባለስልጣን የሄዝቦላህ ማዘዣ ጣቢያ እኛ በመሪው ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ስለመፈጸሙ ተናግረዋል። “ምንም እንኳን (ናስራላህ) እንዲህ ሆኗል ለማለት ጊዜው ባይሆንም አንዳንድ ጊዜ ስኬታማ ስንሆን ነገሮችን ለመሸፋፈን ይሞክራሉ” በማለትም በአየር ድብደባው ናስራላህ ጉዳት ሳይደርስባቸው እንዳልቀረ አመላክተዋል። የሊባኖሱ አል ማናር ቴሌቪዥን የሄዝቦላህ አመራሮች በተደጋጋሚ ይገኙበታል በተባለው አካባቢ በተፈጸመው ጥቃት ሰባት ህንጻዎች መፈራረሳቸውን ዘግቧል። ሄዝቦላህ እስካሁን መሪው ስለሚገኙበት ሁኔታ እስካሁን በይፋ መግለጫ አላወጣም። የኢራኑ ታስኒም የዜና ወኪል በበኩሉ ናስራላህ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰበትና ቴህራን የሚገኝበትን ሁኔታ እየተከታተለች መሆኑን ዘግቧል። የሄዝቦላህን የሚሳኤል ክፍል ሃላፊ ሙሀመድ አሊ ኢስማኤል እና ምክትሉን ሆሴን አህመድ ኢስማኤል መግደሏን ያስታወቀችው እስራኤል በዛሬው እለትም በቤሩት ዙሪያ ድብደባዋን ማጠናከሯን ሬውተርስ ዘግቧል። ለአምስት ስአታት ከ20 በላይ የአየር ድብደባዎች መፈጸማቸውን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ሊባኖሳውያን ቤታቸው ለቀው በአደባባዮች እና ፓርኮች ተሰብስበዋል ነው የተባለው። የእስራኤል ጦር ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ 10 ሮኬቶች ከሊባኖስ ወደ እስራኤል መተኮሳቸውንና “የተወሰኑት” ተመተው መውደቃቸውን ገልጿል። ይሁን እንጂ ምን ያህሎቹ ኢላማቸውን መተው ጉዳት እንዳደረሱ በዝርዝር አልጠቀሰም። የሊባኖስ የጤና ሚኒስቴር በትናንቱ ጥቃት ስድስት ሰዎች መሞታቸውንና ከ91 በላይ መቁሰላቸውን ያመላከተ ሲሆን፥ በአንድ ሳምንት ውስጥ የሞቱ ሊባኖሳውያን ቁጥር ከ700 ተሻግሯል። የትናንቱን የቤሩት ጥቃት “ቀይ መስመሩን ያለፈ ነው” ያለችው ኢራን፥ እስራኤል የአሜሪካን ቦምቦች በመጠቀም ሊባኖስን እያወደመች ነው ስትል ከሳለች። የአሜሪካው መከላከያ ሚኒስትር ሊዩድ ኦስቲን ግን ዋሽንግተን “በንከር በስቲንግ” የተሰኙት ቦምቦች ጥቅም ላይ ከመዋላቸው በፊት በቴል አቪቭ አልተነገሯትም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። በ79ኛው የመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ “ሄዝቦላህ ጦርነትን እስከመረጠ ድረስ እስራኤል ምርጫ የላትም” የላትም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከኒውዮርክ ወደሀገራቸው ተመልሰዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሄዝቦላህ የእስራኤል የደህንነት ስጋት እስከማይሆንበት ድረስ በሊባኖስ የቡድኑ ይዞታዎች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት ይቀጥላል ማለታቸውም እስራኤልና ሄዝቦላህ ከ18 አመት በኋላ ወደለየለት ጦርነት መግባታቸው አይቀሬ መሆኑን አመላካች ነው ተብሏል።
Ko'proq ko'rsatish ...
5 055
4
4 675
2

file

5 914
7
ኢንናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ከድር ሸይኽ ዳውድ ወደ አኼራ መሻገራቸው ተሰማ! በአፋር ክልል ዒልምን በማስተማር ለረጅም ዓመታት ያገለገሉት ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ከድር ዳውድ ዛሬ ጁመአ ወደ አኼራ መሻገራቸው ተሰምቷል። ሸይኽ ከድር የህይወታቸውን ረጅሙን ጊዜ ቁርኣን በማስቀራት ያሳለፉ ሲሆን በርካታ ሰዎችም እስልምናን እንዲቀበሉ እንዲሁም በርካታ መስጂዶች እንዲገነቡ ሰበብ ሁነዋል። -
6 180
2
ጥራታቸውን የጠበቁ፤ የውጪ አረቢያን መጅሊስ የሚያስንቁ ማራኪ የሀገር ውስጥ መጅሊሶችን በተመጣጣኝ ዋጋ፤ ከሀምዛ ዑመር  አረቢያን መጅሊስ እና መጋረጃ ያግኙ 🏬አድራሻ:   መርካቶ ዱባይ ተራ ፓርኪንግ መውጫ አጠገብ የሱቅ ቁጥር B33/1 ስልክ፦NaN          NaN ለበለጠ መረጃና የተለያዩ እቃወችን ለማገኘት የቴሌግራም አድራሻችንን ይቀላቀሉ  
2 078
2
5 478
1
ሐምሰተር ኮምባትና መሰል ኤር ድሮፖች የተስጣቸው ከፍተኛ ትኩረት በሀገራችን ሰርቶ የመለወጥና የማደግ የተሰፋ ጭላንጭሎች መጨላለም አመላካች ተደርጎ ቢወሰድ ስህተት አይሆንም። ከዚህ ባልተናነሰ የሚያሳሰበው መሰል ፕሮጀክቶች የሚፈጥሩት Mindset ነው። ብዙ ሳይለፉና እሴት ሳይፈጥሩ የመለወጥ ህልምን ለብዙዎች ያወርሳሉ። ይህ ደግሞ ከተጨባጭ የራቀ በመሆኑ ይዞት የሚመጣው የሰራ ባህል የብዙ ግለሰባዊና ማህበረሰባዊ ቀውስ ምንጭ ይሆናል። ስለ እድገት፥ ለውጥና ሰኬት የሚኖር ትርጓሜም ከተጨባጭ የራቀ ልብ-ወለዳዊ ይሆናል። ሌላኛው አሳሳቢ ነጥብ በመሰራት፥ ለማደግና ለመለወጥ በመትጋት ሂደት ውሰጥ ለሀላልና ሀራም መጠንቀቅ እየተዘነጋ መጥቷል። ኤር ድሮፖች መቼና በየትኛው ፕላትፎርም ሊስት ይደረጋሉ፥ የምንዛሬ ዋጋቸውና ሪዋርዳቸው ስንት ይሆናል የሚለው እንጂ ሽሪ ዐዊ ብያኒያቸው ትኩረት አልተሰጠውም። አንድ ገቢ የሚያሰገኝ እንቅስቃሴ ላይ ከመሳተፍ በፊት በሽሪ ዐው ሚዛን ላይ ማሰቀመጥና መፈተሽ፡ አዋቂዎችን መጠየቅ፥ ሀራም ላይ ላለመውደቅ ንቁ መሆን የህይወት መርህ መሆናቸው ሲቀር እሰልምና በህይወታችን ውስጥ ያለው ሚና ያንሳል። ገቢ የምናገኝበት መንገድ ላይ መጠንቀቅ ሰናቆም፡ ሰለምንበላውና የምንጠጣው ነገር ሀላልነት የምንሰጠው ትኩረት ይቀንሳል። ይህ ደግሞ የህይወት ዘይቤያችንን "Halal-conscious" ከመሆን እያራቀው በመሄድ እስልምናን መሰጂድ ውስጥ ያሰረዋል። © Ibrahim Abdu
Ko'proq ko'rsatish ...
5 407
17
4 919
4
🍔🍕🧀 እንኳን ደህና መጡ🥘☕️🍴 🚶‍♂️‍➡️🚶‍➡️🏞ወደ ካፌያችን ጎራ ብለው ጣፋጭ ምግቦችን ምቹ በሆነ ሁኔታ  ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተቋድሰው እርካታዎን ያጣጥሙ።🥬🥦🌲🌿 🍮ሲና ካፌና ሬስቶራንት @አለም ባንክ፣ ሙስዐብ መስጅድ መግቢያ ኦሮሚያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ googl አድሬስም ስላዘጋጀን በቀላሉ እኛን ማገኘት ይቻላል ። Tik Tok ቴሌግራም Facebook

file

4 556
4
الحمد لله ثم الحمد لله ውዷ እና ቆንጆዋ ልጄ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የእስኮላር ሽፕ ፕሮግራም መግቢያ ፈተናን 98·51 ከ100 በማምጣት አልፋለች ። ለሀገርና ለወገን አላህ ጠቃሚ እንዲያደርጋት የሁላችሁም ዱአ አይለያት ! !
5 243
7
4 834
2
ጁመዓ የት ሰገዳቹህ??ኹጥባው ስለምን ነበር?
5 004
2
ታላቅ የምስራች  የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት እና የበርካታ ድርጅቶችን website እና system በማበልፀግ የሚታወቀው RiseUp Tech  የሶስተኛ ዙር ምዝገባ መጀመሩን ሲያበስሮ በታላቅ ደስታ ነው። RISEUP TECH በጥቂት ወራት በገሃዱ ዓለም ፕሮጀክቶች በመታገዝ ከመሰረታዊ የኮምፒተር እውቀት ጀምሮ ፕሮፌሽናል ዌብሳይት እና አፕ አበልፃጊ ሊያደርጎት እንዲሁም አለም አቀፍዊ  ተቀባይነትን ያገኙ ዘንድ ልዩ የእንግሊዘኛና የዓረበኛ ቋንቋ ሥልጠና አዘጋጅቷል። በተጨማሪም ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤት ዝቅ አለብኝ ብለው ሳይጨናነቁ በብቁ መምህራኖቻችን ጥራት ያለው ሥልጠና በመዉሰድ ከRiseup Tech ጋር ህልሞን እውን ያድርጉ። አሁኑኑ በዌብሳይታችን ገብተው በመመዝገብ የስራ እድሎን ያስፉ። ቀድመው ለሚመዘገቡ ውስን ተማሪዎች የነፃ እድል እና ልዩ ቅናሽ አዘጋጅተናል። ምዝገባዉ የሚቆየው ለጥቂት ቀናት ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ:: ለሴቶች ሴት መምህራን አዘጋጅተናል!!       የምንሰጣቸው ስልጠናዎች Fullstack website development        Frontend development        Backend  development        Database development Language         English         Arebic Mobile maintenance        Hardware part        Software part ለበለጠ መረጃ ቤተል መስጂድ ወረድ ብሎ ዳሽን ባንክ አጠገብ ወደሚገኘው ቢሮችን ብቅ ይበሉ።   ስልክ 251907667777             251901177716 Telegram                     
Ko'proq ko'rsatish ...
1 806
4
የፍጥረተ አለሙን አይነታ የውዱን መልእክተኛ ሠ.አ.ወ ሕይወት ካለንበት ተጨባጭ ጋር እያስተሣሠርን እንዲሁም ታሪካቸው እያወሣን ስለ ረሱል ተጠራርተን ብንማማር ሲራቸውን ብናውቅ ብለን እለተ እሁድ በሙጀመኣ _ተቅዋ "የኔ ነብይ "በሚል ርእስ ውብና ማራኪ ፕሮግራሞችን አሰናድተን እየጠበቅንሽ ነው ! መቅረት ሳይሆን ማርፈድ አይታሰብም ርእስ : በረሱል ጥላ ስር (በኡስታዛ ሀስና ሙስጠፋ) ማንን ልከተል (ኢክራም በድሩ ) ቀን መስከረም 19/1/2017 ሰኣት : ከጠዋቱ 3:00 ቦታ : ሙጀመኣ_ተቅዋ " ቀጠሮን ማክበር የሙስሊም ስነ_ምግባር ነው "
5 864
6
ዙርያውን የመስጅዱ ይዞታ ለማድረግ ጊዚው አሁን ነው!!! መጅልሱ ይህን እድል ካልተጠቅመበት አንድም ይቆጫል ሁለትም በታሪክ ዘላለም ሲወቀስ ይኖራል!!!
5 858
3
"وما فَقَدَ الماضُونَ مِثلَ مُحَمّد ولا مثلهُ حتى القيامة يفقدُ." ﷺ
5 336
4
የአለማችን ውዱ ሩዝ ከጣዕሙ ባሻገር በፋይበር እና ቫይታሚን ቢ1 ከመደበኛው ነጭ ሩዝ በብዙ እጥፍ ይልቃል ተብሏል ሩዝ በአለማችን በርካቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ይሸምቱታል የሚባልለት ምግብ ነው። የተለየ ጣዕም እና መልክ ያለው ሩዝ ግን ከስጋ ዋጋ በእጅጉ ይልቃል። በጃፓኑ “ቶዮ ራይስ ኮርፖሬሽን” የሚመረተው ሩዝ በአለም የድንቃድንቅ መዝገብ ሰፍሯል። “ኪንሜማይ ፕሪሚየም” የሚል ስያሜ የተሰጠው ሩዝ አምስት በአለማቀፍ ደረጃ በጥራታቸው ሽልማት ያገኙ የሩዝ ዝርያዎችን በማጣመር የተፈጠረ ነው። የሩዝ አምራቹ ኩባንያ ከ17 አመት በፊት ያስተዋወቀው ዘመናዊ ቴክኖሎጂ አምስቱን የሩዝ ዝርያዎች ልዩ ጣዕምና መልክ እንዲኖራቸው አድርጎ ለማዘጋጀት ስድስት ወራት ይፈጅበታል ተብሏል። 10 ሩዝ በብዛት ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡ ሀገራት ከ180 ቀናት ሂደት በኋላ የሚገኘው “ኪንሜማይ ፕሪሚየም” በኪሎ 120 ዶላር (በዛሬው የንግድ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ተመን ከ13 ሺህ 400 ብር በላይ) እንደሚያወጣም ነው ኦዲቲ ሴንትራል ያስነበበው። የአለማችን ውዱ ሩዝ ሲፈለፈል የአልማዝ ፈርጥ ያላቸው የሚመስሉ ፍሬዎችን እንዲያወጣ መደረጉም ለሚወጣበት ወጪ የሚመጥን አስመስሎታል። “ኪንሜማይ ፕሪሚየም” ከልዩ ጣዕሙ ባሻገር በፋይበር እና ቫይታሚን ቢ1 ከመደበኛው ሩዝ በብዙ እጥፍ ይልቃል ተብሏል። ከተለመደው ነጩ ሩዝ 6 እጥፍ በሽታ የመከላከል አቅምን የሚያጎለብቱና ጤናን የሚጠብቁ ንጥረነገሮችን መያዙ የተገለጸ ሲሆን፥ የታጠበ እና ሲቀቀል ደስ የሚል ሽታ ያለው ስለመሆኑ ተነግሮለታል። የአለማችን ውዱን ሩዝ የሚያመርተው የጃፓን ኩባንያ በጥራታቸው አለማቀፍ ሽልማት ያገኙ የሩዝ ዝርያዎችን ከአርሶ አደሮች ሲገዛ ከተለመደው ነጭ ሩዝ በሰባት እጥፍ ዋጋ ጨምሮ ይገዛል ነው የተባለው። ይህም ዋጋውን አንሮት የአለም ድንቃድንቅ መዝገብ በ2016 የአለማችን ውዱ ሩዝ ብሎ እንዲመዘግበው አድርጎታል። ሩዝ በብዛት በመጠቀም ከአለም ሀገራት ቻይና እና ህንድ ቀዳሚውን ደረጃ ሲይዙ ስምንተኛ ላይ ተቀምጣለች።
Ko'proq ko'rsatish ...
10 ሩዝ በብዛት ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡ ሀገራት
ሩዝ በስፋት በማምረትና በሀገር ቤት በመጠቀም ግን ቻይና ከህንድ ትቀድማለች
5 800
8
5 136
3
ጀግና እናስተዋውቃችሁ! በመኖሪያ ግቢያቸው አንድ ብለው የጀመሩት ዛሬ በሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎች ተቀብሎ እያስተማረ ስለሚገኘው አዳማ ቅዱስ ቁርአን ት/ቤት መስራች ሀጂ ጀማል አብደላ ጥቂት ነገር እናካፍላችሁ! - ሀሩን ሚዲያ፦ መስከረም 16/2017 ዛሬ በከፍተኛ ደረጃ ማለትም ከ 1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ ህጋዊ ሆኖ መንቀሳቀስ ከጀመረ 50ኛ ዓመቱን ያስቆጠረው በአዳማ ከተማ በከፍተኛ 1 ቀበሌ 17 ውስጥ የሚገኘው የቅዱስ ቁርዓን የመደበኛና የአረብኛ ት/ቤት ነው። የአመሠራረት መነሻው በ1962 ሀጅ ጀማል የሀጅ ፀሎት ለማድረስ ጉዞ በጀመሩበት ወቅት ከአገራችን ከአዲስአበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ የሀጅ ፀሎት ሥነ ሥርዓት በሚካሄድባቸው በሣዑዲ ሥፍራዎች የሀገሬ ሰዎች ሥነ ሥርአቱን በቋንቋው ችግር ምክንያት በአንድ ቡድን ከ50 ሰዎች በላይ በአንድ ሰው እየተመሩ በአስተርጓሚ የሀጅ ፀሎት ሥነ ሥርዓት ሲፈፀሙ ስመለከት ይቆጨኝና ያንገበግበኝ ነበር ይላሉ። ታዲያ ይህ ችግር የሚቀረፈውና ለተከታዩ ትውልድ ምን መደረግ ይኖርበታል በማለት ዘወትር በሃሣቤ አወጣና አወርድ ጀመር፡፡ የሐጅ ፀሎት አድርጌ ወደ አገሬ ከተመለስኩ በኋላ ት/ቤት በመክፈት የአረብኛን ትምህርት ከመደበኛው ትምህርት ጋር ጎን ለጎን ቢካሄድ በማለት ለዚህም መሠረት መጣል ይኖርብኛል የሚል ሀሳብ መጣልኝ። መቼም ሰው ያስባል ሀያሉ ጌታ አላህ ይፈፀማል እና ይህ ት/ቤት ሲመሠረት ኢትዮጵያዊ ወገኖቼ ሁሉ እንደሚጠቀሙበት መረዳት መጀመራቸው ሀጂ ጀማል ይገልፃሉ። እኔም በወቅቱ የአረብኛውን ቋንቋ ህግ በትንሹ እንደ አቅሜ አውቅ ስለነበር ዝግጅቱ እንዴት መቀየስ እንዳለበት ግልፅ ሆኖልኝ ነበር፡፡ በዚሁ መሠረት ለመጀመሪያ ጊዜ ለመኪናዬ ማቆሚያ በግቢዬ ውስጥ በነበረች አነስተኛ ቤት ውስጥ ሥራው እንዲጀመር በ1964 ዓ.ል ወሰንኩኝ። ከዚያም በመቀጠል በአካባቢው የሚገኙ ሕፃናት ልጆችን በማሰባሰብ አንድ የመደበኛ እና አንድ የአረብኛ መምህር በማቀናጀት ሥራው ተጀመረ፡፡ ለመምህራን ደሞዝ በተማሪ ሁለት ብር በማስከፈል ሥራው ቀጠለ። በመቀጠልም የአካባቢው የሕብረተሰብ ክፍሎች ልጆቻቸውን በመላክ ትብብር በማሣየቱ የተማሪዎቹም ብዛት እየጨመረ ወላጆችም የትምህርቱ አሰጣጥ ጠሜታ ያለው መሆኑን በስፋትና በጥልቀት እየተረዱ በመምጣታቸው ከወላጆች በኩልም የሞራል ድጋፍ ይጎርፍ ጀመር። ቀጥሎም የተማሪዎቹን ብዛት በዚያች በትንሽ ቤት ውስጥ ማስተናገድ አልተቻለምና እኔም በወቅቱ ሌላ የመኖሪያ ቤት ሠርቼ ስዛወር የቀድሞውን መኖሪያ ቤት ሙሉ በሙሉ ለትምህርት ቤቱ ማስፋፊያ እንዲውል አድረኩኝ፡፡ ከዚያም ሥራው በተቀላጠፈ እና ሰፋ ባለ መልኩ ይንቃሳቀስ ጀመር። በዚህ ሁኔታ ትምህርት ቤቱ ህጋዊ ሰውነት ሳያገኝ ሥራው እያማረና ውጤታማ እየሆነ በመሞጣቱ ግንቦት 1/1972 ዓ.ል ላይ የቀድሞ ከፍተኛ 1 ቀበሌ 17 ተወካዮች በተገኙበት የወላጅ ኮሚቴ በህጋዊነት ተቋቋመ። ይህም ኮሚቴ ከተቋቋመ በኋላ ነሐሴ 18/1973 ለሸዋ ት/ቤቶች ጽ/ቤት የቅዱስ ቁርዓን ት/ቤት ህጋዊ ሰውነት እንዲያገኝ በማመልከቻ ጠየቅን፡፡በዚያን ወቅት በት/ቤቱ በዛ ያለ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎችና 3 የመደበኛና 3 የአረብኛ መምህራንም ነበሩት፡፡ በመቀጠልም በወቅቱ የነበረው የሸዋ ት/ቤቶች ጽ/ቤት በወቅቱ ለነበረው ለየረርና ከረዩ አውራጃ ት/ቤቶች ጽ/ቤት ስለ ቅዱስ ቁርዓን ት/ቤት በጥናት የተደገፈ መረጃ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡ በወቅቱም አስፈላጊው የመረጃ ጥናት ተደርጎ በህዳር ወር 1973 የቅዱስ ቁርዓን ት/ቤት ህጋዊ ሰውነት አግኝቶ ሥራውን ማስፋፋት ቀጠለ፡፡ ለተማሪዎች የሚያገለግሉ የመማሪያ ክፍሎች እንዲሁም ተጨማሪ መምህራንን በመቅጠር መስፋፋቱን ቀጥሎ በመጀመሪያ ከአንድ የመኪና ማቆሚያ ቤት ተነስቶ በአሁኑ ወቅት 17 የመማሪያ ክፍሎችና 9 የአስተዳደር ሥራዎች የሚከናወኑባቸው በጠቅላላው 26 ክፍሎችን ይዞ ይገኛል:: በቀጣይም በተደረገ የመማሪያ ክፍሎችን የማስፋፋት ስራ ባለ አንድ ወለል 8 የመማሪያ ክፍሎች እና 4 ክፍሎችን ጨምሮ 12 የመማሪያ ተጨማሪ ክፍሎች ተገንብተዋል፡፡ በዚያን ወቅት ለዚህ መሰሉ በጎ እንቅስቃሴ ሁሉም የተማሪ ወላጅ ቤተሰብ ከፍተኛ እንቅስቃሴና የሞራል ድጋፍ አስፈላጊ በሆነበት ቦታ ሁሉ በመስጠት አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል። አዳማ ቅዱስ ቁርአን የህዝብ ትምህርት ቤት አሁን ላይ ከ800 በላይ መደበኛ እንዲሁም ከ300 የሚበልጡ የዲን ተማሪዎች እያስተማረ የሚገኝ ሲሆን በሺህ የሚቆጠሩ ምሁራን አስተምህሮ ለቁምነገር ያበቃ አንጋፋ ተቋም መሆኑ ተነገሯል።እንዲሁም ትምህርት ቤቱ በሚሰጠው የዲን ትምህርት (አረብኛ ፣ሀዲስ፣ፊቂህ... እና ሌሎች)በማስተማር የአካባቢው ሙስሊም ማህበረሰብ የዲን እውቀት እንዲኖረው አድርጓል። ት/ቤቱ ሀምሌ 07/2016 ዓ.ል የ50ኛ አመት የወርቅዮቤልዩ በዓሉን በደማቅ ሁኔታ ያከበረ ሲሆን ት/ቤቱ አሁን ላይ ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ እስከ 12ኛ ክፍል ለማሳደግ እቅድ መኖር ተነግሯል።በመሆኑም መላው ማህበረሰብ ት/ቤቱን በማገዝ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል። © ሀሩን ሚዲያ
Ko'proq ko'rsatish ...
5 729
5
4 765
1
ነቢ (ሰአወ) የተኙበት ደረቅ ሰሌን ሰንበር ወገባቸው አስምሮት ያዩ ሰሀባዎች "ፍራሽ ቢጤ ብንፈልግልህ" አሏቸው። እሳቸውም "ደሞ እኔና ዱንያን ምን አላምዶን፣ እኔና ዱንያኮ ምሳሌያችን "ልክ ጸሀይ ጠንቶበት ሊጠለል ዛፍ ስር አረፍ እንዳለና (ሲበርድለት) ጥሎት እንደሄደ ሰው ነው" አሏቸው ። የዱንያን ቀድር ልኳን መርሳት አደጋ ነው። ይህንን አይነት የህይወት ዘርፍ ትምህርት መስማት እየራቀን ደዋም እየተሰማን ነውና መቸም ....
6 278
14
ሀምስተር ነው ጋንግስተር በሚባለው ሰው ሁሉ ታብ ታብ ሲል እሰማለሁ ። እና እጁ እስኪመለጥ ድረስ ታብ ታብ ሲል የከረመው ሁሉ ታብ ታብ ሁኖ በባዶ አጨብጭቦ ቀረ እየተባለ ነው ። አቤት ይሄ ሁሉ ታብ ታብ የተደረገው በኢስቲግፋር ቢሆን እስካሁን ድረስ እርዚቁ ተንቧቡቶ ነበር :D
5 444
51
ጥራታቸውን የጠበቁ፤ የውጪ አረቢያን መጅሊስ የሚያስንቁ ማራኪ የሀገር ውስጥ መጅሊሶችን በተመጣጣኝ ዋጋ፤ ከሀምዛ ዑመር  አረቢያን መጅሊስ እና መጋረጃ ያግኙ 🏬አድራሻ:   መርካቶ ዱባይ ተራ ፓርኪንግ መውጫ አጠገብ የሱቅ ቁጥር B33/1 ስልክ፦NaN          NaN ለበለጠ መረጃና የተለያዩ እቃወችን ለማገኘት የቴሌግራም አድራሻችንን ይቀላቀሉ  
4 338
5
5 635
3
🍔🍕🧀 እንኳን ደህና መጡ🥘☕️🍴 🚶‍♂️‍➡️🚶‍➡️🏞ወደ ካፌያችን ጎራ ብለው ጣፋጭ ምግቦችን ምቹ በሆነ ሁኔታ  ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተቋድሰው እርካታዎን ያጣጥሙ።🥬🥦🌲🌿 🍮ሲና ካፌና ሬስቶራንት @አለም ባንክ፣ ሙስዐብ መስጅድ መግቢያ ኦሮሚያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ googl አድሬስም ስላዘጋጀን በቀላሉ እኛን ማገኘት ይቻላል ። Tik Tok ቴሌግራም Facebook

file

5 095
3
ሞት ተፈርዶባቸው ከ50 ዓመታት በላይ በእስር ቤት የቆዩት የ88 ዓመቱ ጃፓናዊ አዛውንት ለተፈረደባቸው ወንጀል የቀረበባቸው ማስረጃ የተቀነባበረ ነው በሚል በነጻ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ወሰነ። ቢቢሲ
5 879
5
5 389
1
ታላቅ የምስራች  የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት እና የበርካታ ድርጅቶችን website እና system በማበልፀግ የሚታወቀው RiseUp Tech  የሶስተኛ ዙር ምዝገባ መጀመሩን ሲያበስሮ በታላቅ ደስታ ነው። RISEUP TECH በጥቂት ወራት በገሃዱ ዓለም ፕሮጀክቶች በመታገዝ ከመሰረታዊ የኮምፒተር እውቀት ጀምሮ ፕሮፌሽናል ዌብሳይት እና አፕ አበልፃጊ ሊያደርጎት እንዲሁም አለም አቀፍዊ  ተቀባይነትን ያገኙ ዘንድ ልዩ የእንግሊዘኛና የዓረበኛ ቋንቋ ሥልጠና አዘጋጅቷል። በተጨማሪም ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤት ዝቅ አለብኝ ብለው ሳይጨናነቁ በብቁ መምህራኖቻችን ጥራት ያለው ሥልጠና በመዉሰድ ከRiseup Tech ጋር ህልሞን እውን ያድርጉ። አሁኑኑ በዌብሳይታችን ገብተው በመመዝገብ የስራ እድሎን ያስፉ። ቀድመው ለሚመዘገቡ ውስን ተማሪዎች የነፃ እድል እና ልዩ ቅናሽ አዘጋጅተናል። ምዝገባዉ የሚቆየው ለጥቂት ቀናት ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ:: ለሴቶች ሴት መምህራን አዘጋጅተናል!!       የምንሰጣቸው ስልጠናዎች Fullstack website development        Frontend development        Backend  development        Database development Language         English         Arebic Mobile maintenance        Hardware part        Software part ለበለጠ መረጃ ቤተል መስጂድ ወረድ ብሎ ዳሽን ባንክ አጠገብ ወደሚገኘው ቢሮችን ብቅ ይበሉ።   ስልክ 251907667777             251901177716 Telegram                     
Ko'proq ko'rsatish ...
4 898
8
ዝሁር ከተሰገደ በኃላ ጀናዛ እንዳለ ተነግሮ ሰላተል ጀናዛ ለመስገድ ተቆመ። ትላንት ሲስቅ ሲጫወት የነበረ አካል ዛሬ ግን "ጀናዛ" ተብሎ ፊት ለፊት አካሉ ተጋድሟል፣ የከፈኑት ሰዎች እንዳደረጉት እንጅ ሟች ምንም የመሆን ምርጫ የለውም። አሁን እራሱን የሚያስተካክልበት ጊዜ ላይ አይደለም። ምናልባት ትላንት አልያም ከአመት በፊት ዛሬ በዚህ ቀን አስክሬን ሁኖ ሰዎች ፊት እንደሚቆም ግን ፈጽሞ አያውቅም። በርካታና ህልምና ትልሞቹን በህሊናው መዝግቦ እየታተረ ሲቆይ በድንገት ሞት ከእነዚያ ህልሞቹ እንደሚያናጥበው ፈጽሞ አይገምትም። በእሱ ዛሬ ውስጥ የኛን ነገ እናያለን፤ ብዙ ብናቅድ፣ ብዙ ብንለፋ በስተመጨረሻ ሁሉኑም ጥለነው ማለፋችን ግን የማይቀር ነው። ሞት መራር እውነት ነው፣ የኛ አለመዘጋጀት የማያስጨንቀው ነገን ስናቅድ ዛሬ "" የሚያሰኘን የማይቀር እውነት..! 😢😞 አሏህ መጨረሻችንን ያሳምረው..!🤲🤲🤲 Via ያህያ ኢብኑ ኑህ
Ko'proq ko'rsatish ...
ተውሂድና ሱና
ቁርአንና ሐዲስን በሰለፎች ግንዛቤ ለመረዳት የሚያስችሉ ተውሂድ፣ሲራ አጠር አጠር ያሉ የነብዩ ﷺ ሓዲሶችን እና የሰለፎችን ንግግሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው።ቻናሉን ይቀላቀሉ ኪታቦችን ይቅሩ
5 581
16
ከሶስት የአረብ ሀገራት የተውጣጡ 40ሺ ታጣቂዎች ሄዝቦላን ለመቀላቀል ጎላን ሀይት አቅራቢያ መድረሳቸው ተዘገበ ከሶስት የአረብ ሀራት የተውጣጡ ቁጥራቸው 40ሺ የሚሆኑ ሚሊሻዎች እና ቅጥረኛ ተዋጊዎች ከሄዝቦላ ጎን ተሰልፈው ለመዋጋት በእስራኤል በተያዘው ጎላን ሀይት አቅራቢያ መድረሳቸውን ሀርቴዝ የተባለውን የእስራኤል እለታዊ ጋዜጣ የትናንት እትም ጠቅሰው በርካታ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የእስራኤል ጦር ከባለፈው ሰኞ ጠዋት ጀምሮ በሊባኖስ ላይ ተከታታይ የአየር ጥቃት እያደረሰ ይገኛል። በጥቃቱ 95 ሴቶችን እና 50 ህጻናትን ጨምሮ 560 ሰዎች መገደላቸውን እና ሌሎች 1835 የሚሆኑ ደግሞ መቁሰላቸውን የሊባኖስ ጤና ሚኒስትር ፊራስ አቢያድ ተናግረዋል። አንደዘገባው ከሆነ ብዙ ሺ ቁጥር እንዳላቸው የተጠቀሰው እነዚህ ታጣቂዎች ከሶሪያ፣ የመን እና ኢራቅ የመጡ ናቸው።
6 333
5
በእስራኤል ባንዲራ ላይ የሚገኙት ሁለቱ ሰማያዊ መስመሮች በኢራቅ የሚገኘው የኤፍራጥስ ወንዝና የዐባይ ወንዝ ምልክቶች ሲሆኑ አይሁዶች ፈጣሪ በሁለቱ ወንዞች መካከል ያለውን ምድር ርስት አድርጎ እንደሰጣቸው ለመግለፅ እንደተጠቀሙበት ይነገራል። በእርግጥ እነሱ መስመሮቹ አይሁዶች በፀሎት ወቅት የሚለብሱት ሽልም ሸማ ለማመልከት ነው ይላሉ። ወደፊት «ታላቋ እስራኤል» የምትባለውን አገር ለመመስረት ካላቸው አላማ አንፃር ሲታይ ግን መስመሮቹ ወንዞቹን ይወክላሉ የሚለው ሊሆን ይችላል። ይህ ታላቋ እስራኤል የሚሉት ግዛት በኢስላም «ሻም» የሚባለው ምድር ሲሆን ከኢራቅ ኤፍራጥስ ወንዝ መለስ ሶርያን፣ ጆርዳንን፣ ሊባኖስን፣ ፍልስጤምንና ሲና በረሃን እስከ ዐባይ ወንዝ መዳረሻ የሚያካልል ነው። እነዚህን አገራት ለመያዝ ደግሞ በቅድሚያ በጦርነት ማውደም የሚገባ ሲሆን ይህንንም ጀምረውታል። ለጊዜው የፍልስጤምና ሊባኖስ ጎረቤቶች እሳቱ የማይደርስ መስሏቸው ዝም ቢሉም የእነሱንም ቤት ማቃጠሉ ግን የሚቀር አይደለም።
Ko'proq ko'rsatish ...
6 367
13
“ሰዎችን የመንገዱ አጋማሽ ላይ አትተው። መንገዱን በናንተ ምክንያት ብቻ ጀምረውት ሊሆን ይችላል።” የሚል የዐረብኛ ጥቅስ አነበብኩና እውነት ነው አልኩኝ። በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ስንት እህቶች ከአንዳንድ ወንዶች በተሰጣቸው አጉል የይሆናል ተስፋ መሀል መንገድ ላይ ቀርተዋል? የማያውቁትን መንገድ ጀምረው። በስራ ምክንያት እኛ እናውቀዋለን ብለው መሀል መንገድ ላይ በሚጠፉ ሰዎች ስንት ነጋዴዎች ከሰሩ? ስንት ወጣቶች በጓደኞቻቸው ውትወታ ጀምረውት… መመለስም ማለፍም የተሳናቸው የሱስ አዘቅት ውስጥ ገብተዋል። አይደል? እስኪ ሀሳብ ስጡበት።
6 052
11
5 203
0
ጥራታቸውን የጠበቁ፤ የውጪ አረቢያን መጅሊስ የሚያስንቁ ማራኪ የሀገር ውስጥ መጅሊሶችን በተመጣጣኝ ዋጋ፤ ከሀምዛ ዑመር  አረቢያን መጅሊስ እና መጋረጃ ያግኙ 🏬አድራሻ:   መርካቶ ዱባይ ተራ ፓርኪንግ መውጫ አጠገብ የሱቅ ቁጥር B33/1 ስልክ፦NaN          NaN ለበለጠ መረጃና የተለያዩ እቃወችን ለማገኘት የቴሌግራም አድራሻችንን ይቀላቀሉ  
1 100
1
❝በሁሉም ሁኔታ ምስጋና ሁሉ ለአላህ ይገባው❞ - በዲኤንኤ ውጤት የነፍስ ግድያ አለመፈጸሙ ቢረጋገጥም በግፍ የሞት ፍርድ የተፈፀመበት ማርሴለስ ከሊፋ ዊሊያምስ የ55 ዓመቱ ማርሴለስ ዊሊያምስ እ.ኤ.አ በ1998 በሴንት ሉዊስ ቤቷ በስለት ተወግታ ተገድላ በተገኘችው ጋዜጠኛ ፌሊሺያ ጌይል ላይ ግድያ ፈፅመሀል በሚል በ2001 ማለትም ከዛሬ 24 ዓመት በፊት የሞት ፍርድ ቢፈረድበትም በተለያዩ ጊዜያት በተደረገ የዲኤንኤ ማስረጃ የዊሊያምስ አሻራ በግድያ መሳሪያው ላይ እንዳልተገኘ ተረጋግጦ ነበር። በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔን ባለመቀየር በትላንትናው ዕለት ሊገደል ችሏል። በአሜሪካ በሚዙሪ በነፍስ ግድያ የተከሰሰው ኢማም ማርሴሉስ 'ካሊፋ' ዊልያምስ ትላንት መስከረም 14 ዓ.ል ገዳይ በሆነ መርፌ ተገድሏል። የዊሊያምስ ጠበቆች እና የሴንት ሉዊስ ካውንቲ አቃቤ ህግ የጋራ አጭር መግለጫ አቅርበው  የሚዙሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት “ለበለጠ አጠቃላይ ችሎት” ግድያውን እንዲያቆም ቢጠይቁም ፍርድ ቤቱ ውሳኔን አልቀይርም በማለት በትላንትናው ዕለት እንዲገደል ትዕዛዝ አስተላልፍዋል። ግድያው የተፈፀመው በቦኔ ቴሬ ማረሚያ ቤት ሲሆን በትላንትናው ዕለት በገዳይ መርፌ ተወግቶ ህይወቱ ማለፉን አስታውቋል። አዲስ የዲኤንኤ ማስረጃዎች የዊልያምስ ዲ ኤን ኤ በግድያ መሳሪያው ላይ እንዳልተገኘ አቃቢ ህግ ተናግሯል። የዊሊያምስ ጠበቆችም ሂደቱ በስህተት የተሞላ እና የግድያው ጊዜ ተራዝሞ እንዲጣራ ቢጠይቁም ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን አልቀየርም በማለት የዘር መድሎ እንደተፈፀመበት እና በሚያሳዝን ሁኔታ እንደተገደለ ገልፀዋል። የሞት ቅጣቱን ለማስቆም  በርካታ ፒቲሽኖች ቢሰበሰቡም ፍርድ ቤቱ ስላልተቀበለ ግድያውን ማስቆም አልተቻለም። የ55 ዓመቱ ጥቁር አሜሪካዊ ሙስሊም የዊሊያምስ የመጨረሻ ቃል "በሁሉም ሁኔታ ምስጋና ሁሉ ለአላህ ይገባው" የሚል ነበር።
Ko'proq ko'rsatish ...
5 586
11
5 268
5
የተባባሰው የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትና የኤርዶጋን ጥሪ፤ ሌሎች መረጃዎች|HarunMedia
1
0
ማየት የተሳናቸው ጀግና እህቶቻችን በሶላታችን፣በሂጃባችን አንደራደርም በሚል ታላቅ ገድልን ይፈጽማሉ ። እኛ ደግሞ አላህ የሰጠንን የሶሻል ሚዲያ ፕላት ፎርም ተጠቅመን ለነሱ ድምጽ ከመሆን መብታቸው እንዲከበር ከመጣር ይልቅ እንቀልድበታለን ። ኢስላማዊ እሴቶቻችንን የሚሸርሽር ተግባር እንፈጽምበታለን ። አሏህ (ሱ.ወ) በተሰጠን ኒእማ ሁሉ እንደሚጠይቀን በግልጽ በቁርዓን ነግሮናል ። የተስጠን ጊዜ፣ገንዘብ፣ወጣትነት ሁሉም ሂሳብ አለበት ። የሂሳብ ቀን ከመምጣቱ በፊት ሂሳብ እንስራ ። ከሁለት ሀገር ኪሳራ አላህ ይጠብቀን !
5 384
2
የግራፊክስ ዲዛይን መፍትሄ ይፈልጋሉ? ወዲህ ወዲያ ሳይሉ ይቀላቀሉ!! ለስራዎቻቸው ምስክሮች ነን ✅ አይን የሚማርኩ በራሪ ወረቀቶች፣ ብሮሸሮች፣ ስቲከሮች እና ባነሮች ✅ ፕሮፌሽናል ቢዝነስ ካርዶች ✅ አነቃቂ የምስክር ወረቀቶች ✅ አስደናቂ ሎጎዎች ✅ የሚያማምሩ የግብዣ ካርዶች ✅ የዩቲዩብ ተምብኔሎችን ✅ እይታን የሚስብ እና ምላሽ ሰጪ ድረ-ገጾች ✅ ሌሎችም አሪፍ የግራፊክስ ዲዛይን ውጤቶች  ከፈለጉ ን  ምርጫዎ ያድርጉ! 📞 በ NaN ይደውሉ አልያም 📧 በ ያዋዩዋቸው 🌐 ለበለጠ መረጃ ይጎብኙ፡-
4 190
6
4 547
0
የቻለ እንዳይቀር
4 946
0
የቅርብ ቤተሰብ ዘመድ መካሪ የላቸውም ወይ ?! ለምን አትመክሯቸውም !? በተለይ ወንድሜ ሰኢድ ስራህ እና መልክህ የፂምህ ሱና ከምትሰራው ስራ ጋር አብሮ አይሄድም :: ትዳር በኢስላም እጅግ የተከበረ ምርጥ ትውልድ የሚፈራበት ተቋም ነው :: ሴቶች ደግሞ የነብያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም አደራ ናቸው :: እንደው ፍራንክ እንኳን ካልሰራሁ ካለ አንድ ሰው አንድ ጊዜ ሰርቶ ዞር ይላል :: በዚህ ልክ መውረድ ትንሽ ያሳፍራል :: ክቡር የሆኑ ኢስላማዊ እሴቶችን በዚህ መልኩ ማራከስ እጅግ አደገኛ ተግባር ነው :: ለሌሎች መጥፎ አርአያ መሆን ደግሞ ክብደቱ በዚያው ልክ ነው :: ሃያእ የሚባል ነገር ቀረ ወይ ?! በቅርብ የሚተዋወቁ ሰዎች ይህን ነገር ተው አላህ አይወደውም ማለት አይብ ሁኗል እንዴ ?! ተው ወንድም እህቶቼ አላህን እንፍራ ! እንኳን እንዲህ በአደባባይ መረን ለቀን አላህ የሰተረልን ወንጀል መቼ አነሰን !? በቅርበት የምታውቋቸው እህት ወንድሞች ምከሯቸው ! ለሁላችንም ሂዳያ ይስጠን !
Ko'proq ko'rsatish ...
203
1
https://vm.tiktok.com/ZMhjBAUSb/
TikTok · FaysulAhmed
Check out FaysulAhmed’s video.
5 190
0
🍔🍕🧀 እንኳን ደህና መጡ🥘☕️🍴 🚶‍♂️‍➡️🚶‍➡️🏞ወደ ካፌያችን ጎራ ብለው ጣፋጭ ምግቦችን ምቹ በሆነ ሁኔታ  ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተቋድሰው እርካታዎን ያጣጥሙ።🥬🥦🌲🌿 🍮ሲና ካፌና ሬስቶራንት @አለም ባንክ፣ ሙስዐብ መስጅድ መግቢያ ኦሮሚያ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ googl አድሬስም ስላዘጋጀን በቀላሉ እኛን ማገኘት ይቻላል ። Tik Tok ቴሌግራም Facebook

file

4 561
2
ለፍልስጤም ዕውቅና ያልሰጡ ሀገሮች ውሳኔ እንዲያሳልፉ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ጥሪ አቀረቡ የቱርኪዬ ፕሬዝዳንት ሬሲብ ጠይብ ኤርዶጋን፤ ለፍልስጤም ዕውቅና ያልሰጡ የዓለም ሀገሮች ውሳኔ በማሳለፍ የሀገርነት ዕውቅና በመስጠት እንዲቀላቀሏቸው ጥሪ አቀረቡ፡፡ ኤርዶጋን ከሒትለር ጋር ላነጻጸሩት የእስራኤሉ ቤንያሚን ኔታንያሁ፤ የሰው ልጆች በቃህ ሊሉት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ ጥሪውን ያቀረቡት በአሜሪካ ኒውዮርክ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው 79ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡ ኤርዶጋን “እስካሁን የሀገርነት መሆን እውቅና ያልሰጡ ሀገራት በዚህ ወሳኝ ጊዜ ከፍልስጤም ጎን እንዲቆሙ ግብዣ አቀርባለሁ” ብለዋል፡፡ ለፍልስጤም የሀገርነት ዕውቅና የመስጠት ውሳኔ ከዚህ በላይ መዘግየት እንደሌለበትም አጽንኦት የሰጡበት ጉዳይ ነው፡፡ በሌላ በኩል በዚሁ ንግግር ላይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጋዛውን ጭፍጨፋ ለማስቆም አለመቻሉን የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ፤ የድርጅቱ ውሳኔ የማሳለፍ አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዳከመ መሄዱንም በማንሳት ትችት ሰንዝረዋል፡፡ አያይዘውም እስራኤል በጋዛ የምትፈጽመውን ጭፍጨፋ ያወገዙ ሲሆን፣ በእስራኤል ጥቃት ጋዛ ከተማ የሕጻናት እና እናቶች ትልቁ መቀበሪያ ሥፍራ መሆኑንም በመጥቀስ አሁንም ትኩረት እንዲደረግ ወትውተዋል፡፡ በጋዛ በሚፈጸመው ጥቃት እየሞቱ የሚገኙት ሕጻናት ብቻ ሳይሆኑ፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአሠራር ሥርዐት ጭምር ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡ በኤርዶጋን ንግግር ላይ ሌላው የተጠቀሰው ጉዳይ፤ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ቀን እሑድ በእስራኤል ወታደሮች ተጥሶ እንዲዘጋ የተደረገው የአልጀዚራ ቴሌቪዥን የራማላህ ቢሮ ነው፡፡ ለዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ጥያቄ አለኝ ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ “በቀጥታ ሥርጭት የተገደሉት እንዲሁም በእስራኤል ወረራ ቢሮ ተጥሶ የተገባባቸው ጋዜጠኞች ባልደረቦቻችሁ አይደሉም ወይ?” ሲሉ ሞጋች ሐሳብ ሠንዝረዋል፡፡
Ko'proq ko'rsatish ...
5 045
2
4 714
0
በሊባኖስ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት የምዝገባ ጥሪ አቀረበ! ጽሕፈት ቤቱ በደቡብ እና ምሥራቅ ሊባኖስ ያለው የፀጥታ ችግር እየተባባሰ መምጣቱን ተከትሎ በአካባቢዎች ያሉ ዜጎችን ለይቶ ማወቅ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ጠቁሟል፡፡ በመሆኑም በአካባቢው የሚኖሩ ወገኖች ከታች በተቀመጠው መሠረት ስማቸውን ፓስፖርት ላይ አንደተፃፈው፣ የፓስፖርት ቁጥር እና ስልክ ቁጥራቸውን እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡ በዚሁ መሠረት በደቡብ ሊባኖስ (ታየር፣ ሱር፣ ቢንት ጅቤል፣ ማርጃዩን፣ ነበትዬ፣ ሳይዳ እና አካባቢው) የሚገኙ ወገኖች በስልክ ቁጥር 03-7354 51 ወይም 03-87-10-89 በምሥራቅ ሊባኖስ (አልቤክ፣ ቤካ ሸለቆ እና አካባቢው) የሚገኙ ደግሞ በስልክ ቁጥር 81 77-62-51 ወይም 81-63-07-98 በመደወል እንዲመዘገቡ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት አሳስቧል፡፡
Ko'proq ko'rsatish ...
5 516
3
ታላቅ የምስራች  የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት እና የበርካታ ድርጅቶችን website እና system በማበልፀግ የሚታወቀው RiseUp Tech  የሶስተኛ ዙር ምዝገባ መጀመሩን ሲያበስሮ በታላቅ ደስታ ነው። RISEUP TECH በጥቂት ወራት በገሃዱ ዓለም ፕሮጀክቶች በመታገዝ ከመሰረታዊ የኮምፒተር እውቀት ጀምሮ ፕሮፌሽናል ዌብሳይት እና አፕ አበልፃጊ ሊያደርጎት እንዲሁም አለም አቀፍዊ  ተቀባይነትን ያገኙ ዘንድ ልዩ የእንግሊዘኛና የዓረበኛ ቋንቋ ሥልጠና አዘጋጅቷል። በተጨማሪም ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤት ዝቅ አለብኝ ብለው ሳይጨናነቁ በብቁ መምህራኖቻችን ጥራት ያለው ሥልጠና በመዉሰድ ከRiseup Tech ጋር ህልሞን እውን ያድርጉ። አሁኑኑ በዌብሳይታችን ገብተው በመመዝገብ የስራ እድሎን ያስፉ። ቀድመው ለሚመዘገቡ ውስን ተማሪዎች የነፃ እድል እና ልዩ ቅናሽ አዘጋጅተናል። ምዝገባዉ የሚቆየው ለጥቂት ቀናት ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ:: ለሴቶች ሴት መምህራን አዘጋጅተናል!!       የምንሰጣቸው ስልጠናዎች Fullstack website development        Frontend development        Backend  development        Database development Language         English         Arebic Mobile maintenance        Hardware part        Software part ለበለጠ መረጃ ቤተል መስጂድ ወረድ ብሎ ዳሽን ባንክ አጠገብ ወደሚገኘው ቢሮችን ብቅ ይበሉ።   ስልክ 251907667777             251901177716 Telegram                     
Ko'proq ko'rsatish ...
4 452
10
4 332
0
4 944
6
6 023
10
በጫጉላ ምሽት ሚስቱን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ተጠርጣሪን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን የሃላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ ለሃሩን ሚዲያ ደቡብ ስቱዲዮ አስታወቋል። - የሟች ሪባቴ ወንድሞችንም ስለተፈጠረው ሁኔታ ስፍራው ድረስ በመሄድ አናግረናል። ሀሩን ሚዲያ ደቡብ ስቱዲዮ፥ መስከረም 14/2017 በጫጉላ ምሽት ሚስቱን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ተጠርጣሪን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄድኩ ነው ሲል የሃላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ ለሃሩን ሚዲያ ደቡብ ስቱዲዮ አስታወቋል። የሟች ሪባቴ ወንድሞችንም ስለተፈጠረው ሁኔታ ስፍራው ድረስ በመሄድ ያናገርናቸው ሲሆን ሟች እና ወንድሟ በተጠርጣሪው አማካኝነች ቁርዓን እንደሚቀሩ ከሟች እህት አመደልሃዲ አንደበት የሰማን ሲሆን ተጠርጣሪው ሟችን ማግባት እንደሚፈልግና ለሟች ወንድም በጓደኛው አማካኝነት ሃሳቡን ይገልጽለታል። የሟች ወንድም አብዱልሃዲም ሟች እህቱን "ተስማምተሻል ወይ" በሚል መጠየቁንና ከሀፍረት መግለጽ ብትፈራም እንደተስማማች በመረዳቴ ወደ ጋብቻ ቅድመ ሁኔታው ማለፋቸውን ይገልጻል። ከዚያም ወደ ጥሎሽና ኒካህ መሄዱን ይገልጻል። ኒካህ ከታሰረ በኃላ ከምሽቱ 10 ሰዓት ገደማ ስልክ ተደወለልኝ የሚለው ወንድሟ "ሪባቴ ታማለች ና" ተብሎ ተነገረኝ ወደ ቤታቸው ስንሄድ ቤቱ በፖሊስ ተከቦ ነበር በማለት ገልጾልናል። ሌላኛው የሟች ወንድም በርገና ደግሞ "አባቴ ኒካህ እሰር ብሎ ከወከለኝ ቀን ጀምሮ ያለው ነገር ብቻ ነው ማውቀው ከዚያም ወንድሜን ወከልኩት ኒካሀው ታሰረ አለኝ ከዛ ለሊት አስር ሰዓት ስልክ ተደወለልኝ ቦታው ስንደርስ ቤቱ በፖሊስ ተከቧል በጭራሽ ያልገመትነው ነገር ሆኖ አገኘን ፖሊሶች እኛ ወደ አስክሬኑ እንዳንጠጋ አድርገው አስክሬኑን ወደ ሆስፒታል ወስደው እሱን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወስዱት" በማለት ያስረዳን ሲሆን ክስ ተመስርቶ ጉዳዩን ህግ ይዞታል የዞኑ መንግስት ኃላፊዎችና የጸጥታ አካላት ከጅምሩ አንስቶ እየተባባሩን ነው ቃሌንም ለመስጠት ወደ ዞን ፖሊስ ስሄድ አብረውኝ አልቅሰው ሃዘኔን ተጋርተው መርማሪዎቹ አጽናንተውኛል ለዚህም ሁሉንም ላመስግናቸው እወዳለሁ ሲል ገልጾልናል። ለሟች እህታች ተገቢው ፍትህ ተሰጥቶን ተጠርጣሪው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኝ እንፈልጋለን በማለት ስሜቱን አጋርቶናል። የሃላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ በበኩሉ ድርጊቱ ከተፈጸመበት ሰዓት አንስቶ ተጠርጣሪውን በህግ ጥላ ስር አውሎ አምስት አባላት ያለው መርማሪ ቡድን በማዋቀር ምርመራ እያካሄደ መሆኑን የሃላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ የታክቲክ ምርመራ ዲቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ኑርዬ ከድር ለሃሩን ሚዲያ ደቡብ ስቱዲዮ ባልደረባ አ/መጂድ አህመድ ገልጸዋል። ኮማንደሩ የዚህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት አረመኔያዊ ወንጀል መፈጸሙን ገልጸው ተጠርጣሪውም የእምነት ክህደት ቃሉን እንደተቀበሉትና በአጭር ጊዜ ውስጥ ምርመራችንን አጠናቀን ውሳኔ እንዲያገኝ እየሰራን ነው ብለዋል። የሃላባ ህዝብ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል እና መረጃ በመስጠት ላደረገው ርብርብም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። - ሀሩን ሚዲያ ደቡብ ደቡብ ስቱዲዮ ያጠናቀረው ሙሉ ዘገባ ወደናንተ የሚያደርስ ይሆናል። © ሀሩን ሚዲያ
Ko'proq ko'rsatish ...
5 922
11
Oxirgi yangilanish: 11.07.23
Privacy Policy Telemetrio