Xizmat sizning tilingizda ham mavjud. Tarjima qilish uchun bosingEnglish
Best analytics service

Add your telegram channel for

  • get advanced analytics
  • get more advertisers
  • find out the gender of subscriber
Kanal joylashuvi va tili

barcha postlar Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ፦ 1) ከቁርኣን፣ 2) ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ] 3) ከታማኝ ዑለማዎችና 4) ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል። √ አዳዲስና ወቅታዊ ኢስላማዊ የሆኑ ጉዳዮችም ይዳሰሳሉ። √ አላማዬ በዲኔ ላይ ያለውን የመረጃ ክፍተት መሙላት ነው። ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ  @Murad_Tadesse  ላይ አስፍሩት። ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ። ጀዛኩሙል`ሏህ ኸይራ! 
Ko‘proq ko‘rsatish
85 063-26
~22 595
~13
28.50%
Telegram umumiy reytingi
Dunyoda
13 944joy
ning 78 777
Davlatda, Efiopiya 
102joy
ning 396
da kategoriya
316joy
ning 2 333
Postlar arxivi
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: ⓵⑤⑨⑥]👌

file

1 808
0
በ50k ... . ... በአንድ ክፍል ቤት ሰሌን ፍራሽ አንሶላ ብርድልብስ ድስትና ሰሀን ገዝተህ ጥሎሽና መህር ከፍለህ ማግባት ትችላለህ ... ይቻላል! . ከ 400-500k አውጥተህም ... ፍሪጅ ማጠቢያ አልጋ ካቢኔት ምንትስ አሟልተህ ሰርቪስ ተከራይተህ ማግባት ትችላለህ . እንደአንተና ተጣማሪህ ወይም በቤተሰዎቻችሁ ቅብጠት መጠን ወጭህን ከፍና ዝቅ ማድረግ ትችላለህ ... . ምንም ሳይኖርህም ኒካህ አስረህ ሰርተህ ጎጆ ልትወጣም ትችላለህ . እንደዱዕህ ... እንደአመራረጥህ ... እንደምኞትህ . ሁኗል ... ይሆናል ... ኑረነዋል ... አይተነዋል! ግን ግን እድሜህ እንዳይሄድ የሰው ሰውም ግዜ እንዳታባክን ከእግርህ የሚሰፋ ጫማ ጋር አትታገል ... እግርህም ይላላጣል ... ጫማውም ይንገላታል ... ብዙም ርቀት አትሄድም! . ©: ቢን ዓሊ
4 751
45
ጭንቅ ብሎሃል/ሻል⁉️ በኡስታዝ ጂብሪል አክመል ©: Hanif Multimedia

file

5 034
27
አሁን ላይ የሰለችኝ ነገር ስለ ስካመሮች መለፍለፍ ነው። ሰው ምንም እየሰማ አይደለም። በዱንያ ጡዟል። ሠርቶ መብላት አይፈልግም። በቃ! የአብዛሃኛው ሰው ሩጫ በአቋራጭ ለመክበር መቋመጥ ነው። ይሄው የሆነ ነገር ታገኟላችሁ ብለው ያጃጅሏቸዋል፤ አካውንታቸውን ጠልፈው ከፊሎች ሁሉንም ግሩፕና ቻነል ያጠፉባቸዋል፣ ከፊሎቹ ሊንኮች ደግሞ ከጠለፉ በኋላ አውቶማቲካሊ ሰዎች መልዕክት መላክ ወደሚችሉበት ግሩፕ፣ ቻነልና ዩዘር ሊንካቸውን ይልካሉ። አሁን እንዲህ አይነት ሰዎችን ምን ባደርግ ይሻለኛል? እንደት አድርጌ ብመክራቸው ያምኑኛል? ተማርና ሠልጥነህ፣ ስኪሉ ኖሮህ ሥራ ሠርተህ ብላ ስል ትንሽ ሰው ብቻ ይሳተፋል፤ የሚያዋጣው ግን ይህ ነበር። ታብ ታብ አድርግ፣ ሊንክ ነካካ፣ 5000 ብር አምጣና 50 ሺህ ብር ልስጥህ ስትለው እሺ ይላል፤ ግን እንኳን ሊያተርፍና ሊያዋጣው ጭራሽ ይዘረፋል። እንዳውም ይሄ ይዘረፋል ሳይሆን የሚባለው አውቆ ይሰጣል ነው መባል ያለበት። አሁን ለተቸገረ ሰው ወይም ለመስጅድ ግንባታ አውጣ ቢባልኮ እንዲህ አይፈጥንም። ለማንኘውም ኦፊሲያል ካልሆነ URL ከምታውቁት ሰው በኩልም ቢሆን ሊንክ ሲላክ እንዳትከፍቱ፤ ያ የምታውቁት ሰው ራሱ ሲስገበገብ ተጠልፎ ይሆናል እንጂ አውቆ አይደለም ሊንኩን የሚልክላችሁ። ከተጠለፈ ጠላፊዎች አውቶማቲካሊ እንዲልክ ስለሚያደርጉት ነው። አላህ ቀልብ ይስጣችሁ፣ በሐላሉና ባላችሁ ያብቃቃችሁ፣ ከእንዲህ አይነት የተወጋ መንፈስ ይጠብቃችሁ። የናንተ ገንዘብ ለተበላ እኔ መጨሴኮ ነው የሚገርመኝ። መግረፍ ነበር! ||
Ko'proq ko'rsatish ...
5 036
17
እውነታ! «ሶላት ባለመስገድህ የሚጠብቅህን ቅጣት ተወውና አለመስገድህ ራሱ ከአላህ የሆነ ቅጣት መሆኑን ተገንዘብ። የውዱ ነቢይ ﷺ የመጨረሻው ምክር « ሶላትን አደራ!» የሚል ነበር።» አደራቸውን መብላት በራሱ ለሌላ የከፋ ቅጣት የሚዳርግ ቅጣት አይደለም ትላለህን?
7 580
51
የባድ ወልዶችን'ኮ የምወዳቸው በምክንያት ነው። ይሄው በግዴታና በጥቅማ ጥቅም እያከፈሩ ወላጆችን ያለ ጧሪና ቀባሪ በማስቀረት በርካታ ቤተሰብ እየፈረሰ ባለበት የሐድያ ዞን ውስጥ ጎራ ብለው ታሪክ ሠርተዋል። ዛሬ ጠዋት ተነስተው የገፈቱ ቀማሽ ወደሆኑት ሆመቾ ከተማ አስተዳደርና ግቤ ወረዳ ከዚያራ አቅንተው፤ የአካባቢው ሙስሊሞች የመቀበሪያ ስፍራ እንኳን የሌላቸዉ በመሆኑ አዲስ ለሚገነባዉ መስጂድም የገንዘብ ድጋፍ አድርገው ተመልሰዋል። አላህ ይቀበላችሁ! 1) ሲሀም ዱቄት ፋብሪካ- 270,000 2) ፈድሉ ዱቄት ፋብሪካ- 140,000 3) ኸድጃ ዱቄት ፋብሪካ- 50,000 4) ወራቤ ዑሥማን መስጂድ ጀመዓህ— 100,000 5) ኢክራም መድኃኒት መደብር-10,000 6) ሸይኽ ሙሰማ – 10,000 7) ሳሊም ሰይድ- 20,000 8) ሙስጠፋ ህንፃ መሳሪያ-10,000 9) ሰይድ- 10,000 10) ዒዘዲን ኮንቴዉና ጓደኞቹ- 50,000 11) ሐጅ ዐብድ-ል-ዓዚዝ አደም-20,000 በሉ! እናንተም አካባቢያችሁን በደንብ አስከብሩ። እናንተ ስትበረቱ ነው ለሌላውም የምትተርፉት። የዛሬ አያድርገውና ሐድያም ከተወሰኑ አስርተረ አመታት የበፊት የሙስሊም ሱልጣኔት ነበረች። ኢንሻ አላህ አሁንም ወደማንነቱ ትመለሳለች። ||
Ko'proq ko'rsatish ...
8 227
7
አላህ አላህ! ይህ በራሱ የሰዓቲቱን መቅረብ አያመላክትምን?
9 298
11
አንዳንድ ጊዜ ሳስበው እንኳን ዩኒቨርስቲና ኮሌጅ ላይ ኢለመንተሪና ሐይስኩል ላይ ያለውን ሁኔታ ወላጆች ቢያዩ፤ ልጆቻቸውን የሚልኩ ሁላ አይመስለኝም። አላህ ይሁነን!
9 281
7
ምክር ለወላጆች‼ ============= (የልጆቻችሁን ጉዳይ አስባችሁበታል?) || ✍ ወላጆች ሆይ! አሁን ያለንበት ዘመን እጅግ በጣም አሳሳቢ ጊዜ ሆኗል። እናንተ የልጅነት ጊዚያችሁን ያሳለፋችሁበት ያ ዘመንና አሁን የናንተ ልጆች ልጅነታቸውን እያሳለፉበት ያለው ጊዜ ፍፁም የተለያዬ ነው። ያኔ በቂ ዲናዊ እንቅስቃሴ ባይኖርም እንኳ አብዛሃኛው ሰው በባህሉም ሆነ በንጹሕ ተፈጥሮው አዕምሮው አልተበረዘም ነበር። ዛሬ ላይ ግን በቂ የዲን ዕውቀት የሚገበይበት አማራጭ ቢበዛም ስንፍናችን ተጨምሮ ወደ ሐራም ነገር ወስዋሱ በዝቷል። ለመሆኑ ልጆቻችሁ ትምህር ቤት ውስጥ በምን መልኩ ከነማን ጋር ውሏቸውን እንደሚያሳልፉ አይታችኋል? ወይንስ ጠዋት በትራንስፖርት አድርሳችኋቸው ቀን ወይም ማታ ላይ ሲወጡ ተቀብላችኋቸው ወደቤታቸው መመለሳችሁን ብቻ ነው ያያችሁት? የቱንም ያክል ጥሩ የሚባል ት/ቤት ውስጥ ብታስገቧቸው፤ ጥሩ ያልሆኑ ተማሪዎች አይጠፉምና ልጆቻችሁ ከነዚያ ጋር ግንኙነት ይኑራቸው አይኑራቸው እውነታውን ማጥራትና መከታተል አለባችሁ። አንዳንድ ፈሳድን ሆነ ብሎ እንዲያስፋፉ ተልዕኮ የተሰጣቸው የሚመስሉ ተማሪ ተብዬዎች አሉ። ልጆቻችሁን አስመስለው በመልካም ነገር ቀርበዋቸው እነርሱም ሳያስቡት እንዳይመርዟቸው ልጆቻችሁን ተከታተሉ። የኔ ልጅ ገና ኢለመንተሪ ነው ያለው፣ የኔ ልጅ ገና ሐይስኩል ነው ያለችው… አሁን ስለ እንደዚህ አይነት ነገር ምንም አያውቁም፣ ቢነግሯቸውም አይገባቸውም… ብላችሁ እንዳትሞኙ። ያላወቃችሁት እናንተ እንጂ ልጆቻችሁ እናንተ ከምታስቧቸው በላይ ተራምደው ሂደዋል። አዕምሯቸው ትምህርቱን ብቻ ሳይሆን ብዙ እያሰበ ነው። አትሸወዱ! ኋላ ከተበከሉ በኋላ ልመልሳቸው ብትሉ እንኳ ወደማትችሉበት ደረጃ ሳትደርሱ፤ ከወዲሁ ልጆቻችሁን በመልካም ተርቢያ እስከ ጥግ አድርሷቸው። እንደ መፍትሄ፦ ①) ገንዘብ ስላላችሁ ብቻ ወይም ከጓደኞቻቸው እንዳያንሱና እንዳይከፋቸው በሚል ቀናነት ብቻ ስልክ፣ ታብሌት፣ ኮምፒዩተር ወይም ላፕቶፕ ገዝታችሁ ያለ አንዳች ቁጥጥር በልቅ መልኩ ዋይፋይ አስገብታችሁላቸው ወይም ዳታ ከፍታችሁ እንዲጠቀሙ የምታደርጉ ወላጆች፤ ሆነ ብላችሁ የልጆቻችሁን ህይዎት እየቀበራችሁ ነው። ለዲናቸው ወይም ለትምህርታቸው ወይም በመጠኑ አዕምሯቸውን ለማዝናናት በሚጠቅማቸው መልኩ ካልሆነ ጭራሽ አትግዙላቸው። ይህን ማድረጋችሁ ነፃነታቸውን መንፈግ ወይም የጠላችኋቸው ቢመስላቸውም ኋላ ስለሚረዷችሁ አትስሟቸው። ለዚህ የሚጠቅማቸው ከሆነ ግን በአግባቡ ተቆጣጠሯቸውና ሳይበዛ በመጠኑ ይጠቀሙ። ገና 11 አመት ላልሞላቸው ህፃናት ጭምር ስልክ ሰጥታችሁ ቲክቶክ የሚቀጠቅጡ አሉ። እነዚህ ህፃናት የዓይናቸው ብርሃን ከሆነ ጊዜ በኋላ የሆነ ችግር ይፈጠርበታል። አዕምሯቸውም ወርኪንግ ሚሞሪው ስለሚመናመን አዳዲስ ነገሮችን በቀላሉ የመቀበል አቅማቸው ይዳከምና ይደነዝዛሉ። ልጆቻችሁ አሁን ላይ በእናንተ መሪነት ነው መሄድ ያለባቸው። እነርሱ ሐራምና ሐላሉን፣ የሚጠቅማቸውንና የሚጎዳቸውን በትክክል አያውቁም። ቢያውቁ እንኳ ልጅነትና ወጣትነት ያዘናጋቸዋል፣ ያሳስታቸዋል። ስለዚህ ተቆጣጠሯቸው። * ②) አሁን ላይ ዋነኛ የመበላሸት መንስዔ የሆነው ት/ቤት ስለሆነ እዛ ያላቸውን ውሎ በብዙ መልኩ ተከታተሉ። የሚይዟቸውን ጓደኞች ሁኔታ አጣሩ። * ③) በሸሪዓው ትምህርት ጥመዷቸው። እስልምናው ከልባቸው ከገባቸው እንኳን እናንተ ልትቆጣጠሯቸው እናንተንም ይመክሯችኋል። ዲናዊ ትምህርት በደንብ ከተማሩ በዋናነት ተጠቃሚዎቹ እናንተ ናችሁ። ምክንያቱም የአላህን ሐቅ ያውቃሉ፣ የእናንተን ሐቅ ያውቃሉ፣ ጊዚያቸውን በምንና እንደት ማሳለፍ እንዳለባቸው ያውቃሉ። በቃ! ትልቅ ሸክም ተላቀቃችሁ። የሚበሉትና ከሚጠጡት፣ ከሚለብሱትና ከክፍያቸው ውጭ ሌላ አሳሳቢ ነገር የለም። * ④) ወላሂ! ይሄ ጉዳይ ከምታስቡት በላይ አሳሳቢ ነውና የወላጅ ዱዓእ ስለሚደርስ ከልባችሁ ለልጆቻችሁ ዱዓእ አድርጉላቸው። ወላሂ የልጅ ፊትና ከባድ ነው። ልጅ ከተበላሸ መጥቀሙ ቀርቶ እናንተንም ያሳፍራል፣ ያዋርዳል፣ ይበድሏችኋል። ምነው ባልተወለዱ የሚያስብሉ ስንት አሉ። ከተስተካከሉ ደግሞ ሁሌም ኩራት ናቸው። ብቻ! እንድትይዙልኝ የምፈልገው ነጥብ፤ ቤት ውስጥ የሆነ የባህሪ ለውጥ ሲያመጡ በደፈናው የ"ጉርምስና እድሜ ላይ ስለሆኑ ነው!" ብላችሁ መዘናጋታችሁን ትታችሁ ጀርባቸውን አጥኑ። ቤት ውስጥ ደፍረው ባህሪያቸው ባይቀየር እንኳ ጀርባቸውን በደንብ አጥኑ። እንደምታስቧቸው አይደሉም። ከምታስቡት በላይ ርቀው ሂደዋል። እናንተ የምታውቁት ቲቪ ላይ ካርቱንና አሻንጉሊት ማየት ነው። ሌላ ሌላ ፈሳድ አለ። ኤሌክትሮኒክስ ነገር ጭራሽ አይያዙ። በቃ! ለነርሱ ለትምህርታቸው ብቻ እንጂ ስልካቸውን ቀሟቸው። ወይም እናንተ ዓይናችሁ እያዬ ይጠቀሙ። ከዚያ ውጭ ስልካቸው ይቆለፍበት። በዲናዊ ነገርም አጠናክሯቸው። ኋላ እንዳትጸጸቱ‼ አላህ መልካም ልጆችን ይወፍቀን፣ የወፈቀንን ሷሊሕ ያድርግልን፣ እኛንም ሷሊሖች ያድርገን። ♠ ወንድማችሁ፦ ሙራድ ታደሰ ========= አፕሪል 28, 2024 G.C. ||
Ko'proq ko'rsatish ...
13 109
124
ሒጃብ የለበሰች ፌሚኒስት ካገባህ፤ ሚስት ሳይሆን ተጋጣሚህን ነው ያገባኸው። አንድ ስትል ሁለት ትልሃለች። ብትቀርብህ ይሻልሃል።
15 411
48
16 039
16
በነገራችን ላይ በርካታ ተቋማት ቢዝነሳችሁንም ሆነ የራሳችሁን ሚዲያ ቲክቶክ ላይ የገነባችሁ ይመስለኛል። ምክንያቱም በቀላሉ ተከታይና ተመልካች በብዛት የሚገኝበት ስለሆነ። ግን አሜሪካ ሙሉ በሙሉ እስከወዲያኛው ልታግደው ጫፍ መድረሷንና ውሳኔውን ማፅደቋን ከሰሞኑ የሰማችሁ ይመስለኛል። እንደዛ ከሆነ ደግሞ ሙሉ ከአሜሪካ ተቋማት ጋር ያለው ግንኙነት ይጠፋል። ለምሳሌ፦ ከጎግል ፕሌይስቶርም ሆነ ከአፕል አፕስቶር መወገዱ አይቀሬ ነው። ያኔ እኛም ከፕሌይስቶር አውርደን መጠቀም አንችልም። ይሄ ያወረድነው አፕደት ባይኖረውም በዚሁ እንቀጥላለን ብለን ብናስብ እንኳ ከፕሌይስቶር ወይም ከአፕስቶር የወረደን አፕ መጠቀም እንዳንችል ማድረግ ይችላሉ። ስለዚህ ላይ ወጥታችሁ ስታበቁ ታች እንዳትፈጠፈጡ፤ ቲክቶክ ላይ ያላችሁን ታዳሚ ወደ ቴሌግራምና መሰል ሚዲያዎች ከወዲሁ ለማምጣት ብትሞክሩ ይሻላል። የተወሰነ ያክል ጉዳታችሁን ለመቀነስ!
Ko'proq ko'rsatish ...
15 544
12
እንደ አለመታደል ሆኖ እንዲህ አይነት ተቋም ውስጥ የሆነ ሐጃ ኖሮብኝ ከሄድኩ ወረፋው ብዙ ነው፣ ወረፋ ደርሶኝ ልስተናገድ ስል በሆነ መልኩ የሆነ ነገር ጎደለ ተብዬ እቀጠራለሁ፣ የጎደለውን ሳሟላ ለሌላ የጎደለ ነገር ያመጣሉ፣ ከአንዱ መስኮት እንደምንም አለፍኩ ስል ሌላኛውም መስኮት ሌላ መሰል ጣጣ ያመጣል፣ እንዲህ እንዲህ እያሉ እግሬ እስኪቀጥን ድረስ ወይ ሙሉ ሳምንት አሊያ እስከ ወር እታሻለሁ። አላህ ይጠብቃችሁ¡ ግን ምኅፃረ ቃሉ ምንድን ነው የሚለው? ወይ የአማርኛ ፈተና ላይ ማውጣት ነው¡
14 979
10
በአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከ/ም/ቤት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የሚገኘውና በልዩ ሁኔታ የተገነባው የዳሩ-ል-ሂጅረተይን መስጂድና መድረሳ የምረቃ ፕሮግራም በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል። በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አመራሮች፣ ዑለማዎች፣ ኡስታዞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል። በርካታ ኡማውን የሚጠቅሙና ለራሳቸው የሚጠቀሙ እንቁ ትውልዶች የሚፈሩበት የዕውቀት ማዕከል የሆነ መስጅድ አላህ ያድርገው። በዚሁ አጋጣሚ አክብራችሁ ጠርታችሁኝ ባለመገኘቴ ዐፍወን!
13 918
12
እናትና አባቱን ሐጅ ሳያስደርግ አንቺን ቀድሞ ካስደረገሽና ዑምራ ደጋግሞ ከወሰደሽ፤ በአንድኛው ጉዟችሁ ላይ ተጨማሪ ሚስት ማግባቱን ሊያበስርሽ መሆኑን ጠርጥሪ¡ እኔ አላልኩም¡
15 049
21
ይህ መራር እውነታ ነው። የወንድ ልፍስፍስ አይረባም! አንዳንድ የተመረቁ ሚስቶች ደግሞ አንተ ብትዘናጋ እንኳ ለወላጆችህ የጎደላቸውን እንድታሟላ ይገፋፉሃል።
14 989
34
ምን ትላላችሁ? በርግጥም ከወላጆች ጋር ማን ይስተካከላል? አቦ! አላህ ሁሉንም አንድ ላይ ሐጅ የምናስደርግበት አቅም ይስጠን።
13 722
11
ይህ በራሱ ሰላም የተሞላበት ህይዎት ነው። ሌላ ራሱን የቻለ ደስ የሚል ልዩ ዓለም! በአህጉረ አፍሪካ ሃገረ ቻድ በጎርጎረሳውያኑ አቆጣጠር 2022 ላይ በሳጅኻን የተቀረፀ ቪድዮ! ||

ocXcslgSXEnglDelAmQUEyIdfqE3wBBQJD5R3F.mp4

13 709
61
ርዕስ፦ ⇨ አላህን መፍራት አቅራቢ → ኡስታዝ ሑሴን ዒሳ

alaahene_maferaate_ba_usetaaze_huseenesaa_nesiha_da_wa_atlanta_x.mp3

12 794
47
የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: ⓵⑤⑨⑤]👌

okGEzEL8VFQeABUdHmvGRcgIIEIUfB1DEQYi5s.mp4

13 397
6
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: ⓵⑤⑨④]👌

oMLDg0WeAEoBlkhNDfMAQgTCjfMAOCRIQTQS8z.mp4

14 801
8
አፋልጓቸው!
15 380
9
እህታችንን እናሳክማት‼ ================ ✍ እህታችን ዘሀራ ዑመር ኢብራሂም ትምህርቷን በጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ በIT 2011 E.C. ላይ ተመርቃ እዛው ጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ በሌክቸረርነት እያገለገለች ትገኛለች። ባጋጠማት የልብ ህመም ምክኒያት ሥራዋን በአግባቡ መስራት አልቻለችም። ሕክምናው የልብ ቀዶ ጥገና ነው። ለዚህም 1,000,000 ብር ገደማ እንደሚያስፈልጋት በሐኪሞች ተነግሯታል። ከዩኒቨርስቲው መምህራን እስከ 680,000 ብር ተሰባስቦላት ለሕክምና አዲስ አበባ መጥቻለች። ቀሪውን 320 ሺህ ብር እንድትሞሉላት በአላህ ስም ጠይቃችኋለችና እህታችንን ተረባርበን እናሳክማት። √ የአካውንት ስም፦ Zehra Umer √ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር፦ 1000148520805  √ አቢሲኒያ ባንክ፦ 77889817 √ ዘምዘም ባንክ፦ 0022015620102 የምትሰድቁበትን ደረሰኝ በውስጥ መስመር ላይ ወይም ኮመንት ላይ ለኸይር ማነሳሻ ይሆን ዘንድ ላኩት።
Ko'proq ko'rsatish ...
17 143
12
እህታችንን እናሳክማት‼ ================ ✍ እህታችን ዘሀራ ዑመር ኢብራሂም ትምህርቷን በጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ በIT 2011 E.C. ላይ ተመርቃ እዛው ጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ በሌክቸረርነት እያገለገለች ትገኛለች። ባጋጠማት የልብ ህመም ምክኒያት ሥራዋን በአግባቡ መስራት አልቻለችም። ሕክምናው የልብ ቀዶ ጥገና ነው። ለዚህም 1,000,000 ብር ገደማ እንደሚያስፈልጋት በሐኪሞች ተነግሯታል። ከዩኒቨርስቲው መምህራን እስከ 680,000 ብር ተሰባስቦላት ለሕክምና አዲስ አበባ መጥቻለች። ቀሪውን 320 ሺህ ብር እንድትሞሉላት በአላህ ስም ጠይቃችኋለችና እህታችንን ተረባርበን እናሳክማት። √ የአካውንት ስም፦ Zehra Umer √ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር፦ 10004001494438  √ አቢሲኒያ ባንክ፦ 77889817 √ ዘምዘም ባንክ፦ 0022015620102 የምትሰድቁበትን ደረሰኝ በውስጥ መስመር ላይ ወይም ኮመንት ላይ ለኸይር ማነሳሻ ይሆን ዘንድ ላኩት።
Ko'proq ko'rsatish ...
1 986
4
አንዳንድ እህቶች ወዲያው ያገባችሁ ሰሞን ባላችሁ ለፈጅር ሶላት መስጅድ ሲሄድ ወይም መጝሪብና ዒሻእ መስጂድ እንደሄደ መብራት ሲጠፋ፤ አይታችኋቸው የምታውቋቸውንም በምናባችሁም አዳዲስ አውሬዎች እየፈጠራችሁም የምትፈሩት ለምንድን ነው? (ላጤዎች ምኑንም ስለማታውቁት ዝም በሉ¡) እና ደግሞ ዶክተሮችና ሳይኮሎጂስቶች ይሄን ምን ትሉታላችሁ? መቼ የሆነ ስም አታጡለትም¡
18 474
51
ግን መጅሊስ የሐጅ ተጓዦችን ክፍያ ሲቀበል፤ ሌሎች የባንክ አማራጮችን ሳይጠቀም በኢስላማዊ ባንኮች ብቻ ቢያደርገው ችግሩ ምንድን ነው? ያው! የውጭ ምንዛሬው ጉዳይ በነርሱ በኩል እንዲስተካከል ተደርጎ!
18 934
0
﴿إذا دُعِيَ أحَدُكُمْ إلى الوَلِيمَةِ فَلْيَأْتِها.﴾
19 210
23
የኛ ባንኮች የት ናቸው? ይህ ከታች በምስሉ ላይ የምትመለከቱት የብር መዓት አብዛሃኛው ማኅበረሰብ ሙስሊም በሆነበት በጅማ ዞን ሲጊሞ ወረዳ በአንድ ቀን ብቻ በስንቄ ባንክ የተሰበሰበ 263, 175, 000 ብር ነው። በሌሎች ወረዳዎችም በተመሳሳይ ቀን በርካታ ሚሊዮኖች ተሰብስበዋል። የኛ ባንኮች በተወሰኑ አካባቢዎችና በተወሰኑ ግለሰቦች ላይ ብቻ ከመንጠልጠል ተላቀው መሬት ላይ ተፋልጠው አቅማቸውን ሊያዳብሩ ይገባል። የሚያስተባብር እንጂ ገና ያልተበላበት አቅም አለ። አሁንም ነቃ ማለትና ከሌሎች ተወዳዳሪ ሆኖ መገኘት ግድ ነው። ||
18 318
22
The sound system in the Haramain ! More than 8000 speakers transmit the Adhan, the Iqāmah, Salahs and the Khutbahs from Al Masjid Al Haram, its courtyards and surroundings. Whereas in Al Masjid Al Nabawī, 2900 speakers are distributed throughout the Haram. Around 22 microphones are distributed in Al Masjid Al Haram whereas in Al Masjid Al Nabawī there are 31. There are 3 sound systems in the Haramain, just in case they fail. - The main sound system - The backup sound system - The emergency sound system More than 170 technicians look after the sound system in the Haramain, and they adjust the system from the Imams and the Muadhins microphone according to what is appropriate for everyone to hear.
Ko'proq ko'rsatish ...
18 712
25
እስኪ አዳምጡት!🎧

398308305.mp4

16 863
35
የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: ⓵⑤⑨③]👌

ocQCkRBmPIGemFo1hK5DkggEU7BfA2kYIIREE3.mp4

17 480
9
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: ⓵⑤⑨②]👌

file

17 202
13
ማን ማንን ተቀበለ⁉️ በአሕመዲን ጀበል ||

file

17 966
79
እባካችሁ ነባሮቹ የተባላችሁት ውጡና ታገሉ¡ ለማንኛውም እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የማናቸውም ውለታ የለብንም። እንዳውም እየጨቆኑ አሰቃይተውናል።

file

18 013
62
የወራሪዋ እስራኤል የሴኩሪቲ ሚኒስቴር የሆነው ጠማማው ቤን ግቪር (Itamar Ben-Gvir) ላይ በምስሉ ላይ የሚታየው ከፍተኛ የመኪና አደጋ ደርሶበታል። አላህ ጨርሶ ይውሰደው!

file

17 350
33
ይሄን ጥቆማ ቲክቫህም ፖስቶታል። የሚያስተምሩት በነፃ ነው፤ 200 ሰው ብቻ ስለሆነ በዚህ ዙር የሚቀበሉት ሳይሞላ ቶሎ ልጆቻችሁን አስመዝግቡ። እኔ በዚህ የኮዲንግና የኤአይ ጉዳይ አግሬስፊሊ ነው የምነግራችሁ፤ አሁን ብትሰላቹም ኋላ ሲገባችሁ ስለምታመሰግኑኝ! ቲክቫህ ስለለቀቀው ብዙ ሰው ሳይቀድማችሁ አስመዝግቡ። ዝርዝር መረጃ ከፈለጋችሁ፦
18 023
71
አንድ ሰው ለአንድ ጥበበኛ «ምከረኝ?» አለው። ጥበበኛውም «አላህ እከለከለህ ነገር ላይ እንዳያይህ፤ ባዘዘብህ ቦታ ላይም እንዳያጣህ!» ህምምም…!
17 193
44
ተጋብዛችኋል!
16 750
2
A statement from the Ministry of Hajj and Umrah.
16 959
6
16 170
5
ሶለዋት ማውረድ የሱፍይነት መገለጫ አይደለም‼ ========================= ✍ እስኪ ስንቶቻችን ነን ሆነ ብለን አስበንበት በውዱ ነቢያችን ላይ ደጋግመን ሶለዋት የምናወርድ? ሶላት በዋናነት ጁሙዓህ ቀን ይበልጥ ይበዛል እንጂ በሌላውም ቀን እንደማንኛውም ዚክር ይደረጋል። ግን ሶለዋት ካበዛን ሱፍያ የሆንን አይነት ስሜት የሚሰማን ስንቶች ነን? በተለይም ሱንናውን አጥብቀን እንይዛለን የምንል ሰዎች፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ያለን ግንዛቤና ትግበራ እንደት ነው? ለዓለማት እዝነት ተደርገው በተላኩልን ውዱ ነቢያችን ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲ-ል'ላህ ﷺ ላይ ሶለዋት ማውረድን በተመለከተ በአፈጻጸሙ ረገድ ከተለያዩ ቡድኖች ግድፈቶች ከመብዛታቸው የተነሳ፤ ብዙዎች በትክክለኛው መንገድ ሶለዋት ከማውረድ ስንዘናጋ ይስተዋላል። እርግጥ ነው በሶለዋት ሽፋን በውዱ ነቢይ ﷺ ላይ ያለ አግባብ ድንበር ማለፎችን እናስተውላለን። ለዚህ ደግሞ መፍትሄው ሶለዋት ከማውረድ መዘናጋት ሳይሆን በትክክለኛው መንገድ ለራስ እያደረጉ ለሌሎችም ማስተማር ነው። ስለ ሶለዋት ትሩፋቶች የተወሰኑ ቁርኣናዊና ሐዲሣዊ ማስረጃዎችን እንዲሁም ከዑለሞች ንግግር እንመልከት። * ①) በውዱ ነቢያችን ﷺ ላይ ሶለዋት ማውረድ የአላህ ትዕዛዝ ነው። አላህ በተከበረው ቃሉ በቅዱስ ቁርኣን ላይ እንዲህ ብሏል፦ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا «አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ ሶለዋት ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ ሶለዋትን (የአክብሮት እዝነትን) አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡» [አል-አሕዛብ: 46] * √ አንቀፁ አላህና መላኢካዎች በርሳቸው ላይ ሶለዋት ያወርዳሉ ስለሚል፤ ታላቁ የዘመናችን የተፍሲር ሊቅ አ-ሽ'ሸይኽ ዐብዱ-ር'ረሕማን አ-ስ'ሰዒዲይ (አላህ ይዘንላቸውና) ይህን አንቀፅ በተፍሲር ኪታባቸው ላይ ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ፦ (…اقتداء باللّه وملائكته ، وجزاء له على بعض حقوقه عليكم ، وتكميلا لإيمانكم ، وتعظيمًا له صلى اللّه عليه وسلم ، ومحبة وإكرامًا ، وزيادة في حسناتكم ، وتكفيرًا من سيئاتكم .) «በአላህና በመላኢኮቹ ለመከተል፣ በናንተ ላይ ባላቸው ከፊል ሐቆች ምንዳ ይሆናቸው ዘንድ፣ ኢማናችሁን ለመሙላት፣ እርሳቸውን ለማላቅ፣ ለመውደድና ለማክበር፣ በመልካም ሥራችሁ ላይ ጭማሬ እንዲሆናችሁ፣ ወንጀላችሁን እንዲያስምርላችሁ።» [ተፍሲር አ-ስ'ሰዒዲይ: 1/671] ★ ②) እርሳቸውም ﷺ በሐዲሣቸው ላይ ይህን ብለዋል፦ ( مَنْ صَلَّى عَلَيَّ صَلَاةً وَاحِدَةً صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ عَشْرَ صَلَوَاتٍ وَحُطَّتْ عَنْهُ عَشْرُ خَطِيئَاتٍ وَرُفِعَتْ لَهُ عَشْرُ دَرَجَاتٍ ) «በእኔ ላይ አንድት ሶለዋትን ያወረደ ሰው፤ አላህ በርሱ ላይ አስር ሶለዋትን ያወርድበታል፣ ከርሱ አስር ወንጀሎች ይታበሱለታል፣ ለርሱ አስር ደረጃዎች ከፍ ይደረጉለታል።» [አ-ን'ነሳኢይ: 1297— አል-ኢማም አል-አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል።] ★ ③) አቢ ቢን ከዕብ (አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና) እንዲህ ይላል፦ (قُلْتُ : يَا رَسُولَ اللَّهِ ، إِنِّي أُكْثِرُ الصَّلَاةَ عَلَيْكَ ، فَكَمْ أَجْعَلُ لَكَ مِنْ صَلَاتِي ؟ …) «እኔ በርስዎ ላይ ሶለዋት ማውረድ አበዛለሁ። ከማወርደው ሶለዋት ምን ያክሉን ላድርግልዎት?» ብዬ ጠየቅኳቸው ይላል። فَقَالَ : ( مَا شِئْتَ ) እርሳቸውም «የፈለግከውን ያክል!» አሉት። قَالَ : قُلْتُ : الرُّبُعَ ؟ «¼?» አልኳቸው አለ። قَالَ : ( مَا شِئْتَ ، فَإِنْ زِدْتَ فَهُوَ خَيْرٌ لَكَ ) ، እርሳቸውም «የፈለግከውን፤ ብትጨምር ላንተ የተሻለ ነው።» አሉት። قُلْتُ : النِّصْفَ ؟ «½ኛ?» አልኳቸው አለ። قَالَ : ( مَا شِئْتَ ، فَإِنْ زِدْتَ فَهُوَ خَيْرٌ لَكَ ) ، እርሳቸውም «የፈለግከውን፤ ብትጨምር ላንተ የተሻለ ነው።» አሉት። قَالَ : قُلْتُ : فَالثُّلُثَيْنِ ؟ «⅔ኛ?» አልኳቸው አለ። قَالَ : ( مَا شِئْتَ ، فَإِنْ زِدْتَ فَهُوَ خَيْرٌ لَكَ ) ، እርሳቸውም «የፈለግከውን፤ ብትጨምር ላንተ የተሻለ ነው።» አሉት። قُلْتُ : أَجْعَلُ لَكَ صَلَاتِي كُلَّهَا ؟ «ሁሉንም ሶለዋቴን ላድርግልዎት?» አልኳቸው አለ። قَالَ : ( إِذًا تُكْفَى هَمَّكَ ، وَيُغْفَرُ لَكَ ذَنْبُكَ ) እርሳቸውም «ስለዚህ ጭንቀትህን ትበቃለህ፣ ወንጀልህ ይማርልሃል።» አሉኝ ይላል። [አ-ት'ቲርሚዚይ: 2457] * በሌላ ሐዲሥ ላይም የርሳቸው ስም ተነስቶ ሶለዋት ያላወረደን ሰው ጂብሪል ሲረግም አሚን በል አለኝ፣ 3 ጊዜ ኣሚን አልኩ ብለዋል። ስማቸው በቃል ሲነሳም ሆነ በጽሑፍ ሲፃፍ ሶለዋት ማውረድ ይገባል። * በርሳቸው ላይ ሶለዋት ስናወርድ አላህ በኛ ላይ 10 ሶለዋት ያወርዳል ማለት፤ የአላህ ሶለዋት ማውረድ ከላይኛው ዓለም ላይ ያንን ሶለዋት ማወረደን ሰው ያወሳዋል፣ ያዝንለታል ማለት ነው። ሶለዋትና ሰላም በርሳቸው ላይ ማውረድ ማለት አኳኋኑን አል-ኢማም ኢብኑ ባዝ በፈታዋቸው ላይ በዚህ መልኩ አስፍረውታል። قال: قولوا: اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد هذه صفة الصلاة عليه عليه الصلاة والسلام، أما السلام فقد بينه السلام عليك أيها النبي ورحمة الله وبركاته ولهذا لما علمهم الصلاة قال: أما السلام فقد علمتم وهو أن يقول الإنسان: السلام عليك أيها النبي ورحمة الله وبركاته، أو السلام عليك النبي ورحمة الله وبركاته، أو السلام على النبي محمد ورحمة الله وبركاته، * √ ስለሆነም ሶለዋት በጀማዓህ ማውረድን በተመለከተ መረጃ የለም። ሁሉም በየግሉ ሶለዋት ማውረድ ይችላል። ሶለዋት የሚወረደው በየትኛውም ቀንና ሰዓት እንደ ማንኛውም ዚክር ነው እንጂ በሳምንት አንድ ቀን ጁሙዓህን ብቻ ተጠብቆ አይደለም። ባይሆን ጁሙዓህ ሲሆን ማብዛቱ ይወደዳል። ሶለዋት ማውረድ የሱፍይነትና የሌላ በርሳቸው ላይ ድንበር አላፊ አካላት መገለጫ አይደለምና በነርሱ የተበላሸ የሶለዋት አወራረድ ጥላቻ የተነሳ በትክክለኛው መንገድ ሶለዋት ከማውረድ አንዘናጋ። አላህ ያግራልን። اللهم صل على محمد وعلى آل محمد ♠ ወንድማችሁ፦ ሙራድ ታደሰ ======== ጁሙዓህ ዴሴምበር 15, 2023 G.C. ||
Ko'proq ko'rsatish ...
17 640
82
خطبة الجمعة من منبر المسجدالحرام لفضيلة الشيخ أ.د.⁧ ⁩ "الذكر طمأنينة للقلوب" | 17-10-1445هـ

خطبة الجمعة.mp3

18 569
46
የሌለን እስኪኖረን ያለን በቂያችን ነው። ለኛ የተሰጠን ለሌሎች ግን ያልተሰጣቸው ብዙ ነውና የሌለን እንዲኖረን ከፈለግን ባለን አላህን ዘወትር ማመስገን አይረሳ። አል-ሐምዱ ሊላህ‼
19 189
53
ጁሙዓን የት ሃገር፣ የት መስጅድ ሰገዳችሁ? ኹጥባው ስለምን ነበር? ለሌሎችም እንዲጠቅም ከሰማችሁት ውስጥ የኹጥባውን ጭብጥ በአጭር አስፍሩት።
18 665
4
#ጁሙዓህ
18 896
28
የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: ⓵⑤⑨①]👌

file

18 454
19
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: ⓵⑤⑨∅]👌

o4Y0nAe47SQRvIEMUTLeCCgYH3qG2sIejBGqIj.mp4

18 669
13
በነገራችን ላይ የጁሙዓህ ትጥበት ሱንናው የሚገኘው የጁሙዓህ ቀን የፈጅር ወቅት ከወጣ በኋላ ነው። በላጩ ደግሞ ጸሐይ ከወጣ በኋላ ነው። እጅግ በጣም በላጩ ደግሞ ወደ መስጅድ ሊሄድ ሲል ነው። ለምን መሰላችሁ ይሄን ያነሳሁት? (ላጤ ሳታነብ እለፍ፤ ግን በርካታ ባለ ትዳሮች የፈጅር ወቅት ከመድረሱ በፊት ጁሙዓህ ሌሊት የምትወስዱት ሻወር የጁሙዓውንም ስለማያብቃቃችሁ ጸሐይ ከወጣች በኋላም ሻወር ውሰዱ ለማለት ነው¡ ደግሞ ድጋሜ ላለመታጠብ ብለህ ፈጅርን በጀማዓህ መስገድ አሳልፍ አሉህ! እጅግ በጣም በላጩ ሶላት በጁሙዓህ ቀን በጃማዓህ የሚሰገደው የፈጅር ሶላት ነው።) እያነበባችሁ፦ وقتُ غسلِ الجُمُعة يبدأ من بعدِ طلوعِ الفَجرِ يومَ الجُمُعة، والأفضلُ أن يكونَ عندَ الرَّواحِ إلى صلاةِ الجُمُعة، وهو مذهبُ الشافعيَّة، والحَنابِلَة، وهو قول بعض المالكية وقولُ الحسنِ مِن الحَنَفيَّة الدَّليلُ مِنَ السُّنَّة: عن أبي هُرَيرَةَ رَضِيَ اللهُ عنه، أنَّ رسولَ اللهِ صلَّى اللهُ عليه وسلَّم قال: ((مَنِ اغتَسَلَ يومَ الجُمُعةِ غُسلَ ، ثم راحَ في السَّاعةِ الأُولى، فكأنَّما قَرَّبَ بَدنةً...  )) وَجْهُ الدَّلالَةِ: أنَّ اليومَ من طُلوعِ الفَجرِ فرعٌ: حُكْمُ الاغتسالِ بعد الصلاةِ لا تَحصُل سُنَّةُ الاغتِسالِ إلَّا قبلَ صلاةِ الجُمُعةِ؛ فلو اغتَسلَ بعدَ الصلاةِ لم يكُن آتيًا بفضيلةِ الغُسْلِ المأمورِ به، وهذا باتِّفاق المذاهبِ الفقهيَّة الأربعة: الحَنَفيَّة، والمالِكيَّة، والشافعيَّة، والحَنابِلَة، وحُكي الإجماعُ على ذلك الأَدِلَّةُ مِنَ السُّنَّة: 1- عن أبي هُرَيرَة رَضِيَ اللهُ عنه، أنَّ رسولَ اللهِ صلَّى اللهُ عليه وسلَّم قال: ((مَن اغتَسَلَ يومَ الجُمُعةِ غُسلَ ، ثم راح في السَّاعةِ الأُولى، فكأنَّما قرَّب بَدنةً...  )) وَجْهُ الدَّلالَةِ: قوله: ((ثم راح)) يدلُّ على أنه لا تَحصُل سُنَّةُ الاغتسالِ للجُمعةِ إلَّا قبلَ صلاةِ الجُمُعةِ 2- عنِ  رَضِيَ اللهُ عنهما، أنَّه قال: سمعتُ رسولَ اللهِ صلَّى اللهُ عليه وسلَّم يقولُ: ((مَن جاءَ مِنكُم الجُمُعةَ فلْيَغْتَسِلْ  ))
Ko'proq ko'rsatish ...
19 916
76
ታዲያ አንተ ለምን ዱንያን ሙጭኝ ትላለህ?
18 583
21
18 893
66
ጥቆማ‼ ======= (የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ልጅ ላላችሁ ወላጆች በሙሉ!) || ✍ እኔ በዚህ ጉዳይ የምነግራችሁን ነገር ጆሯችሁን አቁማችሁ ማዳመጥ፣ ዓይናችሁን ከፍታችሁ ማየት ግደታ አለባችሁ። ልጆቻችሁን ፍጠኑን ለቀጣይ ክረምት ለዚህ ትሬይኒንግ አሁኑኑ መዝግቧቸው። የሚቀበሉት 200 ሰው ብቻ ነው። ማስታወቂያውን የለቀቁት ገና አሁን ነው። ልጆቻችሁ ገና ከወዲሁ ለቀጣዩ ጊዜም ተራማጅ የሆኑ መስኮችን በማወቅ ዓይን እንዲከፍቱና ፍላጎቱ እንዲያድርባቸው ያደርጋቸዋል። ተናግሪያለሁ! «ማስታወቂያ ለኤ.አይ ሰመር ካምፕ 2024 የክረምት ስልጠና ፈላጊ ታዳጊዎች በሙሉ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለ2 ወራት የሚቆይ የኤ.አይ ሰመር ካምፕ 2024 የስልጠና መርሓ ግብር በአዲስ አበባ አዘጋጅቷል፡፡ ስልጠናዉ በ 🎯AI basics 🎯Robotics 🎯Programming 🎯Machine learning 🎯Internet of Things (IoT) ላይ ትኩረቱን ያደርጋል፡፡ የመመዝገቢያ መስፈርቶች 👉🏼የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ የሆነ/ የሆነች 👉🏼ስልጠናውን በሳምንት 4ቀን መከታተል የሚችል/ የምትችል የምዝገባ ቀናት 👉🏼ከሚያዝያ 17 - ግንቦት 07፣ 2016 ዓ.ም ባሉት ቀናት አመልካቾች ከታች የተቀመጡትን ሊንኮች በመጠቀም መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ 👉🏼 👉🏼 በተጨማሪም እውቀት እና ክህሎታቸውን ለተማሪዎች በማካፈል በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ትውልዱን ለመገንባት ዕድሉን የሚፈልጉ አሰልጣኞች ተከታዮቹን ሊንኮች በመጠቀም መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ 👉🏼 👉🏼 ለበለጠ መረጃ ይጠቀሙ ወይም ድረ ገጻችንን ይጎብኙ፡፡ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በሁሉም!»
Ko'proq ko'rsatish ...
20 944
449
የባድ ወልድ መስጅድና መድረሳ ሲያስገበባ እንጂ ኡስታዝና ሸይኽ ይመስል ለዘፋኝ መኪና እንግዛ ሲል አያምርበትም። በስልጥኛ የተዘፈነም ሐራም ነው። አላህ ለዘፋኞች ተውበትን ይወፍቃቸው።
18 315
14
ቁርአን ውስጥ የተጠቀሱ ምኞቶች‼ ======================== «ዋ ምኞቴ! ምነው አፈር በሆንኩ!» [አ-ን'ነበእ: 40] «ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራ) ባስቀደምኩ ኖሮ!» [አልፈጅር: 24] «ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ!» [አል ሃቀህ: 25] «ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ አድርጌ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ!» [አል ፉርቃን: 28] «ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን፤ መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ!» [አል አሕዛብ: 66] «ዋ ምኞቴ! ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በሆነ!» [አል ፉርቃን: 27] «ወይ ምኞቴ! ታላቅ ዕድልን አገኝ ዘንድ ከነሱ ጋር በሆንኩ!» [አንኒሳእ: 73] ሁሉም የሟቾች ምኞቶ ናቸው። ቀብር ውስጥ ያሉት ሰዎች ምኞታቸው ወደ ዱንያ አንዴ መጥተው ለአኺራቸው ጥሩን ነገር መስራት ነው። ግን ምን ዋጋ አለው! አልፏል ተቀድሟል! ቀብር ገብተህ አንተም ይህን ከምትመኝ ነፍስህ አካልህ ውስጥ እስካለች ድረስ ለአኺራህ አስቀድም። ብልህ የሆነ ሰው ከመጸጸቱ በፊት ሥራውን ይሥራ አላህ ሆይ! ከነዚህ ከንቱ ምኞቶችበእዝነትህ ጠብቀን።
Ko'proq ko'rsatish ...

oQeEpEUDQmDBCr3FfSlRBgAtQGh8x0IbP3u2TJ.mp4

20 872
324
🎞 ሰለዋት! 🎙ኡስታዝ ጂብሪል አክመል …………………………………………… ☑️Telegram ☑️Facebook: ☑️TikTok ☑️YouTube

file

18 969
36
ምርጥ ምክር ለእህቶች!
19 913
38
﴿لو أنَّكم توَكَّلتم على اللهِ حقَّ توَكُّلِهِ، لرزقَكم كما يرزقُ الطَّيرَ، تغدو خماصًا، وتروحُ بطانًا.﴾
20 204
17
ተመልከት ይህን የኢማሙ አሕመድ ቤተሰቦችና የኢማሙ አሕመድ አስተማሪ የሆኑት የኢማሙ ሻፊዒይ ሁኔታ!

owIgEQBRRRUIAiDmyFEBfWpchQeEUEEgU9EOB2.mp4

19 263
83
በፊትና ዘመን ለአንድ ወጣት ከሐጅ ይልቅ ማግባት ይበልጣል ይላሉ አል-ኢማም አል-ቡኻሪይ። በርግጥ አቅሙ ለቻለ ሐጅ ዋጂብ'ኮ ነው። ግን ፊትና ካለና ከትዳር ውጭ መቋቋም የማይችለው ፊትና ከሆነ ማግባቱ የበለጠ ይወጅበበታል። الزواج للشباب في زمن الفتن، أوجب مـن الحج! إذا كان الرجل يحتاج إلى الزواج ، ويشق عليه تأخيره فإنه يقدم الزواج على الحج . أما إذا كان لا يحتاج إلى الزواج فإنه يقدم الحج . قال ابن قدامة رحمه الله في "المغني" (5/12) : وَإِنْ احْتَاجَ إلَى النِّكَاحِ , وَخَافَ عَلَى نَفْسِهِ الْعَنَتَ ( أي المشقة ) , قَدَّمَ التَّزْوِيجَ , لأَنَّهُ وَاجِبٌ عَلَيْهِ , وَلا غِنَى بِهِ عَنْهُ , فَهُوَ كَنَفَقَتِهِ , وَإِنْ لَمْ يَخَفْ , قَدَّمَ الْحَجَّ ; لأَنَّ النِّكَاحَ تَطَوُّعٌ , فَلا يُقَدَّمُ عَلَى الْحَجَّ الْوَاجِبِ اهـ . وانظر أيضاً : "المجموع" (7/71) للنووي . وسئل الشيخ ابن عثيمن رحمه الله : هل يجوز تأجيل الحج إلى ما بعد الزواج للمستطيع ، وذلك لما يقابل الشباب في هذا الزمن من المغريات والفتن صغيرة كانت أم كبيرة ؟ فأجاب : لا شك أن الزواج مع الشهوة والإلحاح أولى من الحج لأن الإنسان إذا كانت لديه شهوة ملحة فإن تزوجه حينئذٍ من ضروريات حياته ، فهو مثل الأكل والشرب ، ولهذا يجوز لمن احتاج إلى الزواج وليس عنده مال أن يدفع إليه من الزكاة ما يُزوج به ، كما يعطى الفقير ما يقتات به وما يلبسه ويستر به عورته من الزكاة . وعلى هذا فنقول : إنه إذا كان محتاجاً إلى النكاح فإنه يقدم النكاح على الحج لأن الله سبحانه وتعالى اشترط في وجوب الحج الاستطاعة فقال : ( وَلِلَّهِ عَلَى النَّاسِ حِجُّ الْبَيْتِ مَنْ اسْتَطَاعَ إِلَيْهِ سَبِيلا ) آل عمران / 97 . أما من كان شاباً ولا يهمه أن يتزوج هذا العام أو الذي بعده فإنه يقدم الحج لأنه ليس في ضرورة إلى تقديم النكاح اهـ فتاوى منار الإسلام (2/375) .
Ko'proq ko'rsatish ...
19 553
69
የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: ⓵⑤⑧⑨]👌

oEQQnkgxEIE9yvMTlYZiBpBULciLADi2SXOA4.mp4

18 197
5
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: ⓵⑤⑧⑧]👌

oAfmXSR4EpDHEedE2vFw3QdKBiC0IgBzr0gQ9A.mp4

19 795
19
የመልካም ሚስት መገለጫዎች ምን ምን ናቸው? መልሱን ከኢብኑ ባዝ!
20 750
89
አል-ኢማም ኢብኑ ባዝን አላህ ይዘንላቸው። የሚጎዳው የልብ መታወር እንጂ የዓይን መሸፈን አይደለም። በነገራችን ላይ ሳይንሱ እንደሚለው ከሆነ ዓይነ ስውራን ከኛ ዓይናችን ከሚያየው የበለጠ ምጡቅ አዕምሮ አላቸው። ምክንያቱም በዓይናቸው የሆነ ያልሆነውን እየተመለከቱ የአዕምሯቸውን working memory ስለማያጣብቡት፤ free ቦታ ያገኛሉ። ደግሞ ይሄን ስላችሁ ኢንቲሊጀንት እንሆናለን ብላችሁ ዓይናችሁን አጥፉ አሏችሁ¡ ባይሆን አላስፈላጊ ነገር እያያችሁ ስትሞሉት መልካም ነገር ማስቀመጫ እንዳታጡ ነው።

oYG9OqIRgFAXnE2e94LktefEM5CVLRAyGEeGAx.mp4

19 767
38
ረሒመሁ-ል'ሏህ ሸይኽ ሉሐይዳን!

oAPfeQNIDhzDvE8ggEfWAGg5dFcwDLGIV6cjEe.mp4

19 669
20
🤲🤲🤲

oAjBPDpfAEDRzAeMMngWQ8zJgCE81X6MWAMfI1.mp4

19 449
14
ንጹሕ ልብ፣ ደግነት፣ አላህን ብቻ ማምለክና አላህን ብቻ መፍራት! እስኪ በአላህ ይህን ደግ ግጥም በጥሞና አዳምጡት! ደስ የሚል ለስላሳ ድምፅ! ግሩም ትርጉምና ይዘት ያለው መልዕክት‼ ||

file

22 191
221
ከዱባይ መኪና የምታስገቡ ነጋዴም ሆናችሁ ለግል ያሰባችሁ፤ ከሰሞኑ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ከ3 አመት በፊት ከዱባይ ወደ አገር ውስጥ መኪና ባትሞክሩት የተሻለ ነው። ቀሪውን እናንተ ታውቃላችሁ! እስከዛሬ ስለተጫወታችሁብን ትንሽ ብትቀምሱ እንኳ ደግ ነበር፤ ስለምታሳዝኑኝ አንጀቴ ስለማይችል ነው መንገሬ¡
21 265
19
FYI: عبدالمجيد الزنداني دجال من الدجاجلة لفضيلة الشيخ الإمام مقبل بن هادي الوادعي رحمه الله

file

21 558
32
እነሆ ሁለቱ ሐረሞች ሑጃጆችን ከዛሬው ዕለት ጀምሮ ለመቀበል ዝግጁ ሆነዋል። Hajj season 1445/2024 begins today! The Two Holy Mosques and the Holy Sites in Makkah begin their preparations to welcome the Hujjaj for the Great Pilgrimage. ሁሉን ቻይ የሆነው አዛኙ አላህ ይወፍቀን!
21 669
12
ሒጃብን ከመልበስ ምን ከለከለሽ ? በኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ

ሒጃብን ከመልበስ ምን ከለከለሽ .mp3

20 575
136
የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: ⓵⑤⑧⑦]👌

398308305.mp4

21 889
10
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: ⓵⑤⑧⑥]👌

oEAKACKzoieQIIyEPKSPAiyCEBwRQWI0rmQoVw.mp4

21 530
21
21 020
41
ይነበብ‼ ======== በተለይም ነጋዴው ማኅበረሰብ አንብብ! * «የገቢና የወጪ ንግድን ጨምሮ በጅምላና በችርቻሮ የሚሳተፉ የውጭ ባለሀብቶች የሚያሟሉት የካፒታል መጠን ይፋ ተደረገ!» ይላል ከትናንት በፊት ሪፖርተር ጋዜጣ ይዞት የወጣው ዜና! ባይሆን በዋናነት ተጎጂ የሚሆኑት እነዚያ ከቻይና፣ ከዱባይ፣ ከቱርክ በርካሽ ዋጋ ያመጡትን እቃ በሁለትና ሦስት እጥፍ አትረፍው በብቸኝነት ሲሾፍሩን የነበሩ በጣት የሚቆጠሩ ፈላጭ ቆራጭ አምጪና ላኪዎች ናቸው። ተጠቃሚ እንኳ ልትጠቀም ትችላለህ። ለማንኛውም ኢኮኖሚስቶች ዕውቀት ተኮር አስተያየት ስጡበት። || ✍ ማንበብ ይጠቅማልና የካሳን አስተያየት ልጋብዛችሁ። «[ኢትዮጵያ] የውጭ ሀገር ዜጎች በገቢ ንግድ (import)፣ በጅምላና ችርቻሮ ንግድ እንዲሰማሩ የፈቀደች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር ሆናለች፣ አዋጁ ተዘጋጅቷል፣ መፅደቅ ብቻ ይቀረዋል። ይህ ምን ማለት እንደሆነ ለማስረዳት መሞከር ይቻል ይሆናል፣ የሚገባውን ግዝፈትና ትኩረት እንዲያገኝ ማድረግ ግን አይቻልም፣ ውጤቱ ከቃላት በላይ ነው፣ bullet point ለማስቀመጥ ልሞክር፣ ⏺️ከማዳበሪያና ነዳጅ በስተቀር የፈለጉትን ምርት ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፣ ⏺️ይህ አዋጅ በፀደቀ ማግስት ኢትዮጵያ የቻይና፣ የህንድ፣ የቱርክ ምርቶች ማራገፊያ ሀገር ትሆናለች፣ ⏺️የትኛውም ኢትዮጵያዊ ከውጭ ዜጎቹ ጋር ተወዳድሮ ገበያ ውስጥ መቆየት አይችልም፣ የራሳቸው መርከብና የጭነት አውሮፕላን ካላቸው ነጋዴዋች ጋር እንዴት ብሎ ነው የሚወዳደረው? አንድ ኢትዮጵያዊ ከውጭ አምጥቶ ትርፋን ጨምሮበት 500 ብር የሚሸጠውን ጅንስ ሱሪ አንድ ቻይናዊ አስመጭ በ100 ብር ገበያ ውስጥ ያቀርበዋል፣ እነሱ የደረሱበት economy of scale ላይ የተጠጋ የለም። ⏺️ አንድ ቻይናዊ፣ ህንዳዊ ወይም የቱርክ ሰው ከአንድ ኢትዮጵያዊ እኩል መብት ይኖረዋል፣ እንደውም የዲፕሎማቲክ ከለላ ስላለው የውጭ ዜጎቹ የተሻለ ጥበቃና መብት ይኖራቸዋል፣ ⏺️ የውጭ አስመጪዋቹ፣ ጅምላ አከፋፋዬችና ቸርቻሪዋች ቢያንስ አምስት የመሸጫ ሱቅ እንዲከፍቱ በአዋጅ ስለሚገደዱ በየህንፃው ላይ 2×2 ሱቅ ይዘው የሚቸረችሩ ዜጎች ሱቁን ዘግተው፣ መብራት አጥፍተው፣ ቁልፋን አስረክበው ላይመለሱ ወደቤታቸው እንዲገቡ ይገደዳሉ፣ ⏺️ አደጋው የጅምላና የችርቻሮ ንግድን ብቻ የሚያጠፋ ከመሰላችሁ ትሳሳታላችሁ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ሊመረት የሚችል ነገር አይኖርም፣ ጭቃ ጠፍጥፈህ ጀበና መስራት አትችልም፣ ለውቃቢ የሚስማማ ያሸበረቀ ጀበና በርካሽ ዋጋ ከቻይና ይመጣልሀል፣ ⏺️ በጀምላና የችርቻሮ ንግድ የሚሳተፋት የውጭ ባለብቶች ቁሳቁሱን የሚገዙት የውጭ ምንዛሬውን ከራሳቸው የውጭ አካውንት ከፍለው ነው፣ በሀገር ውስጥ በብር ይቀበላሉ፣ ብሩን ወደ ዶላር ቀይረው ትርፋቸውን ከሀገር የሚያወጡበት ቀጥተኛና ህጋዊ መንገድ እስካሁን የለም፣ ጥያቄው ከኢትዮጵያ ድንበር ውጭ የትም ቦታ ተቀባይነት የሌለውን ብር ምን ያደርጉታል? የሚል ነው፣ ከላይ ከተጠቀሰው አዋጅ ጋር አብሮ የሚፀድቅ ሌላ አዋጅ አለ፣ አዋጁ የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ ውስጥ ንብረት እንዲኖራቸው የሚፈቅድ ነው፣ ⏺️ የጅምላና በችርቻሮ ንግድ የተሰማሩት የውጭ ሀገር ዜጎች የሰበሰቡትን ብር ቤትና ቦታ ግዥ ላይ እንደሚያውሉት አይጠረጠርም፣ ቤትና ቦታ እንደ ኢትዮጵያ ባለ ሀገር ገንዘብን ከኢኮኖሚ አደጋ የምትከላከልበት መንገድ (hedge) ነው፣ ይህ የቤት ዋጋ ላይ የሚኖረውን ጫና አስታውሳችሁ የኢትዮጵያዊያኑን ዕጣ ፈንታ ገምቱት፣ ሲፈልጉ ንብረቱን ወደ ዶላር ቀይረው መውሰዱም አይከብዳቸውም፣ ⏺️ አንድ የቻይና ኩባንያ አምስት መርከብ ዕቃ አምጥቶ የኢኮኖሚ ጡንቻውን ማፈርጠም ይችላል፣ ኢኮኖሚው ላይ ቀላል የማይባል ተፅዕኖ የሚያስችል አቅም ያደረጃል፣ ⏺️ ብዙዋቻችሁ ግር ሊላችሁ እንደሚችል እገምታለሁ፣ የውጭ ባለሀብት [FDI] የሚፈለገው ገንዝበ ይዞ እንዲመጣ ነው፣ የጅምላ ነጋዴዋቹና ቸርቻሪሪዋቹ ደግሞ ሸቀጥ እንጂ ገንዘብ ይዘው አይመጡም፣ FDI የሚበረታታው ስራ ስለሚፈጥር ነው፣ ይህ (በተቃራኒው) በአስር ሚሊዬን የሚቆጠር ስራ በአንድ ሰሞን እምሽክ የሚያደርግ ነው፣ የታሰበው አንድ ነገር ነው፣ ⏺️ ኢትዮጵያዊያን አስምጭዋች የውጭ ምንዛሬ ከብሔራዊ ባንክ እያገኙ አይደለም፣ መንግስት የለውም፣ ያላቸው ብቸኛ አማራጭ ዶላር ከጥቁር ገበያ ገዝተው ዕቃዋችን ማስገባት ነው፣ የንግድ ዘርፋ ለውጭ ዜጎች ክፍት ከሆነ ኢትዮጵያዊያኑ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፣ ያ ደግሞ የዶላርን የጥቁር ገበያን ያዳክማል፣ የምንዛሬ መጠኑን ከፍ አድርገን ስናበቃ ዶላር እንዝቃለን የሚል ስንኩል ትንታኔ የካሊጉላ አማካሪዋች ሳይሰሩ አልቀሩም፣ እጅግ ከባድ ቀውስ እየጠመቁ መሆናቸው አልገባቸውም፣ …»
Ko'proq ko'rsatish ...
21 146
289
ካነበባችኋቸው መጽሐፍቶች ውስጥ የምንጊዜም ምርጥ የምትሏቸውንና የተመቿችሁን መጽሐፍቶች ጥቀሱ እስኪ?
17 663
9
ስሙ'ማ ቅመሞች… የአንብብ ትውልድ ሆነን ማንበብ ቢያቅተን ወደ ማቃጠል'ማ መሄድ የለብንም። ስለዚህ እነዚህን ስሜታዊ ወንድሞች ያቃጠሏቸውን መጽሐፍቶች በስፋት ታትመው በየቦታው እንዲነበቡ አናሰራጫቸውም? ለምሳሌ፦ የኢብኑ ሙነወርን አልበያን፣ ተውሒድ የሁለት ሃገር የስኬት ቁልፍ፣ ኢብኑ ተይሚያ የሱንናው አንበሳ፣ ከዐርሹ በላይ፤ እንዲሁም የሳዳት ከማልን አሏህን ማወቅ፣ መንዙማ እና ተውሒድ የሚሉትን መጽሐፍቶች በብዛት ለማሳተም ስፖንሰር ለመሆን ፈቃደኞች ካላችሁ አናግረናቸው በስፋት ታትመው ይሰራጫሉ። ዝግጁ?
20 734
35
21 399
30
ዛሬ የመጽሐፍ ቀን ነው አሉ መሰል። አላማዬ ስለቀኑ ሳይሆን ኢስላማዊ መጽሐፍ ስለሚያቃጥሉት ጉዶች ነው። ያቃጠሏቸውና ለማቃጠል ያዘጋጇቸው እንዲሁም በውሃ ሊዘፈዝፏቸው ያሰቧቸው መጽሐፍት "መንዙማ" የሚለው የሳዳት ከማል መፅሐፍ፣ "መውሊድ!፣ ኢብኑ ተይሚይያህ… ወዘተ የሚሉትን የኢብኑ ሙነወርን መጽሐፍቶች ነው። ለማቃጠል ያነሳሳቸው ከመጽሐፍቶቹ ጸሐፊዎች ጋር አለመግባባታቸው እንጂ መጽሐፍቶቹ ውስጥ ለመቃጠል የሚዳርግ መጥፎ መልዕክት ኖሮ አይደለም። ይህን የፈጸሙት ሰዎች ሙስሊሞች ናቸው። ከሙስሊምም አልፈው ብቸኛና እውነተኛ "ሰለፊይ" ነን ብለው የሚሞግቱ ናቸው። እኔ እነዚህን ፌክ ሰለፊያ ነው የምላቸው። እነዚህ ትክክለኛውን የሰለፎች ጎዳና እና ትክክለኛ ሰለፊዮችን የሚያሰድቡና መንገዱን ሌሎች እንዲጠሉት የሚያደርጉ፣ የሚያወሩትንና የሚተገብሩትን የማያውቁ ጉዶች እንጂ ሰለፊይ ናቸው ማለት ይከብደኛል። "መውሊድ" የሚለውን መጽሐፍ መውሊድ አክባሪ የሆኑ አሕባሾችና መሰል ቡድኖች እንኳ አቃጥለው ጀብዱ እንደሠራ ሰው አላሳዩንም። "መንዙማ" የሚለውን መጽሐፍ መንዙማ ወዳጆች አቃጥለው አላሳዩንም። ታዲያ መውሊድና መንዙማን እቃወማለሁ የሚል ሰው ደራሲውን በመጥላት ብቻ ተነሳስቶ መውሊድና መንዙማ የሚቃወሙ መጽሐፍትን ያቃጥላልን? እኔ እንዲህ አይነት ሰለፊይ ነኝ ባይ ሰምቼም አይቼም አላውቅም። እነዚህ ስሜታቸውን ያላሸነፉ በእውር ድንበር የሚጓዙ ያልተገራ አንደበት ያላቸው ናቸው፤ አላህ ይምራቸው። ምክንያቱም ባቃጠሏቸው መጽሐፍቶች ውስጥ ያለን ሐዲሥና ቁርኣን አቃጥለዋል። ሐሰን ታጁን ጠላሁ ብዬ የተረጎመውን የኢማሙ ነወዊይ ሪያዱ-ስ'ሷሊሒን ወይም የኢብኑ ሐጀርን ቡሉጙ-ል-መራም ወይም የሸይኽ ፈውዛንን አል-ኢርሻድ… በእሳት አላቃጥልም። በዚህ አካሄዳቸው ሳዳትና ኢብኑ ሙነወር አላህ አግርቶላቸው ቁርኣንን ቢተረጉሙም ሊያቃጥሉት ነው ማለት ነው። አሁን ይሄ እብደት ምን አይነት ሰለፊይነት ነው? ወላሂ ትክክለኛ የደጋግ ሰለፎች መንገድ ከነዚህ ስሜት ከጋለባቸው ሰዎች አካሄድ የጠራ ነው። አላህ ወደ ትክክለኛው ሐዲድ ይመልሳቸው። ሚዛናዊነትን ያላብሳቸው፣ ካሉበት ጡዘትና እልህ ያብርዳቸው። እኛንም ወደ ቀጥተኛው ጎዳና ይምራን። ||
Ko'proq ko'rsatish ...
21 829
76
በሐቅ ላይ ከሆነ መቀራረብና አንድነት ሸሪዓው የሚደግፈውና የሚበረታታ ነው። በሱንና ኢኒስቲትዩት ስር የሚገኘው የሱንና ኢኒስቲትዩት መስራችና ዋና ፕሬዝደንት ሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን (ዶ/ር) ተቋማቸው በሰሞኑ ያዘጋጀውን የምሩቃን ኮንፈረንስ የመዝጊያ ፕሮግራም ከኢብን መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ጋር የልምድ ልዉዉጥ ያደረጉ ሲሆን አብረዉ መሥራት የሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ ዉይይት አድርገዋል። ፕሬዝዳንቱ "እዉቀትን በማስፋፋት ዘርፍ ኢስለምን ለማገልገል  እየሰራን እንደመሆኑ ይህን አላማችንን ከግብ ለማድረስ ከመሰል ተቋማት ጋር ህብረት እንደሚያሻ እናምናለን!" ብለዋል። ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ በበኩላቸው "የአንድነት መገለጫ በአንድ ተቋም ዉስጥ በመሰብሰብ ብቻ አለመሆኑን ገልፀው ከዚህ በፊት ኢስላምን በማገልገል ረገድ ከፍተኛ ሚና ሲጫወቱ እንደ ነበረዉ ሁሉ ወደፊት እንደ ተቋም ተጋግዘን  ሕያዉ እንደምናደርግ ተስፋ አለኝ!" ሲሉ ገልፀዋል። ጥሩ ነው! አሁንም ውስጣዊና ውጫዊ መከፋፈሎች ቀርተው፤ ሁሉም ኢጎውንና ዱንያዊ ነገርን ወደ ጎን በመተው ነፍስያውን አሸንፎ በሰለፎች ጎዳና ላይ አንድ ቢሆን በአላህ ፈቃድ ብዙ መጥቀምና መጠቀም እንችላለን። ♠ ©: Photo Crdeit: ዳዕዋ ቲቪ ||
Ko'proq ko'rsatish ...
19 349
53
ገራሚ ታሪክ‼ ========== (በተለይ ወላጆች ይህን ሸይኽ ፕሮፌሰር ዐብዱ-ር'ረዛቅ አል-በድር የሚነግሩንን ታሪክ በደንብ አዳምጡት!) || ✍ ከሆነ ሃገር ለዑምራ የመጣ አንድ ሰው ጠዋፉን ጨርሶ በካዕባ ዙሪያ ሐጀረ-ል-አስወድ አካባቢ ዱዓእ እያደረገ ነበር። አስተውላችሁ ከሆነ ሐጀረ-ል-አስወድ ጋር ከፍተኛ የህዝብ መገፋፋት ስላለ እጃቸውን በሆነ መያዣ ላይ አስደግፈው የሚቆሙ ወታደሮች አሉ። በዚያ አጋጣሚ እዛ ጋ ቆሞ የነበረው ወታደር ገጠመኙን እንዲህ ይተርከዋል። "በጣም ለቅሶው የበረታ ሰው ድምፅ ሰማሁ። ምንድን ነው ብዬ ዘወር ሲል አንድ ሰው ከባድ ለቅሶ እያለቀሰ አላህን ይለምናል። ለቅሶው ስለሳበኝ ምን እያለ ይሆን ብዬ ሳዳምጠው በዱዓቅ መሃል «ያ ረብ! (ጌታዬ ሆይ!) ሰዎች ልጆች አሏቸው። እኔ ልጅ የለኝም!» ይህን ቃል እየደጋገመ በጣም በብርቱው ያለቅሳል። ሲደጋግመው ስለነበር በጆሮዬ ይህንን ድምፁን ሸምደጀዋለሁ። ከዚያም ከ18 ወይም 20 አመታት በኋላ በዚሁ በሐጀረ-ል-አስወድ ቦታ ሳለሁ፤ ራሱኑ ያኔ የሰማሁትን ድምፅ ሰማሁ። ግለሰቡን አስታወስኩና ፊቱን ለመመልከት ዞርኩ። ራሱ የያኔው ሰውዬ ነበር። ልክ እንደዛው በብርቱው እያለቀሰ አላህን ይለምናል። ምንድን ይሆን የሚለምነው ብዬ ማዳመጥ ጀመርኩ። "ያ ረቢ! (ጌታዬ ሆይ!) ይህንን ልጅ አጥፋልኝ!" ይላል። እዛ ዱዓእ ማድረጊያው ዘንድ ሆኖ ልጄን አጥፋልኝ እያለ አላህን ይማፀናል። ከቆምኩበት ቦታ ወረድኩና ከዚያ ከካዕባው ዙሪያ ይዠው ወደ ውጭ (ወደ ዳር) ወጣን። እንዲህም አልኩት፦ «ከዛሬ 18 አመታት በፊት በዚሁ ቦታ አላህ ልጅ እንዲሰጥህ ስትለምን የነበርከው ሰው አይደለህምን?» «አዎ!» አለኝ። እኔም «አንተ በዚህ ቦታ ልጅህን ሁለት ጊዜ በድለኸዋል። የመጀመሪያው በደልህ፤ እኔ ያኔ ሰምቸሃለሁ፣ ዱዓህን ሐፍዤዋለሁ፣ ዝም ብለህ "ልጅ ስጠኝ!" ነበር እንጂ ስትል የነበረው "መልካም ልጅ ስጠኝ!" አልነበረም ያልከው። አሁን ደግሞ ሁለተኛው በደልህ ራሱ ቦታ መጥተህ አላህ እንዲያጠፋው ትለምናለህ። በመጀመሪያውም በመጨረሻውም አላሳመርክለትም። አሁንም ወደዛው ቦታ ተመለስና አላህ እንዲመራው ዱዓእ አድርግለት። ልክ እንደበፊቱ ራሱኑ ለቅሶ እያለቀስክ ቀልቡን እንዲመራለት ዱዓእ አድርግለት። ይህን አስረዳሁትና ይዤው መልሼ ወደዛው ቦታ ወሰድኩት።  ከዚያም ለቅሶውን ጀመረና ለልጁ ሂዳያ እንዲሰጠው አላህን መለመን ጀመረ። ከዚያም ከአንድ አመት በኋላ ከልጁ ጋር መጣ። ሰላምታ አቀረቡልኝና ለልጁ ታሪክህን ንገረው አለው። ከዚያም ልጁ መሃላ እየማለ፤ ያኔ አባቴ በዚያ ቦታ እያለቀሰ አላህ ሂዳያ እንዲሰጠኝ በሚማፀንበት ሰዓት ተነስቼ ውዱእ አድርጌ ሶላት ጀመርኩ። ከዚያም በኋላ ሁኔታዬ ተስተካከለ። በብዙ መልኩ ወላጆቹን አዛ የሚያደርግና በሐራም ነገሮች ላይ ሲያሳልፍ የነበረ ልጅ ነው።» ከዚህ የምንማረው፤ ወላጆች አላህ ልጅ እንዲሰጣችሁ ስትፈልጉ፣ ልጅ ብቻ ሳይሆን ማንኛውንም ነገር ስትጠይቁት መልካሙን (ሷሊሑን) ጠይቁት። አንዳንዱ ፊትና ይሆናል። አይበለውና መጥፎ ካጋጠማችሁ ለውሳኔ ቸኩላችሁ በንደት አትራገሙ፤ በምትራገሙበት ምትክ አላህ እንዲያስተካክለው ዱዓእ ብታደርጉበት የበለጠ ነው። አላህ መልካምን ሁሉ ይወፍቀን። ||
Ko'proq ko'rsatish ...
23 215
253
ይህንን ጠቃሚ ገጠመኝ አዳምጡት። ||

o0Ff0DTXeAXAF89QEuO77G4EkC9fEtdwRNeAID.mp4

20 340
92
የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: ⓵⑤⑧⑤]👌

file

20 621
12
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: ⓵⑤⑧④]👌

oAfmXSR4EpDHEedE2vFw3QdKBiC0IgBzr0gQ9A.mp4

21 046
13
ይደመጥ‼ ሙስሊምነት እና አማራነት ያላዳናቸው የጎንደር (እንፍራዝ ከተማ አካባቢ ሙስሊሞች‼ ©: Harun media ሃሩን ሚዲያ

file

20 071
112
«አምና ስለምንሽ ፥ ልጅ ነህ ብለሽኛል፣ ዘንድሮ ተራዬን ፥ አርጅተሽብኛል።» አለ አሉ አንዱ እረኛ!
19 225
76
የሆነን ነገር አታሳከውም ብለው ንቀውህ እገዛቸውን ስትጠይቃቸው ጀርባቸውን ያዞሩብህ ሰዎች፤ አላህ መንገዱን አግርቶልህ ካሳከኸው በኋላ ስትለምናቸው መንገድ ቀይረው እንዳልሸሹ ሁሉ ሳትጠራቸው ሳያፍሩ የሚመጡት ነገርስ? አንተም ትዞርባቸዋለህ ወይንስ ታስተናግዳቸዋለህ?
19 775
45
19 920
3
መጅሊስና የሐጅ ጉዳይ‼ ================== ✍ በቅድሚያ የዘንድሮው የሐጅ ምዝገባ ቀደም ብሎ ተጀምሮ ስለነበር በመሃል ተጠናቋል ብለው ቢያሳውቁም፤ ተጨማሪ ኮታዎች ስላሉ አሁንም መመዝገብ እንደምትችሉ አሳውቀዋልና፤ ምናልባት ዘንድሮ ሐጅ የማድረግ ሙራዱ ኖሯችሁ ተዘግቷል የሚለውን ሰምታችሁ ከሆነ መከፈቱን ላልሰማችሁ ላሳውቃችሁ እወዳለሁ። √ ወደ ዋናው ነጥቤ ስመጣ፤ መጅሊስ በባለፈው አመትና ከዚያም በፊት በነበሩ አመታት የነበሩ ክፍተቶችን ካላስተካከለ ምዝገባውን ቢያቆመው ይሻላል። ከበፊቶቹ አመታት ይልቅ የባለፈው አመት በርካታ መሻሻሎች እንደነበሩት በፊት ከነበሩ ወንድሞች አንደበት ሰምቻለሁ። ግን ይሄን ከበፊቱ አመታት ተሻሽሏል የተባለውን ራሴ በብረት ዓይኔ ስላየሁት፤ ያለበትን ክፍተት ስታዘብ የበፊቶቹ ምን ያክል ክፍተት ቢኖርባቸው ነው ብያለሁ። ለማንኛውም፦ አንድ ሰው ሐጅ የሚሄደው በዋናነት ለደርሶ መልስ ወይም ምግቡና መኝታው እንዲመቻችለት ሳይሆን ዒባዳውን ሸሪዓው በሚያዘው መልኩ ፈፅሞ ልክ እናቱ እንደወለደችው ህፃን ከወንጀሉ ታጥቦ መምጣት ነው አይደል? በዚህ ከተስማማን ዒባዳውን በትክክል ይፈፅም ዘንድ የሚያግዘው ነገር መሟላት አለበት። ምግብና መኝታ እንዲሁም ትራንስፖርት አይመቻች አላልኩም። ግን መጅሊስ በዚህ አመት ቁጥር አንድ ማስተካከል ያለበት ጉዳይ የአስተባባሪዎችን ጉዳይ ነው። √ በየ አመቱ አስተባባሪ ተብለው በዘመድ አዝማድ የሚሄዱ አሉ። ባለፈ አመት ግን እንደዛ ነገር አለ ብዬ ባልደፍርም፤ ለስሙ አስተባባሪ ተብለው ተልከዋል፤ ግን ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም። አንዳንድ ወንድሞች ከሚጠበቅባቸውም ኃላፊነት በላይ ሠርተዋል። ግን ብዙዎቹ እንዳውም ሌላ አስተባባሪ ይፈልጋሉ። የመጡበትን ኃላፊነት ዘንግተው በራሳቸው ሐጃ ተጠምደው ነበር። አንዱ እኛ ጎን ነው ተኝቶ ያሳለፈው። ቢያንስ እንኳን ሌላ ድንኳን ድረስ ሊንቀሳቀስ፤ የኛን ድንኳን እንኳ መኻደም አልቻለም። እንኳን የሌሎች ሃገራት፤ የአፍሪካ ሃገራትን እንኳ ብናይ፤ ያላቸው መናበብ አስደማሚ ነው። ገና መዲና ሲደርሱ ጀምረው ረውዳን መግባትን ጨምሮ ወደ መካ ሂደው ዑምራቸውን እስኪፈፅሙ፣ ከዚያም የሐጅ ተግባር ሲጀመር ወደ ሚና ሂደው አድረው ወደ ዐረፋ ሲሄዱ፣ ከዚያም ሙዝደሊፋ አድረው ጀመራታቸውን ወርውረው ዳግም ወደ ሚና ተመልሰው ቀናቶችን ጨርሰው ሃገራቸው እስኪገቡ ድረስ በአንድ ወይም ሁለት አስተባባሪዎች መሪነት በቡድን በቡድን ሁነው ሁሉን ዒባዳህ ተናበው ይፈፅማሉ። የኛ ሰው ግን ገና ወደ ሚና ሂዶ እንዳደረ ከፊሉ መንገድ ጠፍቶት ዐረፋ ሊያልፈው ይችላል፣ ዐረፋህ ገብቶም ከክልሉ ውጭ ሆኖ ባለማወቅ ያሳልፋል፣ ከፊሉ ከሙዝደሊፋ ወደ ሚና ሲሄድ ይጠፋል፣ ከፊሉ ጀመራት ወርውሮ ሲመለስ ይጠፋል፣ አንዳንዱ ለሱቅ ወጥቶ ራሱ የሚና ድንኳኖች ስለሚያሳስቱ በዛው ይጠፋል። እንዳይጠይቁ የቋንቋ ችግር አለ። አለፍ ሲልም ብዛት ከገጠራማው ክፍል የሚመጡ አባቶችና እናቶች (በተለይም ከኦሮሚያና ሱማሊያ ክልሎች) ስላሉ፤ map እንኳ ተጠቅመው መመለስ አይችሉም። ስልክም በብዛት ባትሪ ይዘጋል። ድንኳናቸውን ለመፈለግ የሚያባክኑት ጉልበት ስለሚያደክማቸው ሐጁን ተማረው ነው የሚፈፅሙት። ዳግም የመሄድ ሞራል ራሱ የላቸውም። በርግጥ ብዙዎች ድንኳናቸውን ሲያገኙ ድካማቸውን ቢረሱትም! √ ስለዚህ፦ መጅሊስ ዘንድሮ ሁሉንም ሑጃጅ ማስተናገድ የሚችሉ አስተባባሪዎችን ይመድብ። አስቀድሞ አደረጃጀት ይፍጠር፣ ስልጠና ይስጥ፣ ኃላፊነቱን በማይወጣ ላይ የሚወሰድ እርምጃ ያስቀምጥ፣ አንድ አስተባባሪ በስሩ ምን ያክል ሰዎችን እንደሚያስተባብር ይመደብ። ከዚያም ከ ሀ–ፐ ኃላፊነቱን በአግባቡ ይወጣ። የአስተባባሪዎች አስተባባሪም ይኑር። ህዝቡ በራሱ እንደት የሐጅ ጊዜውን ከአስተባባሪዎች ጋር ማሳለፍ እንዳለበት በየመመዝገቢያ ጣቢያው ስልጠና ይሰጠው፤ ተጨማሪ የሐጅ አፈፃፀም ኮርሶችም ይሰጡት። ባይሆን አንዳንድ ሰዎች ልምድ አለን ካሉና በራሳችን እንፈፅማለን ካሉ መብታቸው ነው፤ አብረው ማስተባበር ካልፈለጉ ቢሳሳቱ እንኳ ኃላፊነቱን ራሳቸው ይወስዳሉ። መጅሊስ ይህንን ካላደረገ፤ ውጭ ሃገር ሆናችሁም ሆነ ከዚሁ ከሃገር ውስጥ ወላጃችሁን ሐጅ ለማስደረግ ገንዘብ ሰጥታችሁ አስመዝግባችሁት የምትልኩ ከሆነ፤ መጅሊስ ይህን አሠራር መዘርጋቱን አጣሩና ካልዘረጋ ወይም ለመዘርጋት ፈቃደኛ ካልሆነ ያልከፈላችሁ አትክፈሉ፣ የከፈላችሁ ተቀበሉ። ዝም ብሎ በአውሮፕላን ደርሶ መልስ ነው የሚሆንባቸው። ገንዘብ አውጥታችሁ፣ ልፋቱ ሳይቀርላችሁ ተቀባይ ካልሆነ ምን ዋጋ አለው! መጅሊስ አስተባባሪ በአግባቡ ካልመደበና ራሳችሁን ችላችሁ መፈፀም ካልቻላችሁ ወይም የሚያግዛችሁ አብሯችሁ የሚሄድ ቡድን ወይም ጓደኛ ከሌለ፤ ይቅርባችሁ። ዘንድሮ ለናንተም ለወላጃችሁም መክፈል ካልቻላችሁ፤ ተፍ ተፍ በሉና ቀጣይ ወላችሁን ኢንሻ አላህ እናንተው ይዛችሁት ትሄዳላችሁ። ልብ በሉ! 200 ወይም 300 አስተባባሪ መመደብ ብቻውን ዋጋ የለውም። ለመመደብማ በየአመቱ ተደርጓል። ግን ኃላፊነታቸውን የሚወጡ መሆን አለባቸው። ማን በማን ስር የሚለው አደረጃጀት ገና ከዚሁ ተመድቦና ታውቆ መጨረስ አለበት። አላህ ይቀበላችሁ! ||
Ko'proq ko'rsatish ...
22 836
38
አንዱ ሙነሺድ «ያ ረሱለላሊ ባንቱ ነው ማማሬ፣ ባንቱ ነው መዋቤ!» አለ። ሰውዬውም ቀበል አደረጉና «እንዴት አያምርብህ፣ መተዳደሪያ አድርገሃቸው!» ኧረ! ተው ክፉ አታናግሩን! 5 ኪሎ ቦርጭ ተሸክሞ "በአንቱ ናፍቆት ከሳሁ ገረጣሁ!" ይላል! ቢያንስ በሚመስል ነገር እንኳ ዋሹን!
22 861
83
② ምክሮች ለ② ሰዎች‼ ================== ①) በቢዝነስ ጉዳይ፦ አንተ ማሻ አላህ ጎበዝ ተማሪ ነገር ነህ፣ ጥሩ ትሠራለህ። ዩኒቨርስቲ ገብረህ ድግሪህን ጨርሰሃል፣ ከዚያም ማስተርስና ፒኤችዲ እያልክ ሂደሃል፣ ወይም ስፔሻላይዝ ካደረግክ በኋላ ሰብ ስፔሻሊስት ሆነሃል። ግን ይህን ሁሉ አድርገህ ስትመለስ የምትቀጠረው ያኔ 10ኛ ክፍል ላይ ማትሪክ ወድቆ ውጤት ሳይመጣለት ሲቀር ሙያና ቴክኒክ ገብቶ ተምሮ ከተመረቀ በኋላ ባቋቋመው ተቋም ውስጥ ነው። ሰብ ስፔሻሊስት ሆነህ ወጥተህ ተቀጥረህ የምትሠራው ጭራሽ ሜዲስን እንኳ ሳይገባ ገና ከድፕሎማ ጀምሮ ተምሮ ራሱን አስተዳድጎ በከፈተው የGP ክሊኒክ ውስጥ ነው። ዕውቀትህ ከርሱ በላይ፤ ግን ገቢህ ከርሱ በታች። የተማርከው አካዳሚ ለአኺራህ ጥያቄ መልስ የሚሆን ሸሪዓዊ ነገር ሳይሆን ዱንያህን በአግባቡ ልትጠቀምበትና በርሱም አኺራህን ልትሻበት ነው። ስለዚህ የልፋትህን ማግኘት አለብህ። መፍትሄ፦ ቢያንስ ድግሪህን እንደያዝክ በፊልድህ የሚሄድ ቢዝነስ ጀምር። የተወሰኑ አመታት እርሱን ቢዝነስ አጠናክረኸው በሁለት እግሩ ሲቆምና ከአንተ ትከሻ ሲወርድ ሌላ ባለሙያ ቀጥረህ አንተ ትምህርትህን ቀጥል፤ በጎድንም በፓርት ታይም ሥራ። ያኔ እየተማርከው ያለው ዕውቀት ተቋምህንም ያጠናክረዋል፤ ትምህርቱም ቢዝበሱም አልቀረም። ተመርቀህ ጸጉርህን መልጠህ ስትመጣ መግቢያ አታጣም፤ ቀድመህ የሰራኸው ቤት ስላለ። * ②) በትዳር ጉዳይ፦ ገና ሃይስኩልና ካምፓስ ተማሪ እያለሽ የትዳር ጥያቄ ሲቀርብልሽ «ቆይ ትምህርቴን ልጨርስ!» እያልሽ ስትመልሺ ነበር። ወላጆችም ልጃችሁን ስትጠየቁ «ገንዘብ (ቤትና መኪና) የሌለው መናጢ ድሃ ነው!» ከሚለው ባሻገር እነዚህን ያሟላ ቢመጣ እንኳ «ቆይ! ተምራ ትጨርስ!» እያላችሁ ስንትና ስንት ሰዎችን ስትመልሱ ነበር። ድግሪዋን ስትጨርስ 23ና 24 አመት አካባቢ ይሆናታል። ሥራ ፍለጋ ይባልና በትንሹ አንድ አመት ጫማዋ እስኪገረጣ ልትሯሯጥ ትችላለች። ሥራው ከተገኘ በኋላ አንድ ሦስት አመታት ያልፋል። እነዚያ ለትዳር የሚጠይቁ ሰዎች ቁጥር ባልተጠበቀ ሁኔታ እየቀነሱ ይመጣሉ። እንዲህ እንዲህ ይልና 30ዎቹ መግባት ይጀምራሉ። ያኔ ጭራሽ ጠያቂም ይጠፋል። ከማንም በላይ መከረኛዋ እናት በሯን ዘግታ ማልቀስ ትጀምራለች። ልጅም ወላጅም ያኔ ከእንቅልፋቸው መንቃት ይጀምራሉ፤ ግን ምን ዋጋ አለው! ብዙውን ነገር አሳልፈውታል። ያኔ ለሁለተኛም ሆነ ለሦስተኛ ብቻ በተገኘ ወደሚል ስሜት ይመጣል። አለፍ ሲልም የማይመጥን ወንድም ቢሆን ችግር የለም ወደሚል ተናዙል ይወረዳል። እነዚያ ከአንድ ገፅ በላይ የሚሆኑ የሚደረደሩ መስፈርቶች ወደ አንድ ሃረግ ይወርዳሉ። 40 ሲገባ አንድ ቃል ብቻ መሆናቸው አልቀረም። ምን የመሰለ መልክና ቁንጅና፣ ምን የመሰለ ዲንና ጥንካሬ፣ ምን የመሰለ ውብ ቤተሰብና ዘር እያለ፤ ምን የመሰለችዋን ልጅ ጊዜዋን አሳለፉባት። አይበለውና ተስፋ መቁረጥ ከተደረሰ ወደ በቀላሉ ወደ ሐራም ግንኙነቶች፣ አላህ ይጠብቀንና ከካ'ፊ'ርም ጋር ቢሆን መጃጃል ይመጣል። መፍትሄ፥ ገና ሃይስኩል እያለሽም ይሁን ግቢ ላይ እያለሽ ሸሪዓው ባዘዘው መልኩ የሚሆንሽ የትዳር አጋር ከተገኘ በጊዜ ተሰተሪ። በዚህ ወቅት አማርጠሽ የማግባት ሰፊ እድል አለሽ። ማግባት ትምህርትን አያስቋርጥም። ካገባሽ በኋላ ያስተምርሽ። ካላስተማረሽ ንገሪኝ! ወላጆችም ኋላ ከመጨነቅ በዚህ ወቅት ብዙም ሳታካብዱ በሐላሉ ሰትሯቸው። ኋላ ለናንተም ስቃይና ጭንቀት ነው። በመጨረሻም፦ ምንም ይሁን ምን፤ ያለነው በጠፊዋ ዓለም በዱንያ ላይ ነውና ለሁሉም ነገር በሐላሉ ሰበብ ማድረስ፣ አላህን መፍራትና እርሱን መለመን፣ ጉዳይን ወደርሱ ማስጠጋትና በርን ዘግቶ ከርሱ ጋር ማንሾካሾክ መረሳት የለበትም። ያኔ አይሆንም ብለን ያሰብነውን ሁሉ አድርጎት እናገኘዋለን። ሆኖም ግን መዳረሻችን አኺራህ ነውና ለሁሉም ነገር ሶብር ማድረግ፣ ለሙእሚን ከዱንያ ይልቅ አኺራህ የተሻለ መኖሪያው መሆኑን ማሰብ፣ ዱንያ ሁሉ ነገሯ ፈተና የሆነች መሆኗን ማወቅ ያስፈልጋል። አላህ በሪዝቁም ይሁን በትዳር በኩል መልካሙን ይወፍቃችሁ። ♠ ወንድማችሁ፦ ሙራድ ታደሰ ========= ሸዋል 13, 1445 H.C. ሚያዚያ 14, 2016 E.C አፕሪል 22, 2024 G.C. ||
Ko'proq ko'rsatish ...
25 008
239
🎧

አፀያፊው ዝሙትን አትቅረቡ.mp3

22 079
111
«ዚና ሲቀል → ኒካሕ ይከብዳል‼» ወሏሁ-ል-ሙስተዓን!
22 767
25
﴿ثلاثةٌ حقٌّ على اللهِ عونُهم: المجاهِدُ في سَبيلِ اللهِ، والمكاتَبُ الَّذي يريدُ الأداءَ، والنّاكِحُ الَّذي يُريدُ العفافَ﴾
23 359
65
እስኪ ይህን ጽሑፍ አንብቡት፦ «ዛሬ ልጄን ለማሳከም ወደ አንድ ሀኪም ቤት አመራሁኝ ። የላብራቶሪ ውጤት እስኪደርስ ድረስ ዶክተሩ አንድ የማወያይህ ነገር አለ ብሎኝ ቁጭ አልኩኝ ። አንዲህም አለኝ አንድ የሚያሳስበኝ ነገር አለ ይኸውም የሙስሊም ሴት እህቶቻችን ጉዳይ ነው አለኝ ። በመቀጠልም እኔ ከሞያዪ አንፃር በተለያዮ ሀኪም ቤቶች ላይ እሰራለው በየቦታው የሚያጋጥመኝ አንድ ችግር አለ ይኸውም የሴቶች ውርጃ ነው አለኝ ። የተለያዮ ሴቶች ለማስወረድ ይመጣሉ ለምን የሚል ጥያቄ ሳነሳ አብዛኛው መልሳቸው ቤተሰብ አላወቀም የሚል ነው ይህ ማለት ደግሞ ያለ ኒካህ የተረገዘ የዝሙት ልጅ በመሆኑ ነው ። እኛ ጉዳዮ ከተፈፀመ በኃላም ቢሆን የተቻለንን ምክር እንለግሳቸዋለን ነገር ግን በዚህ ዙሪያ የሚሰጥ ትምህርት አሊሞች ፣ ዱአቶች ዘንድ አናሳ ነው ለምን በዚህ ላይ አትሰሩም ፣ ለምን እህቶቻችንን አታነቁም ፣ …  ወቀሳውን ጠበቅ እያደረገው መጣ ።   ከመፍቴዎቹ መሀከል አንዱ ሁለት ሶስት አራት ማግባት ነው ስለዚህም የሚሰጥ ትምህርት የለም ቆይ ግን ለምንድን ነው?  እያለ ወላሂ ብዙ ወሳኝ ነጥቦችንና ገጠሞቹን አወራኝ   በበኩሌ ያለንበት ደካማ ጎኖቹን እያነሳ እያወራኝ ስለነበር እውነት ነው እያልኩኝ ተቀበልኩኝ እላችኃለው ከዚህ በፊትም አንድ ዶክተር ይህን ጉዳይ ቦታውን ሁሉ እየጠቀሰ ነግሮኛል አንዳንዶች እንደውም ይህን ተግባር/ማስወረድን/ ከቢዝነስ አንፃር ብቻ በመመልከት የተለያዮ ክሊኒኮችን በቦታው እንደሚከፍቱ ነግሮኛል ስለዚህ ወንድሞቼ እንዲሁም ኡስታዞች በዚህ ዙሪያ ለየት ያለ ትኩረት ተሰጥቶት በዚህ ርዕስ ላይ ዘመቻ ቢደረግ መልካም ነው።» ©: ኡስታዝ ዳውድ ያሲን
Ko'proq ko'rsatish ...
21 491
107
የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: ⓵⑤⑧③]👌

file

21 383
9
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: ⓵⑤⑧②]👌

oQEPwABPbEzjiYSeqqvAI98MzwnZvlCXAiAOjI.mp4

21 295
13
ሐቀን!
20 519
20
Oxirgi yangilanish: 11.07.23
Privacy Policy Telemetrio