Best analytics service

Add your telegram channel for

  • get advanced analytics
  • get more advertisers
  • find out the gender of subscriber
Category
Channel location and language

audience statistics EthioipaNews

⚠️ Warning: Many users report that this account impersonates a famous person or organisation. 
34 731-27
~16 743
~0
48.17%
Telegram general rating
Globally
26 879place
of 78 777
204place
of 396
In category
1 608place
of 3 169

Subscribers gender

Find out how many male and female subscibers you have on the channel.
?%
?%

Audience language

Find out the distribution of channel subscribers by language
Russian?%English?%Arabic?%
Subscribers count
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

User lifetime on the channel

Find out how long subscribers stay on the channel.
Up to a week?%Old Timers?%Up to a month?%
Subscribers gain
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

Hourly Audience Growth

    Data loading is in progress

    Time
    Growth
    Total
    Events
    Reposts
    Mentions
    Posts
    Since the beginning of the war, more than 2000 civilians have been killed by Russian missiles, according to official data. Help us protect Ukrainians from missiles - provide max military assisstance to Ukraine #Ukraine. #StandWithUkraine
    16 057
    24
    የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተወያዩ! የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡በውይይታቸውም÷ በሀገራቱ የድንበር አዋሳኝና ከቀጠናው የሰላምና ፀጥታ ሁኔታ አንፃር አብረው መስራት በሚገባቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ መክረው መግባባት ላይ መድረሳቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡የኤርትራ የጦር ጀነራሎችና ከፍተኛ መኮንኖች ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት እያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡ @EthioipaNews
    13 842
    3
    የአድማስ ሎተሪ እጣ መደብ ቁጥር 009 አሸናፊ እጣ ቁጥሮች ይፋ ሆነዋል!! 9ኛው ዙር የአድማስ ሎተሪ የሽልማት መጠን ወደ 3 ሚሊየን ከፍ ብሎ በትናንትናው እለት እጣው ወጥቷል። 1ኛ እጣ ሶስት ሚሊየን ብር የሚያስገኘው እጣ ቁጥር 0091844739 2ኛ እጣ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሚያስገኘው እጣ ቁጥር 0090540530 3ኛ እጣ 8 መቶ ሺሕ ብር አሸናፊ እጣ ቁጥር 0092021699 4ኛ እጣ 4 መቶ ሺሕ ብር አሸናፊ እጣ ቁጥር 0090412316 5ኛ እጣ 2 መቶ 50 ሺሕ ብር አሸናፊ ቁጥር 0092260801 6ኛ እጣ 1 መቶ 50 ሺሕ ብር አሸናፊ እጣ ቁጥር 0090567816 7ኛ እጣ 1 መቶ ሺሕ ብር አሸናፊ እጣ ቁጥር 0091588711 8ኛ እጣ 50 ሺሕ ብር አሸናፊ እጣ ቁጥር 0090361764 9ኛ እጣ 30 ሺሕ ብር አሸናፊ እጣ ቁጥር 0090947970 10ኛ እጣ 25 ሺሕ ብር አሸናፊ ቁጥር 0090876951 በመሆን ወጥቷል፡፡ @EthioipaNews
    Show more ...
    12 458
    9
    የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ድረስ ባለበት ይቀጥላል‼️ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በመጋቢት ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ እንዲቀጥል ተወሰነ። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለኢቢሲ በላከው መግለጫ፣ እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ የመሸጫ ዋጋ በመጋቢት ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ እንዲቀጥል ተወስኗል። @EthioipaNews
    9 508
    7
    ነዳጅ ላኪ ሀገራት አቅርቦት ለመቀነስ መወሰናቸውን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል! የዓለማችን ግዙፍ ነዳጅ ላኪ ሀገራት ያልተጠበቀ የምርት ቅነሳን ይፋ ካደረጉ በኋላ የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል። ያልተጣራ ድፍድፍ ነዳጅ በበርሚል ከ5 ዶላር ወይም ከ7 በመቶ በላይ ጭማሪ አሳይቷል። ይህንኑ ተከትሎ ያልተጣራ ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል ከ80 ዶላር ወደ 85 ዶላር ከፍ ብሏል። ጭማሪው የተከሰተው ሳዑዲ አረቢያ፣ ኢራቅ እና በርካታ የባህረ ሰላጤው ሀገራት በቀን ከአንድ ሚሊዮን በርሜል በላይ ከምርታቸው ላይ እየቀነሱ መሆናቸውን ተከትሎ ነው። ሩሲያ ዩክሬንን በወረረችበት ወቅት የነዳጅ ዋጋ ጨምሮ የነበሩ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ግጭቱ ከመቀስቀሱ በፊት ወደነበረበት ተመልሷል። ይሁን እንጂ አሜሪካ የነዳጅ ዋጋን ዝቅ ለማድረግ አምራቾች ምርታቸውን እንዲጨምሩ ስትጠይቅ ቆይታለች። ባለፈው አመት ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መደረጉ በመሰረታዊ ምርቶች ላይ ግሽበት እንዲፈጠር ማድረጉ ይታወሳል።የዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ የጸጥታ ምክር ቤት ቃል አቀባይ ስለ ቅርብ ጊዜ የምርት ቅነሳ በሰጡት መግለጫ ቅነሳው በአሁኑ ጊዜ ጠቃሚ ነው ብለን አናምንም ይህንንም ግልፅ አድርገናል ብለዋል። የምርት ቅነሳው በኦፔክ የነዳጅ ዘይት አምራቾች አባላት ሀገራት እየተደረገ ይገኛል። የኦፔክ አባል ሀገራት ከዓለም ድፍድፍ ዘይት ምርት 40 በመቶውን ድርሻ ይይዛሉ። ሳዑዲ አረቢያ በቀን 500,000 ፣ ኢራቅ 211,000 በርሜል ያልተጣራ ድፍድፍ ነዳጅ ምርትን እየቀነሱ ይገኛል። የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ፣ ኩዌት፣ አልጄሪያ እና ኦማን ቅነሳ በማድረግ ላይ ናቸው። የሳውዲ ኢነርጂ ሚኒስቴር ባለስልጣን እርምጃው የነዳጅ ገበያውን መረጋጋት ለመደገፍ የታለመ የጥንቃቄ እርምጃ ማለቱን የሳውዲ ፕሬስ ኤጀንሲ ዘግበል። [ዳጉ ጆርናል] @EthioipaNews
    Show more ...
    9 668
    4
    ጀርመኖች በዓለም የመጀመሪያውን ፈጣን ቢራ ሠሩ። በቀላሉ ሁለት የሾርባ ማንኪያ የቢራ ዱቄት በብርጭቆ ውስጥ በማድረግና ከውሃ ጋር ቀላቅሎ በማማሰል ቢራውን ሰርተውታል። ቀማሾች ምርቱ የሚጣፍጥ እና ልክ እንደ መደበኛ ቢራ ነው ይላሉ። @EthioipaNews

    file

    8 268
    11
    አቡበከር ናስር ከጉዳት በተመለሰበት ጨዋታ ጎል አስቆጥሯል! ከሁለት ወራት በላይ በጉዳት ከሜዳ ርቆ የነበረው ኢትዮጵያዊው የማሜሎዲ ሰንዳውንስ አጥቂ አቡበከር ናስር ቡድኑ በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ኮተን ስፖርትን 2ለ1 በረታበት ጨዋታ በ62ኛው ደቂቃ ተቀይሮ በመግባት በ86ኛው ደቂቃ ሁለተኛው ጎል በስሙ አስመዝግቧል። @EthioipaNews
    9 196
    2
    የዓለማቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት መመስረቻ ስምምነት ፈራሚዋ ደቡብ አፍሪካ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቱን ለ"ብሪክስ" አገራት የመሪዎች ጉባኤ ሲሄዱ እንደምታስተናግዳቸው ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ ናለዲ ፓንዶር በኩል አስታውቃለች። የዓለማቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ፑቲን በዩክሬን "የጦር ወንጀል ፈጽመዋል" በማለት የእስር ማዘዣ ማውጣቱን ተከትሎ፣ በቀጣዩ ነሐሴ የ"ብሪክስ" አገራት የመሪዎች ጉባኤ አዘጋጇ ደቡብ አፍሪካ አቋሟ ምን እንደሚኾን በጉጉት ሲጠበቅ ነበር። ደቡብ አፍሪካና ሩሲያ በሌሎች አገራት ግፊት በድንገት ጠላት ሊኾኑ አይችሉም ያሉት ፓንዶር፣ ፑቲንን በጉባኤው እንዲገኙ እንደተጋበዙ ተናግረዋል። በዓለማቀፉ ፍርድ ቤት ስምምነት መሠረት፣ ደቡብ አፍሪካ ፑቲን ግዛቷን ከተረገጡ አስራ ለፍርድ ቤቱ የማስረከብ ግዴታ አለባት። "ብሪክስ" በፍጥነት በማደግ ላይ ያሉት ኃያላኑ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሩሲያ፣ ቻይና፣ ሕንድና ብራዚል የመሠረቱተ ቡድን ነው። @EthioipaNews
    Show more ...
    9 818
    2
    ሰበር ዜና‼️ የክልል ልዮ ሀይል የተባለው ወታደራዊ አደረጃጀት መሉ በሙሉ እንዲፈርስ ትዕዛዝ ተላልፏል። ልዮ ሀይሉ ሲፈርስ ወደ መደበኛ መከላከያ ስራዊት የሚቀላቀሉ ሲሆን የቀረው መደበኛ ፖሊስ ሆኖ ይቀጥላል። ልዮ ሀይሉ የያዛቸውን የስራ ድርሻ ፌደራል ፖሊስና መከላከያ ስራዊት ይረከባቸዋል። አንድ ፖሊስ ( በፌደራል ፖሊስ ዕዝ የሚመራ) አንድ የኢትዮዽያ መከላከያ ስራዊት ብቻ ሆነው ይቀጥላሉ። @EthioipaNews
    11 182
    15
    ከዕስር ተፈቱ‼️ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ እና ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ ከእስር ተፈቱ! በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እና በጄነራል ታደሰ ወረደ መዝገብ ተከስሰው በእስር ላይ የነበሩ የህወሓት ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 21፤ 2015 አመሻሽ ላይ ከእስር መፈታታቸውን የተከሳሾቹ ጠበቆች አስተባባሪ የሆኑት አቶ አቶ ሃፍቶም ከሰተ ተናገሩ። በዛሬው ዕለት ከእስር ተለቅቀው ወደ ቤታቸው መግባታቸው ከተረጋገጡ ተከሳሾች ውስጥ፤ የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ እና ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ እንደሚገኙበት ጠበቃው አስታውቀዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር) @EthioipaNewss
    9 852
    1
    ቻይና እና ብራዚል የአሜሪካ ዶላር መጠቀምን ለማቆም ወሰኑ በዓለም በኢኮኖሚዋ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ቻይና እና በላቲን አሜሪካ ትልቁ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው ብራዚል የአሜሪካ ዶላርን እንደ መገበያያ ላለመጠቀም ተስማሙ፡፡ ሁለቱ አገራት የንግድ ልውውጣቸውን ከዶላር ነጻ በማድረግ በራሳቸው ገንዘብ ለመገበያዬት መወሰናቸው የአሜሪካ ዶላር አቅም እንዲዳከም እና ተፅዕኖም እንዲቀንስ ያደርጋል ተብሏል፡፡ ቻይና ባለፈው ዓመት በሁለትዮሽ ንግድ ሪከርድ 150 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር በማስመዝገብ የብራዚል ትልቋ የንግድ አጋር ሆና እንደነበርም የሲጂቲኤን ዘገባ አስታውሷል፡፡ በተመሳሳይ ኬንያ ከሳውዲ አረቢያ ነዳጅ ለመግዛት የአሜሪካ ዶላር ሳይሆን የኬኒያ ሽልንግ ለመጠቀም መስማማቷ ይታወሳል፡፡ @EthioipaNews
    8 862
    4
    ቻይና ቲክ ቶክን በመጠቀም ልትሰልል እንደምትችል አሜሪካ ተናገረች ባለፈው ሳምንት የቲክ ቶክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ለአምስት ሰአት በፈጀው የዩናይትድ ስቴትስ ህግ አውጪዎች ጥያቄ ላይ ቻይና በጣም ተወዳጅ የሆነውንና በከፊል በቻይና መንግስት ባለቤትነት ስር በተያዘው መተግበሪያ አሜሪካውያንን ለመሰለል ልትጠቀም እንደምትችል ዋሽንግተን ተናግራለች። የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት አለም አቀፍ ኢንተርኔትን በብቃት የተቆጣጠሩ የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እንዴት እንደሚጠቀሙ ግን የምክር ቤቱ አባል የጠቀሱት ነገር የለም። ዩናይትድ ስቴትስ ከ150 ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን የሚጠቀሙበትን አጭር የቪዲዮ መተግበሪያ ለማገድ ስታስብ፣ የሕግ አውጭ አካላት እንደ ጎግል፣ ሜታ እና አፕል ያሉ ኩባንያዎች በባህር ማዶ የሚገኙ የአሜሪካ ነዋሪ ባልሆኑ ዜጎች ላይ ያልተገደበ የስለላ ሥራ እንዲያመቻቹ እያደረጉ መሆኑ ግን ተጠቁሟል።የኮንግረሱ አባል የሆነችውን አሌክሳንድሪያ ኦካሲዮ-ኮርትዝ ጨምሮ ተጠቃሚዎች በቲክቶክ ላይ የህግ አውጭዎች ብሔራዊ እገዳን ለማድረግ ማቀዳቸውን ተከትሎ አደባባይ በመውጣት ተቃውመዋል። ከአሜሪካ በተጨማሪ ቲክ ቶክን ለማገድ ካናዳ፣ብሪታኒያ ፣ፈረንሳይ ፣የአውሮጳ ህብረትና የኒውዝላንድ የምክር ቤት አባላት የደህንነት ስጋት ደቅኖብናል በሚል እየተንቀሳቀሱ ይገኛል። Via:- ዳጉ ጆርናል @EthioipaNews
    Show more ...
    8 755
    1
    የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ስብሰባውን እያካሄደ ነው! የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል።የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄዎችን እየቀረቡ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀረቡላቸው ጠያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። እስካሁንም ከኦነግ ከሸኔ፣ ከአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ፣ ከሰሜኑ የሰላም ስምምነት፣ ከዜጎች መፈናቀልና ግድያ፣ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ስለተከለከሉ ዜጎች፣ አርሶ አደሩ ምርቱን ለመሸጥ ከመቸገሩ ጋር በተያያዘ፣ ወደ አዲስ አበባ ምርት እንዳይገባ ከመከልከሉ ጋር፣ ከክልሎች የርስ በርስ መናበብ አለመቻል፣ የሱዳን ወታደሮች ወረው የያዙትን የኢትዮጵያ መሬትና ያወደሟቸውን ንብረቶች የተመለከቱ ጥያቄዎች ቀርበዋል።አሁንም የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄዎችን በማቅረብ ላይ ናቸው። @EthioipaNews
    Show more ...
    8 962
    4
    የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምዝገባ ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዝያ 15 ይካሄዳል!! የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዝያ 15 ድረስ በበይነ-መረብ እንደሚካሄድ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) የመደበኛ እና የማታው ክፍለ ጊዜ ተማሪዎች ምዝገባ በትምህርት ቤቶች እንደሚካሄድ ጠቅሰዋል። የድጋሚ ተፈታኞች እና የርቀት ተማሪዎች ምዝገባ ደግሞ በተመረጡ የወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች የሚካሄድ መሆኑም ተጠቁሟል። የምዝገባ ሂደቱ በተጠቀሱት ቀናት ባሉ ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚከናወን ይሆናልም ብለዋል። @EthioipaNews
    8 772
    7
    8 517
    14
    ጠቅላይ ሚንስትሩ ለፓርላማ ማብራሪያ ሊሰጡ ነው! ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች፤ ነገ በፓርላማ ተገኝተው ማብራሪያ ሊሰጡ መሆኑ ታውቋል፡፡የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ማክሰኞ መጋቢት 19፤ 2015 በሚኖረው መደበኛ ስብሰባው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከፓርላማ አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎችን የሚሰጡትን ምላሽ እና ማብራሪያ እንደሚያዳምጥ እና የፓርላማ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ያስገቡት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር መረጃዎች ደርሰውኛል ብሏል፡፡ ከአንድ ወር ዕረፍት በኋላ የተመለሱት የፓርላማ አባላቱ፤ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ መጋቢት 9፤ 2015 በተወካዮች ምክር ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በነበራቸው ስልጠና ይኸው እንደተነገራቸው ምንጮቹ ገልጸዋል።ይህንኑ ያረጋገጡት አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የፓርላማ አባል፤ “ ‘በአስቸኳይ አስገቡ’ ብለው ባለፈው ቅዳሜ ነገሩን። ቀን ላይ ነግረውን፤ ‘እስከ ማታ ድረስ’ አሉን” ሲሉ ለጥያቄ ማቅረቢያ የተሰጠው አጭር ጊዜ እንደነበር አስታውሰዋል። የፓርላማ አባሉ አክለውም፤ “ብዙዎቻችን ‘አይሆንም፤ ተረጋግተን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርብ አይነት ጥያቄ በአግባቡ ማዘጋጀት አለብን’ ስንል እስከ እሁድ አመሻሽ ድረስ አቅርቡ ተባለ” ሲሉ ጥያቄ የማቅረቢያ ጊዜው በአንድ ቀን እንዲራዘም መደረጉን አስረድተዋል።በዚህ አካሄድ እስከ ባለፈው ሳምንት እሁድ አመሻሽ ድረስ፤ የፓርላማ አባላቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚያቀርቧቸውን ጥያቄዎች አስገብተው ማጠናቀቃቸውን ጨምረው ገልጸዋል። በነገው ዕለት በሚካሄደው የፓርላማ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሚቀርቡ ጥያቄዎች መካከል፤ “የኑሮ ውድነትን የተመለከቱ ይኖራሉ” ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮች ጠቁመዋል። “ወደ አዲስ አበባ አትገቡም እየተባለ ወደ አማራ ክልል የሚመለሱ ሰዎች” ጉዳይን የተመለከቱ ጥያቄዎችም፤ በነገው የፓርላማ ስብሰባ ጥያቄ ሊቀርብ እንደሚችል ምንጮች ግምታቸውን አስቀምጠዋል። [Ethiopia Insider] @EthioipaNews
    Show more ...
    8 651
    4
    ወልቂጤ ዝም ጭር ብላለች። @EthioipaNews
    9 431
    2
    ጌታቸው ረዳ‼️ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ በክልሉ ለሚገኙ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል። በዚህም መግለጫቸው ፤ " የትግራይ ህዝብ እራሱን ከጥፋትና ውድመት ለማዳን ሁሉንም አይነት መስዋዕትነት ከፍሏል። " ያሉ ሲሆን " ጊዜያዊ አስተዳደሩም የትግራይ ህዝብ የታገለለትንና መስዋእትነት የከፈለበትን ዓላማ ለማሳካት ይሰራል " ብለዋል። አቶ ጌታቸው አስተዳደራቸው የትግራይን ግዛታዊ አንድነትን ማረጋገጥ፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቄያቸው መመለስ እና የህዝቡን ሁለንተናዊ ችግሮች በፍጥነት መፍታት ዋነኛው አላማው አድርጎ እንደሚሰራ በሰጡት መግለጫ መናገራቸውን ከክልሉ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል። አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን እንዲመሩ በህወሓት ማዕከላይ ኮሚቴ አብላጫ ድምፅ አግኝተው ከተመረጡ በኃላ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ክልሉን እንዲያስተዳድሩ ርዕሰ መስተዳደር አድርገው እንደሾሟቸው ትላንት የጠ/ሚ ፅ/ቤት ማሳወቁ ይታወሳል። @EthioipaNews
    Show more ...
    10 113
    2
    ሰሜን ኮሪያ ኒውክሌር ተሸካሚ የውሃ ውስጥ ድሮን ሙከራ አደረገች!! የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ኒውክሌር የመሸከም አቅም ያለው የውሃ ውስጥ ሰው አልባ አነስተኛ አውሮፕላን (ድሮን) ሙከራ ማካሄዳቸውን የሀገሪቱ የዜና ጣቢያ ገለጸ፡፡ የውሃ ውስጥ ድሮኑ ከ80 እስከ 150 ሜትር ባለ ጥልቀት ውስጥ በውሃ ውስጥ ከ59 ሰአታት በላይ ከተጓዘ በኋላ በምስራቃዊ የባህር ዳርቻ መፈንዳቱን ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል። ድሮኑ በውሃ ውስጥ ከተተኮሰ በኋላ “የራዲዮአክቲቭ ማዕበል” ሊያስነሳ የሚችል መሆኑንም ዘገባው አክሎ ገልጿል፡፡ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ይህንን ሙከራ በበላይነት የመሩ ሲሆን አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ “የሰሜን ኮሪያ ያልተገደበ የኒውክሌር ጦርነትን የመከላከል አቅም በከፍተኛ ፍጥነት እየተጠናከረ መሆኑን እንዲገነዘቡ” ማስጠንቀቂያ ሊሆን ይገባል ብለዋል። ፖሲዶን ከተሰኙት የሩሲያ የውሃ ውስጥ ተተኳሾች ጋር እንደሚመሳሰሉ የተነገረላቸው የሰሜን ኮሪያ የቅርብ ጊዜ መሳሪያዎች የባሕር ላይ ማዕበል በማስነሳት በአሜሪካ የባህር ዳርቻ ከተሞችን ሊያወድሙ ይችላሉም ነው የተባለው። “ሚስጥራዊው መሳሪያ” ማክሰኞ ከደቡብ ሃምጊዮንግ ግዛት ወጣ ብሎ በሚገኘው ውሃ ውስጥ መቀመጡም ነው የተነገረው። “ሃኤይል” የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ የጦር መሳሪያ የጠላት መርከቦችን እና ወደቦችን በከፍተኛ የራዲዮአክቲቭ ሞገድ ለማጥቃት ታስቦ የተነደፈ መሆኑንም ተሰምቷል፡፡ አሜሪካና ደቡብ ኮሪያ በአምስት ዓመታት ውስጥ ትልቅ የተባለ የጋራ ልምምዳቸውን ባለፈው ረቡዕ ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ በኮሪያ ልሳነ ምድር ዳግም ውጥረት መንገሱ ይነገራል። ይሁንና የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ዩን ሱክ-ዮል÷ ሰሜን ኮሪያ በግዴለሽነት ለምታደርገው ትንኮሳ ዋጋ ትከፍላለች ሲሉ ተደምጠዋል። @EthioipaNews
    Show more ...
    8 769
    3
    የዘንድሮ የሐጅ ተጓዦች 315 ሺህ ብር እንዲከፍሉ ተወሰነ‼️ የዘንድሮ የሐጅ ተጓዦች 315 ሺህ ብር እንዲከፍሉ መተመኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል፡፡ ምክር ቤቱ በሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት እግድ የተጣለባቸውን ዜጎች በቅዱሱ ጉዞ አላሳትፍም ብሏል፡፡ ቀድሞ በፌደራል ጠቅላይ ምክር ቤቱ ብቻ ይሰጥ የነበረው የምዝገባ አገልግሎት በዘንድሮው የሐጅ ጉዞ መስተንግዶ ወደ ሐጃጁ በማቅረብ ምዝገባውን በ16 ጣቢያዎች በየአካባቢው እንደሚከናወን ተገልጿል። በመግለጫው የሐጅ ተጓዥ ለምዝገባ በአካል መቅረብ ይኖርበታል የተባለ ሲሆን ማንኛዉም ተመዝጋቢ የሚከተሉትንን መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅበታል ፦ 1. የታደስ የነዋሪነት መታወቂያ/ መንጃ ፈቃድ 2. የጉዞ ሰነድ (ፖስፖርት ) የመጠቀሚያ ጊዜው ለመጠናቀቅ ከ9 ወራት በላይ የቀረው መሆን ይኖርበታል፡፡ 3. አንድ ጉርድ ፍቶ ግራፍ 4. የኮቪድ ክትባት የወሠደበት ማስረጃ እንዲሁም የቢጫ ወባ ክትባት ካርድ (ቢጫ ካርድ) ማቅረብ ይጠበቅበታል። 5. እራሳቸዉን ችለው የሐጅ ስርዓቱን መፈፀም የሚችሉ ወይም አስፈላጊውን መስፈርት አሟልተዉና ክፍያ ከፍለው ሊያግዛቸው የሚችል ሰው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው። @EthioipaNews
    Show more ...
    7 948
    4
    አንድሪው ቴትና ወንድሙ በእስር እንዲቆዩ ፍርድ ቤት ወሰነ! አወዛጋቢና ጾተኛ የሚባለው አንድሪው ቴት እና ወንድሙ ትሪስታን በሮማኒያ በእስር እንዲቆዩ ፍርድ ቤቴ ብይን ሰጥቷል።ወንድማማቾቹ ለአራተኛ ወርም በእስር ይቆያሉ ተብሏል።አንድሪውና ትሪስታን በመድፈር፣ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና የተደራጀ የወንጀል ቡድን አቋቁመዋል በሚልም ክስ እየተመረመሩም ይገኛሉ።ሁለቱም ወንጀሎቹን አልፈጸምንም ሲሉ አስተባብለዋል። የአንድሪው ቴት ጠበቆች ደንበኛቸው እስከ ሚያዝያ መጨረሻ ድረስ በእስር እንደሚቆይ ተናግረዋል።ቃለ አቀባያቸው ማቲያ ፔትሬስኩ ውሳኔው ቃል እንዳሳጣቸው ነው የተናገሩት።የወንድማማቾቹ ጠበቆች በቡካሬስት ረቡዕ ዕለት በነበረው ዝግ ችሎት ላይ አቃብያነ ህግ ምንም አዲስ ማስረጃ አለማቅረባቸውን ተናግረዋል።የደንበኞቻቸው ታዋቂነት በእስር እንዲቆዩ ለመወሰን የራሱን አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል። ማቲያ ፔትሬስኩ እንዳሉት ዳኛው ለመጀመሪያ ጊዜ ከአገር ሊወጡ ይችሉ ይሆን ወይም ለህዝብ ስርዓት አደጋ ደቅነዋል ለሚለው ክርክር በቀጥታ ምላሽ እንዲሰጡም ነው የተጠየቁት።ሆኖም ዳኛው በመጨረሻ ሁለቱም ወንድማማቾች እስከ ሚያዝያ ድረስ ለተጨማሪ 30 ቀናት በእስር እንዲቆዩ ወስኗል።የቀጠለው እስር በወንድማማቾቹ ላይ ከፍተኛ ጥላሽት እንደቀባቸውና ስማቸውን ለማደስ ዓመታት እንደሚወስድም ተናግረዋል። በአሜሪካ የአንድሪው ቴት ጠበቃ በቅርቡ ደፍሮኛል ያለችውን ተጎጂ ከነቤተሰቧ የምታቀርበውን ክስ ካልተወችው በ300 ሚሊዮን ዶላር በስም ማጥፋት ክስ እንደሚመሰረትባት አስፈራርተዋታል ተብሏል። [BBC] @EthioipaNews
    Show more ...
    7 730
    4
    ጌታቸው ረዳ‼️ የሕወሃት ከፍተኛ አመራር ጌታቸው ረዳ የትግራይ የጦር ጉዳተኞች ሰሞኑን ያነሷቸው ቅሬታዎች በከፍተኛ ትኩረት እንደሚታዩ እና ማጣራት እንደሚደረግባቸው መናገራቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል። የጦር ጉዳተኞቹ ለእነሱ ተብሎ የተገዛ የሕክምና አቅርቦት እየተሸጠ ስለመሆኑ ነግረውኛል ያለው ዜና ምንጩ፣፣ የጦር ጉዳተኞቹ የጉዳት ካሳ እንዲከፈላቸው መጠየቃቸውንም ጠቅሷል። የጦር ጉዳተኞቹ ከፍተኛ የሆነ የምግብ፣ የሕክምናና የንጽሕና መጠበቂያ አቅርቦት እጥረት እንዳለባቸው በሰላማዊ ሰልፍና ከጌታቸው ጋር ባደረጉት ውይይት መናገራቸው ተዘግቦ ነበር። የጦር ጉዳተኞቹ፣ በመቀሌ አካባቢ ኩዊሃ እና ደጀን ሆስፒታል በተባሉ ሁለት ማገገሚያ ማዕከሎች የሚገኙ ናቸው። @EthioipaNews
    7 577
    2
    6 881
    3
    ሰይጣን ቤት ታሸገ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስነዋሪ ድርጊት እና ትውልድን በሚጎዳ ስራ ላይ የተሰማሩና ሲጠቀሙ የተገኙ 68 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ ሰይጣን ቤት ወይም ፒራሚድ አዲስ እና ባስ አዲስ ክለብ በማህበረሰቡ ተቀባይነት የሌላቸው አፀያፊ ድርጊቶች ሌሎች ህገወጥ ተግባራት ሲፈፅሙ በመገኘታቸው ቤቶቹ ታሽገዋል:: የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ እና የሠላምና ፀጥታ ቢሮ በጋራ በመሆን ትላንት ከምሽቱ 4:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ ህገወጥ ተግባራት ሲፈጸምባቸው የተገኙት የምሽት ቤቶች ታሽገዋል:: በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ከ100 በላይ የሺሻ ዕቃዎች ፣ በርካታ መዋሰሎች፣ ከ 6 በላይ ሀሺሽ የያዙ እቃዎች እንዲሁም በወቅቱ በቦታው የነበሩ ከ 68 በላይ የሚሆኑ ተጠቃሚዎችን እና ወጣቱን በዚህ እኩይ ድርጊት ላይ እንዲሳተፍ ሲያደርጉ የቆዩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዉለዋል ሲል ከተማ መስተዳደሩ ገልፇል። @EthioipaNews
    Show more ...
    6 854
    3
    6 515
    5
    ረመዳን ሙባረክ‼️ በሳውዲ አረቢያ የረመዳን ወር መግቢያ ጨረቃ ባለመታየቷ የረመዳን ወር ሐሙስ መጋቢት 14 አንድ ብሎ እንደሚጀምር ታውቋል። @EthioipaNews
    7 152
    5
    ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) አረፉ‼️ በቀድሞ ስማቸው አባ ኃይለማርያም መለሰ (ዶ/ር) በጵጵስና ስማቸው ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ የድሬዳዋ እና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።  ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ ዕድ ከሾሙት ጳጳሳት 14 ኤጲስ ቆጶሳት መካከል አንዱ ነበሩ።  ብፁዕነታቸው ለረጅም ጊዜ ከሀገር ውጪና በሀገር ውስጥ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሊሻላቸው ሳይችል ቀርቶ ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ መለየታቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት ዘግቧል። @EthioipaNews
    Show more ...
    7 462
    5
    ዜና እረፍት!! ታዋቂው የአካባቢ ጉዳይ ሳይንስቲስት ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገብረእግዚአብሄር ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ታውቋል፡፡ ዶ/ር ተወልደብርሃን በትግራይ ክልል በአድዋ ከተማ አቅራቢያ ባለችው ‹‹አዲ-ስላም›› የተሰኘች የገጠር መንደር የተወለዱ ሲሆን ፣ በቀለም ትምህርት ገፍተው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በ1955 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተቀበሉ በኋላ የሁለተኛ እና ዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከዌልስ ዩኒቨርሲቲ ያገኙ ናቸው፡፡ በአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ አገልግሎት የተከበረ ሥም ያላቸው ዶክተር ተወልደ በዘርፉ ላደረጉት ምርምርና በጉዳዩ ዙሪያ ከፍተኛ ግንዛቤ እንዲፈጠር ላደረጉት ጥረት በፈረንጆቹ 2000 Right Livlihood Award ሽልማት አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በፈረንጆቹ 2006 ዓመት የተባበሩት መንግሥታት በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሰዎች የሚሰጠውን Champions of the Earth ሽልማት አግኝተዋል፡፡ የተማሩበት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በ1997 የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷቸዋል፡፡ ዶ/ር ተወልደ በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ፋኩልቲ ዲን ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፣ ከ1975 እስከ 1983 በነበረው ዘመን ደግሞ የአስመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ነበሩ፡፡ ከደርግ መንግሥት መውደቅ በኋላ ለብዙ ዓመታት በሚታወቁበት የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርነት አገልግለዋል፡፡ ዶክተር ተወልደ ገብረእግዚአብሔር የደራሲ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ወንድም መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ምንጭ :- ደራሲና ጋዜጠኛ ዘነበ ወላ @EthioipaNews
    Show more ...
    8 234
    8
    አዲሱ የዓባይ ድልድይ የመገጣጠሚያ ሙሌት ሥራ ትናንት ምሽት ተጠናቀቀ። በባሕር ዳር ከተማ እየተገነባ የሚገኘው አዲሱ የዓባይ ወንዝ ድልድይ ግንባታ ፕሮጀክት በሁለቱም አቅጣጫ ሲካሄድ የነበረው ወንዙ መካከል ላይ የመገጣጠሚያ ሙሊት ትናንት ምሽት ተጠናቋል። ፕሮጄክቱ 94 ነጥብ 15 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን ሰኔ 30 ላይ ለትራፊክ ክፍት ይሆናል ተብሏል። የድልድዩ ግንባታ ሲጠናቀቅ በአንድ ጊዜ ስድስት መኪኖችን ማሳለፍ የሚያስችልም ነው። @EthioipaNews
    7 680
    4
    አላማጣ‼️ "አማራ ነን እንጂ አማራ እንሁን አላልንም" የራያ አላማጣ ሰልፈኞች ዛሬ በአላማጣ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ!! @EthioipaNews
    8 455
    4
    Last updated: 11.07.23
    Privacy Policy Telemetrio