Best analytics service

Add your telegram channel for

  • get advanced analytics
  • get more advertisers
  • find out the gender of subscriber
Category
Channel location and language

audience statistics Addis መረጃ™

 @Addis_Mereja  ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ 🇪🇹 🇪🇹 . ⏬ምርት እና አገልግሎቶን ለማስተዋወቅ ከፈለጉ⏬ ⏬ ꜰᴏʀ ᴘᴀɪᴅ ᴘʀᴏᴍᴏᴛɪᴏɴ ⏬ መረጃዎችን ለመላክ  @Adis_Merejaa_bot  
56 776-24
~13 817
~54
22.53%
Telegram general rating
Globally
17 337place
of 78 777
137place
of 396
In category
719place
of 2 347

Subscribers gender

Find out how many male and female subscibers you have on the channel.
?%
?%

Audience language

Find out the distribution of channel subscribers by language
Russian?%English?%Arabic?%
Subscribers count
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

User lifetime on the channel

Find out how long subscribers stay on the channel.
Up to a week?%Old Timers?%Up to a month?%
Subscribers gain
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

Since the beginning of the war, more than 2000 civilians have been killed by Russian missiles, according to official data. Help us protect Ukrainians from missiles - provide max military assisstance to Ukraine #Ukraine. #StandWithUkraine
የስሎቫኪያ ጠቅላይ ሚንስትር በጥይት ተመተው ሆስፒታል ገቡ! የስሎቫኪያ ጠቅላይ ሚንስትር በጥይት ተመተው ሆስፒታል ገቡ።ባሳለፍነው ጥቅምት በተደረገ ምርጫ ወደ ስልጣን የመጡት የስሎቫኪያ ጠቅላይ ሚንስትር በጥይት ተመተው ሆስፒታል ገብተዋል ተብሏል። ሮይተርስ የአይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ጠቅላይ ሚንስትር ሮበርት ፊኮ የካቢኔ ስብሰባ አድርገው ሲወጡ ከአንድ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት ተመተዋል።ፖሊስ ተጠርጣሪውን ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር አውሎታል የተባለ ሲሆን በተጠርጣሪው ላይ ተጨማሪ ምርመራ በመካሄድ ላይ እንደሆነም ተገልጿል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ለህክምና ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል የተባለ ሲሆን የሀገሪቱ መንግሥት እስካሁን ስለ ጉዳዩ በይፋ ያለው ነገር የለም።ጠቅላይ ሚንስትር ፊኮ ኔቶን ጨምሮ ምዕራባዊያን ሀገራት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ማድረግ የለባቸውም በሚል አቋማቸውም ይታወቃሉ።ዩክሬን ከሩሲያ ጋር እያደረገችው ያለው ጦርነት እንዲቆም ከተፈለገ ኪቭ ክሪሚያ የሩሲያ መሆኗን ማመን እና መቀበል እንዳለባት በተደጋጋሚ ሲናገሩ ይደመጣሉ። Via Al-ain
Show more ...
7 903
4
ቀሲስ በላይ መኮንን በተጠረጠሩበት በሀሰተኛ ሰነድ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ዝውውር ወንጀል ለምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደ! የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀሲስ በላይ መኮንን በተጠረጠሩበት በሀሰተኛ ሰነድ የዶላር ዝውውር ወንጀል ለምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ መፍቀዱ ተሰምቷል፡፡ የፌደራል ፖሊስ መርማሪ ቀሲስ በላይ መኮንን ከትናንት በስቲያ በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ጊቢ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ በአካል ቀርበው ሀሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን በመያዝ ለ3 ግለሰቦች እና ለአንድ የግል ድርጅት ሒሳብ 6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ሊያዘዋውሩ ሲሉ በአፍሪካ ህብረት ሴኪዩሪቲዎች ተይዘው ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ተላልፈው መሰጠታቸውን ጠቅሶ የጥርጣሬ መነሻውን ለችሎቱ ማቅረቡን ዳጉ ጆርናል ከፋና ዘገባ ተመልክቷል። በዚህ መነሻ መሰረትም መርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ ሥራ ለማከናወን የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።ተጠርጣሪ ቀሲስ በላይ መኮንን ድርጊቱ መፈጸሙን አምነው፤ ይሁን እንጂ ወንጀል አለመፈጸማቸውን አስረድተዋል።ስለሆነም የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።የግራ ቀኝ ክርክሩን የተመለከተው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ተጠርጣሪው ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ በማለፍ ለፖሊስ የ7 ቀናት የምርመራ ፈቅዷል።
Show more ...
24 366
28
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ገንዘብ 95 በመቶውን ማስመለስ መቻሉን አስታወቀ! የኢትዯጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከተከሰተው የሲስተም ችግር ጋር በተገናኘ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ገንዘብ 95 በመቶ የሚሆነውን ማስመለሱን አስታውቋል።ባንኩ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ በተጠቀሰው ዕለት በተፈጠረ ችግር ምክንያት ብር 801 ሚሊዮን 417 ሺህ 747.81 ያለአግባብ ተወስዶ እንደ ነበር መገለፁ ይታወሳል። ከተወሰደው ገንዘብ 762 ሚሊዮን 941 ሺህ 341 ብር ማስመለስ መቻሉን ባንኩ በማኅበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።ይህም መሰብሰብ ከነበረበት ገንዘብ ውስጥ 95 በመቶ የሚሸፍን ሲሆን ቀሪውን 38 ሚሊዮን 474 ሺህ 938 ብር የማስመለስ ስራ እንደሚቀጥልም ባንኩ ገልጿል።
15 174
2
«ከትናንት ታሪካዊ ስህተቱ መማር የተሳነው ህወሓት ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል» ሲል የአማራ ክልል መግለጫ ሰጠ! ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ ከትናንት ታሪካዊ ስህተቱ መማር የተሳነው ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሓት) የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመጣስ ለአራተኛ ዙር ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል፡፡ ጀንበር ጠልቃ በወጣች ቁጥር ከጦርነት ውጭ ማሰብ የማይችለው የህወሓት ቡድን ከዉጭ እና ከዉስጥ ጠላቶቻችን ጋር ተናቦና ተቀናጅቶ በእርካሽ ፖለቲካዊ ብያኔና ፍረጃ በጊዜያዊ አሥተዳደሩ ካቢኔ አማካኝነት መጋቢት 16/2016 ዓ.ም የአማራ ክልል ተማሪዎችን መማሪያ መጽሐፍ እንደ ሰበብ ተጠቅሞ በይፋ ጦርነት ማወጁና መቀስቀሱ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ይህን የመላ ኢትዮጵያ ጠላትና የደኅንነት ስጋት የሆነውን የህወሓት ቡድን ባለፉት ሦስት ዙሮች ከተደረገው ደም አፋሳሽ ጦርነት ትምህርት ሊወስድ ይችል ይሆናል በሚል ጭላንጭል ተስፋ የፌዴራል መንግሥት እጅግ እልህ አስጨራሽ ትዕግስት ተላብሶ ውይይቶች እንዲካሄዱ ተደጋጋሚ ጥረት ሲያደረግ ቆይቷል፡፡ የአማራ ክልል መንግሥትም በተደጋጋሚ ከትግራይ ጊዜያዊ አሥተዳደር ጋር በፌዴራል መንግሥት አማካኝነት ውይይት ለማድረግ በርካታ ሙከራዎች የተደረጉ ቢሆንም ህወሓት ይህን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን በመተው የማንነት ጥያቄ ያለባቸውን የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረምና ዛታ አካባቢዎች ላይ ወረራ ፈፅሟል፡፡ ህወሓት ወረራ የፈፀመባቸው የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረምና ዛታ እንዲሁም የወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት አካባቢዎች የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት ከመፅደቁ በፊት በነበሩ አሥተዳደራዊ መዋቅርና አደረጃጀት በኀይል ጠቅልሎ ከመውሰድ ጀምሮ የዘር ማጥፋት ወንጀል እስከመፈፀም ድረስ አሰቃቂ ጥፋት የፈፀመባቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡ እነዚህ አካባቢዎች ስቃይ በተሞላበት ችግር ውስጥም ሆነው በወቅቱ ለነበረው መንግሥት የማንነትና ራስን በራስ የማሥተዳደር ጥያቄዎችን በማንሳት፣ መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ሲጠይቁ የነበሩ መሆኑ በበርካታ ታሪካዊ ማስረጃዎች የተረጋገጥ ጉዳይ ነው፡፡ ተቸንካሪነት ዋና መለያ የሆነው የህወሓት የጥፋት ቡድን ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የፈፀመውን አሰቃቂና ታሪክ ምንጊዜም የማይዘነጋው የባንዳነት ተግባር ተከትሎ በተቀሰቀሰው ጦርነት በመላ ኢትዮጵያዊያን እና በጀግኖች የፀጥታ ኀይሎች አማካኝነት የሽንፈት ፅዋን ከመጎንጨቱ ባሻገር የማንነትና የራስ አሥተዳደር ጥያቄ ያለባቸውን አካባቢዎች በጉልበት ተገፎባቸው የነበረውን ራሳቸውን የማሥተዳደር ነጻነት መቀዳጀት ችለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ሁኔታ ያልተመቸው ተቸንካሪው የህወሓት ቡድን በሦስት ዙሮች ከተደረገው ጦርነት ማግሥት የፕሪቶሪያውን ስምምነት በማክበር በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የድርሻውን ከመወጣት ይልቅ ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ በመጣስ የተለያዩ ጥፋቶችን ሲፈጽም ቆይቷል፡፡አሁንም እየፈጸመ ይገኛል፡፡ ስለሆነም የአማራ ክልል መንግሥት ይህን መሰሉን የህወሓትና የግብረ አበሮቹን ፖለቲካዊ ግልሙትና እና ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማድረግ ከመሞከር እንዲታቀብና የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በማክበር በአጭር ጊዜ በወረራ የያዛቸውን አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ እየጠየቅን ይህ የማይሆን ከሆነ የአማራ ክልል መንግሥትና ሕዝብ ከሌሎቹ ወንድምና እህት ኢትዮጵያዊያን ጋር በጋራ በመሆን ሀገርን ከማፍረስ መታደግና ሕዝባችንንም ከጥቃት ለመከላከል የምንገደድ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ የተከበራችሁ በክልላችን በየደረጃው ያላችሁ የፖለቲካና የጸጥታ መዋቅር አባላት፡- ከሰሜን ዕዝ ጥቃት በኋላ ትህነግ በቀሰቀሰው ጦርነት ሕዝባችን ቀጥተኛ ተጠቂ በመሆኑ ምክንያት ለበርካታ ችግሮች ተዳርጎ የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን በየደረጃው የሚገኙ የመዋቅር አባላት ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ጥምር የጸጥታ ኃይሎችና ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን ሀገር አፍራሽ የጥፋት ኀይሉ ላይ የተቀዳጀው ድል ታሪክ አይዘነጋውም፡፡ ዛሬም እንደ ትናንንቱ በፅናትና በቁርጠኝነት ሕዝቡን በማደራጀት አካባቢያችሁን በመጠበቅ ታሪካዊ ኀላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ የተከበርከው የክልላችን ሕዝብ፡- በተደጋጋሚ ጥቃት የፈፀመብህ የጥፋት ኀይል ዛሬም እንደ ትናንቱ ወረራ ፈፅሟል፡፡ በመሆኑም መላ የክልላችን ሕዝብ ከሀሰት ፕሮፓጋንዳ እና ሠርጎ ገቦች ራስህን በመጠበቅ ከክልል መንግሥትና በየአካባቢው ከሚገኙ አሥተዳደሮች ጋር የጠበቀ ቁርኝት በመፍጠር ጠላቶቻችን የከፈቱብንን ጥቃት ለመመከት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ከመንግሥት ጎን በመሰለፍ የድርሻህን እንድትወጣ የከበረ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት፡- የፌደራል መንግሥት ህወሓት የቀሰቀሰው ደም አፋሳሽ ጦርነት በሰላም እንዲቋጭ ማድረጉን ሳናደንቅ አናልፍም፡፡ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላም ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የተደረገውን ጥረት በሙሉ ልብ በመደገፍ ለውጤታማነቱ የድርሻችንን ስንወጣ ቆይተናል፡፡ ሆኖም ግን ህወሓት በተደጋጋሚ የተሰጠውን ዕድል ባለመጠቀም የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሲያፈርስ ቆይቷል፡፡ አሁንም በሙሉ አቅሙ ወደ ጦርነት ገብቷል፡፡ ይህን እኩይ ድርጊቱን የአፍሪካ ሕብረትና የዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በቦታው ተገኝተው አረጋግጠዋል፡፡በመሆኑም ይህን እብሪተኛ ቡድን በአጭር ጊዜ ከወረራቸው አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ በማድረግ ሕዝባችንን ከጥፋት መታደግና የሀገራችንን ሉዓላዊነት ማስከበር ይገባል፡፡ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ህወሓት ከምስረታዉ ጀምሮ ለአማራ ሕዝብ ባለው ሥር የሰደደ ጥላቻ ምክንያት በአማራ ሕዝብና በመላ ሀገሪቱ ሕዝብ ላይ የማያባራ ደም አፋሳሽ ጦርነትን ሲቀሰቅስ ኖሯል፡፡ ለዚህም ነው ህወሓት የኢትዮጵያም ሆነ የአፍሪካ ቀንድ አለመረጋት ምንጭ ነው የምንለው፡፡ ሆኖም በአሳሳች የፕሮፖጋንዳ ሥራዎቹ ምክንያት የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተደጋጋሚ በህወሓት ጉዳይ ላይ የተሳሳተ አቋም ሲይዝ ተስተውሏል፡፡ ዛሬ ግን ለዚህ አሳሳች ፕሮፖጋንዳው ያልተመቼ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በጠራራ ጸሐይ የአፍሪካ ሕብረትና ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በተገኙበት ወቅት ወረራ መፈጸሙ በገሃድ ታይቷል፡፡ በመሆኑም ከዚህ ቀደም እንዳደረገው በአሁኑ ወቅት የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ማወናበድ አይችልም፡፡ የአማራ ክልል መንግሥትና ሕዝብ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ህወሓት የፈጸመብንን ወረራ በጥብቅ እንዲያወግዝና ከጎናችን እንዲቆም የከበረ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሚያዚያ 08 /2016 ዓ‹ም ባሕር ዳር
Show more ...
21 344
16
የኢትዮጵያ እና ኬንያ አትሌቶች ሆን ብለው ቻይናዊ ሯጭ እንዲያሸንፍ በማድረግ ተከሰሱ! አንድ የኢትዮጵያ እና ሁለት ኬንያውያን አትሌቶች ቻይናዊ ሯጭ የቤይጂንግ ግማሽ ማራቶንን እንዲያሸንፍ አድርገዋል ተብለው ምርመራ ተጀመረባቸው። የውድድሩ አዘጋጅ ቤይጂንግ ስፖርትስ ቢሮ ክስተቱን እየመረመርኩ ነው ሲል ለፈረንሳይ የዜና ወኪል - ኤኤፍፒ ተናግሯል። ኢትዮጵያዊው አትሌት ደጀኔ ኃይሉ ቢቂላ እንዲሁም ኬንያውያኑ ሮበርት ኬተር እና ዊሊ ማናንጋት ቻይናዊው አትሌት ሂ ጂ እንዲያሸንፍ ያደረጉበት ሁኔታን የተመለከቱ ቻይናውያን “ስፖርታዊ ሥነ ምግባር የሌለበት አሳፋሪ ተግባር” ሲሉ ገልጸውታል። ሦስቱ አትሌቶች ከውድድሩ መጀመሪያ አንስቶ እስከ ማጠናቀቂያው ድረስ ቻይናዊውያን አትሌት አጅበው ሲሮጡ ነበር።በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት በተጋራው ቪዲዮ ላይ የውድድሩ መጨረሻ አካባቢ ሦስቱ የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቶች ፍጥነታቸውን በመቀነስ ቻይናዊው አትሌት እንዲያልፋቸው በእጃቸው ሲጠቁሙት ይታያሉ። በመጨረሻም የመላው እስያ ጨዋታዎች የማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊው ቻይናዊ አትሌት ሦስቱን የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቶች አስከትሎ በአንድ ሰከንድ ልዩነት ብቻ ውድድሩን አሸንፏል። የውድድሩ አዘጋጆች ለኤኤፍፒ “ምርመራ እያደረግን ነው። ምርመራችን ሲጠናቀቅ ውጤቱን ይፋ እናደርጋለን” ብሏል።
Show more ...

Beijing half-marathon - Search _ X.mp4

16 855
20
⚡️⚡️ቦሌ የነበረው ተኩስ ዛሬ ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ተኩስ ነበር የተኩሱ መነሻ የጎንደር ፋኖ መሪ የነበረው ናሁሰናይ በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች በመያዙ ምክንያት ነው ተብሏል። ናሁሰናይን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ሊያውለው ሲሞክር ከፀጥታ ኃይሎች ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርጓል ያሉ ሲሆን አብረውት ከነበሩት ሁለት ሰዎች ውስጥ አንዱ ወዲያውኑ የሞተ ሲሆን ናሁሰናይ ቆስሎ ቢያዝም ህይወቱ አልፏል ተብሏል። አንደኛው ምንም ሳይሆን ተይዟል ተብሏል። ከፀጥታ ኃይሎች በኩል አንድ የሞተ ሲሆን የቆሰሉም መኖራቸውን ነው የመረጃ ምንጮቹ የገለፁት። ከቦሌ SNAP PLAZA እስከ ቦሌ መድሃኒያለም ያለው መንገድ ዝግ ተደርጓል ብለዋል።
22 913
61
ዛሬ በሳዑዲ ጨረቃ ባለመታየቷ የዒድ-አልፈጥር በዓል የፊታችን ረቡዕ ይከበራል! ዛሬ በሳዑዲ ዓረቢያ አካባቢ ጨረቃ ባለመታየቷ የዒድ-አልፈጥር በዓል የፊታችን ረቡዕ እንደሚከበር ተገልጿል፡፡
26 450
5
ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የሚያግዛትን 5ኛ ዙር ድርድር በግንቦት ወር ታካሂዳለች! ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የሚያግዛትን 5ኛ ዙር ድርድር በግንቦት ወር እንደምታካሂድ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረ መስቀል ጫላ ገለፁ።አቶ ገብረ-መስቀል ጫላ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ከ20 ዓመታት በፊት የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እንቅስቃሴ ጀምራለች። ይሁንና በኮቪድ 19 ወረርሽኝና በሌሎች ምክንያቶች ድርድሩ ተቋርጦ እንደነበር ይታወሳል። ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የጀመረችውን ጥረት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከቆመበት ለማስቀጠል የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል።ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በሐምሌ 2015 ዓ.ም ወደ ጄኔቫ አቅንተው ከድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውሰዋል። በውይይቱም ኢትዮጵያ በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የድርድር ሂደቱ እንዲጠናቀቅና የድርጅቱ አባል እንድትሆን ከሥምምነት መደረሱንም ጠቁመዋል።በዚህም ከኢትዮጵያ ጋር ድርድር ለማድረግ ፍላጎት ካላቸው አባል ሀገራት 180 የሚጠጉ ጥያቄዎችና 9 ሰነዶች መቅረባቸውን ተናግረዋል። በቅርብ ጊዜ ውስጥ ድርጅቱ በሚያመቻቸው መድረክ ድርድሩ እንደሚጀመር ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል እንድትሆን የሀገሪቱን ጥቅም በሚያስጠብቅ እንዲሁም የኢኮኖሚ ልማትና የንግድ ተወዳዳሪነት በሚያረጋግጥ አግባብ ለመደራደር ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝም አስረድተዋል።ኢትዮጵያ በዓለም ንግድ ድርጅት ውስጥ በታዛቢነት መሳተፍ የጀመረችው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጠጣር በ2003 ነበር። ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል ለመሆን የእቃዎችና የአገልግሎት ንግድ ኦፈር፣ የገቢ ንግድ ፈቃድ አሰራር መረጃዎች፣ የመንግሥት የንግድ ድርጅቶች መረጃ፣ ንግድና ንግድ ነክ ሕጎች መርኃ ግብር እንዲሁም የወጪ ንግድ ድጎማና የግብርና ምርቶች ድጋፍ ሰነዶችን የማሟላት ሥራ እየሰራች መሆኗን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።
Show more ...
26 697
9
የዒድ አል ፈጥር በዓል ጨረቃ ሰኞ ማታ ከታየች ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ ረቡዕ ይከበራል! የዘንድሮው የዒድ አል ፈጥር በዓል ጨረቃ በመጪው ሰኞ ማታ ከታየች ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ ረቡዕ አንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል።ምክር ቤቱ 1 ሺህ 445ኛው ዓመተ ሒጅራ የዒድ አል ፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ መግለጫ ሰጥቷል። በመግለጫውም ፥ የዒድ አል ፈጥር በዓል ጨረቃ ሰኞ ማታ ከታየች ማክሰኞ ሚያዚያ 1 ቀን 2016 ካልታየች ደግሞ ረቡዕ ሚያዚያ 2 ቀን 2016 ዓ.ም አንደሚከበር አስታውቋል።ሕዝበ ሙስሊሙ የዒድ አልፈጥር በዓልን ሲያከብር በጾም ወቅት ሲያደርግ እንደነበረው እርስ በርስ በመደጋገፍና ለተቸገሩ ወገኖች በማካፈል ሊሆን እንደሚገባም አሳስቧል፡፡ Via FBC
18 915
4
12 394
2
ኣርጅናል ሽቶ በተመጣጠነ ዋጋ በ Elegant cosmetic store ከነፃ ትራንስፓርት ጋር
13 406
2
https://t.me/+94RpAh2cWPs2ODlk ሰላም ኣርጅናል የአሜሪካ product በelegant cosmetics store በተመጣጠነ ዋጋ በነፃ delivery እኛ ጋር ይሸምቱ
38
0
ፑንትላንድ እና ሶማሌላንድ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶችን እንደማይዘጉ አስታወቁ! ፑንትላንድ እና ሶማሌላንድ በግዛቶቻቸው የሚገኙትን ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶችን እንዲዘጉ የተሰጠውን ትዕዛዝ እንደማይቀበሉ ዛሬ አስታወቁ።ሶማሊያ፣ በሞቃዲሾ የሚገኙት የኢትዮጵያ አምባሳደር ከሀገር ለቀው እንዲወጡ ማዘዟን፣ የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ትላንት ኀሙስ፣ መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አስታውቆ ነበር። ኢትዮጵያ በሶማሊያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቷን በመግለፅ ክስ ያሰማው የሶማሊያ መንግሥት፤ ሞቃዲሾ የሚገኙት የኢትዮጵያ አምባሳደር በ72 ሰአት ውስጥ ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ መጠየቋን እና አዲስ አበባ ያሉትን አምባሳደሯንም መጥራቷን ትናንት አስታውቃ ነበር።በተመሳሳይም ከሶማሊያ የተገነጠለችውን የሶማሊላንድ ግዛት እና ከፊል ራስ ገዟን ፑንትላንድ በዚያ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤቶች በሰባት ቀናት ውስጥ እንዲዘጉ አዛለች። ይሁንና ሶማሌላንድ በዋና ከተማዋ ሀርጌሳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት እንዲዘጋ ሞቃዲሾ ያቀረበችውን ጥያቄ የሶማሌ ፌደራል መንግሥት እንደዚያ ያለ ትዕዛዝ የመስጠት ሥልጣን እንደሌለው በመግለጽ ውድቅ አድርጋለች።ሶማሊያ ኢትዮጵያ ባለፈው ጥር ወር ከሶማሌላንድ ጋራ የተፈራረመችውን የባህር በር የተመለከተ ስምምነት፣ “ህገ-ወጥ” እና ሉአላዊነቴን የጣሰ ነው ስትል ከኢትዮጵያ ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባቷም ይታወቃል። Via VoA @Addis_Mereja
Show more ...
15 533
5
የአዲስ አበባ 'ልማት ኮሪዶር' ፕሮጀክትን በተመለከተ ዘ ጋርዲያን የተነሺዎችን ቅሬታ የያዘ መረጃ አጋርቷል "ተነሺዎች ለዘመናት ከኖሩበት ቤት እንዲወጡ አምስት ቀን ብቻ እንደተሰጣቸው፣ ከዛም ከሶስት ቀን በኋላ ውሀ ሆን ተብሎ እንደተቋረጠባቸው እና ንብረታቸውን በማውጣት ትርምስ ውስጥ ዝርፊያ እና ውድመት እንደደረሰባቸው ለሚድያው ተናግረዋል"። ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ከስር ያለውን ሊንክ ተጫኑ
14 835
3
መንግስት ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች/startups እንዲያብቡ በርካታ የፖሊሲ ለውጦችን ለማድረግ መወሰኑ ተዘገበ!! ከነዚህም መካከል ከስራ ፈቃድ፣ ግብር፣ ቢሮ ኪራይ፣ ፋይናንስ አቅርቦት፣ ጉምሩክ አሰራር ጋር በተያያዘ ወሳኝ ለውጥ የሚደረግባቸው ይሆናሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተገኙበት ዛሬ ይፋ የተደረጉት ለውጦች በተለይ ስራ ፈጣሪዎች ከውጭ ለሚኖራቸው ግዥ የቀጥታ ክፍያ መፈፀም እንዲችሉ እንዲሁም ያገኙትን የውጭ ምንዛሪ ሙሉ ለሙሉ መጠቀም እንዲችሉ የሚፈቅድ ነው። Via Capital
14 394
10
በቀጣይ ዓመት ብሔራዊ መታወቂያ የሌላቸው ነጋዴዎች የንግድ ፈቃድና ምዝገባ አገልግሎት አያገኙም እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የንግድ ፍቃድ ምዝገባ አገልግሎት እስካሁን በነበረው አሰራር የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ያላቸው ሰዎች አገልግሎቱን አንደሚያገኙ እና ለቀጣይም በዛው እንደሚገለገሉ ተነግሯል፡፡በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የላይሰንሲንግ እና ሬጉላቶሪ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጅራታ ነመራ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እነደተናገሩት የተሰራጨዉ መረጃ ስህተት ነዉ ብለዋል፡፡ ከሁሉም ተቋማት ጋር በመተባበር ለንግድ ስራ ፈቃድ አገልግሎት የሚያስፈልግ ግብአቶች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣የግብር ክሊራንስ እና በሰነድ የሚረጋገጡ ነገሮችን በሙሉ ከተቋማቶቹ በቀጥታ ማግኘት የሚቻልበትን አሰራር እየዘረጋን እንገኛለል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ አሰራሩ ተግባራዊ ሲሆን መረጃዎቹን ከተቋማቱ ማግኘት ስለሚቻል ሰዎች አገልግሎት ሲፈልጉ ጥያቄ የማቅረብ ስራ ብቻ እንደሚኖርባቸው አንስተዋል፡፡አሁን ላይ አሰራሩን ተግባራዊ ለማድረግ የሚቀሩ ስራዎች እንዳሉት የገለፁት መሪ አስፈፃሚው እስከቀጣይ አመት ተጠናቆ ስራ ላይ ይውላል የሚል እቅድ መያዙን ተነግረዋል፡፡ Via Ethio FM
Show more ...
13 077
8
#NewsAlert 👉በአዲስ አበባ ከአሁን በኋላ የሚገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ከዋና ከመንገድ በ10 ሜትር ርቀት መሆን እንደሚገባቸው ውሳኔ ተላለፈ። 🌟የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 3ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ በ3 ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። 🚧ከውሳኔዎቹ አንዱ ግንባታዎችን የሚመለከት ነው። ⏺በዚህም የከተማዋን ስታንዳርድ እና መዋቅራዊ ፕላን ለማስጠበቅ እንዲሁም መልሶ ማፍረስ እንዳይገጥም ፤ ግንባታዎች ከመንገድ ያላቸው ርቀት ከዚህ በኋላ ወጥነት ያለው የከተማ አሰራር አንዲኖር በማሰብ ከመንገድ መራቅ ያለባቸውን 3 ደረጃዎች ወጥተዋል። 🖱ከአሁን በኋላ የሚገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ፦ ➡ ከዋና ከመንገድ በ10 ሜትር ርቀት መሆን እንደሚገባው ፤ ➡ ከንዑስ ዋና መንገድ 5 ሜትር ርቀት፤ ➡ ሰብሳቢ መንገድ ደግሞ 3 ሜትር ርቀት ➡ በተጨማሪ የውስጥ ለውስጥ መንገድ 2 ሜትር ርቀት መጠበቅ እንዳለባቸው ካቢኔው ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። @Addis_Mereja
Show more ...
12 927
19
#Update : የመኖሪያና ንግድ ቤቶች ጨረታ የአሸናፊዎች ስም ዝርዝር ይፋ ተደረገ። የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽንና የአዲስ አበባ ከተማ ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ቢሮ አስገንብተው ለጨረታ ያቀረቧቸው የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች ጨረታ አሸናፊዎች ዝርዝር ከላይ ተያይዟል። በከተማው በመንግስት በተመደበ ካፒታል በጀት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተሰሩ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች ለጨረታ መቅረባቸው ይታወሳል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአሸናፊዎች ስም ዝርዝሩን የያዘው ፋይል ምንጭ የአ/አ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ መሆኑን ይገልጻል። @Addis_Mereja

የጨረታ አሸናፊዎች ዝርዝር(1)(1).pdf

12 347
12
በመሬት አገልግሎት ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ተነሳ! ላለፉት ሦስት ወራት እግድ ተጥሎበት የነበረው የመሬት አገልግሎት ካለፈው ሰኞ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ መነሳቱ ተገለጸ። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በተጠናው የመዋቅር ጥናት መሠረት የሰራተኞች ድልድል ተካሂዶ ምደባ እስከሚካሄድ ድረስ ከጥር  21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ሦስት ወራት ታግዶ የቆየው የመሬት አገልግሎት፣ የዜጎችን መብት የጣሰ እንደነበር በመናገር  ተገልጋዮች ሲያማርሩ ቆይተዋል። አስተዳደሩ እንደገለጸው አጠቃላይ የሰራተኛ ድልድሉ በመጠናቀቁ ከቀን ከመጋቢት 23 ቀን2016 ዓ.ም ጀምሮ የመሬት አገልግሎት የተጀመረ መሆኑን አስታውቋል። Via Reporter @Addis_Mereja
12 756
29
ስፔን ለፍልስጤም ሀገርነት እውቅና ልትሰጥ ነው! ስፔን ለፍልስጤም ነጻ ሀገርነት እውቅና ለመስጠት መዘጋጀቷን አስታወቀች።ማድሪድ እውቅናውን የምትሰጠው በመጪው ሀምሌ ወር መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ገልጸዋል። የመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝታቸውን በዮርዳኖስ የጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በኳታር እና ሳኡዲ አረቢያ በሚኖራቸው ቆይታ በጋዛው ጦርነት ዙሪያ ይመክራሉ መባሉን የስፔን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ከ27ቱ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ውስጥ ለፍልስጤም ነጻ ሀገርነት እውቅና የሰጡት ዘጠኙ ብቻ ናቸው።የስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ በአማን ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃለምልልስ፥ በርካታ የህብረቱ አባል ሀገራት ለፍልስጤም እውቅና እንዲሰጡ ግፊት እየተደረገ ነው ብለዋል። አየርላንድ፣ ማልታ እና ስሎቫኒያም እስራኤል በሃይል የያዘችው ዌስትባንክ እና የጋዛ ሰርጥ የፍልስጤም ሉአላዊ ግዛት መሆኑን በመቀበል እውቅና ለመስጠት መስማማታቸውን ሳንቼዝ ይፋ አድርገዋል። እስራኤል የአራቱ ሀገራት ለፍልስጤም እውቅና የመስጠት እቅድ “ለሽብርተኝነት የሚቀርብ ሽልማት” አድርጋ እንደምትመለከተውና የጋዛውን ጦርነት በንግግር ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት የሚያውክ ነው በሚል ተቃውሞዋን ማሰማቷን ሬውተርስ ዘግቧል። Via Alain @Addis_Mereja
Show more ...
14 832
4
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ108ሺ እስከ 305ሺ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ምስል ይፋ አደረገ! በባንኩ የሲስተም ማዘመኛ ሥራ ላይ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ያለአግባብ ከባንካችን የወሰዱትን ገንዘብ እንዲመልሱ እስከ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ መሠረት 10,857 የሚሆኑ ግለሰቦች ያለባቸውን ገንዘብ አጠናቀው መመለሳቸውን ባንኩ ገልጿል፡፡ ባንኩ "የተሰጠውን ተደጋጋሚ እድል ተጠቅመው ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦች አሉ ያለ ሲሆን ባንካችን ገንዘቡን ለማስመለስ በተከታታይ ስለሚወስዳቸው እርምጃዎች በተደጋጋሚ ባሳወቀው መሠረት እስካሁን ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን የመጀመሪያ ዙር ፎቶግራፍ በባንካችን ድረ-ገጽ እና የማህበራዊ ትስስር ገፆች ለማውጣት ተገደናል ብሏል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ባንካችን የተለያዩ ምክንያቶችን ግምት ውስጥ በማስገባት የገንዘብ መመለሻ ጊዜውን ለመጨረሻ ጊዜ እስከ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ያራዘመ በመሆኑ፣ ይህን የመጭረሻ እድል ተጠቅማችሁ ገንዘቡን እድትመልሱ እያሳሰብን፣ በተሰጠው የጊዜ ገደብ የማይመልሱትን ወደ ህግ የምናቀርብ መሆኑን በድጋሚ እናሳስባለን ብሏል፡፡ ከ108ሺ እስከ 305ሺ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ምስል ከዚህ በታች ባለው ሊንክ ይፋ አድርጓል። @Addis_Mereja
Show more ...
13 510
11
አቶ አድም ፋራህ በም/ል ጠ/ሚ ማዕረግ ተሾሙ! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቶ አደም ፋራህን ከመጋቢት 23/2016 ዓ.ም ጀምሮ በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ማስተባበሪያ ሃላፊ አድርገው መሾማቸውን ዳጉ ጆርናል ተሰምቷል። @Addis_Mereja
14 214
5
በአዲስ አበባ የሚገኙ ሁሉም የመሬት ይዞታ ማህደሮች ዲጂታላይዝ ተደርገዋል ተባለ! የአዲስ አበባ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በስድስት ወራት ውስጥ በሰራው የሪፎርም ስራ በከተማዋ የሚገኙ ሁሉም የይዞታ ማህደሮችን ዲጂታላይዝ ማድረጋቸውን አስታወቀ። የአዲስ አበባ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ አቶ ሲሳይ ጌታቸው ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ቢሮው ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በጋራ በመሆን ለስድስት ወራት የሪፎርም ስራ ሲሰራ ቆይቶል። በዚህም በ 11ዱም ክፍለከተሞች የሚገኙ 670 ሺህ 568 የይዞታ ማህደሮችን ዲጂታላይዝ የማድረግ እና እንደአዲስ ተቆጥረው እንዲታወቁና አዲስ ኮድ እንዲሰጣቸው በማድረግ ተደራጅቷል። በተካሄደው የሪፎርም ስራ ቢሮው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች የሚያዘምኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶች እንዲሁም የሚስተዋለውን ብልሹ አሰራርና ሌብነት ለመፍታት የሚያስችሉ የህግና መመሪያ የማሻሻል ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን 27 የሚሆኑ አገልግሎቶችን በኦንላይን መስጠት የሚያስችል ሲስተም ተግባራዊ እንደሚደረግም አስታውቀዋል። Via EPA
Show more ...
14 463
9
የነዳጅ ግብይት በሁሉም ባንኮች እንደሚጀመር የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ! በውስን የክፍያ አማራጮች ብቻ የነበረው የነዳጅ ግብይት በቀጣይ በሁሉም ባንኮች እንደሚጀመር የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል።የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር በቀለች ኩማ እንዳሉት÷ ከነዳጅ ግብይትጋር በተያያዘ በተገልጋዮችና ሌሎች ባንኮች የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት አገልግሎቱን ማስፋት አስፈልጓል፡፡ በዚህ መሰረትም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ እና በቴሌ ብር ብቻ ሲደረግ የነበረው የነዳጅ ግብይት ዲጂታል የክፍያ አማራጮችን በማስፋት ሌሎች ተጨማሪ ባንኮች እንዲካተቱ ይደረጋል ብለዋል። ይህ አሰራር መተግበሩ ደንበኛው በተመቸው የክፍያ አማራጭ አገልግሎቱን እንዲያገኝ ያስችለዋል ነው ያሉት፡፡አሰራሩን ለማስጀመር ረቂቅ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመው÷ ሥርዓቱ በቅርቡ ተጠናቅቆ ወደ ትግበራ እንደሚገባ አረጋግጠዋል፡፡አሰራሩ ተግባራዊ ሲደረግም የነዳጅ ግብይቶችን ሪፖርት በአንድ ማዕከል ለመከታተል እንደሚያግዝ ተናግረዋል። Via FBC
Show more ...
14 162
0
ተጠናቋል‼ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ የራሳቸውን ያልሆነውን ገንዘብ ከባንኩ ወስደው ሙሉ በሙሉ ያልመለሱ (በከፊል የመለሱ) 5166 ግለሰቦች የሚቀረውን ብር እንዲመልሱ የሰጠው የመጨረሻ ቀነ ገደብ ዛሬ ቅዳሜ 11:00 ላይ ተጠናቋል። ባንኩ ፤ ገንዘቡን የማይመልሱ ካሉ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ዘዴዎችን በመጠቀም ሙሉ ስማቸው፣ፎቷቸው፣ በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ በመውሰድ ወንጀል መጠርጠራቸውን በመግለፅ ለሚመለከታቸው የሕግ አካላትና ተቋማት እንዲሁም ለህዝብ እንደሚያሳውቅ አሳስቦ ነበር።ቀጣይ የሚሆነው እስካሁን አልታወቀም። @Addis_Mereja
16 561
8
የመስመር ማሻሻያ ስራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦቱ ይቋረጣል ነገ እሁድ መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ከጧቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 2016 ዓ.ም ድረስ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት የማሻሻያ ስራ ለማከናወን ሲባል በአዲስ አበባ ከተማ እንዳንድ አካባቢዎች የኃይል አቅርቦቱ ይቋረጣል ፡፡ በመሆኑም በአቃቂ ገበያ፣ ቤጂንግ ሆስፒታል፣ አዲስ መድሐኒት ፋብሪካ፣ መኸር ቃጫ ፋብሪካ፣ የሺ ቶታል መስጊድ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ አቃቂ ብረታ ብረት ማቅለጫ እና አካባቢዎቻቸው የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉና በከፊል ስለሚቋረጥ ክቡራን ደንበኞቻችን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡ Via:- የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት @Addis_Mereja
16 513
9
ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት እያቀረበች ያለውን የኤሌክትሪክ ሀይል እስከ ደቡብ አፍሪካ ድረስ ለማድረስ እየሰራች ነው ተብሏል። ኢትዮጵያ ለጎረቤት አገራት እያቀረበች ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል የበለጠ ለማስፋፋት እየሰራች መሆኑን ተነግሯል። ኢትዮጵያ ለሱዳን፣ ለጅቡቲና ለኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል እያቀረበች መሆኑን የተገለጸ ሲሆን ለውጭ ገበያ የሚቀርበውን የኤሌክትሪክ ኃይል እስከ ደቡብ አፍሪካ የማድረስ ዕቅድ መያዙን ነው የተነገረው። በቅርቡም ለታንዛኒያ ኃይል ለማቅረብ መግባባት ላይ መደረሱን እና ደቡብ ሱዳን፣  ኡጋንዳና ሩዋንዳ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመውሰድ ፍላጎት ማሳየታቸውን ተጠቁሟል። ይህንንም ተከትሎ ኢትዮጵያ ከሀገራቱ ጋር ንግግር መጀመሯን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ገልጿል። @Addis_Mereja
15 012
3
በአምቦ ወረዳ የ90 ዓመት አዛውንት አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ! በምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ወረዳ ኢላሙ ጎሮሙጢ የተባለ አካባቢ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በእስራት መቀጣጡት የምዕራብ  ሸዋ ዞን  ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታውቋል፡፡  የምዕራብ ሸዋ ዞን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት  በተለይም ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን የላከው መረጃ እንደሚያመላክተው ተከሳሽ ለቴራ ቀና የተባለው ግለሰብ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 7 ሰዓት ላይ የ90 ዓመት ኣዛውንት በመኖሪያ ቤታቸው ተኝተው ባሉበት ቤታቸውን ሰብሮ በመግባት አስገድዶ የመድፈር ወንጀል እንደፈጸመ በማስረጃ ተረጋግጧል፡፡ ተከሳሽ በእድሜ የደከሙ ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ አዛውንትን በጉልበት አስገድዶ መድፈሩ ፖሊስ በህክምና ማስረጃ ያረጋገጠ እና የምርመራ መዝገቡን አጠናክሮ ለ ዓቃቢህግ መላኩን ብስራት ተመልክቷል ፡፡ በዚኅም  ዓቃቢ ህግ  ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ ተመልከቶ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ መሰረት ክስ መስርቷል፡፡ክሱን ሲመለከት የነበረው የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ለቴራ ቀና በስምንት ዓመት እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ የተላለፈበት መሆኑን የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡ Via Bisrat FM
Show more ...
16 989
59
12 788
12
#ኢፍጧር በመስቀል አደባባይ ነገ ስለ ሚካሄድ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆነዋል። በነገው ዕለት በአዲስ አበባ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመስቀል አደባባይ ከሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር መርኃ ግብር  ጋር ተያይዞ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህም መሰረት፡- - ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን - ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ   ኦሎምፒያ - ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ  አሽከርካሪዎች ለከባድ መኪናዎች  አጎና ሲኒማ፤ለሌሎች ተሸከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ ጋር ዝግ የሚደረግ ይሆናል፡፡ - ከጦር ኃይሎች በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሸከርካሪዎች  በተለምዶ አጠራሩ ክቡ ባንክ አካባቢ - ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ሐራምቤ መብራት ላይ - ከ4 ኪሎ በውጭ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛው ላይ - ከአዋሬ አካባቢ በካሳንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ኢንተርኮንትኔታል አካባቢ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ የኢፍጧር ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ ዝግ ይደረጋሉ። በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅመ ሰዓታት ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ የተከለከለ ነው ተብሏል። ኅብረተሰቡ ማንኛውም ዓይነት አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በፖሊስ የመረጃ ስልኮች 0111 11 01 11 እና ነፃ የስልክ መስመር 991 ላይ በመደወልና መረጃ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።
Show more ...
17 769
37
Last updated: 11.07.23
Privacy Policy Telemetrio