Best analytics service

Add your telegram channel for

  • get advanced analytics
  • get more advertisers
  • find out the gender of subscriber
Category
Channel location and language

audience statistics TIKVAH-MAGAZINE

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።  #ኢትዮጵያ  ያግኙን +251913134524 
196 567-22
~35 896
~4
18.37%
Telegram general rating
Globally
4 557place
of 78 777
23place
of 396
In category
21place
of 280

Subscribers gender

Find out how many male and female subscibers you have on the channel.
?%
?%

Audience language

Find out the distribution of channel subscribers by language
Russian?%English?%Arabic?%
Subscribers count
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

User lifetime on the channel

Find out how long subscribers stay on the channel.
Up to a week?%Old Timers?%Up to a month?%
Subscribers gain
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

Since the beginning of the war, more than 2000 civilians have been killed by Russian missiles, according to official data. Help us protect Ukrainians from missiles - provide max military assisstance to Ukraine #Ukraine. #StandWithUkraine
ግብርና ሚኒስቴር ፀረ ተባይ እና የግብርና ኬሚካሎችን የሚረጩ አውሮፕላኖችን በኪራይ ሊያቀርብ ነው ተባለ የግብርና ሚኒስቴር ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ለማግኘት በማሰብ እርሻዎች ላይ ፀረ ተባይ እና ሌሎች የግብርና ኬሚካሎችን ለመርጨት የሚያስችሉ አውሮፕላኖችን በኪራይ ሊያቀርብ መሆኑን ሪፖርተር አስነብቧል። ሚኒስቴሩ በሀገሪቱ በምስራቅ እና ሰሜን የአንበጣ ወረራ መከሰቱን ተከትሎ 5 አውሮፕላኖች መግዛቱን ሲገልፅ የኢንሹራንስ እና የጥገና ወጪዎችን እንዲሁም ተባዮችን ለመቆጣጠር የሚያስችል አቅም ለማዳበር አውሮፕላኑን ለግሉ ዘርፍ ሊያከራይ እንደሆነ ገልጿል። የግብርና ሚኒስቴር ግርማ አመንቴ እነዚህን አውሮፕላኖች ለግሉ ሴክተር እና ለትልልቅ እርሻዎች አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችለውን አሰራር ለመዘርጋት መመሪያ መዘጋጀቱን የገለፁ ሲሆን አገልግሎቱ በቅርቡ ይጀምራል ብለው እንደሚጠብቁ ገልፀዋል።
Show more ...
13 646
8
#ጥቆማ የአውራ አምባ ማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን በ Branch Manager, Accountant, Coustomer service officer እና Cahshier የስራ መደቦች ላይ ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። በመሆኑም አመልካቾች የስራ መደቦቹ የሚፈልጉትን ልምድ እና መስፈርት ከተያያዘው ምስል ላይ በመመልከት በአዲስ አበባ ለገሃር አቅራቢያ በሚገኘው የአማራ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ ሁለተኛ ፎቅ ላይ በመገኘት ማመልከት እንድትችሉ ጥቆማ ቀርቧል። ለተጨማሪ መረጃ በ 251918317021 ወይም 251955991544 መደወል እንደምትችሉም ተገልጿል።
15 941
35
ለዓይነ ስውራን፣ መጻፍ እና ማንበብ ለማይችሉ ምእመናን የሚያገለግል የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ የድምፅ ቅጂ ተመረቀ ለዓይነ ስውራን፣ መጻፍ እና ማንበብ ለማይችሉ ምእመናን እንዲሁም ለአብነት ተማሪዎች የሚያገለግል በዘመናዊ መሣሪያ የተዘጋጀ የአማርኛ እና የግእዝ የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ የድምፅ ቅጂ ተመረቀ። የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ይህ የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ የድምፅ ቅጂ እንግዶች እና የሀይማኖት አባቶች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በቦሌ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል ተመርቋል። የድምጽ ቅጂ መሣሪያው አገልግሎት ላይ እንዲውል ከ 11 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሲሆን ከ 26 በላይ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት እና ባለሙያዎች በሥራው ላይ መሳተፋቸው ተገልጿል። የድምፅ መሣሪያውን አዘጋጅቶ ለማጠናቀቅ ሁለት ዓመታትን የወሰደ ሲሆን አጠቃላይ ወጪው "Faith comes by hearing" በተሰኘ ዓለም አቀፍ ተቋም እንደተሸፈነ ተጠቁሟል። ዘገባው የማህበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ነው።
Show more ...
14 899
9
#Update: በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን በመመለስ ስራ እስካሁን ከ25,800 በላይ በላይ ዜጎች መመለሳቸው ተነገረ ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ25,800 በላይ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ እንደተቻለ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። በዛሬው እለትም 1 ሺህ 147 ዜጎች ከሳውዲ አረቢያ ሲመለሱ  ከተመለሱት 1 ሺህ 147 ዜጎች ውስጥ 1046 ወንዶች፣ 80 ሴቶች እና 21 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 54 እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።
13 277
1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 50 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገበትን የሀገር ውስጥ በረራ ማስተናገጃ ተርሚናል አስመረቀ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የማስተናገድ አቅሙ ከበፊቱ ከሁለት እጥፍ በላይ የሚልቅ የሀገር ውስጥ በረራ ማስተናገጃ ተርሚናልን በዛሬው እለት አስመረቀ። ተርሚናሉ የመንገደኞች አገልግሎት ጥራትን ከፍ በማድረግና የጎብኚዎችን ምቾት በመጨመር ለቱሪዝም ዘርፍ ተወዳዳሪነት አበርክቶ እንደሚኖረው የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ገልፀዋል። በምርቃት ስነ-ስርአቱ ላይ የቱሪዝም ሚንስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ እና ሌሎች የመንግስት ስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል ተብሏል።
11 908
3
#Tecno የሞባይል ቴክኖሎጂን ጨምሮ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አምራች የሆነው እና ከ70 በላይ ሀገራት  ምርቶቹን በስፋት የሚያቀርበው ቴክኖ አዲስ የሞባይል ቴክኖሎጂ ውጤት የሆነውን ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴል በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት አስተዋወቀ። አዲሱ ካሞን 30 ፕሮ 5G የሶኒ(SONY) የካሜራ ሴንሰር ቴክኖሎጂን ጨምሮ የተለያዩ የቴክኖ ምርምር ውጤት የሆኑ የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን አካቶ የተመረተ ሞዴል ነው። የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ማርኬቲንግ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ሰኢድ አራጋው በዝግጅቱ ላይ እንደተናገሩት ‘’ ኢትዮ ቴሌኮም እና ቴክኖ ሞባይል በጋራ በመሆን ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ይሰራሉ’’ ብለዋል።  
Show more ...
11 492
5
🏠 ለ 1 ወር ብቻ የሚቆይ ልዩ የበአል ቅናሽ !! 📌ጊዜዉን የሚመጥን አስተማማኝ እና ትርፋማ የሚያደርግዎትን የኢንቨስትመንት አማራጮችን በብስራተ ገብርኤል ,በቦሌ ደምበል, በገርጂ መብራት ሃይል,በጃክሮስ,በአያት,በመካኒሳ አቅርበንልዎታል። 📌በዚህ ወቅት የገንዘብ የመግዛት አቅም በወደቀበት ዘመን ተሻጋሪ አማራጮችን ማየት ብልህነት ብቻ ሳይሆን ትልቅነትም ጭምር ነው። 📌 ከዘመን ዘመን እንደደመቁ እና እንዳማሩ የሚዘልቁ ቅንጡ አፓርትመንት ቤቶችን 15% ቅድመ ክፍያ ስንጋብዝዎ በደስታ ነው። 📌ግንባታቸው 100% ያለቀ እንዲሁም በግንባታላይ ያሉ ቤቶችንና የንግድ ሱቆችን 📌 የባንክ ብድር የተመቻቸለት 📲NaN 📲NaN
13 621
0
ባለፉት አስራ ስድስት ቀናት በጉጂ፣ በምዕራብ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ በተከሰረተ ጎርፍ የ14 ሰዎች ህይወት አለፈ ባለፉት 16 ቀናት በምዕራብ ጉጂ፤ በሲዳማ፤ ማእከላዊ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ14 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ106 ሺ ሰዎች በላይ መፈናቀላቸውን የአውሮፓ ኮሚሽን የአስቸኳይ ድጋፍ ማስተባበሪያ ማዕከል ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል፡፡ በሪፖርቱ መሰረት ፦ - በምእራብ ጉጂ 120 ሺ 481 ሰዎች በጎርፍ ተጠቅተዋል፡፡ በተጨማሪም 102 ሺ 128 ሰዎች ተፈናቅለው የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተመላክቷል፡፡ ከ 3ሺ በላይ ቤቶች በከፊል እና ሙሉ ለሙሉ መውደማቸው ሲገለጽ ከፍተኛ የምግብ ዋስትና ችግር እንዳለ ተመላክቷል፡፡ - በደቡብ ኢትዮጵያ ደግሞ 4ሺ ሰዎች በጎርፍ ተጠቅተው የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተጠቁሟል፡፡ - በማእከላዊ ኢትዮጵያ 4ሺ 65 ሰዎች ሲፈናቀሉ የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተመላክቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በግጭቶችና ከአየር ንብረት ጋር በተያያዘ በሚደርሱ ድንገተኛ አደጋዎች ምክንያት አፋጣኝ ምላሽ ለማድረግ የሚያስችል የአቅም ውስንነት እንዳለ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አሳውቋል፡፡ ፎቶ፦ ፋይል
Show more ...
21 921
14
#ጥቆማ የኢትዮጵያ ደም እና ህብረ ህዋስ ማዕከል በነገው እለት ግንቦት 10/ 2016 ዓ/ም ስታዲየም በሚገኘው የቀይ መስቀል ማህበር ጊቢ ውስጥ ከጠዋቱ 4 እስከ 11 ሰዓት የደም ልገሳ መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን ለቲክቫህ በላከው መረጃ ገልጿል። ስለሆነም በመርሃግብሩ ላይ እንድትሳተፉ ጥሪ አቅርቧል። ደም ሁሌ ተፈላጊ እንዲሆን የሚያረጉት ምክንያቶች ምንድናቸው ? - የተፈጥሮ እና የ ሰው ሰራሽ አደጋዎች መጨመር - የድንገተኛ ወረርሽኝ መከሰት - ዘመናዊ የህክምና አገልግሎት መስፋፋት - የደም እና የደም ተዋፅኦ የአገልግሎት ጊዜ አጭር መሆን/ ፕላስማ 1 አመት - ደም አማራጭ/መትክ/ የሌለው መድሀኒት መሆኑ  - ደም በ አይነት ብቻ ለ ታካሚው የሚሰጥ መሆኑ ደም የሚያስፈልጋቸው እነማን ናቸው? - የደም ማነስ ህመምተኞች - ከፍተኛ የቀዶ ህክምና የሚስፈልጋቸው እና የካንሰር ህመምተኞች - በወሊድ ወቅት ብዙ ደም የሚፈሳቸው እናቶች - በተለያዩ የጤና ችግሮች ሳቢያ እንደተወለዱ ደም ሚፈሳቸው ህፃናት - በዘር ውርስ የሚመጡ የደም መድማትና መሟሸሽ ችግሮች ያሉባቸው። ደም ከመለገስ የሚገኙ ጥቅሞች ምንድናቸው? - የደም አይነት ያለ ክፍያ ማወቅ ይቻላል። - ሰዎች በ ደም እጥረት ምክንያት አይሞቱም። - የጤና ጠቀሜታ እንዳለው በ አንዳንድ ምርምሮች ሲገለፅ ማለትም ከ ሌሎች ደም ከማይለግሱት የተሻለ በ heart attack  የመጋለጣቸው አድል አነስተኛ ነው። ለበለጠ መረጃ፦ በ NaN ይደውሉ
Show more ...
22 703
10
በአሶሳ ዞን ባምበሲ ወረዳ ሁለት የ8 አመት ህፃናትን የደፈረ ጎልማሳ በ10 አመት ፅኑ እስራት ተቀጣ በአሶሳ ዞን ባምበሲ ወረዳ መንደር 44 ቀበሌ በሁለት የ8 አመት ህፃናት ላይ የግብረ- ስጋ ድፍረት ወንጀል የፈፀመ የ41 አመት ጎልማሳ በ10 አመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን የአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ። ተከሳሽ አብዱ ወዚር መሀመድ ነዋሪነቱ አሶሳ ዞን ባምበሲ ወረዳ መንደር 44 ቀበሌ ሲሆን በጥር 3/2016 ዓ/ም ከቀኑ 9 ሰዓት በአካባቢው የማሽላ ሰብል ማሳ ውስጥ በመደበቅና ህፃናቱን " ጥንቅሽ ልስጣችሁ ብሉ " ብሎ በመጥራት ወደ ውስጥ ካስገባቸው በኋላ ሁለቱንም በሀይል አስሮ የግብረ ስጋ- ድፈረት መፈፀሙ ተገልጿል። በተጨማሪም በህፃናቱ ላይ ያደረሰባቸውን ሁለንተናዊ ጉዳትም ለማንም ትንፍሽ እንዳይሉ አስፈራርቶና በገንዘብ አታሎ ከቦታው መሰወሩ ተጠቁሟል። በጉዳዩ ዙሪያ ከአካባቢው ህብረተሰብ ጥቆማና  መረጃ የደረሰው ፓሊስም ወንጀለኛውን በቁጥጥር ስር አውሎ በሰውና የሰነድ ማሰረዳዎች አረጋግጦ ውሳኔ እንድያገኝ ለባምበሲ ወረዳ ፍርድ ቤት አቅርቧል። የወረዳው ፍርድ ቤትም የክስ መዝገቡን ዝርዝር ማስረጃ በመመርመር አቃቢ ህግ በከሰሰው ወንጀልና ባቀረባቸው የሰውና የህክምና ማስረጃዎች መሰረት ግለሰቡን በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ደ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 60(ሐ)እና 627(1)ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ጥፍተኛ በማድረግ በ10 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል። ይሁን እንጅ ግለሰቡ የወረዳው ፍርድ ቤት ሚያዝያ 17/2016 ዓ.ም የወሰነበት ውሳኔ ላይ ቅር በመሰኘት ሚያዝያ 19/2016 ዓ.ም ይግባኝ ብሎ ጉዳዩ በአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኩል እንዲታይ ተጠይቋል። የባምበሲ ወረዳ ፍርድ ቤት የሰጠውን የእስር ውሳኔ ሲያከራክርና ሲመለከት የነበረው የአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ከትላንት በስቲያ በዋለው ሁለተኛ የምድብ ወንጀል ችሎት  የ10 አመት ፅኑ እስራት ውሳኔውን " በአስተማሪነቱ በማፅደቅ መዝገቡን ዘግቷል" በማለት የአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አሳውቋል።
Show more ...
22 419
15
በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ዋርካ አካዳሚ የተሰኘ አንደኛና መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አቤም አቤም ሆቴል ጀርባ ከካባቢ፣ ዋርካ አካዳሚ የተሰኘ አንደኛና መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዛሬው እለት ተመረቀ። አካዳሚው በ2017 የትምህርት ዘመን ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍሎችን በመክፈት ትምህርት እንደሚጀመር ተጠቁሟል። በተጨማሪም ትምህርት ቤቱ የበለጠ ውጤት የሚያመጡ ተማሪዎችን ለማበረታታት በየዓመቱ በሚኖር መስፈርት መሰረት የአንድ ዓመት የትምህርት ቤት ክፍያ ስኮላርሽፕ እንደሚሰጥ የትምህርት ቤቱ ኃላፊዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጠቅሰዋል።
21 472
15
" በሀገር ውስጥ ለ47 ሺ ከሀገር ዉጭ ደግሞ ለ2 ሺ 583 ወጣቶች የስራ እድል ፈጥሬአለሁ " - የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች  ልማት ቢሮ ከሀገር ውስጥ ከ47 ሺ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች ከሀገር ዉጭ ደግሞ ለ2 ሽህ 583 ወጣቶች የስራ እድል መፍጠሩን አስታወቀ። በዚህም ቢሮው እቅዱን ከ100 ፐርሰንት በላይ ማሳካቱን ሲገልፅ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ከሰላሳ ሽህ በላይ የስራ እድል እንዲፈጠር ለመስራት በእቅድ መያዙን ገልጿል። ለዚህ ሲባል በክልሉ አምስት መአከላት ማለትም በአራቱ ዞኖችና በሀዋሳ ከተማ ለርካታ ወጣቶች የማይንድ ሴት ስልጠና መሰጠቱ ሲገለፅ ከዚህ ቀደም በጥቂት ባለሀብቶች ተይዞ የቆየው የመአድን ዘርፍ አሁን ላይ በዲግሪና በዲፕሎማ  ለተመረቁ ወጣቶች መሰጠቱ ተገልጿል።
Show more ...
19 843
5
🏠 ለ 1 ወር ብቻ የሚቆይ ልዩ የበአል ቅናሽ !! 📌ጊዜዉን የሚመጥን አስተማማኝ እና ትርፋማ የሚያደርግዎትን የኢንቨስትመንት አማራጮችን በብስራተ ገብርኤል ,በቦሌ ደምበል, በገርጂ መብራት ሃይል,በጃክሮስ,በአያት,በመካኒሳ አቅርበንልዎታል። 📌በዚህ ወቅት የገንዘብ የመግዛት አቅም በወደቀበት ዘመን ተሻጋሪ አማራጮችን ማየት ብልህነት ብቻ ሳይሆን ትልቅነትም ጭምር ነው። 📌 ከዘመን ዘመን እንደደመቁ እና እንዳማሩ የሚዘልቁ ቅንጡ አፓርትመንት ቤቶችን 15% ቅድመ ክፍያ ስንጋብዝዎ በደስታ ነው። 📌ግንባታቸው 100% ያለቀ እንዲሁም በግንባታላይ ያሉ ቤቶችንና የንግድ ሱቆችን 📌 የባንክ ብድር የተመቻቸለት 📲NaN 📲NaN
18 204
4
ስትጠብቁት የነበረው የ12 ክፍል ማትሪክ ፈተና አጋዥ አፕሊኬሽናትችን አሁን playstore ላይ ይገኛል። ዳውንሎአድ እና Upgrade አድርጎ መጠቀም ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ። ✅በነጻ ለውስን ቀናት ✅አዲሱን ስር አተ ትምህርት ያካተተ ✅አጫጭር ኖቶችና አጋዥ ቪድዮዎች የያዘ አሁኑኑ ይሞክሩት!!!!!!!!! ለማውረድ ይህን ማስፈንጠሪያ መጠቀም ይቻላል ➝ በተጨማሪም የተለያዩ ማህበራዊ ገፆቻችን ቤተሰብ ይሁኑ። | | | | |
20 008
37
ለፆታዊ ጥቃት ሰለባዎች ባደረገችው ድጋፍ ከካናዳው ድርጅት ዕውቅና የተሰጣት ሲስተር ካህሳ ሀጎስ . . . በአዲግራት ሆስፒታል ነርስ የሆነችው ሲስተር ካህሳ ሀጎስ በትግራይ ጦርነት ወቅት ጾታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች ላደረገችው ሙያዊና ሰብአዊ ድጋፍ ግሎባል አፌይርስ ከተባለው የካናዳ ድርጅት ሽልማት ተበርክቶላታል። ሲስተር ካህሳ ሀጎስ፤ የካናዳ ድርጅት ከተባበሩት መንግስታት ጋር በመተባበር የሚያበረክተው “ሰላምና ደህንነት በሴቶች” የተሰኘው ሽልማት ተቀባይ ሆናለች። ካህሳ “ከ2013 ጀምሮ ላበረከትኩት አስተዋጽዖ የተሰጠኝ ነው። ለሁለት ዓመታት ያህል የፆታዊ ጥቃት ሰለባዎችን እንከባከብ ነበር” ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። የትግራይ ኃይሎች እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለሁለት ዓመታት ባደረጉት ጦርነት ምክንያት በርካታ ሴቶች፣ እናቶች እና ሕፃናት የፆታዊ ጥቃት ሰለባ መሆናቸውን በርካታ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች አረጋግጠዋል። ጦርነቱ ሲቀሰቀስ ሲስተር ካህሳ ሀጎስ በአዲግራት ሆስፒታል የእናቶች እና ህጻናት እንክብካቤ ክፍል አስተባባሪ ሆና ትሰራ ነበር። ውጊያው ሲባባስ የጾታዊ ጥቃት ሰለባ ሆነው ወደ ሆስፒታል የሚመጡ ሴቶች እና እናቶች ቁጥር እየጨመረ መጣ። ሲስተር ካህሳ እንደምትለው ጦርነቱን ተከትሎ ከ4 ሺህ በላይ ተጎጂዎች ወደ አዲግራት ሆስፒታል መጥተው ሪፖርት አድርገዋል። ሲስተር ካህሳ በጦርነቱ ምክንያት ተጎጂ ለሆኑ ከ400 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ቤት ተከራይታ፤ ሙያዊ ክትትልና ድጋፍ ማድረጓ ተነግሯል። እሷ ተጎጂዎችን ለመርዳት በምታደርገው ጥረት በሆስፒታሉ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች የሚረዱበት የሥነ-ልቦና፣ የሥነ-አእምሮ እና የሥነ-ተዋልዶ ማዕከል እንዲከፈት ተደርጓል። ለአበርክቶዋም አፌይርስ ከተባለው ድርጅት እውቅና ማግኘቷ ነው የተገለፀው።
Show more ...
28 619
14
ከ12 ሀገራት 122 ተሳታፊዎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እና መፍትሄዎችን የሚያቀርቡቡት የንግድ ትርኢት ተከፈተ ፕራና ኢቨንትስ እና የጀርመኑ ፌርትሬድ በጋራ ያዘጋጁት እና ከ12 ሀገራት 122 ተሳታፊዎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና መፍትሄዎችን ለኢትዮጵያ ገበያ የሚያቀርቡቡት 6ኛው አግሮ ፉድ ፕላስት ፕሪንት ፓክ ኢትዮጲያ የንግድ ትርኢት  ተከፈተ። የንግድ ትርኢቱ ከግንቦት 8-10 /2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ የሚቆይ ሲሆን በግብርና፣ በምግብና መጠጥ ግብዓትና ማቀነባበሪያ ቴክኖሎጂ፣ እንዲሁም በፕላስቲክ ህትመት እና የማሸጊያ ቴክኖሎጂ እና መፍትሄዎች ላይ ትኩረት ያደረጉ ኩባንያዎች ይሳተፉበታል ተብሏል። ተሳታፊዎቹ ከቻይና፣ ኢትዮጵያ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ህንድ፣ ጣሊያን፣ ኬንያ፣ ታይዋን፣ ታይላንድ፣ ቱርክ፣ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና እንግሊዝ የተውጣጡ ሲሆን 122 ተሳታፊዎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና መፍትሄዎችን ለኢትዮጵያ ገበያ ያቀርባሉም ነው የተባለው።
Show more ...
25 517
36
ትምሕርት ቤቶች በተዘጉባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ሴት ተማሪዎች በግዳጅ እየተዳሩ ነው ተባለ በአማራ ክልል የሰላም እጦት ሰበብ በአንዳንድ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው፣ ሴት ተማሪዎች ወደ ጋብቻ በግዳጅ እየገቡ እንደሆነ ነዋሪዎችና ወላጆች መናገራቸውን ዶይቼ ቬለ ዘግቧል። በክልሉ ባለፉት 9 ወራት 1132 መዳር ከሚገባቸው እድሜ በታች የሆኑ ሴቶች ለመዳር መዘጋጀታቸውን ጥቆማ እንደደረሳቸው የአማራ ክልል ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የህፃናት መብትና ድህንነት ማስጠበቅ ዳይሬክተር አቶ አሻግሬ ዘውዴ ተናግረዋል። በዚህም መሰረት የ335ቱ ተማሪዎች የጋብቻ ዝግጅት እንዲቋረጥ የተደረገ ሲሆን 216 ደግሞ የእድሜ ምርመራ ተደርጎ እድሜያቸው ባለመድረሱ የትዳር ዝግጅቱ መቋረጡን ዳይሬክቱሩ ጠቁመዋል። ያም ሆኖ 192 ሴቶች ከእድሜያቸው በታች መዳራቸውንና ድርጊቱን ለመከላከል አሁን ያለው የፀጥታ ሁኔታ አንድ አንቅፋት እንደሆነም ተናግረዋል። በ9 ወሩ 41 ጠለፋ በክልሉ ሲመዘገብ 354 ደግሞ አስገድዶ መድፈር ሪፖርት እንደተደረገና በድርጊቱ የተሳተፉ 79 ግለሰቦች ከ3 አስከ 14 ዓመት በሚደርስ የፍርድ ቤት የእስር ቅጣት እንደተወሰነባቸውም ነው የተገለፀው።
Show more ...
24 723
18
ስልኮትን ለመቀየር አስበዋል?   አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል📱ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ 📞 NaN 📩 inbox 📍አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ 📨 ክፍለ ሀገር ላላቸሁ ደንበኞችቻችንም በ DHL መላክ ጀምረናል
23 712
6
#Big5Ethiopia ቢግ ፋይቭ ኮንስትራክት ኢትዮጵያ አውደ ርዕይ ያካተተው የሲፒዲ ነጥብን የሚያስገኘው መድረክ ስድስት የሙያ ዘርፎችን የያዘ ነው። እነዚህም ቴክኖሎጂ፣ የፕሮጀክት አስተዳደር፣ አርክቴክቸርና ንድፍ፣ ዘላቂነት(ሰስተነብሊቲ)፣ ምህንድስና እና መሠረተ ልማት ናችው። ሁሉም ውይይቶች በየራሳቸው ብቁ ባለሙያዎች የሚመሩ ሲሆን፣ ፋይዳ ያላቸው እይታዎችንና አመለካከቶችን ያጋራሉ። የውሃ አቅርቦት መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች፣ ሞጁላር ግንባታ በዲጅታል ንድፍ ልምምድ ውስጥ፣ የመገኛ ቦታ(geospatial) ቴክኖሎጂና ቢም እንዲሁም አርክቴክቸር በከተማ ቅየሳ ውስጥ ያለው ሚና፣ ከሚዳሰሱ ርዕሶች መካከል ይገኛሉ። በነጻ ለመጎብኘትና ለመታደም አሁኑኑ ይመዝገቡ፡- የሁነቱን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ፡-

animation.gif.mp4

26 120
6
ቦይንግ የ346 ሰዎችን ህይወት በቀጠፈው የ737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ ክስ ሊመሰርትበት እንደሚችል ተገለፀ በኢትዮጵያው አየር መንገድ እና የኢንዶኔዥያው የ737 ማክስ 9 አውሮፕላን አደጋዎች የ346 ሰዎችን ህይወት በቀጠፈው አደሳ ምክንያት ቦይንግ ላይ ክስ ለመመስረት እያጤነ እንደሆነ የአሜሪካ የፍትህ መስሪያ ቤት አስታወቀ። ቦይንግ የሚያመርታቸውን አውሮፕላን ምርቶች ደኅንነት እና ጥራት ለማስጠበቅ ከ3 ዓመት በፊት ከአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ጋር የገባውን የቁጥጥር መርሃ ግብር ስምምነት መጣሱንም መስሪያ ቤቱ ስለመግለፁ ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል። ቦይንግ ስምምነት ጥሷል የተባለውን ክስ አስተባብሏል። ይህ አስከፊ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ በኢትዮጵያው 157 እንዲሁም በኢንዶኔዥያው አየር መንገድ 189 ሰዎች ህይወት መቅጠፉ ይታወሳል።
31 574
13
የፌደራል መንግሥት በኤሌክትሪክ እና በውሃ አገልግሎት ላይ ቫት የሚጥል ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ አቀረበ የኤሌክትሪክ እና የውሃ አገልግሎት በገደብ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እንዲከፈልባቸው የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ። ከታክሱ ነጻ የሚሆኑት የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ ከሚወሰን በታች የኤሌክትሪክ እና ውሃ ፍጆታ ያላቸው እንደሆኑ ተገልጿል። አዋጁ ሲጸድቅ ለሁለት አስርት ዓመታት በስራ ላይ ቆየውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ እና ከዛ በኋላ እሱን ለማሻሻል ሁለት ጊዜ የወጡትን የማሻሻያ አዋጆች ሙሉ በሙሉ የሚሽር ነው ተብሏል። “አነስተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል ያለበትን ወጪ ለማርገብ ሲባል” የኤሌክትሪክ እና የውሃ አገልግሎት ከታክሱ ነጻ ተደርገው እንደነበር ሲገለፅ ረቂቁ “የተጨማሪ እሴት ታክስ ከሚታይበት ጉድለት አንዱ እና ዋነኛው በርካታ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ከታክሱ ነጻ መደረጋቸው ነው” ይላል። በረቂቅ አዋጁ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ በማድረግ የተሰጠውን “ልዩ መብት” እንደገና በመፈተሽ ማስተካከያዎች መደረጋቸውን ማብራሪያው ይገልጻል። ከታክስ ነጻ ተደርገው አሁን ታክስ እንዲከፈልባቸው ከተደረጉ አግልግሎቶች መካከል የውሃ እና ኤሌክትሪክ እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎቶች ይገኙበታልም ተብሏል። በስራ ላይ ያለው አዋጅ የኤሌክትሪክ፣ የኬሮሲን [ናፍጣ] እና የውሃ እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎትን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ እንዲሆኑ እድርጎ ነበር። ይህን አዋጅ የሚሽረው አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ግን የውሃ የኤሌክትሪክ፣ የውሃ እና የትራንስፖርት አገልግሎቶች በገደብ ታክስ እንዲከፈልባቸው አድርጓልም ነው የተባለው። Credit: BBC Amharic
Show more ...
33 332
76
የፕላስቲክ አምራቾች የወረቀትና የጨርቅ ከረጢቶችን በአፋጣኝ ማምረት እንዲጀምሩ ማሳሰቢያ ተሰጠ አካባቢን ሊበክሉ የሚችሉ ስስ ፕላስቲኮችን የሚያመርቱ ድርጅቶች የአካባቢ ብክለትን የሚቀንሱ የወረቀትና የጨርቅ ከረጢቶች በአፋጣኝ ማምረት እንዲጀምሩ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አሳሰበ፡፡ ፕላስቲክ በማምረት የተሰማሩ ድርጅቶችና ባለቤቶች ከተፈቀደላቸው 0.03 ማይክሮ ሜትር በታች ሲያመርቱ ከተገኙ፣ ከመዝጋታቸው ባሻገር፣ ከሦስት ዓመት እስከ አሥር ዓመት የእስር ቅጣት እንደሚያስከትልባቸው ሪፖርተር አስነብቧል። በተጨማሪም ለኅብረተሰቡ ዳቦ የሚያከፋፍሉና ሌሎች ሸቀጦችን በፕላስቲክ ምርቶች ጠቅልለው የሚሸጡ ቸርቻሪዎችም ሆኑ አከፋፋዮች፣ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ይደረጋል ተብሏል። ሸማቾች ማንኛውንም ዕቃ ሲሸምቱ የፕላስቲክ ውጤቶችን ከመጠቀም ይልቅ፣ ከወረቀትና ከጨርቅ የተሠሩትን መጠቀም ይገባል በማለት ባለስልጣኑ አመልክቷል።
Show more ...
28 858
95
ስልኮትን ለመቀየር አስበዋል?   አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል📱ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ 📞 NaN 📩 inbox 📍አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ 📨 ክፍለ ሀገር ላላቸሁ ደንበኞችቻችንም በ DHL መላክ ጀምረናል
27 048
9
❇️ ሰምተዋል ? ❇️ የትርፋማው የአያት አክሲዮን ሽያጭ ሊጠናቀቅ ነው :: ❇️ በ2014 ዓ.ም 44% እንዲሁም በ2015 ዓ.ም 51.38% የአክሲዮን ትርፍ ለባለ አክሲዮኖች አከፋፍሏል ❇️ የአንድ ሚሊዮን አክሲዮን የነበራቸው በ2015 ዓ.ም ብቻ 513,800 ብር አትርፈዋል ❇️ ከ112,500 ብር ጀምሮ የአክሲዮን ባለቤት በመሆን በቶሎ የትርፍ ተካፋይ ይሁኑ ❇️ አክሲዮኑን በገዙ ከመጀመሪያው ወር ጀምሮ የትርፍ ተካፋይ ይሁኑ ❇️ ትርፋማ የሆነውን የአያት አክሲዮንን ለእርስዎ ፣ ለታዳጊ ልጅዎ  ፣ ለቤተሰብዎ እና ለወዳጅ ዘመድዎ በስጦታ ያበርክቱ ❇️ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባላችሁበት ሆናችሁ በወዳጆቻችሁ በኩል መግዛት ትችላላቹህ ⏱📞 ☎️ አሁኑኑ በ NaN በቀጥታ ወይንም በቴሌግራም በዋትሳፕ ይደውሉ
25 178
11
በኢትዮጵያ 95 በመቶ የሚሆኑት የቴሌቭዥን ተጠቃሚዎች በኢትዮ-ሳት ስርጭት እያገኙ መሆኑ ተገለፀ በኢትዮጵያ ከ18.2 ሚሊዮን ቲቪ ተጠቃሚዎች መካከል 17 ሚሊዮን ወይም 95 በመቶ የሚሆኑት በኢትዮ-ሳት ስርጭት እያገኙ መሆኑን የዓለም አቀፉ የሳተላይት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አቅራቢ (SES) አስታወቀ። በኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ተጠቃሚዎች ቁጥር በ 2017 ከነበረበት በ400% አድጎ ተጠቃሚዎቹ 18.2 ሚሊዮን መድረሳቸው ሲገልፅ ከ2021 ጀምሮ የኢትዮ ሳት የኤችዲ ቲቪ ቻናሎች ከ15 በመቶ ወደ 62 በመቶ ማደጉ ተነግሯል። በአሁኑ ወቅት በሳተላይቱ 136 ቻናሎች ለ17 ሚሊዮን የቴሌቪዥን ባለቤቶች እየተሰራጩ ሲሆን ከ136 የሬዲዮና የቴሌቪዥን ቻናሎች መካከል ደግሞ 70 የሚሆኑት የሀገር ውስጥ ቻናሎች መሆናቸው ተጠቁሟል። 'ኢትዮ-ሳት' ን የኢትዮጵያ ሚዲያ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ)፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስተሮች ማህበር (ኤቢቢ) እና SES በጋራ በመሆን ከ4 አመት በፊት ይፋ እንዳደረጉት ይታወሳል።
Show more ...
31 188
11
በሀገር አቀፍ ደረጃ በመድኃኒት ቤቶችና መደብሮች ላይ አስገዳጅ ደረጃ ሊተገበር ነው በሀገር አቀፍ ደረጃ የመድኃኒት ቤቶችና መድኃኒት መደብሮች ላይ አስገዳጅ ደረጃ በቅርቡ ሊተገበር መሆኑን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ገለጸ። አስገዳጅ ደረጃው መድኃኒት ቤትም ሆነ መድኃኒት መደብር ምን ዓይነት ባለሙያዎች ሊኖሯቸው ይገባል፣ ምን ዓይነት መድኃኒት ይይዛሉ፣ የመድኃኒት ቤቱ ወይም መደብሩ ስፋት የሚለውንና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ያካተተ መሆኑንም የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ ለኢዜአ ገልፀዋል። ክልሎች ለመድኃኒት ቤትና መድኃኒት መደብር ፈቃድ የሚሰጡበት መስፈርት የተለያየ መሆኑን ያነሱት ዳይሬክተሯ፤ ወጥነት ያለው ለማድረግ ደረጃው መዘጋጀቱን ተናግረዋል። ደረጃው መውጣቱን ተከትሎ አሠራሩ እስኪተገበር ድረስ ለአዲስ መድኃኒት ቤትና መድኃኒት መደብር ፈቃድ እንዳይሰጥ መደረጉንም አንስተዋል። በዚህም በሁሉም ተቆጣጣሪ አካላት ሊተገበር የሚችል ሀገራዊ መስፈርት ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ደረጃው መውጣቱንና በደረጃው የተቀመጡ መስፈርቶች ላይ መመሪያ ተዘጋጅቶ ለክልል ተቆጣጣሪ አካላት ሥልጠና መሰጠቱን እና ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁም ተነግሯል።
Show more ...
31 922
157
ፕራና ኢቨንትስ እና የጀርመኑ ፌርትሬድ በጋራ የሚያሰናዱት 6ኛው አግሮ ፉድ ፕላስት ፕሪንት ፓክ ኢትዮጲያ ዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢት ከሁለት ቀናት በኋላ ይካሄዳል። በኹነቱ በግብርና፣ በምግብና መጠጥ ግብዓትና ማቀነባበሪያ ቴክኖሎጂ፣ እንዲሁም በፕላስቲክ ህትመት እና የማሸጊያ ቴክኖሎጂ እና መፍትሄዎች ላይ ትኩረት ያደረጉ የቱርክ የቻይናና የህንድ ብሄራዊ ተሳትፎን ጨምሮ ከ 12 ሃገራት የተውጣጡ ከ 120 በላይ ኩባንያዎች  ይሳተፉበታል። ከግንቦት 8 – 10 /2016 በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ  በሚቆየው ዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢት የገበያ ትስስር ሰንሰለት፣ አለም አቀፍ ግብይት፣ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ሽግግር እንደሚካሄድ ይጠበቃል። ለጎብኚዎች ምዝገባ  የተሳታፊዎች መረጃ ለማግኘት  ለበለጠ መረጃ www. ወይም                     NaN/64 ኹነቱን ለመጎብኘት ምንም አይነት ክፍያ አይጠየቅም።
Show more ...
27 348
24
❇️ ሰምተዋል ? ❇️ የትርፋማው የአያት አክሲዮን ሽያጭ ሊጠናቀቅ ነው :: ❇️ በ2014 ዓ.ም 44% እንዲሁም በ2015 ዓ.ም 51.38% የአክሲዮን ትርፍ ለባለ አክሲዮኖች አከፋፍሏል ❇️ የአንድ ሚሊዮን አክሲዮን የነበራቸው በ2015 ዓ.ም ብቻ 513,800 ብር አትርፈዋል ❇️ ከ112,500 ብር ጀምሮ የአክሲዮን ባለቤት በመሆን በቶሎ የትርፍ ተካፋይ ይሁኑ ❇️ አክሲዮኑን በገዙ ከመጀመሪያው ወር ጀምሮ የትርፍ ተካፋይ ይሁኑ ❇️ ትርፋማ የሆነውን የአያት አክሲዮንን ለእርስዎ ፣ ለታዳጊ ልጅዎ  ፣ ለቤተሰብዎ እና ለወዳጅ ዘመድዎ በስጦታ ያበርክቱ ❇️ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባላችሁበት ሆናችሁ በወዳጆቻችሁ በኩል መግዛት ትችላላቹህ ⏱📞 ☎️ አሁኑኑ በ NaN በቀጥታ ወይንም በቴሌግራም በዋትሳፕ ይደውሉ
22 664
12
ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳንን የሚያገናኘው የመንገድ ግንባታ በቅርቡ ይጀመራል ተባለ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳንን የሚያገናኘው የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በቅርቡ እንደሚጀመር በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ እንደገለፁ ዘ ሲቲ ሪቪው የተሰኘው የሀገሪቱ የዜና ምንጭ ዘግቧል። አምባሳደሩ ይህንን የገለፁት በኢትዮ-ደቡብ ሱዳን የቢዝነስ ፎረም ላይ ሲሆን ሁለቱን ሀገራት የሚያገናኘው አገር አቋራጭ መንገድ የሚገነባው በጋምቤላ እና በፓሎች የላይኛው የናይል ግዛት በኩል ነው ተብሏል። አገር አቋራጭ መንገዱን ለማስጀመር በሚቻልበት ሁኔታ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንግግር እንዲያደርጉ ባላስልጣናቸውን ከወራት በፊት ማዘዛቸውን አምባሳደሩ ሲገልፁ ኢትዮጵያም የመንገዱን ግንባታ ለማስጀመር ቁርጠኛ አቋም እንዳላት ጠቁመዋል።
22 137
3
#ጥቆማ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ14 የስራ ዘርፎች ብቁ ሠራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር እንደሚፈልግ አሳውቋል። ስለሆነም ፍላጎት ያላችሁ ከዚህ በታች ያለዉን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ማመልከት እንትችሉ ጥቆማ ቀርቧል። እዚህ ላይ ይጫኑ፡👉
25 251
78
Last updated: 11.07.23
Privacy Policy Telemetrio