Best analytics service

Add your telegram channel for

  • get advanced analytics
  • get more advertisers
  • find out the gender of subscriber
Category
Channel location and language

audience statistics Ethiopia Check

ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል። 
26 073+4
~5 078
~16
19.84%
Telegram general rating
Globally
33 311place
of 78 777
245place
of 396
In category
1 415place
of 2 793

Subscribers gender

Find out how many male and female subscibers you have on the channel.
?%
?%

Audience language

Find out the distribution of channel subscribers by language
Russian?%English?%Arabic?%
Subscribers count
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

User lifetime on the channel

Find out how long subscribers stay on the channel.
Up to a week?%Old Timers?%Up to a month?%
Subscribers gain
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

Hourly Audience Growth
Since the beginning of the war, more than 2000 civilians have been killed by Russian missiles, according to official data. Help us protect Ukrainians from missiles - provide max military assisstance to Ukraine #Ukraine. #StandWithUkraine
#FactCheck ዘ ኢኮኖሚስት መጽሔት 'እረፍት የለሹ የኢትዮጵያው ጠ/ሚር አዲስ አበባን በፍጥነት እያዘመኗት ነው' ብሎ የሰራው ዘገባ የለም ከ6,890 በላይ ተከታታዮች ያሉት እና 'CHERBOLE' የሚል ስያሜ የሚጠቀም የትዊተር አካውንት ከዘ ኢኮኖሚስት መጽሔት ድረ-ገጽ የተወሰደ የሚመስል አንድ የስክሪን ቅጂ (ስክሪንሾት) በትናትናው ዕለት ማጋራቱን ተመልክተል። በስክሪን ቅጂው ላይም 'Ethiopia's restless prime minister is modernising Addis Ababa too fast' ወይም ወደ አማርኛ ሲተረጎም 'እረፍት የለሹ የኢትዮጵያው ጠ/ሚር አዲስ አበባን በፍጥነት እያዘመኗት ነው' የሚል ርዕስ ይነበባል። በተጨማሪም ዝቅ ብሎ 'Abiy Ahmed is making the city too clean for Africa' የሚል ተቀጥያ ርዕስ ይነበባል። በዚህ ስክሪን ቅጂ ላይ ጽሁፉ እ.አ.አ ሚያዚያ 25/2024 ዓ.ም መታተሙን የሚገልጽ ቀን አመላካች መስመር (dateline) ይታያል። ከላይ የተጠቀሰውን ስክሪን ቅጂም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መልሰው ሲያጋሩት አስተውለናል። ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት ስክሪን ቅጂው ኤዲት ተደርጎ የተሰራ (doctored) መሆኑን አረጋግጧል። ዘ ኢኮኖሚስት መጽሔት ከላይ በተጠቀሰው ቀን አዲስ አበባን የተመከተ ዘገባ ያስነበበ ሲሆን የተጠቀመው ርዕስ ግን 'The historic heart of Addis Ababa is being demolished' የሚል ወይም ሲተረጎም 'የአዲስ አበባ ታሪካዊ መሀል ቦታ እየፈረሰ ነው' የሚል ነበር። በተቀጥያ ርዕስነት ደግሞ ያስነበበው ጽሁፍ 'Abiy Ahmed is imposing his vision on Ethiopia's capital' የሚል ነበር። መፅሄቱ በዚህ ዘገባው 'የኮሪደር ልማት' በተባለው እንቅስቃሴ ሰለባ የሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎችን አነጋግሮ ሰፋ ያለ መረጃ አጋርቶ ነበር። በተጨማሪም ኤዲት በተደረገው ስክሪን ቅጂ የሆሄያትና የስርዐተ ነጥቦች አቀማመጥ ግድፈቶች በግልጽ እንደሚታዩ አስተውለናል። ትክክለኛውን የመጽሔቱን ዘገባ ይህን ማስፈንጠሪያ በመከተል ማግኘት ይቻላል: መረጃውን አጋርተው የነበሩ አንዳንድ ግለሰቦች እና ባለስልጣናት ምናልባትም ስክሪን ቅጂው ሀሰተኛ መሆኑን ከተረዱ በኋላ በሚመስል መልኩ ቆይተው እንዳጠፉ መመልከት ችለናል። ኤዲት ተደርገው የሚሰራጩ ስክሪን ቅጂዎች ለሀሠተኛ መረጃ ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችንና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ጥንቃቄና ማጣራት እናድርግ።
Show more ...
The historic heart of Addis Ababa is being demolished
Abiy Ahmed is imposing his vision on Ethiopia’s capital
2 249
5
1 637
1
#EthiopiaCheck Kaartaa Guugil (Google Map) suuraan tokko eessatti akka kaafame baruuf (geolocating) nu gargaara. Akkaataa itti fayyadama Kaartaa Guugil baruuf viidiyoo kana yaa daawwannu.
#EthiopiaCheck Explainer Guugil suuraan tokko eessatti akka kaafame baruuf nu gargaara.
2 395
0
#EthiopiaCheck Video Explainer Google Earth በመጠቀም አንድ ምስል የተወሰደበትን ቦታ ማጣራት ይቻላል! እንዴት? ኢትዮጵያ ቼክ ያዘጋጀውን ይህን አጭር ቪድዮ እንመልከት።

file

4 501
7
#EthiopiaCheck Video Explainer Bootiiwwan miidiyaa hawaasaa (Social Media Bots) maali? Akkamiin adda baafanna? Viidiyoo gabaabaa Itoophiyaa Cheek dhimmicharratti qopheesse yaa daawwannu!

file

4 666
1
#MediaMonitoring የብልፅግና ፓርቲ ‘የሚዲያ ሠራዊት’ አባላት በሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት እና አሳሳች የፌስቡክ ዘመቻዎች ላይ መሳተፋቸውን እንዳረጋገጠ ቢቢሲ ይፋ አድርጓል በገዢው ብልፅግና ፓርቲ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስር የሚንቀሳቀሱ እና ‘የሚዲያ ሠራዊት’ የሚል መጠሪያ ያላቸው የፓርቲው አባላት፤ መንግሥትን በሚተቹ እና በሚቃወሙ ግለሰቦች ላይ በፌስቡክ በተደረጉ የሐሰተኛ መረጃ እንዲሁም ‘የጥላቻ ንግግር’ ተብለው ሊቆጠሩ የሚችሉ ጽሑፎች እና ምስሎች ሥርጭት ላይ እንደተሳተፉ ቢቢሲ ባደረግኩት ምርመራ አረጋግጫለሁ ብሏል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወረዳ አመራሮችም በፓርቲው የወረዳ መዋቅሮች ትዕዛዝ በተለይም የመንግሥትን ገፅታ በሰው ሰራሽ መንገድ ለመገንባት ፌስቡክ ላይ በሚደረጉ አሳሳች ዘመቻዎች ላይ እንደሚሳተፉም ምርመራው አሳይቷል። ቢቢሲ ለዚህ ዘገባ በአዲስ አበባ ከተማ የወረዳ አመራር፣ የፓርቲ አባል እንዲሁም በከተማዋ እና በፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የሚሰሩ የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች አነጋግሯል። የአዲስ አበባ ከተማ ሰባት ክፍለ ከተሞች ውስጥ የሚገኙ የፓርቲው የወረዳ መዋቅሮች በዋትስአፕ እና ቴሌግራም ግሩፖች ውስጥ ለሶሻል ሚዲያ ዘመቻዎች የተለዋወጧቸውን መልዕክቶች ተመልክቷል። በግሩፖቹ ውስጥ ለወረዳ አመራሮች እና ሚዲያ ሠራዊት አባላት የሚሰጡ ትዕዛዞችን እና አፈጻጸማቸውን ተከታትሏል። የፌስቡክ ዳታዎችን በመውሰድም ተንትኗል። የፌስቡክ እናት ኩባንያ ሜታ፤ ለቢቢሲ በሰጠው ምላሽ “ሐሰተኛ አካውንቶችን” በመጠቀም “በኢትዮጵያ መንግሥት” የፌስቡክ ልጥፎች ላይ “ብዛት ያላቸው አዎንታዊ አስተያየቶች” መሰጠታቸውን በምርመራ እንደደረሰበት አስታውቋል። ሜታ፤ በዚህ ድርጊት ላይ በተሳተፉ ሐሰተኛ አካውንት እና ገፆች ላይ እርምጃ መውሰዱን የገለጸ ሲሆን፣ ቢቢሲ ሲከታተላቸው የነበሩ አካውንቶችም እንዲወገዱ ተደርገዋል። የብልፅግና ፓርቲ በበኩሉ ‘የሚዲያ ሠራዊት’ የሚባል አደረጃጀት “አለመኖሩን” በመግለፅ ለቢቢሲ በሰጠው የፅሁፍ ምላሽ ጉዳዩን አስተባብሏል። የፓርቲው ዋና ፅህፈት ቤት፤ “በተለይ ‘ሐሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር ተብለው ሊቆጠሩ የሚችሉ ጽሑፎች እና ምስሎች [ተሠራጭተዋል]’ በሚል የተገለጸው ፍጹም ተቀባይነት የሌለው አገላለጽ ነው” ብሏል።
Show more ...
6 273
15
4 383
1
#EthiopiaCheck Video Explainer ናይ ሓሶት ከምኡውን ተመሳሲሎም ዝኽፈቱ ኣካውንትታትን ቻናላትን ንምልላይ እንታይ ዓይነት ምልክታት ኣለዉ? ነዚብዝምልከት ኢትዮጵያ ቼክ ንዘዳለዎ ቪዲዮ ንርአ።

file

4 807
1
#EthiopiaCheck Explainer Suuraawwan qooduu keenyaan dura yaa qalbeeffannu! Suuraawwan miidiyaalee hawaasummaarra naanna'an qooduu yookiin amanuu keenyaan dura kan hin gulaalamne ta'uu mirkaneeffannu. Mirkaneeffachuuf:
5 267
1
#EthiopiaCheck የተቋማትን ስም እና አርማ በመጠቀም የሚጻፉ ሀሠተኛ ደብዳቤዎችን ለመለየት የሚረዱ ነጥቦች ባለፉት ጥቂት ሳምንታት የትላልቅ ተቋማትን ስም እና አርማ በመጠቀም የተጻፉ ሀሠተኛ ደብዳቤዎች በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ ገጾች መሰራጨታቸውን ተመልክተን ነበር። ከነዚህም መካከል በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) እና በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር እንደተጻፉ ተደረገው የተሰራጩትን ሀሠተኛ ደብዳቤዎች መጥቀስ ይቻላል። ምንም እንኳን ከላይ የተጠቀሱት ደብዳቤዎች በግልጽ የሚታዩ ግድፈቶች የሚታዩባቸው ቢሆኑም ቀላል የማይባሉ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ደጋግመው ሲያጋሯቸው ተስተውሏል። ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) እና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ደብዳቤዎቹ ሀሠተኛ መሆናቸውን የሚገልጹ የማስተባበያ መልዕክቶችን በኦፊሴላዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻቸው ማጋራታቸውን ተመልክተናል። እንዲህ ያሉ የተቋማት ስምን እና አርማን በመጠቀም የሚጻፉ ደብዳቤዎች ለሀሠተኛና ለተዛቡ መረጃዎች የማጋለጥ ዕድላቸው ሰፊ ስለሆነ ከማመናቸንና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ቆም ብለ ማሰብና መመርመር ይጠበቅብናል። ሀሠተኛ ደብዳቤዎችን ለመለየትም የሚከተሉት ነጥቦች ይረዱናል በመጀመሪያ በማህበራዊ ሚዲያ የምናያቸውን ደብዳቤዎች ከማመናችናን መልሰን ከማጋራታቸን በፊት ደብዳቤዎቹን ያጋራውን ግለሰብ ወይም ገጽ ማንነት፣ ታማኝነት እንዲሁም ፍላጎት ማጤን ይኖርብናል። ደብዳቤው የተቋም ስምንና አርማን በመጠቀም የተጻፈ ከሆነ በተጠቀሰው ተቋም የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች ወይም ድረገጾች መጋራታቸውን ማየት ጠቃሚ ይሆናል። በተጨማሪም ተቋሙን በስልክ፣ በኢሜል ወይም በውስጥ መልዕክቶች መጠየቅ ስለ ደብዳቤው ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ይረዳል። የደብዳቤውን ቅርጽና ይዘት በሚገባ መፈትሽም ስለትክክለኛነቱ መረጃ ሊሰጠን ይችላል። ለምሳሌ ደብዳቤው የተጻፈበት የፊደል አይነት (font type) ፣ የፊደል መጠን (font size) ፣ የተቋሙ አርማ አቀማመጥ፣ የደብዳቤ ቁጥር፣ ቀን፣ ማህተም ፊርማ፣ ስም ወዘት በጥንቃቄ ማስተዋል እንዲሁም ቀደም ካሉ የተቋሙ ደብዳቤዎች ጋር ማመሳከር እውነታውን ለማወቅ ይረዳል። ለማመሳከሪያነት የሚጠቅሙ በተቋሙ የተጻፉ ቀደም ያሉ ደብዳቤዎችን ከየተቋማቱ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች ወይም ድረገጾች በቀላሉ ማግኘት ይቻላል። የመረጃ አጣሪ ተቋማት ደብዳቤውን በተመለከተ ያጋሩት የተጣራ መረጃ መኖሩን መፈተሽ አልያም ጥቆማ መስጠት እውነታውን ለማወቅ ሌላው አማራጭ መንገድ ነው። የተቋማትን ስምና አርማ በመጠቀም የሚሰራጩ ደብዳቤዎች ለሀሠተኛ መረጃ ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችንና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ጥንቃቄና ማጣራት እናድርግ።
Show more ...
5 656
1
4 964
0
#Explainer ቑጽርታት ንሓሶትን ዝተዛብዐን መረዳእታ ከየቃልዑና ነስተውዕል።
6 276
0
#EthiopiaCheck Video Explainer የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል ማን ምን ሚና ሊጫወት ይገባል? ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ ያዘጋጀውን አጭር ቪድዮ እንመልከት።

file

6 522
1
#EthiopiaCheck Explainer በኦንላይን የሚፈፀሙ የማጭበርበር ድርጊቶች (online scams) እየጨመሩ ይገኛሉ። ለእንዲህ አይነት ድርጊቶች እንዳንጋለጥ እነዚህን ነጥቦች ልብ እንበል:
7 945
3
#EthiopiaCheck Explainer Dhimma odeeffannoowwan bifa oduu ammeetiin dhiyaatan! Odeeffannoowwan bifa oduu ammeetiin dhiyaatan amanuufi qooduu keenyaan dura qabxiilee kunneen qalbeeffachuun oduu sobaaf akka hin saaxilamne nutaasisa:
8 126
1
#EthiopiaCheck Explainer Video ፊሺንግ፣ ስሚሺንግ እና ቪሺንግ የተባሉትን የማጭበርበርያ መንገዶች ምንድን ናቸው? እንዴትስ መከላከል እንችላለን? በዚህ ዙርያ ኢትዮጵያ ቼክ ያዘጋጀውን አጭር ቪድዮ እንመልከት።

file

6 524
4
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የኢድ አልፈጥር በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን። ኢድ ሙባረክ! ኢትዮጵያ ቼክ ።
5 835
0
#EthiopiaCheck የተነካኩ ወይም አውድ እንዲስቱ የሚሰሩ ቪድዮዎች እና መለያ መንገዶች በ2014 (እ.ኤ.አ.) ከተሸጡ የተንቀሳቃሽ ስልክ አይነቶች ውስጥ 55% የሚሆኑት ከተፈጠረ ሁለት አስርት ዓመታትን ያስቆጠረው የስማርትፎን ቴክኖሎጂ ያላቸው ስልኮች ነበሩ። ዛሬ ከአጠቃላይ የተንቀሳቃሽ ስልኮች ሽያጭ የስማርትፎን ድርሻ እጅ ከፍ ያለ ሆኗል። ተንቀሳቃሽ ስልክ ብቻ ግን አይደሉም፣ ከፍተኛ ጥራት ያለው ፎቶ እና ቪዲዮ ይቀርጻሉ። በኢንተርኔት መገናኘትን እና ለሌሎች ማጋራትን ይፈቅዳሉ፣ ያበረታታሉም። ይዘቶችን ይፈጥራሉ። ይዘቶችን ያሰራጫሉ። የመረጃ ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እነዚህን ይዘቶች ‘በተጠቃሚ የመነጩ ይዘቶች’ (user-generated contents) ይሏቸዋል። እኛም አገር፣ በተጠቃሚ የመነጩ ይዘቶችን በብዛት ማየት ከጀመርን ዓመታትን አስቆጥረናል። የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚነት መጨመርን ተከትሎም እነዚህ ይዘቶች በስፋት ይሰራጫሉ፣ ሐሰተኛ እና አሳሳች የቪድዮ ይዘቶችም በየድረ ገጹ ይዘዋወራሉ። እነዚህን ቪድዮዎች የሚያይ፣ አይቶም የሚያምን ሰው እስካለ ድረስም በሰፊው መሰራጨታቸውን ይቀጥላሉ። ይህንን ለመግታት ታዲያ ማየት ማመን ነው የሚለውን ዘመን ተሻጋሪ አባባል በድጋሚ ማጤን ያስፈልጋል። ከሩቅ ሲታይ፣ ሐሰተኛ ቪድዮዎችን መለየት እጅግ አስቸጋሪ ተግባር ሊመስል ይችል ይሆናል። በመሰረቱ ግን ሐሰተኛ ቪድዮዎችን መለየት ምንነታቸውን ከማወቅ ይጀምራል። በቀላል ቋንቋ ሐሰተኛ ቪድዮ ማለት የተነካካ ቪድዮ ወይም በቅንብር የቀረበ ማለት ነው። አውዱን እንዲያጣ/እንዲስት ሆኖ የተቆረጠ ቪድዮ፣ አሳሳች አርትዖት እንዲሁም ተንኮል አዘል ለውጥ የተደረገበት ቪድዮ ሐሰተኛ ሊባል ይችላል። ሁሉም የተቆረጠ ወይም የአርትዖት ስራ የተሰራበት ቪድዮ ሐሰተኛ ቪድዮ ነው ማለት ግን አይደለም። ሆኖም በመቆረጡ ምክንያት ከአውዱ ውጭ የሆነ ትርጓሜን የሚፈጥር ከሆነ ወይም ከቪድዮው ላይ የተቀነሰ/የተጨመረ ነገር ሲኖር፣ ይህ ቪድዮ ሐሰተኛ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው። ይህ ተግባር ከዚህ በታች ያሉትን ያጠቃልላል: * አንድን ጉዳይ በስህተት ማስቀመጥ (Misrepresentation) * የተወሰነውን የቪድዮ ክፍል ነጥሎ ማውጣት ወይም ቆርጦ ማስወገድ * የቪድዮውን የተለያዩ ክፍሎች ቆርጦ መቀጣጠል * የቪድዮውን መጠን (ቁመት እና ጎን) መቀየር * የቪድዮውን ፍጥነት፣ የፍሬም ፍጥነት (frame rate)፣ ድምፅ እና ሌሎች መረጃዎችን መቀየር * በቪድዮው ላይ ማንኛውም ‘የቀዶ-ጥገና’ (Doctoring) ስራ መስራት * በኮምፒውተር ፈጠራ የተሰራን ምስል ወይም የምስል ክፍልን በቪድዮው ላይ መጠቀም (fabrication using artificial intelligence) ልምድ ያላቸው አይኖች አንድ ቪድዮ ከተቀረጸ በኋላ የተፈጠሩ (የተጨመሩ ወይም የተቀነሱ) ልዩነቶችን መለየት አይቸገሩም። ጥሩው ነገር ብዙ ልምድ የሌለው ሰው በቪድዮዎች ላይ ከቀረጻ በኋላ የተፈጠሩ ልዩነቶችን አንጥሮ ለመለየት InVID የተባለውን ተሰኪ (Plugin) በክሮም ወይም ፋየርፎክስ አሳሾች (Chrome Firefox browsers) ላይ በማከል በቀላሉ መጠቀም መቻሉ ነው። InVID ለዩትዩብ፣ ፌስቡክ እና ትዊተር ቪድዮዎች የተጎላበተ የሜታዳታ መመልከቻ (metadata viewer) ነው። ይህ ተሰኪ (Plugin) በነጻ የሚገኝ ሲሆን አንዴ ከተጫነ በኋላ ስምንት የተግባር አዝራሮችን (buttons) በአሳሹ ላይ ይፈጥራል። ሁሉም አዝራሮች ከላይ የተጠቀሱትን ከቀረጻ በኋላ በቪድዮው ላይ የተፈጠሩ ልዩነቶችን ለመለየት የተለያየ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ። ሐሰተኛ ቪድዮ የመለየት ስራንም በእጥፍ ያቃልላሉ። ዝርዝር ትምህርታዊ ቪድዮዎችን በገጹ የላይኛው ረድፍ ላይ ካሉት አዝራሮች ውስጥ “Tutorial” የሚለውን በመጫን ሊያገኟቸው ይችላሉ። መልካም ንባብ!
Show more ...
6 922
0
5 779
0
#EthiopiaCheck Explainer Video ፊሺንግ፣ ሺሚንግን ቪሺንግን ተባሂሎም ዝጽውዑ ናይ ምትላል መገድታት እንታይ እዮም? ከመይ’ከ ክንከላኸሎም ንኽእል? ብዛዕባኦም ኢትዮጵያ ቼክ ንዘዳለዋ ሓጻር ቪዲዮ ንርአ።

file

7 472
0
#EthiopiaCheck Explainer Haasaa jibbiinsaa jechuun maal jechuudha? Maal of keessatti qabata?
6 645
0
#EthiopiaCheck Explainer በኢትዮጵያ ህግ መሰረት የጥላቻ ንግግር ምን ማለት ነው? ምንን ያካትታል? ራሳችንን ከጥላቻ ንግግሮች እና ከሀሰተኛ መረጃ በመጠበቅ ሀላፊነታችንን እንወጣ።
1
0
ይህ ቪዲዮ የአዲስ አበባን ወቅታዊ ሁኔታ አያሳይም ከ37 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉትና 'Amhara Youth Association' የሚል ስያሜ ያለው የትዊተር አካውንት በአዲስ አበባ የተደረገን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ያሳያል ያለው ቪዲዮ ማጋራቱን ተመልክተናል። ከላይ የተጠቀሰው አካውንት ያጋራው ቪድዮዎም በመቶዎች የሚቆጠር ግብረመልስ ማግኘቱን አስተውለናል። ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት የተጋራው ቪድዮ ከአውድ ውጭ የቀረበና የቆየ መሆኑን አረጋግጧል። ቪድዮው ከአምስት አመት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ተከስቶ የነበረን ግጭትና አለመረጋጋት የሚያሳይ ሲሆን በወቅቱ በርከት ባሉ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ተጋርቶ ነበር። ከነዚህም አንዱን ይህን ማስፈንጠሪያ በመከተል መመልከት ይቻላል: ጊዜያቸውን ባልጠበቀና ከአውድ ውጭ በሆነ መልኩ የሚጋሩ ቪዲዮዎች ለሀሰተኛና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ጥንቃቄና ማጣራት እናድርግ።
Show more ...
6 088
4
#EthiopiaCheck Explainer ንስእልታት ቅድሚ ምክፋልና ነስተውዕል! ብማሕበራዊ ሚዲያ ዝተዘርግሑ ስእልታት ቅድሚ ምክፋልና ወይ ምእማንና ኤዲት ዘይተገበሩ ምዃኖም ክነጻርይ ኣለና። ንምጽራይ ከዓ:
7 230
2
#EthiopiaCheck Video Explainer ለውጢ ዝተገበረሉ (ብልምዲ ፎቶሾፕ ዝተገበረ ንብሎ) ምስሊ ብፎረንሲካሊ (Forensically) ተጠቒምና ከመይ ክናጻርይ ከምንኽእል ኢትዮጵያ ቼክ ንዘዳለዋ ሓጻር ቪዲዮ ንርአ።

file

6 634
0
#EthiopiaCheck Video Explainer ዲፕ ፌክ (deep fake) እንታይ እዩ? ኣብዚ እዋን እዚ ብዝተራቐቐ መልክዕ ዝስርሑ ስእልታት፣ ቪዲዮታትን ድምጽታትን ዝሓዙ ትሕዝቶታት ክረኣዩ ጀሚሮም ኣለዉ። እሞ ንዞም ዘተሓሳስቡ ትሕዝቶታት ንምልላይ እንታይ ክንገብር ንኽእል?? ነዚ ብዝምልከት ኢትዮጵያ ቼክ ንዘዳለዋ ሓጻር ቪዲዮ ንርአ።
#EthiopiaCheck Video Explainer ዲፕ ፌክ (deep fake) እንታይ እዩ?
2
0
“ከጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ እና ከዳሽን ባንክ ጋር ያለው ግንኙነት እስካሁን አልተቋረጠም”--- የጤና ሚኒስቴር "በተያዘው በፕሮግራም መሰረት በዓመት አራት ጊዜ እጣ መውጣት እያለበት እስካሁን 2 ጊዜ ብቻ ወጥቷል"--- የጤና ባለሙያዎች ከሰሞኑ “ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ከጤና ሚኒስቴር ጋር የተፈራረመውን የጤና ዘርፍ ሰራተኞች ቤት ግንባታ ስምምነት አፍርሷል፤ ቤት ለማግኘት ክፍያ የፈጸሙ የጤናው ዘርፍ ሰራተኞችም ተጭበርብረዋል” የሚሉና ኢትዮጵያ ቼክ ጉዳዩን እንዲያጣራ የሚጠይቁ መልዕክቶች ከተከታታዮቻችን ደርሰውናል። የጤና ባለሙያዎች ለኢትዮጵያ ቼክ ባደረሱት ተከታታይ መረጃ የከፈሉት ብር ይመለሳል የሚል መረጃ ሲዘዋወር እንደተመለከቱና ይህም ማለት ማህበሩ ፈርሷል ብለው እንዲያስቡ እንዳረጋቸው ጠቁመዋል። የጤና ባለሙያዎቹ አክለውም የጎጆ ዕጣ በተያዘው በፕሮግራም መሰረት በዓመት አራት ጊዜ መውጣት እያለበት እስካሁን 2 ጊዜ ብቻ ወጥቷል፣ በውል ስምምነቱ መሰረት በየ 3 ወሩ ነው ዕጣ ይወጣል ቢልም በ ውሉ መሰረት ዕጣ አልወጣም እንዲሁም ችግሮች እንኳን ቢኖሩ እነዚህ ችግሮች ሲፈጠሩ ወቅታዊ መረጃ ለተመዝጋቢዎች አልተሰጡም የሚሉ ቅሬታዎች ቀርበዋል። የጤና ሚኒስቴር የጤና ዘርፍ ሰራተኞች የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክትን በተመለከተ ከጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ እና ዳሽን ባንክ ጋር የሶስትዮሽ ስምምነት ተፈራርሞ የመጀመሪያ ዙር እጣ ማውጣት ስነ ሰርዓት የተካሄደው ሰኔ 2015 ላይ ነበር። በስነ ሰርዓቱም 200 ጤናው ዘርፍ ሠራተኞች የመጀመርያ ዙር የዕጣ እድለኞች ሲሆኑ ዕጣ የማውጣት ሂደቱ በየሶስት ወሩ እንደሚቀጥልና እየሰፋ እንደሚሄድም ተጠቁሞ ነበር። ይህ መረጃም በወቅቱ በሚኒስቴሩ የተረጋገጠ የፌስቡክ ገጽ ተጋርቶ ነበር፡ ይሁን እንጂ “ሁለቱ ተቋማት መካከል የተፈረመው ስምምነት ፈርሷል” የሚለውን መረጃ መነሻ በማድረግ ኢትዮጵያ ቼክ ከጤና ሚኒስቴር እና ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ መረጃዎችን ለማግኘት ጥረት አድርጓል። በጤና ሚኒስቴር የጤና ዘርፍ ሰው ሀብት ልማት ማሻሻያ መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ አሰግድ ሳሙኤል ጉዳዩን በተመለከተ ለኢትዮጵያ ቼክ መረጃ የሰጡ ሲህን ‘በሁለቱ ተቋማት መካከል የተፈረመው ስምምነት ፈርሷል’ የሚለው መረጃ ሀሰት መሆኑን ነግረውናል። “ጤና ሚኒስቴር ከጎጆ እና ከዳሽን ባንክ ጋር ያለው ግንኙነት እስካሁን አልተቋረጠም። ያንን የሚያደርግ ከሆነ ጤና ሚኒስቴር በባለሙያው በኩል ነው የቆመው” ያሉት አቶ አሰግድ፤ “ማንኛውም በዚህ ሂደት ውስጥ የሚያልፍ ነገር ባለሙያው ላይ ማንኛውም አይነት ችግር የሚፈጥር ከሆነ (ጤና ሚኒስቴር) በፍጹም ዝም ብሎ የሚያይበት ነገር አይኖርም። ስለዚህ የመግባቢያ ስምምነቱ እስካሁን አልተቋረጠም” ብለዋል። የጤና ሚኒስቴር ከጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ጋር ስምምነት ሲፈጽም የተቋሙን ህጋዊ ሰነዶችን ተመልክቶ መሆኑን የሚናገሩት ስራ አስፈጻሚው ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ፤ ዳሽን ባንክና ጤና ሚኒስቴር የተፈራረሙት ስምምነት አላማ 10 ሺህ ቤቶችን በ10 አመት ገንብቶ ለመጨረስ እንደሆነም ነግረውናል። ባጠቃላይ ከ8000 በላይ ሰራተኞች የፕሮግራሙ አካል መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ አሰግድ፤ እስካሁን በሁለት ዙሮች 400 የጤናው ዘርፍ ሰራተኞች በጋራ የማህበር ቤት እንዲገነቡ እጣ እንደወጣላቸውም ይናገራሉ። ይሁን እንጂ “እጣዎቹ ከወጡ በኋላ ችግር የሆነው ከመሬት አስተዳደር፤ ከአዲስ አበባ ማህበራት ማደራጃ ጋር ተያይዞ የተወሰኑ የአሰራር ለውጦች ተደረጉ። ከተማ ውስጥ ያለው ከመሬት ጋር ተያይዞ ያለው ችግርም የሚታወቅ ነው። ከተማ አስተዳደሩ ያንን ማኔጅ ለማድረግ በየጊዜው የሚያወጣቸው አዳዲስ ህጎች አሉ። እነሱ (ሂደቱን) አፌክት አድርገውታል” ብለዋል። ስለዚህም እጣ የወጣላቸው እድለኞች በሚፈለገው ጊዜ ግንባታ ያለመጀመራቸውን በመጥቀስ “ትልቁ እኛም የገመገምነው ችግር አሁን ባልኩት ዉስጣዊም ዉጫዊም ችግሮች፤ ጎጆም ጋር ባለው ግንባታው ዘግይቷል የሚል ነው” ብለዋል። በተጨማሪም ጤና ሚኒስቴር የጤናው ዘርፍ ሰራተኞችን ለማበርታትና ለማትጋት ከጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ በተጨማሪ ሌላ የመኖሪያ ቤት ማግኛ አማራጮች ላይ እየሰራ መሆኑንም አቶ አሰግድ ሳሙኤል ለኢትዮጵያ ቼክ ነግረዋል። በሌ በኩል ጉዳዩን በተመለከተ የጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግን አስተያየት ለማግነት ለዋና ስራ አስኪያጁ አቶ አለማዉ ጋሪ ብንደዉልም ለጊዜው መረጃ ማግኘት አልቻልንም።
Show more ...
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
8 484
29
6 327
2
#EthiopiaCheck መረጃን በማጣራት ስራ ስኬታማው ፖሊቲፋክት ምን ያስተምረናል? ግዜው እ.ኤ.አ. በ2009 ዓ.ም. ነበር። ከተመሰረተ 2 ዓመት እንኳን ያልሞላው ፖሊቲፋክት የተባለ የመረጃ አጣሪ ቡድን የፑሊትዘር ሽልማትን (Pulitzer Prize) ብዙዎችን ባስደነቀ መልኩ ተሸልሞ ነበር። አምስት ጋዜጠኞች እና አርታኢዎችን ጨምሮ ጥቂት ተመራማሪዎችን የያዘው ይህ ቡድን በቀድሞ ስሙ ሴይንት ፒተርስበርግ ታይምስ በሚባል ጋዜጣ ውስጥ የ2008 (እ.ኤ.አ.) የአሜሪካ ምርጫን ምክንያት አድርጎ የተፈጠረ የዘገባ ፕሮጀክት ነበር። ቡድኑ በዚህ ጊዜ ውስጥ በአሜሪካውያን ፖለቲከኞች የተነገሩ ከ750 በላይ ንግግሮችን አጣርቶ እውነቱን ከውሸት፣ ፍሬውን ከገለባ በመለየቱ ነበር ይህንን የከበረ ሽልማት የተሸለመው። እነዚህ ጋዜጠኞች የመረጃ ማጣራት ስራውን ሲጀምሩ ታድያ ነገሮች ቀላል እንደማይሆኑ ያውቁ ነበር። ምንም እንኳን የጋዜጠኞቹ ፕሮጀክት በፍሎሪዳ ግዛት ትልቁ የሚባለው ጋዜጣ በባለቤትነት የሚያስተዳድረው ቢሆንም፣ ከሁሉም አቅጣጫ ቁጣን እንደሚያስተናግዱ ምንም አልተጠራጠሩም። ቶሎ ብለውም ትኩረትን ማግኘት ነበረባቸው። በጥቂት ጋዜጠኞች እና ተመራማሪዎች የተመሰረተው ይህ የመረጃ ማጣራት ፕሮጀክት ትኩረት ማግኘት የጀመረው ’የሀቅ-መለኪያ’ (Truth-o-Meter) የሚል ስም በተሰጠው በዓይነቱ ልዩ በሆነ የደረጃ አሰጣጥ ሂደት፣ እነዚህን ንግግሮች ‘እውነት’፣ ‘እንደነገሩ እውነት’፣ ‘ግማሽ ውሸት’፣ እና ‘ውሸት’ በሚል መመደብ ከጀመረ በኋላ ነበር። በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥም ይህንን ስራ መስራት የሚችሉ ሰፊ ልምድ ያላቸው ጋዜጠኞች እና የሚድያ ተቋማት እንዳሉ ይታወቃል። የፖሊቲፋክትን ምርጥ ተሞክሮ በኢትዮጵያ አውድ ውስጥ ለመተግበር ቀጠሮ መያዝም አያስፈልግም። ከነዚህ በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች ከመሰረቱት ፕሮጀክት (አሁን ራሱን የቻለና ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆነ ድርጅት) ብዙ ልምድ ማግኘት እንችላለን። ዘግይቶም ቢሆን ጥቂት መረጃ የማጣራት ስራዎችን የሚሰሩ ተቋማት በሀገራችን ብቅ ማለታቸው ጥሩ ቢሆንም፣ ከዚህ በበለጠ መስራት እንደሚቻል ግን እሙን ነው። አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን መግታት በይደር የማይተው ስራ ነው። በይደር የማይተው ስራ መሆኑ ላይ ብዙዎች የሚስማሙበት አንዱ ምክንያት አፍራሽ የሆነ አዙሪት ውስጥ ሊከተን የሚችል ጉዳይ በመሆኑ ነው። ሌሎችን ማሳመን የሚጠይቁ ስራዎችን የሚሰራ ማንኛውም ሰው አንድን እውነታ የማዛባት፣ የማጋነን ወይም የመሸፈን ገፊ ምክኒያት አለው፣ ሰበብ ሊባልም ይችላል። አዙሪቱ ታዲያ ያለው እዚህ ላይ ነው: በዚህ ሀሰተኛ ይዘት ምክንያት የተፈጠረውን ‘የሃይል መዛባት' ማስተካከል በሚል ሌላ ገፊ ምክኒያት ሌላ ሀሰት የሆነ ይዘት ይፈጠራል። እንዲያ እንዲያ እያለ ማለቂያ ወደሌለው ዓለም - የውሸት፣ የቅጥፈት፣ የጥፋት ዓለም - ጉዞ ይጀመራል። ለዚህ ነው የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን መግታት ለነገ የሚባል ስራ አይደለም የሚባለው/የምንለው።
Show more ...
7 122
1
6 012
1
Last updated: 11.07.23
Privacy Policy Telemetrio