Best analytics service

Add your telegram channel for

  • get advanced analytics
  • get more advertisers
  • find out the gender of subscriber
Category
Channel location and language

audience statistics ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

Journalist-at-large 
103 151-7
~27 384
~6
45.63%
Telegram general rating
Globally
17 681place
of 78 777
143place
of 396
In category
805place
of 2 793

Subscribers gender

Find out how many male and female subscibers you have on the channel.
?%
?%

Audience language

Find out the distribution of channel subscribers by language
Russian?%English?%Arabic?%
Subscribers count
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

User lifetime on the channel

Find out how long subscribers stay on the channel.
Up to a week?%Old Timers?%Up to a month?%
Subscribers gain
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

Since the beginning of the war, more than 2000 civilians have been killed by Russian missiles, according to official data. Help us protect Ukrainians from missiles - provide max military assisstance to Ukraine #Ukraine. #StandWithUkraine
እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን! መልካም በዓል።
45 417
62
100,000 followers on አመሰግናለሁ! Galatoomaa! የቐንየለይ!
90 457
22
አስተያየት እና ጥቆማ ለምታደርሱኝ፣ አካውንቶቼ ለተወሰኑ ሳምንታት ዝግ ሆነው ይቆያሉ፣ ሁሉንም መልእክቶቻችሁን ላልመለከት ስለምችል አቆዩልኝ። መልካም ግዜ 👋👋
110 751
22
#Update የአለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ዙርያ ባቀረብኩት መረጃ ላይ ያደረሰኝ መረጃ በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ውስጥ ከሚገኝ የምግብ ማከማቻ መጋዘን ውስጥ ለተራቡ ዜጎች ተብለው የሚወጡትን የምግብ አይነቶች እዛው የንግድ ቀጠና ውስጥ ፓኬጁ ላይ ባንዲራ በመጨመር እየታሸጉ እንደሆነ አንድ መረጃ አቅርቤ ነበር። በዚህ ዙርያ የአለም ምግብ ፕሮግራም ይህን መረጃ አድርሶኛል: "WFP procured 50,000 MT of wheat on behalf of the EDRMC from WFP’s Global Commodity Management Facility (GCMF) - WFP's regional storage facility for purchased commodities - for EDRMC’s humanitarian support to communities affected by drought, floods, and conflict in Ethiopia. The wheat purchased from WFP by EDRMC is being collected from WFP’s warehouses in Dire Dawa after it has been transferred from UN bags to those provided by the government, ready for distribution. WFP occasionally leverages its extensive procurement expertise and networks to provide food procurement services to partners allowing them to respond to food needs in a timely manner." ለመረጃው የአለም ምግብ ፕሮግራምን እያመሰገንኩ ከለጋሽ ድርጅቶች የሚለገሱ የምግብ አይነቶችን 'በኢትዮጵያ የተመረተ' በሚል ማሸግያ ቀይሮ ማውጣት ለምን እንዳስፈለገ የሚመለከተው የመንግስት አካል አስተያየት ቢሰጥበት መልካም ነው እላለሁ። በቅርብ ወራት የእርዳታ ምግብ ምን ሲደረግ እንደነበር የሰማን/የምናውቅ እና እርዳታው ለተጠቃሚው ህዝብ እንዲደርስ የምንፈልግ ሁሉ ይህን መጠየቅ አለብን።
Show more ...
103 157
51
68 158
7
👌👌
73 382
87
የትብብር ጥያቄ! ዶ/ር እደግልኝ ሀይሉ ፓስፖርታቸው ትናንት (ቅዳሜ) አዲስ አበባ ብሔራዊ አካባቢ ጠፍቶባቸዋል። ፓስፖርቱን ያገኘ ሰው ቢተባበራቸው ውለታውን ይከፍላሉ። ስልክ ቁጥራቸው: 0936454509
61 640
13
የዛሬ 50 አመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከካናዳ፣ ከሳውዲ አረቢያ፣ ከቱርክ፣ ከአውስትራሊያ፣ ከጣልያን... ወዘተ ይበልጣል? አንዳንድ 'ተቀፅላዎች' ይህን ስክሪንሾት በስፋት ሲያጋሩ እንደነበር ጥቆማዎች ደርሰውኝ ነበር፣ እንዲጣራም የጠየቁ አሉ። ነገሩ እንዲህ ነው፣ መረጃው በ Goldman Sachs የ 2022 ሪፖርት ላይ የተመሰረተ ሲሆን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እ.አ.አ በ 2075 ወይም የዛሬ 50 አመት 6.2 ትሪሊየን ዶላር የማደግ እድል እንዳለው ይጠቁማል። በዚህ መረጃ ላይ ታድያ እነ ከካናዳ፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ቱርክ፣ አውስትራሊያ፣ ጣልያን ከኢትዮጵያ በታች የተቀመጡ ሲሆን ቻይና፣ ህንድ እና አሜሪካ ከ 1-3 ያለውን ቦታ ይዘዋል። እውነታው ግን ወዲህ ነው፣ እንዲህ አይነት የኢኮኖሚ እድገት ትንበያዎች በአብዛኛው የወደፊት የማደግ አቅምን የሚያሳዩ ሲሆን በርካታ አሁናዊ እና የወደፊት እድሎችን እና መሰናክሎችን አያካትትም። በተጨማሪም ይህ አሀዝ በከፍተኛ ደረጃ የሚንተራሰው የህዝብ ብዛት ቁጥር ላይ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት በ2075 አካባቢ 281 ሚልዮን ዶላር ይገመታል፣ ይህም ለከፍተኛ ምርታማነት እና የኢኮኖሚ እድገት መሰረት የመሆን እድል አለው። ሪፖርቱ የጠቀሰውም ይህን ነው። ይሁንና ተቀፅላዎቹ ሊያቀርቡት እንደፈለጉት ይህ ብቻውን የሀብት ወይም እድገት መለኪያ እንዳልሆነ አለም ተግባብቷል። ትክክለኛ እድገት መለኪያው ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል፣ የኑሮ ደረጃ መሻሻል፣ እንደ ውሀ፣ መኖርያ ቤት እና ኤሌክትሪክ ላሉ አገልግሎቶች ያለ ተደራሽነት... ወዘተ መሆናቸውን ራሱ Goldman Sachs ይጠቅሳል። - የጋሪ እና ፈረስ ትራንስፖርት እናመጣለን እየተባለ ወደ ቀደመው ክፍለ ዘመን ወደኋላ ለመሄድ እየተንደረደርን - በአለም ትላልቅ የሚባሉ ግጭቶች፣ ጦርነቶች፣ መፈናቀሎች እና ስደቶች እያስተናገድን - የህዝብ የመኖር፣ የቤት ባለቤትነት፣ የስራ እና ተንቀሳቅሶ የማምረት አቅም እየተፈተነ... ወዘተ ባለበት ወቅት ይህን ትንበያ ይዞ ከካናዳ እና አውስትራልያ ልንበልጥ ነው ማለት ማደንዘዣ እንጂ ምንም ሊሆን አይችልም። ብቻ መልካሙን ለሀገራችን እንመኛለን።
Show more ...
73 484
57
64 964
29
ለእርሻ፣ ለኮንስትራክሽን እና ተያያዥ አገልግሎቶች የሚውሉ ትራክተሮች እና ከባድ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዳያስገቡ እንደተከለከሉ አስመጪዎች መናገራቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነበበን ይህም የሆነው ካለምንም መመርያ ሲሆን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ያለ ምንም በቂ ምክንያት "የመኪና ማስገቢያ ፈቃድ አልሰጣችሁም" እንዳላቸው ገልጸዋል። ስለጉዳዩ ዝርዝር መረጃም የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤትን ጠይቁ መባላቸውን አመልክተዋል። ከሁሉም ግር የሚለው ደግሞ በቅርቡ በከተሞች በእንስሳት የታገዘ ትራንስፖርት እንዲኖር ስራ እየሰራ እንደሆነ የጠቆመው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከባድ ተሽከርካሪዎች በኤሌክትሪክ እንዲሰሩ መጠበቁ ነው። በኤሌክትሪክ የሚሰራ ትራክተር? ገልባጭ መኪና? ግሬደር? ቡልዶዘር? ታድያ ይህ እየሆነ ያለው በቢልዮን ዶላሮች የሚቆጠር ገንዘብ ለጫካ ፕሮጀክት እየፈሰሰ፣ ተጨማሪ በመቶ ሚልዮን ዶላሮች የሚቆጠር ደግሞ ለከተማ ማስዋብ እና ለቱሪዝም ስፍራዎች ግንባታ እየዋለ ባለበት ወቅት ነው። ነዳጅ ለማስገባት የዶላር በእጅጉ መመናመን እንዳለ እንረዳለን፣ ግን በአንድ በኩል ለወደፊት ሊቆዩ የሚችሉ የከተማ ማስዋብ ፕሮጀክቶች ላይ ገንዘብ እየፈሰሰ፣ በዚህ በኩል ደግሞ ያውም ለኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ የሆኑትን ግብርናን እና ግንባታን የሚያከናውኑ ቅንጡ ያልሆኑ ተሽከርካሪዎችን መከልከል ምን ያህል misplaced priorities እንዳሉብን ማሳያ ነው።
Show more ...
52 965
70
“ከጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ እና ከዳሽን ባንክ ጋር ያለው ግንኙነት እስካሁን አልተቋረጠም”--- የጤና ሚኒስቴር "በተያዘው በፕሮግራም መሰረት በዓመት አራት ጊዜ እጣ መውጣት እያለበት እስካሁን 2 ጊዜ ብቻ ወጥቷል"--- የጤና ባለሙያዎች ከሰሞኑ በተከታታይ ከሚደርሱኝ ጥያቄዎች አንዱ በጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ተጭበረበርን የሚሉ ዜጎች ይገኙበታል። ኢትዮጵያ ቼክ የሰራውን ዘገባ ላጋራችሁ ⬇️ ከሰሞኑ “ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ከጤና ሚኒስቴር ጋር የተፈራረመውን የጤና ዘርፍ ሰራተኞች ቤት ግንባታ ስምምነት አፍርሷል፤ ቤት ለማግኘት ክፍያ የፈጸሙ የጤናው ዘርፍ ሰራተኞችም ተጭበርብረዋል” የሚሉና ኢትዮጵያ ቼክ ጉዳዩን እንዲያጣራ የሚጠይቁ መልዕክቶች ከተከታታዮቻችን ደርሰውናል። የጤና ባለሙያዎች ለኢትዮጵያ ቼክ ባደረሱት ተከታታይ መረጃ የከፈሉት ብር ይመለሳል የሚል መረጃ ሲዘዋወር እንደተመለከቱና ይህም ማለት ማህበሩ ፈርሷል ብለው እንዲያስቡ እንዳረጋቸው ጠቁመዋል። የጤና ባለሙያዎቹ አክለውም የጎጆ ዕጣ በተያዘው በፕሮግራም መሰረት በዓመት አራት ጊዜ መውጣት እያለበት እስካሁን 2 ጊዜ ብቻ ወጥቷል፣ በውል ስምምነቱ መሰረት በየ 3 ወሩ ነው ዕጣ ይወጣል ቢልም በ ውሉ መሰረት ዕጣ አልወጣም እንዲሁም ችግሮች እንኳን ቢኖሩ እነዚህ ችግሮች ሲፈጠሩ ወቅታዊ መረጃ ለተመዝጋቢዎች አልተሰጡም የሚሉ ቅሬታዎች ቀርበዋል። የጤና ሚኒስቴር የጤና ዘርፍ ሰራተኞች የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክትን በተመለከተ ከጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ እና ዳሽን ባንክ ጋር የሶስትዮሽ ስምምነት ተፈራርሞ የመጀመሪያ ዙር እጣ ማውጣት ስነ ሰርዓት የተካሄደው ሰኔ 2015 ላይ ነበር። በስነ ሰርዓቱም 200 ጤናው ዘርፍ ሠራተኞች የመጀመርያ ዙር የዕጣ እድለኞች ሲሆኑ ዕጣ  የማውጣት ሂደቱ በየሶስት ወሩ እንደሚቀጥልና እየሰፋ እንደሚሄድም ተጠቁሞ ነበር። ይህ መረጃም በወቅቱ በሚኒስቴሩ የተረጋገጠ የፌስቡክ ገጽ ተጋርቶ ነበር፡ ይሁን እንጂ “ሁለቱ ተቋማት መካከል የተፈረመው ስምምነት ፈርሷል” የሚለውን መረጃ መነሻ በማድረግ ኢትዮጵያ ቼክ ከጤና ሚኒስቴር እና ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ መረጃዎችን ለማግኘት ጥረት አድርጓል። በጤና ሚኒስቴር የጤና ዘርፍ ሰው ሀብት ልማት ማሻሻያ መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ አሰግድ ሳሙኤል ጉዳዩን በተመለከተ ለኢትዮጵያ ቼክ መረጃ የሰጡ ሲህን ‘በሁለቱ ተቋማት መካከል የተፈረመው ስምምነት ፈርሷል’ የሚለው መረጃ ሀሰት መሆኑን ነግረውናል። “ጤና ሚኒስቴር ከጎጆ እና ከዳሽን ባንክ ጋር ያለው ግንኙነት እስካሁን አልተቋረጠም። ያንን የሚያደርግ ከሆነ ጤና ሚኒስቴር በባለሙያው በኩል ነው የቆመው” ያሉት አቶ አሰግድ፤ “ማንኛውም በዚህ ሂደት ውስጥ የሚያልፍ ነገር ባለሙያው ላይ ማንኛውም አይነት ችግር የሚፈጥር ከሆነ (ጤና ሚኒስቴር) በፍጹም ዝም ብሎ የሚያይበት ነገር አይኖርም። ስለዚህ የመግባቢያ ስምምነቱ እስካሁን አልተቋረጠም” ብለዋል። የጤና ሚኒስቴር ከጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ጋር ስምምነት ሲፈጽም የተቋሙን ህጋዊ ሰነዶችን ተመልክቶ መሆኑን የሚናገሩት ስራ አስፈጻሚው ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ፤ ዳሽን ባንክና ጤና ሚኒስቴር የተፈራረሙት ስምምነት አላማ 10 ሺህ ቤቶችን በ10 አመት ገንብቶ ለመጨረስ እንደሆነም ነግረውናል። ባጠቃላይ ከ8000 በላይ ሰራተኞች የፕሮግራሙ አካል መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ አሰግድ፤ እስካሁን በሁለት ዙሮች 400 የጤናው ዘርፍ ሰራተኞች በጋራ የማህበር ቤት እንዲገነቡ እጣ እንደወጣላቸውም ይናገራሉ። ይሁን እንጂ “እጣዎቹ ከወጡ በኋላ ችግር የሆነው ከመሬት አስተዳደር፤ ከአዲስ አበባ ማህበራት ማደራጃ ጋር ተያይዞ የተወሰኑ የአሰራር ለውጦች ተደረጉ። ከተማ ውስጥ ያለው ከመሬት ጋር ተያይዞ ያለው ችግርም የሚታወቅ ነው። ከተማ አስተዳደሩ ያንን ማኔጅ ለማድረግ በየጊዜው የሚያወጣቸው አዳዲስ ህጎች አሉ። እነሱ (ሂደቱን) አፌክት አድርገውታል” ብለዋል። ስለዚህም እጣ የወጣላቸው እድለኞች በሚፈለገው ጊዜ ግንባታ ያለመጀመራቸውን በመጥቀስ “ትልቁ እኛም የገመገምነው ችግር አሁን ባልኩት ዉስጣዊም ዉጫዊም ችግሮች፤ ጎጆም ጋር ባለው ግንባታው ዘግይቷል የሚል ነው” ብለዋል። በተጨማሪም ጤና ሚኒስቴር የጤናው ዘርፍ ሰራተኞችን ለማበርታትና ለማትጋት ከጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ በተጨማሪ ሌላ የመኖሪያ ቤት ማግኛ አማራጮች ላይ እየሰራ መሆኑንም አቶ አሰግድ ሳሙኤል ለኢትዮጵያ ቼክ ነግረዋል። በሌ በኩል ጉዳዩን በተመለከተ የጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግን አስተያየት ለማግነት ለዋና ስራ አስኪያጁ አቶ አለማዉ ጋሪ ብንደዉልም ለጊዜው መረጃ ማግኘት አልቻልንም።
Show more ...
57 580
186
51 115
9
#ጥቆማ በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና (Dire Dawa Free Trade Zone) ውስጥ ከሚገኘው የ UN የምግብ ማከማቻ መጋዘን ውስጥ ለተራቡ ዜጎች ተብለው የሚወጡትን የምግብ አይነቶች እዛው የንግድ ቀጠና ውስጥ ፓኬጁ ላይ ባንዲራ በመጨመር ለሌላ አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርገው ከስፍራው እየወጡ እንደሆነ ከስፍራው እየደረሱኝ ያሉ ተደጋጋሚ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የሚመለከተው አካል ካለ በዜጎች ረሀብ የሚጫወቱትን እነዚህ አካላት ስርዐት ሊያስይዝ ይገባል።
55 662
32
#የሚድያነፃነት የዛሬ 5 አመት ግንቦት 2011 ዓ/ም ላይ የአለም የፕሬስ ነፃነት ቀንን ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ግዜ አዘጋጅታ ነበር፣ በፕሮግራሙ ላይ ከዓለም ዙርያ የተውጣጡ የሚድያ ባለሙያዎች ታድመው ነበር፣ እኔም ተገኝቼ ነበር። እለቱ በኢትዮጵያ እንዲከበር የተደረገው በወቅቱ በእጅጉ ተሻሽሎ የነበረውን የፕሬስ ነፃነት recognition ለመስጠት ጭምር ነበር። የተደረጉት ንግግሮች፣ ቃል የተገባባቸው ጉዳዮች እና ተስፋ ሰጪ ምልክቶች በርካቶች ነበሩ። በኢህአዴግ ስርዐት ውስጥ ለበርካታ አመታት በችግር ውስጥ ጋዜጠኝነት እንደሰራ አንድ ባለሙያ እኔም ተስፋ ታይቶኝ ነበር።  ዛሬስ? ዛሬ ላይ ያ ሁሉ ተቀይሮ ከድሮው እጅግ የባሰ የፕሬስ መብት ረገጣ ያለበት ግዜ ሆኗል። ጋዜጠኛ አይደለም ስህተት ሰርቶ ገና ለገና ለተቃዋሚ ድጋፍ ሊሰጥ ይችላል፣ ግፎችን ሊያጋልጥ ይችላል እና ሚስጥር ሊያወጣ ይችላል ተብሎ ወደ እስር ቤት ተግዟል። ከሰሞኑ እየሰማሁት እንደሆነው ደግሞ የመንግስት ሚድያዎች ውስጥ የሚሰሩ ጋዜጠኞች ጭምር ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እየገቡ ነው። በባለስልጣናት ቀጭን ትእዛዝ ይህን ዘግብ፣ ያንን አትዘግብ እየተባሉ ማስፈራርያ ጭምር እየደረሰባቸው ነው። ሌላው ቀርቶ አንዳንድ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሙስናና እና ሌሎች ወንጀሎች ሰራተኞቻቸው ሲታሰሩ "የቀድሞ ሰራተኛ ብላችሁ ዘግቡ" በማለት በተለይ የመንግስት ሚድያዎችን እያስገደዱ ይገኛሉ። "በፕሮግራም ላይ ተገኝቼ ለምን ዜና አልሰራህም?" ተብሎ ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከስራው የተባረረው ነፍሱን ይማረው ጋዜጠኛ በቀለ ሙለታ አንድ ምስክር ነበር። በቅርቡ ከአዲስ ዘመን፣ ከኢዜአ፣ ከኢቲቪ፣ ከፋና... ወዘተ ስራቸውን የለቀቁም አሉ። Free the media!
Show more ...
58 330
10
ስርዐት የሚጎድላቸው እና ያልተገሩ መልዕክቶችን ማህበራዊ ሚድያ ላይ በስፋት ከሚያሰራጩ ግለሰቦች አንዱ አምባ. ሱሌማን ደደፎ መሆናቸውን ብዙዎች ያነሳሉ የሜቴክ (ኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የሚባለው) ሀላፊው አሁን ደግሞ BYD ስለተባለ የቻይና መኪና አምራች ኩባንያ ትዊት ባደረጉበት አንድ ፅሁፍ ህፃናት እንዲያዩት የማይመከር ድረ-ገፅ ከፍተው ሲያዩ እንደነበር የሚያሳይ ምስል አብረው ትዊት አርገው ነበር (ምስሉ ተያይዟል)፣ ኋላ ላይ እሱን አጥፍተው እና ድረ-ገፁን ቆርጠው መልሰው መረጃውን አጋርተዋል። ለልጆቻችን ምን እናስተምር? Pics: Sad Engineer
50 030
122
https://t.me/boost/eliasmeseret boost
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
Boost this channel to help it unlock additional features.
68 816
5
ግድያን ለመሸፋፈን መሯሯጥ?! በርካቶችን ያሳዘነውን የበቴ ኡርጌሳን የጭካኔ ግድያ "ከወንድማቸው ጋር ድብድብ ውስጥ ገብተው ነበር" እና አሟሟታቸው ከእርሻ ስራቸው ጋር በተያያዘ እንደሆነ ህዝብን ለማሳመን የሚደረገውን የማህበራዊ ሚድያ ዘመቻ አያይዤዋለሁ፣ የፕሮፋይል ፎቷቸው እንኳን የአንድ ምድብ ሰዎች እንደሆኑ ያስታውቃል። ለማንኛውን ተአማኒነት ያለው ምርመራ ተደርጎ ውጤቱ ለህዝብ ይፋ ሊደረግ ይገባል።
85 951
62
ለበርካታ ወራት በእስር ሲሰቃዩ የነበሩት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሩ አቶ በቴ ኡርጌሳ በትውልድ ከተማቸው መቂ ከተማ በትናንትናው እለት ተገድለው እንደተገኙ ታውቋል አርፈውበት ከነበረው ሆቴል እንዲወጡ ተደርገው የተገደሉት አቶ በቴ በንግግራቸው እና በሰከነ አስተሳሰባቸው በብዙዎች ዘንድ የሚታወሱ ናቸው። ነፍስ ይማር
80 533
60
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን፣ እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ። ኢድ ሙባረክ!
71 741
30
በአዲስ አበባ እየተከናወነ የሚገኘው አፈሳ እና የታሰሩ ሰዎችን ለማስለቀቅ በገንዘብ የሚደረግ ድርድር ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ በከተማው 'ወቅታዊ' በሚል ምክንያት ከፍተኛ አፈሳ እየተፈፀመ እንደሆነ፣ በዚህም በርካታ ግለሰቦች ወደ እስር ቤቶች እየተጋዙ እንደሆነ የሚደርሱኝ መረጃዎች ያመለክታሉ። እስሩ በብዛት የአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ፣ ከሬስቶራንት፣ መዝናኛ ስፍራዎች እና የስራ ቦታ ጭምር አፈሳው እየተፈፀመ እንደሆነ ምንጮች የጠቆሙኝ ሲሆን ጉዳዩ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር ደርሶ ምርመራ እየተደረገበት እንደሆነም ታውቋል። አፈሳውን በአብዛኛው የሚፈፅሙት ሲቪል የለበሱ 'ክትትል' የሚባሉ አካላት ሲሆን ለምሳሌ 22 አካባቢ አደይ አበባ ስታዲየም ፊት ለፊት የሚገኘው ፖሊስ ጣብያ አይነት ማቆያዎች ለዚህ ተግባር እየዋሉ እንደሆኑ እና ከሞሉ ደግሞ ኮንቴይነሮች ውስጥ እንዲታሰሩ እየተደረገ እንደሆነ ታውቋል። ታዲያ ይህን እስር ለየት የሚያደርገው አንዳንድ የፀጥታ አካላት በግልፅ የገንዘብ ድርድር በማድረግ ታሳሪዎችን በገንዘብ መልቀቃቸው ነው፣ ከ30,000 ብር እስከ 80,000 ብር ያውም በግልፅ በባንክ ትራንስፈር እንደሚደረግ ታውቋል። በርካታ ምስጉን የፀጥታ አካል እንዳሉ ብናውቅም እንዲህ አይነት በጫካ ከሚደረግ እገታ ያልተናነሰ ወንጀል መሀል ከተማ እንደሚፈፀም መንግስት መረጃው ይኖረው ይሆን?
Show more ...
67 975
154
የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) የተባለ እንቅስቃሴ እንዲቆም መደረጉ መልካም ነው፣ ብዙ ማህበረሰባዊ ቀውሶች ፈጥሯል እሱ እንዳለ ሆኖ የቤቲንግ ድርጅቶች አከራዮች ላይ እየተፈፀመ ያለው መረን የለቀቀ የህግ ጥሰት እና እንግልት ሀይ ሊባል ይገባል። ንግድና ኢንድስትሪ ቢሮ በብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ድርጅት በኩል ንግድ ፈቃድ ሰጥቶ፣ ከአከራዮች የኪራይ ግብር ሲሰበስብ ቆይቶ፣ ገቢዎች ካሽ ሬጅስተር ሰጥቶ ቫት እና ተያያዥ ግብሮችን እየሰበሰበ ቆይቶ አሁን ላይ ቤቲንግ እንዲቆም ሲደረግ እነሱን ኢላማ ማድረጉ አግራሞትን ያጭራል። እንደምትመለከቱት አሁን ላይ በየአካባቢው በተዋቀሩ የሰላም እና ፀጥታ ግብረ ኃይሎች ይሄን ማህተም፣ ፊርማ ወይም ከመዝገብ ቤት ወጪ የሆነበት ቁጥር እንኳን የሌለውን ወረቀት በማስፈረም ላይ ይገኛሉ። በኋላ ተመልሰው መጥተው በገንዘብ ለመደራደር በር ከፋች ነው። ቀድመው ህግ ጥሰው አከራይተው ቢሆን ባልከፋ፣ ፈቃድ ሰጥቶ እና ግብር ሲሰበስብ ቆይቶ ይህ መሆኑ ከንብረት እና ተያያዥ ህግጋት አንፃር አያስኬድም። በዚህ አካሄድ የተጎዱ በርካታ ዜጎች እየጠየቁ ያሉት: - ወደፊትስ በሌሎች ዘርፎች ላሉ ብናከራይ እና እነሱም ህገወጥ ቢባሉ ተጠያቂ የማይኮንበት ዋስትና አለን ወይ? - ካልሆነ ህጋዊ የሚባሉትን ዘርፎች ዝርዝር መንግስት ይስጠን
Show more ...
55 675
80
#Update በቦሌ አየር ማረፊያ አንድ ተጓዥን በማጉላላት እና በማስፈራራት 'የያዝሽውን ጌጣ ጌጥ እና ዶላር አካፍዪኝ' በማለቷ ተይዛ የነበረችው ተጠርጣሪ ግለሰብ በዋስ መለቀቋን የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል የጉምሩክ ሰራተኛዋ ድርጊት በዚህ ቻናል ላይ ከተጋለጠ በኋላ መረጃው በካሜራ እገዛ በተደረገ ክትትል መታየት ችሎ ነበር። ይህን ተከትሎም በቁጥጥር ስር ውላ ቆይታለች። ዛሬ የደረሰኝ መረጃ እንደሚጠቁመው ደግሞ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ለምርመራ ማጣሪያ በቂ ጊዜ መሰጠቱን ገልጾ ግለሰቧ በ50 ሺህ ብር ዋስ ከስር እንድትፈታ ትዕዛዝ ሰጥቶ መለቀቋን ታውቋል፣ በወቅቱም ፖሊስ ይግባኝ አልጠየቀም።
55 723
29
#FactCheck ይህን ቪድዮ በርካታ ሰዎች እያጋሩት ይገኛል ቪድዮው መሬት ላይ የሌለ እና ሀሰተኛ ሲሆን ከአምስት አመት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ተከስቶ የነበረን ግጭትና አለመረጋጋት የሚያሳይ ነው። ማረጋገጫ: ጊዜያቸውን ባልጠበቀና ከአውድ ውጭ በሆነ መልኩ የሚጋሩ ቪዲዮዎች ለሀሰተኛና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ጥንቃቄና ማጣራት እናድርግ። Courtesy: Ethiopia Check
65 784
12
በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ትላንት መጋቢት 29 የመግሪብ ሰላት ሰግደው ሲመለሱ የነበሩ አባት ከ3 ልጆቹ እንዲሁም አንድ ጎረቤታቸውን ጨምሮ አጠቃላይ 5 ሰዎች በተከፈተባቸው የጥይት እሩምታ መገደላቸው ተነግሯል። ትላንትና ምሽት በግፍ የተገደሉት አቶ ሙሄ ፣ልጃቸው አበባዉ ሙሄ፣ ሽኩር ሙሄ፣ ሙላት ሙሄ እና ጎረቤታቸው አቶ እንድሪስ የተባሉ ሲሆኑ ስርዓት ቀብራቸው በዛሬው ዕለት ተፈፅሟል። እስካሁን ገዳዮች ስለመያዛቸው የተባለ ነገር የለም። በከተማዋ ከተገደሉት ሰዎች ባሻገር ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ የሚገኘው መስጂድ ከፍተኛ የመሳሪያ ድብደባ እንደተፈፀመበት ተገልጿል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዛሬ የባህር ዳር ሙስሊሞች በክልሉ በሙስሊሞች ላይ አነጣጥረዋል ያሉትን ግድያ እና እገታ በመቃወም ሰልፍ ማድረጋቸውን "ሀሩን ሚዲያ" ዘግቧል። እስካሁን በአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትም ሆነ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ አስተያየት የለም። Via Tikvah Ethiopia
Show more ...
62 217
34
ፈጣን እና አስደሳች ስራ በአዲስ አበባ ፖሊስ! አሁን እነዚህን ጭካኔያቸውን የሚመጥን ፍትህ በመስጠት ማስተማርያ ማድረግ ነው።
77 580
51
አሁን ደግሞ በቀጣይ የተቃውሞ ሰልፍ ተፈቅዶ ተቃውሞ ያለው ድምፁን እንዲያሰማ ቢፈቀድ የስርዐቱን ታጋሽነት፣ ዴሞክራሲያዊነት እና ሁሉን አካታች ህብረ-ብሄራዊነት ያሳይ ነበር... ያው ነበር ነው!
78 478
31
የሰጣችሁት ድምፅ ውጤት ይህን ይመስላል! 9 ፐርሰንት ወይም 1,585 ሰው >>> በፈቃዴ ድጋፍ ለመስጠት ሰልፍ እወጣለሁ 91 ፐርሰንት ወይም 15,994 ሰው >>> ካልተገደድኩ በቀር ደግፌ ሰልፍ አልወጣም በአጠቃላይ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ህዝብ፣ ማለትም 17 ሺህ 579 ሰው ድምፅ በመስጠት ተሳትፏል።
81 154
46
የህግ ትምህርት ቤት እያለን ጀምሮ ወዳጄ የሆነው ጠበቃ ሙሉጌታ በላይ ንግድ ባንክ ከሰሞኑ እያወጣ ያለውን የተጠርጣሪዎች ፎቶ በተመለከተ ይህን ብሏል። ቪድዮው ሲጠቃለል: - የግለሰቦችን ምስል ለህዝብ ማውጣት በልዩ ሁኔታ የተፈቀደላቸው ፖሊስ እና ፍርድ ቤት ብቻ ናቸው - ባንኩ ማድረግ የሚችለው በእነዚህ ፍቃድ ባላቸው ተቋማት በኩል ግለሰቦቹን ለመያዝ ካስፈለገ ለጥቆማ እንዲያግዝ ፎቷቸውን ይፋ ያስደርጋል እንጂ ራሱ ማድረግ አይችልም፣ - ባንክ ግለሰቦችን ወንጀለኛ ማለት አይችልም፣ ፖሊስም አይችልም። ብቸኛው ይህ መብት ያለው ፍርድ ቤት እና ፍርድ ቤት ብቻ ነው  ትናንት ይህን ድርጊት በተመለከተ አንድ መረጃ አጋርቼ "ለሌባ ጠበቃ ቆምክ፣ አንተም ወስደሀል መሰለኝ..." አይነት ዝባዝንኬ አስተያየት የሰጡ ነበሩ። ዛሬ ይህ ተቋም ከህግ ውጪ ፎቶ ሲለጥፍ "ለምን?" ካላልን ነገ የፈለገው ድርጅት እና ግለሰብ እየመጣ ፎቶህን ለጥፎ ያሻውን ያደርጋል። ባለኝ መረጃ መሰረት በዚህ አስነዋሪ ድርጊት ላይ ያልተሳተፉ ሰዎች ጭምር ፎቷቸው ወጥቶ ፍርድ ቤት እያመሩ ነው፣ ሌሎቹ ደግሞ የወሰዱትን ብር መልሰው ፎቷቸው ግን ወጥቷል። ሌብነትን እናውግዝ፣ ለህግ የበላይነት እና መከበርም እንቁም። መልካም አዳር።
Show more ...

file

83 392
95
አዳዲስ የዚህ የቴሌግራም ቻናል ሰብስክራይበሮች እንኳን በደህና መጣችሁ! እስቲ የቻናሉ ነባር ኗሪዎች በ reaction ተቀበሏቸው። 👍 🙏🏽 ❤️ 👋 🫱🫲 🤝
74 400
10
እንኳን ለሲዳማ ህዝብ የዘመን መለወጫ 'ፍቼ ጫምበላላ' በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን! Ayidde Cambalaalla!
80 717
14
Last updated: 11.07.23
Privacy Policy Telemetrio