አምላካችን አሏህ ሰው እርስ በእርስ ሥጋውን እንዲበላላ ሐላል አላደረግም፥ ከዚያ በተቃራኒ የሰው ሥጋ መብላት ሐራም ነው፦
49፥12 ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ! አንደኛችሁ የወንድሙን ሥጋ የሞተ ኾኖ ሊበላው ይወዳልን? መብላቱን ጠላችሁት ሐሜቱንም ጥሉት፡፡ አሏህን ፍሩ! አሏህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡ وَلَا يَغْتَب بَّعْضُكُم بَعْضًا ۚ أَيُحِبُّ أَحَدُكُمْ أَن يَأْكُلَ لَحْمَ أَخِيهِ مَيْتًا فَكَرِهْتُمُوهُ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ تَوَّابٌ رَّحِيمٌ
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 106
አነሥ ኢብኑ-ማሊክ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ወደ ሰማይ በተወሰድኩኝ ጊዜ ከነሐስ የሆነ ጥፍር ኖሯቸው ፊቶቻቸውን እና ደረቶቻቸውን የሚቧጥጡ በሆኑ ሰዎች በኩል አለፍኩ። እኔም፡- "ጂብሪል ሆይ! እነማናቸው እነዚህ? ስለው፥ እርሱም፦ "እነዚህ የሰዎችን ሥጋ የሚበሉ እና ክብራቸውን የሚነኩ ናቸው" አለኝ"። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم " لَمَّا عُرِجَ بِي مَرَرْتُ بِقَوْمٍ لَهُمْ أَظْفَارٌ مِنْ نُحَاسٍ يَخْمِشُونَ وُجُوهَهُمْ وَصُدُورَهُمْ فَقُلْتُ مَنْ هَؤُلاَءِ يَا جِبْرِيلُ قَالَ هَؤُلاَءِ الَّذِينَ يَأْكُلُونَ لُحُومَ النَّاسِ وَيَقَعُونَ فِي أَعْرَاضِهِمْ "
እዚህ ቁርኣን እና እዚህ ሐዲስ ላይ ሐሜት ልክ የሰውን ሥጋ እንደ መብላት ሐራም ከሆነ የሰውን ሥጋ ለምግብነት መጠቀም ሐራም ነው። ሰው ከሞተ በኃላ ሥጋው ሬሳ ነውና መቅበር እንጂ የሞተ ሰው ሥጋ መብላት በቁሙ ያለው ሰው ሥጋ እንደ መብላት ይቆጠራል፦
ሡነን እብኑ ማጃህ መጽሐፍ 6, ሐዲስ 184
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የሞተ ሰው አጥንት መስበር በሕይወት እያለ እንደ መሰባበር ነው"። عَنْ عَائِشَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ " كَسْرُ عَظْمِ الْمَيِّتِ كَكَسْرِهِ حَيًّا "
ኢማም ሙሐመድ ኢብኑ ኢድሪሥ አሽ ሻፊዒይ "የሞተ ሰው ሥጋ ሕይወትን ለማትረፍ በረሃብ ጊዜ ይፈቀዳል" ብለዋል፥ ለዚህ አባባል ምንም ዓይነት የቁርኣን ሆነ የሐዲስ ደሊል እንከሌለ ድረስ ንግግራቸው ውድቅ ይሆናል። እርሳቸው በ 204 ዓመተ ሒጅራህ በትህትና "የእኔን ንግግር የሚቃወም ሶሒሕ ሐዲስ ሲኖር በሐዲሱን ተግብሩ! ቃሌን ተዉት" ብለዋል፦
"የእኔን ንግግር የሚቃወም ሶሒሕ ሐዲስ ሲኖር በሐዲሱን ተግብሩ! ቃሌን ተዉት"። إذا صح الحديث خلاف قولي فاعملوا بالحديث واتركوا قولي
ጃሚዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 37 ሐዲስ 106
አቢ ሠዒድ አል ኹድሪይ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ማንም ይሁን መልካሙን የበላ፣ በሡናህ የተገበረ እና ሰዎች ከሚያስከትለው መዘዝ የታደገ ወደ ጀናህ ይገባል"። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم " مَنْ أَكَلَ طَيِّبًا وَعَمِلَ فِي سُنَّةٍ وَأَمِنَ النَّاسُ بَوَائِقَهُ دَخَلَ الْجَنَّةَ " .
"ሐላል" حَلاَل ማለት "የተፈቀደ" ማለት ሲሆን በተቃራኒው "ሐራም" حَرَام "የተከለከለ" ማለት ነው። አንድ ጉዳይ ሐላል ወይም ሐራም ማለት የሚቻለው የዓለማቱ ጌታ አሏህ በቁርኣን የነገረን እና ተወዳጁ ነቢያችን”ﷺ” በሐዲሳቸው የነገሩን ብቻ እና ብቻ ነው፥ ሐላል የሆነ ጉዳይ ሆነ ሐራም የሆነ ጉዳይ በሸሪዓችን በግልጽ የተቀመጡት ብቻ ናቸው፦
7፥157 "መልካም ነገሮችንም ለነርሱ ይፈቅድላቸዋል፥ መጥፎ ነገሮችንም በእነርሱ ላይ እርም ያደርግባቸዋል"፡፡ وَيُحِلُّ لَهُمُ الطَّيِّبَاتِ وَيُحَرِّمُ عَلَيْهِمُ الْخَبَائِثَ
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 23, ሐዲስ 4
አን-ኑዕማን ኢብኑ በሺር እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ሐላል ግልጽ ነው፥ ሐራምም ግልጽ ነው። በሁለቱ መካከል ያለው ግን አጠራጣሪ ነገር ነው”። قَالَ سَمِعْتُ النُّعْمَانَ بْنَ بَشِيرٍ، – وَلاَ أَسْمَعُ أَحَدًا بَعْدَهُ يَقُولُ – سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ” إِنَّ الْحَلاَلَ بَيِّنٌ وَإِنَّ الْحَرَامَ بَيِّنٌ وَبَيْنَهُمَا أُمُورٌ مُشْتَبِهَاتٌ ”
አንድ ጉዳይ በግልጽ መፈቀዱ እና መከልከሉ ካልተገለጸ "ተፈቅዷል" "ተከልክሏል" ማለት የለብንም፥ ያልተፈቀደ እና ያልተከለከለ ነገር ጉዳይ አጠራጣሪ ነው፥ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ደግሞ፦ "የሚያጠራጥርህን ትተህ ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት ያረጋጋል፥ ውሸት ግን ያጠራጥራል" ብለውናል፦
ጃምዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 2708
አቢል ሐውራእ አሥ-ሠዕዲይ እንደተረከው፦ "እኔ ለሐሠን ኢብኑ ዐሊይ፦ "ከአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ምን ሐፈዝክ? ብዬ አልኩኝ፥ እርሱም፦ "ከአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሐፈዝኩኝ፦ "የሚያጠራጥርህን ትተህ ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት ያረጋጋል፥ ውሸት ግን ያጠራጥራል"። عَنْ أَبِي الْحَوْرَاءِ السَّعْدِيِّ، قَالَ قُلْتُ لِلْحَسَنِ بْنِ عَلِيٍّ مَا حَفِظْتَ مِنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ حَفِظْتُ مِنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم " دَعْ مَا يَرِيبُكَ إِلَى مَا لاَ يَرِيبُكَ فَإِنَّ الصِّدْقَ طُمَأْنِينَةٌ وَإِنَّ الْكَذِبَ رِيبَةٌ "
"መሽቡህ" مَشْبُوه የሆኑ ነገሮችን መተው ተመራጩ ሒክማህ ነው። አምላካችን አሏህ በግልጠተ መለኮት "ሐላል" ያለው "ሐላል" ማለት "ሐራም" ያለው "ሐራም" ማለት ትልቅ ታዛዥነት ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 29, ሐዲስ 117
ሠልማን አል ፋርሢይ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” ስለ ቅቤ፣ ስለ ዓይብ እና ስለ አህዮች ተጠየቁ፥ እርሳቸው እንዲህ አሉ፦ "ሐላል አሏህ በመጽሐፉ የፈቀደው ነው፥ ሐራም አሏህ በመጽሐፉ የከለከለው ነው። عَنْ سَلْمَانَ الْفَارِسِيِّ، قَالَ سُئِلَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ عَنِ السَّمْنِ وَالْجُبْنِ وَالْفِرَاءِ قَالَ " الْحَلاَلُ مَا أَحَلَّ اللَّهُ فِي كِتَابِهِ وَالْحَرَامُ مَا حَرَّمَ اللَّهُ فِي كِتَابِهِ " .
አምላካችን አሏህ ሡናን ከሚተገብሩ ሙእሚን ያድርገን! አሚን።
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም
ادامه مطلب ...