The service is also available in your language. For translation, pressEnglish
Best analytics service

Add your telegram channel for

  • get advanced analytics
  • get more advertisers
  • find out the gender of subscriber
دسته بندی
زبان جغرافیایی و کانال

audience statistics Abebe English

Abebe English official Telegram Channel 
11 4120
~0
~0
0
رتبه کلی تلگرام
در جهان
53 265جایی
از 78 777
در کشور, اتیوپی 
335جایی
از 396
دسته بندی
706جایی
از 960

جنسیت مشترکین

می توانید بفهمید که چند زن و مرد در این کانال مشترک هستند.
?%
?%

زبان مخاطب

از توزیع مشترکین کانال بر اساس زبان مطلع شوید
روسی?%انگلیسی?%عربی?%
تعداد مشترکین
چارت سازمانیجدول
D
W
M
Y
help

بارگیری داده

طول عمر کاربر در یک کانال

بدانید مشترکین چه مدت در کانال می مانند.
Up to a week?%Old Timers?%Up to a month?%
رشد مشترکین
چارت سازمانیجدول
D
W
M
Y
help

بارگیری داده

Hourly Audience Growth

    بارگیری داده

    Time
    Growth
    Total
    Events
    Reposts
    Mentions
    Posts
    Since the beginning of the war, more than 2000 civilians have been killed by Russian missiles, according to official data. Help us protect Ukrainians from missiles - provide max military assisstance to Ukraine #Ukraine. #StandWithUkraine
    #Monkeypox የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Monkeypox) በተለያዩ ሀገራት እየተሰራጨ ነው። ጎረቤት ኬንያም ከዚህ ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪ አግኝታ ናሙናዎችን ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሴኔጋል ልካለች። ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ጋር በተያያዘ ማወቅ ያለብን ጉዳዮች ፦ ምልክቶቹ ምንድን ናቸው ? በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዙ ሰዎች መጀመሪያ ላይ ሙቀት፣ራስ ምታት፣ የጀርባ ሕመም፣ የጡንቻ ሕመም፣ የሰውነት ማበጥ እና በማንኛውም ነገር ላይ ፍላጎት ማጣት ይታይባቸዋል። ሙቀቱ ጋብ ሲል ሰውነት ከፊት ጀምሮ ማሳከክ ይጀምራል። መላው ሰውነትን ቢያሳክክም ክንድና እግር የበለጠ ያሳክካሉ። የሚከሰተው እከክ በጣም የሚያምና በተለያየ ደረጃ የሚያልፍ ነው። ቆዳ ላይ የሚከሰተው እብጠት ኋላ ላይ ቆዳ እንዲቆስልና እንዲረግፍም ያደርል። ጠባሳ ጥሎም ሊያልፍ ይችላል። ሕመሙ በራሱ ጊዜ የሚጠፋ ሲሆን ከ14 - 21 ቀናት ይወስድበታል። በሽታው እንዴት ይይዛል ? በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ሰዎች ተጋላጭ ናቸው። በቆዳችን ክፍተቶች በኩል፣በዓይን፣ በአፍንጫ ወይም በአፍ በኩል ቫይረሱ ወደ ሰውነታች ይገባል። በወሲብ ወቅት ባለ ንክኪም ቫይረሱ ይተላለፋል። በቫይረሱ ከተያዙ ዝንጀሮዎች፣ አይጦች ወይም ሌሎች እንስሳት ጋር ንክኪ ከተደረገ ቫይረሱ ወደሰው ይተላለፋል። ቫይረሱ በልብስ/በሌሎች ንክኪ ባላቸው ጨርቆች በኩል ይተላለፋል። ምን ያህል አስጊ ነው ? አብዛኞቹ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ለከፋ ሕመም አይዳረጉም። ልክእንደ ፈንጣጣ በተወሰኑ ሳምንታት ውስጥ ይጠፋል። ሆኖም ግን በሽታው ከፍተኛ ደረጃ ሊደርስም ይችላል። በምዕራብ አፍሪካ በበሽታው ሳቢያ የሞቱ ሰዎች አሉ። ሕክምና አለው ? ሕክምና የለውም። ስርጭቱን ግን መቆጣጠር ይቻላል። Via BBC/WHO
    ادامه مطلب ...
    2 205
    10
    ሁለት ጥርስ ያለው ልጅ ተወለደ። በወላይታ ዞን በገሱባ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አንዲት እናት ሁለት ጥርስ ያለው ልጅ ትላንት ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ/ም ተገላገለች። ይህ ክስተት " Natal teeth " ተብሎ እንደሚጠራ የዘርፉ ባለሙያዎች የሚገልፁ ሲሆን ከዚህ በፊት ብዙም ያልተለመደ ቢሆንም አዲስ ከሚወለዱ ከ2000 - 3000 ሕጻናት ውስጥ በአንዱ ላይ ሊከሰት እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ትላንትና የተወለደው ሁለት ጥርስ ያለው ልጅ ምንም ሳይቸገር ጡት እየጠባ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ የወላይታ ዞን ኮሚኒኬሽን መረጃ ያሳያል። በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ሊሰጥ የሚችል ፅሁፍ በዚህ ድረገፅ ማግኘት ይቻላል ፦
    ادامه مطلب ...
    default - Stanford Children's Health
    Natal teeth are teeth that are present when a baby is born. The teeth are often not fully developed and may have a weak root.
    2 560
    5
    የአሁኑ የኢንትራንስ ፈተና ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል መሆኑ ይታወቃል፡፡ ለዚህም ኢትዮማትሪክ ላይ በቅርቡ አዲስ update ለቀናል፡: ይህም ✅ ከ9-10 እና ከ11-12 ያለውን ያለምንም ችግር በቀላሉ እየቀያየራቹ መጠቀም የምትችሉበት መንገድ እና ✅ ከ9-10ኛ ክፍል ላሉት ደግሞ ተጨማሪ ፈተናዎችን አካትተናል፡፡ ይህ የሚገኘው በአዲሱ ቨርዥን (6.1) ብቻ ሲሆን ፤ በዚህ ሊንክ update ማድረግ ትችላላቹ
    2 279
    5
    #ሀሰት_ነው ! " ተማሪዎች ዘንድሮ በያላችሁበት ትደግማላቸሁ " በሚል የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል። በ2014 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ማጠቃለያ ላይ ተማሪዎች ማጠቃለያ ፈተናዎችን ለመውስድ እየተዘጋጁ ይገኛሉ። ነገር ግን ማህበራዊ ኃላፊነት በጎደላቸው አካላት ሆን ተብሎ ተማሪዎችን ለማዘናጋት በዘንድሮ ዓመት ከክፍል ወደ ክፍል መዘዋወር የለም ተብሎ በማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች የሚናፈሰው ወሬ ፍፁም ከእውነት የራቀ መሆኑን ቢሮው ገልጿል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ከኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የወረደ አቅጣጫ የለም ያለው የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ተማሪዎች " ተማሪዎች ዘንድሮ በያላችሁበት ትደግማላቸሁ" በሚል አሉባልታ ሳይምታቱ ለትምህርታቸው ትኩረት ስጥተዉ ለተሻለ ውጤት እንዲተጉ መልዕክት አስተላልፏል። በተጨማሪ ⬇️ የትምህርት ሚኒስቴር ፤ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚኒስቴሩን ስም እና አርማ በመጠቀም የተሳሳቱ እና የተዛቡ መረጃዎች እየተለቀቁ መሆኑን ገልጾ ተማሪዎች እና ወላጆች የሚሰረጩት መረጃዎች ከእውነት የራቁ መሆናቸውን በማወቅ በትኩረት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ አሳስቧል። Source: tikvah
    ادامه مطلب ...
    1 932
    14
    #የምስራች🎉 አባይ ኃይል መስጠት ጀመረ። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዛሬ ኃይል መስጠት ጀምሯል። ግድቡ ዛሬ ኃይል ማመንጨት የጀመረው ካሉት 13 ተርባይኖች ውስጥ በአንዱ ተርባይን አማካኝነት ነው። አንዱን ተርንባይን በመጠቀም ወደ ስራ የገባው ግድቡ 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተገልጿል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሙከራ ሂደት ሲያደርግ የነበረ ሲሆን የሙከራ ሂደቱ ተጠናቆ የኤሌክትሪክ ኃይል መስጠት ጀምሯል። ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ የግድቡን የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት ሂደቱን በይፋ አስጀምረዋል፡፡ ፎቶ ፦ አሚኮ & TK.SS ~ tikvah
    5 750
    3
    #Update በሳምንት ከአምስት ጊዜ በላይ ገንዘብ ማስተላለፍ የሚከለክለው መመሪያ ማንሳቱን ብሄራዊ ባንክ አስታወቀ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሳምንት ከአምስት ጊዜ በላይ ገንዘብ ማስተላለፍ የሚከለክለው መመሪያ መነሳቱን ይፋ አድርጓል። ብሔራዊ ባንክ ካለፈው ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ የባንኮች ደንበኞች በሳምንት ከአምስት በላይ የባንክ ዝውውሮችን እንዳያደርጉ የሚያዝ መመሪያ ማውጣቱ ይታወሳል። ይህም መመሪያ መደበኛ ባልሆነው የልውውጥ ገበያ ውስጥ ያሉ ተጫዋቾችን ተስፋ ለማስቆረጥ ያወጣው ደንብ መሆኑን አስታውቆ ነበር። ይሁን እንጂ ካሳለፍነው ሳምንት ታህሳስ 27 ቀን 2014 ጀምሮ ይህ መመሪያ መነሳቱን በብሔራዊ ባንክ የባንክ ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር ፍሬዘር አያሌው፣ መግለፃቸውን ሪፖርተር ዘግቧል። “ የዝውውር ገደቡ አሁን ሙሉ በሙሉ በመመርያ ተነስቷል ” ያሉት ፍሬዘር፣ ነገር ግን ባሳለፍነው ዓመት የወጣው የገንዘብ ወጪ ገደብን ጨምሮ ሌሎች ገደቦችም አሁንም ድረስ ተፈፃሚ ሆነው ይቀጥላሉ ሲሉ ተናግረዋል። ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ / አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ~ tikvah
    ادامه مطلب ...
    9 145
    17
    #JobVacancy የኢንፎርሜሽን መረብ ደህነንት ኤጀንሲ (ኢንሳ) በተጠቀሱት ክፍት የስራ መደቦች ሰራተኞችን አወዳድሮ በቋሚነት መቅጠር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ዝቅተኛ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሉት ሰባት/07/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የትምህርትና የስራ ልምድ ማስረጃ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል። አመልካቾች ወሎ ሰፈር በሚገኘው የኤጀንሲዉ ዋና መስሪያ ቤት የሰው ሃይል አቅርቦትና ቅጥር ቡድን ቢሮ 2ኛ ፎቅ በመቅረብ እንዲመዘገቡ ነው ኤጀንሲው ያስታወቀው።
    6 795
    21
    የ12ኛ ክፍል ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች ፈተናውን የሚወስዱበት ቀን ይፋ ተደረገ። በ2013 የጸጥታ ችግር በተከሰተባቸው አካባቢዎች የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ላልወሰዱ ተማሪዎች ከጥር 24 እስከ 27 ቀን 2014 ዓ.ም ፈተናው እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል። በሁለተኛ ዙር የሚሰጠውን ፈተና 58 ሺህ 936 ተማሪዎች እንደሚወስዱም የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ተናግረዋል።  በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች በፀጥታ ምክንያት ፈተና መወሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ አቶ ተፈራ አብራርተዋል። የመጀመሪያው ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያለምንም ችግር መጠናቀቁን ያስታወሱት ዳይሬክተሩ ሁለተኛ ዙርም በሰላም እንዲጠናቀቅ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል። ህብረተሰቡና የሚመለከታቸው አካላት ፈተናው በሰላም መጠናቀቅ እንዲችል የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ዳይሬክተሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢቢሲ ዘግቧል። via: tikvahethiopia
    ادامه مطلب ...
    6 482
    16
    የአብርሆት ቤተ-መፃህፍት ዛሬ ይመረቃል በአዲስ አበባ 4 ኪሎ በዘመናዊ መልኩ የተገነባው ቤተ መፃህፍት የማንበብ ባህልን ለማዳበር ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተመላክቷል። ቤተ መፃህፍቱ በዛሬው  እለት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት የሚመረቅ ይሆናል። በአንድ ጊዜ ከ2 ሺህ በላይ ተጠቃሚዎችን ማስተናገድ የሚችለው ቤተ መፃህፍት በውስጡ ከማንበቢያ ስፍራ በተጨማሪ፥ 8 የመጽሐፍ መሸጫ ሱቆች፣ የስብሰባ አዳራሽ፣ ካፍቴሪያ፣ የህፃናት ማንበቢያ ስፍራዎችን ያካተተ ነው። ከዚህ ባለፈም የተለየ ፍቃድ ያላቸው ሰዎች የሚያነቡበት የመጽሐፍ ክፍል እንዳለው የቤተ መፃህፍቱ ፕሮጀክት ማናጀር ታሪኩ ታደሰ ተናግረዋል፡፡ ቤተ መፃህፍቱ የተሟላ የመኪና ማቆሚያ እንዳለውም ተገልጿል፡፡(FBC)
    4 349
    5
    በ'ሰሞኑ ጉንፋን መሰል' ወረርሽኝ ላይ በጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተሰጠ ማብራሪያ ከላይ በፎቶ ተያይዟል
    4 533
    7
    "የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት የሚገለጽበት ጊዜ አልተወሰነም።" - አቶ ረዲ ሽፋ ከ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር የተያያዙ በርካታ ጥያቄዎች ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ደርሰዋል። የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ረዲ ሽፋ "ፈተናው ገና እየታረመ" መሆኑን ገልጸዋል። የፈተናው ውጤት የሚገለጽበት ጊዜ አለመወሰኑንም ነግረውናል። "የፈተናው ውጤት በዚህ ቀን ይገለጻል ተብሎ የተቀመጠ ቀነ ገደብ የለም። ስለዚህ በዚህ ቀን ይፋ ይደረጋል ልንል አንችልም" ብለዋል ዳይሬክተሩ። የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ለፈተናው ያልተቀመጡ ተማሪዎች ከአንድ ወር በኋላ ፈተናውን እንዲወስዱ ይደረጋል ተብሎ የነበረ ቢሆንም አሁን ባለው ሁኔታ ፈተናውን መስጠት እንደማይቻል ገልጸዋል። አካባቢዎቹ ገና እየተረጋጉ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ተማሪዎቹ ፈተናውን ለመውሰድ በስነ ልቦና መዘጋጀት እንደሚያስፈልጋቸው ጠቁመዋል። via: tikvahuniversity
    ادامه مطلب ...
    6 303
    15
    የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ! የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ከጥቅምት 29 እስከ ኀዳር 02/2014 ዓ.ም የሚሰጠውን የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። በመግለጫው የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦ • 617, 991 ተፈታኞች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናውን ለመውሰድ ተመዝግበዋል። ይህም ከባለፈው ዓመት የተፈታኞች ቁጥር በእጥፍ ይበልጣል። • የፈተናውን ዝግጅት ለማስተባበር በተቋቋመው ኮማንድ ፖስት አማካኝነት ፈተናውን ወደ መፈተኛ ጣቢያ የማድረሱ ሥራ በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል። ለዚህም የየብስ እና የአየር ትራንስፖርት ግልጋሎት ላይ ውሏል። • ፈተናው በመጀመሪያ ዙር የጸጥታ ችግር በሌለባቸው አካባቢዎች ይሰጣል ተብሏል። • በአማራ ክልል በፌደራል በተወሰነ ውሳኔ መሰረት በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ወሎ በኦሮሞ ብሔረሰብ በዋግኽምራ ዞኖች፤ በሰሜን ጎንደር ዞን አዲአርቃይ ጠለምት ወረዳዎች፤ በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም፣ አንጾኪያ ጋምዛ እና ግሼ ራበን ወረዳዎች በሁለተኛው ዙር ተካተዋል። • በአጠቃላይ በአማራ ክልል 36, 340 ተማሪዎች ፈተናውን አይወስዱም ተብሏል። • በሌሎች ክልሎች ያለውን የጸጥታ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ወደ ሁለተኛ ዙር ሊጠቃለሉ እንደሚችሉ ተጠቁሟል። • ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡ ተማሪዎች ከ92 እስከ 94 በመቶ ያህሉ በፈተና ወንበራቸው ላይ ይቀመጣሉ ተብሏል። via: tikvahuniversity
    ادامه مطلب ...
    9 815
    31
    ከዛሬ ጀምሮ በመላ አገሪቱ በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተከለከሉ ተግባራትና ግዴታዎች • ሁሉም ሰው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ በአዋጁ መሰረት የሚያወጣቸውን መመሪያዎችና የሚሰጣቸውን ትዕዛዞች የመቀበል ግዴታ አለበት • የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዙን እንቅስቃሴ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ዓላማ የሚቃረን፣ የሚቃወም እና ለሽብር ቡድኖች ዓላማ መሳካት አስተዋፅዖ የሚያደርግ፣ የሽብር ቡድኖችን የሚያበረታታ፣ ሰላማዊ ዜጎችን የሚያሸብር ንግግር በማንኛውም መንገድ ማድረግ ወይም ማሰራጨት የተከለከለ ነው • በየትኛውም መንገድ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሽብር ቡድኖች የገንዘብ፣ የመረጃ፣ የቁስም ሆነ የሞራል ድጋፍ ማድረግ የተከለከለ ነው • የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዙ በተዋረድ ውክልና ከሰጣቸው አካላት ፈቃድ ውጭ ማንኛውንም የአደባባይ ስብሰባ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ የተከለከለ ነው • ከመከላከያ፣ ከፌዴራል ፖሊስ ወይም ሌሎች ፈቃድ ከሚሰጣቸው የፀጥታ አካላት ወይም ከነዚህ አካላት እውቅናና ፈቃድ ውጭ ማናቸውንም የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው • በከተሞች አካባቢ የነዋሪ መታወቂያ፣ የመንጃ ፈቃድ፣ የሰራተኛ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም ከነዚህ ተመጣጣኝ የሆነ መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው • ማንኛውም ወሳኝ በሆነ የአገልግሎት ዘርፍም ሆነ በምርት ሂደት ላይ የስራ ማስተጓጎል ወይም የኢኮኖሚ አሻጥር መፈፀም የተከለከለ ነው • የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም ሰበብ በማድረግ የግል ጥቅም ለማግኘት ስልጣንን አላግባብ መጠቀም፣ ምክንያታዊ የሆነ ጥርጣሬ ሳይኖር ሆን ብሎ ዜጎችን ማሰር ወይም መሰል እርምጃ መውሰድ የተከለከለ ነው።(yenetube)
    ادامه مطلب ...
    7 088
    24
    #BREAKING በኢትዮጲያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ! የሚንስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው ነው በሀገር አቀፍ ደረጃ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን የፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዴዎን ጢሞቴዎስ ገለፁ፡፡ የፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዴዎን ጢሞቴዎስ አሁን መግለጫ እየሰጡ ነው።()
    5 318
    3
    አሜሪካ አንድን ከፍተኛ የአልቃይዳ መሪ መግደሏን አስታወቀች! በሶሪያ በፈጸመችን የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት አንድን ከፍተኛ የአልቃይዳ መሪ መግደሏን አሜሪካ አስታወቀች፡፡ጥቃቱ በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ የተፈጸመ ነው ያለው የአሜሪካ መከላከያ መስሪያ ቤት (ፔንታጎን) አብዱል ሃሚድ አል ማታር ይባላል ያለውን አንድን ከፍተኛ የአልቃይዳ አመራር መግደሉን አስታውቋል፡፡እንደ አረብ ኒውስ ዘገባ ፔንታጎን አልቃይዳ ሶሪያን እንደገና ለመደራጀት፣ ራሱን ለመገንባት፣ የውጭ አጋሮቹን ለማስተባበር እና የውጭ ሥራዎችን ለማቀድ እንደ አስተማማኝ መሸሸጊያ እየተጠቀመ ይገኛልም ነው ያለው፡፡()
    7 855
    11
    ለ 12ተኛ ክፍል ተማሪዎች የኢንትራንስ መፈተኛ ቀን ተቃርቧል በዚህ ወቅት ከማጥናት ባሻገር ያለፉትን ዓመት ጥያቄዎች መስራት ጥሩ ውጤት ለማምጣት ጉልህ ሚና አለው። ለዚህም በኢትዮጵያ ከ100,000 በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት EthioMatric አፕሊኬሽን ቀርቦላችኋል። - EthioMatric ከ2008-2012/13 ዓ.ም የ4 እና የ5 ዓመት የኢንትራንስ ፈተናዎች ከነመልሶቻቸው እና ከነማብራሪያቸው በየምዕራፉ ከፋፍሎ አስቀምጧል፡፡ EthioMatric አፕሊኬሽን ለማውረድ 👇👇 ለበለጠ መረጃ
    6 697
    10
    የኢትዮጵያ ሀገር መከላከየ ሰራዊት ዛሬ ተጨማሪ የአየር ጥቃት ፈፅሟል። ጥቃቱ በዚህ ሳምንት ብቻ 4ኛው መሆኑ ነው። የዛሬው የአየር ድብደባ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) የማሰልጠኛ ማዕከል መሆኑን በፌዴራል መንግስት ስር ያለው የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ገፅ አሳውቋል። ገፁ የአየር ድብደባው የት እንደተፈፀመ በግልፅ ባይጠቅስም " ሌላው የአሸባሪው ቡድን የህወሓት ማሰልጠኛ ማዕከል ዛሬ የአየር ጥቃት ዒላማ ሆኗል" ሲል ገልጿል። አክሎም ፥ " ይህ ማዕከል ለአሸባሪው ቡድን ወታደራዊ ሥልጠና ከመዋሉ በፊት የኢፌዴሪ መከላከያ ማሠልጠኛ ማዕከል ነበር በአሁኑ ወቅት አሸባሪው ቡድን በዚህ ተቋም ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና የሚሠጥበት፤ የዉጊያ ግንኙነት ኔት ወርክ ያለበት ነው" ብሏል። ሮይተርስ እና አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪሎች ደግሞ የዛሬው የአየር ድብደባ በመቐለ የተፈፀመ መሆኑን ዘግበዋል።(tikvahethiopia)
    ادامه مطلب ...
    5 853
    9
    በዛሬው ዕለት በትግራይ ክልል መዲና መቐለ የአየር ጥቃት መፈፀሙን ሮይተርስ ዘግቧል። የዛሬው ጥቃት በአራት ቀናት ውስጥ ለ3ኛ ጊዜ የተፈፀመ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ ዶክተር ለገሰ ቱሉ ዛሬ ሐሙስ የአየር ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጠዋል። የዛሬው የአየር ድብደባ ኢላማ ያደረገው የቀድሞ የኢትዮጵያ ሠራዊት ይዞታ የነበረና በአሁኑ ጊዜ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር /TPLF/ የማሰልጠኛ ማዕከል መሆኑን ዶ/ር ለገሰ ለሮይተርስ ተናግረዋል። ዶክተር ለገሰ ፥ የአየር ድብደባው የተፈፀመው በወታደራዊ ስፍራ ስለሆነ ምንም የሲቪሎች ጉዳት አልደረሰም ብለዋል። የዛሬው ጥቃት ከሰዓት ከ9 ሰዓት በኋላ የተፈጸመ መሆኑን ተገልጿል።
    4 970
    4
    አርቲስት መሰረት መብራቴ ለልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል ያሰባሰበችውን 6 ሚሊዮን ብር አስረከበች! አርቲስት መሰረት መብራቴ በአሜሪካን ሀገር በነበራት ቆይታ ያሰባሰበችውን 6 ሚሊዮን ብር ለልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል በዛሬው ዕለት አስረክባለች፡፡ ገንዘቡ የልብ ህመም ላለባቸው 60 ህጻናት ህክምና የሚውል እንደሆነም ተገልጿል። አርቲስቷ ላለፉት 3 ዓመታት በማዕከሉ በአምባሳደርነት እያገለገለች የምትገኝ ሲሆን ሕክምናን ለማግኘት ወረፋ እየጠበቁ የሚገኙ ህጻናትን ለመታደግ የተለያዩ የገቢ ማሰባሰብ ስራዎችን እየሰራች ትገኛለች። በ1981 ዓ.ም የተመሰረተው የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል ላለፉት 32 ዓመታት ከ9 ሺ 500 በላይ ህጻናት ህክምና እንዲያገኙ ማድረጉን መረጃዎች ያሳያሉ።()
    4 918
    2
    #SafaricomEthiopia ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አዲስ ተመራቂዎችን ለመቅጠር ማስታወቂያ አውጥቷል። በቅርብ የተመረቃችሁ በዚህ ሊንክ ማመልከት ትችላላችሁ። 👇👇👇
    4 863
    31
    መከላከያ ሠራዊት በህወሀት ጦር መሳሪያ ማምረቻዎች ላይ የአየር ድብደባ መፈጸሙ ተገለጸ፡፡ የመንግስት የአስቸኳይ ጊዜ የመረጃ ማጣሪያ የአየር ድብደባውን በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል፡፡ ሰራዊቱ የፈጸማቸውን የአየር ድብደባዎች በተመለከተ የተዛባ ግንዛቤ መኖሩን የጠቆመው መግለጫው ጥቃቶቹ በተቃራኒው የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎችን ብቻ ዒላማ ማድረጋቸውን አስታውቋል። የአየር ላይ ድብደባው የሽብር ድርጅቱ ከባድ የጦር መሣሪያዎችን እና ሌሎች ሕገወጥ የጦር መሣሪያዎችን ለመሸሸግ የሚጠቀምባቸውን እና ወደ ወታደራዊ መገልገያነት የቀየራቸውን የተወሰኑ ቦታዎች ከጥቅም ውጭ ለማድረግ በማሰብ መፈጸሙንም ገልጿል። * ሆኖም ግን የአስቸኳይ ጊዜ የመረጃ ማጣሪያው ድብደባው በየትኛው አካባቢ እንደተፈጸመ አልገለጸም፡፡ ከትናንት በስቲያ ሰኞ ጥቅምት 8 ቀን 2014 ዓ/ም በመቀሌ የአየር ድብደባዎች መፈጸማቸውን የሚያመለክቱ መረጃዎች በተለያዩ የመገናኛ መንገዶች ሲሰራጩ ነበረ፡፡ በጥቃቱ በገበያ ስፍራ ላይ የተፈጸመ እንደሆነ ሲገልጹ የነበሩ የህወሓት አመራሮች ንጹሃን መገደላቸውን በመጠቆም በተለያዩ የማህበረሰብ ትስስር ገጾች ሲጽፉም ነበረ፡፡ ድብደባውን በተመለከተ ከአል ዐይን አማርኛ ጋር የስልክ ቆይታ ያደረጉት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ተከታዩን ብለዋል: - የኢትዮጵያ መንግስት የራሱ ዜጎች የሚኖሩበትን ከተማ እንዲሁም የራሱን ዜጎች ሊያጠቃ የሚችልበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ነገር ግን መንግስት ለሀገር ስጋት ችግር ይፈጥራል ያለውን ጉዳይ በየትኛውም ሰዓት እና በማንኛውም ሁኔታ ንጹሃን ዜጎችን በጠበቀ መልኩ ሊመታ እንደሚችል አልሸሸጉም፡፡ ለዚህ ማንንም ማስፈቀድ እንደማይጠበቅበት ተናግረዋል።()
    ادامه مطلب ...
    4 532
    8
    ለ 12ተኛ ክፍል ተማሪዎች የኢንትራንስ መፈተኛ ቀን ተቃርቧል በዚህ ወቅት ከማጥናት ባሻገር ያለፉትን ዓመት ጥያቄዎች መስራት ጥሩ ውጤት ለማምጣት ጉልህ ሚና አለው። ለዚህም በኢትዮጵያ ከ100,000 በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት EthioMatric አፕሊኬሽን ቀርቦላችኋል። - EthioMatric ከ2008-2012/13 ዓ.ም የ4 እና የ5 ዓመት የኢንትራንስ ፈተናዎች ከነመልሶቻቸው እና ከነማብራሪያቸው በየምዕራፉ ከፋፍሎ አስቀምጧል፡፡ EthioMatric አፕሊኬሽን ለማውረድ 👇👇 ለበለጠ መረጃ
    4 315
    20
    ዘ ቴሌግራፍ በጠ/ሚር አብይ ንግግር ዙርያ የሰራው የተሳሳተ ዘገባ! የእንግሊዙ ዘ ቴሌግራፍ "የኢትዮጵያው ጠ/ሚር የእርዳታ ምግብ ወደሀገራቸው መግባቱን አስቆማለሁ ብለው ዛቱ" የሚል ዘገባ ትናንት ሰርቶ አስነብቧል። ሚድያው አክሎም ጠ/ሚሩ ይህንን ያሉት የአለም አቀፍ ጫናን ለመቀነስ አስበው እንደሆነ ፅፏል። ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ አጭር ማጣራት ያረገ ሲሆን ጠ/ሚር አብይ አህመድ በአማርኛ የተናገሩት ንግግር "... በደንብ ሰርተን ስንዴ የሚባል ነገር እንዳይገባ ካደረግን 70 ፐርሰንት የኢትዮጵያ ችግር ይራገፋል" የሚል እንደሆነ ተመልክቷል። ጠ/ሚሩ በዚሁ ንግግራቸው "ሁሉም የኢትዮጵያ ክልል በቀጣይ አመት የስንዴ ክላስተር 30 እና 40 ፐርሰንት ከተገበረ አንድ ኪሎ ስንዴ ኢትዮጵያ አይገባም" ብለው ነበር። ይህንንም ያሉት በቅርብ ቀናት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በመሄድ የግብርና እንቅስቃሴዎችን በጎበኙበት ወቅት ነበር። ይህም በግልፅ እንደሚያሳየው "...ስንዴ የሚባል ነገር እንዳይገባ..." የሚለው አገላለፅ ራስን በምግብ ከመቻል ጋር ተያይዞ የቀረበ እንጂ የእርዳታ ምግብ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ለማድረግ ከመዛት ወይም ከማስፈራራት ጋር የተያያዘ አይደለም። Credit : via: tikvahethmagazine
    ادامه مطلب ...
    4 325
    4
    በትግራይ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተወሰነ፡፡ በሀገራችን የሰሜኑ ክፍል በህወሃት አሸባሪ ቡድን በተፈጠረው ችግር ምክንያት በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎችና በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና ወልዲያ የኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲ በጊዜያዊነት ለመመደብ የመመዝገቢያ ገፅ ተከፍቶ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ እና ምደባ እንደሚካሄድም ተገልጿል፡፡ በዚህም በዩኒቨርስቲዎቹ ትምህርትቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃቸውን በማዘጋጀት ከ ዛሬ ጀምሮ መመዝገብ እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡ ለመመዝገብ በመጠቀም የተቀመጠውን ፎርም እንዲሞሉ እና ምዝገባ እንዲያካሂዱ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡ Via MoE
    ادامه مطلب ...
    4 576
    19
    Last updated: ۱۱.۰۷.۲۳
    Privacy Policy Telemetrio