✳️ ቪፒኤን ለምን እንጠቀማለን? ጥቅሙስ ምንድን ነው?
✴️ቪፒኤን (VPN) የኢንተርኔት ግንኙነታችንን ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን እና የምንለዋወጣቸዉ መረጃዎች ከመረጃ
#በርባሪዎች ጥቃት የተጠበቁ እንዲሆኑ የሚረዳ
#ሶፍትዌር ነው፡፡
✴️ተጠቃሚዎች የቪፒኤን ግንኙነት ሲፈጥሩ ደህንነቱ የተረጋገጠ የመረጃ መተላለፊያ መንገድ ይፈጥራሉ፡፡
#ቪፒኤን በተለየ ማስተላለፊያ መንገድ የሚተላለፉ ዳታዎችን ሚስጥራዊ የሚያደርግ በመሆኑ
#ማንኛዉም የመረጃ በርባሪ የመረጃዉን ይዘት ማዎቅ እንዳይችል ከማድረጉ ባሻገር የመረጃ ግንኙነቱ የሚሆነዉ
#በሁለቱ ባለመብት(ባለፍቃድ) አካላት ብቻ ነዉ፡፡
✴️ሶፍትዌሩ የቀጥታ የበይነ-መረብ ግንኙነት 'የኦንላይን' እንቅስቃሴ በመደበቅ እንዲሁም እንዳይታይ በማድረግ(የትኛዉን ድረ-ገጽ እንደጎበኘን እና ምን አይነት ዳታዎችን እያስተላለፍን መሆኑን) ባለማሳዎቅ ያግዘናል፡፡
✴️ይህን አገልግሎት በተገቢው መንገድ ማግኘት የምንችለው ደግሞ የቪፒኤን ሶፍትዌር ደንበኛ በመሆን አገልግሎቱን መጠቀም ስንጀምር ነዉ፡፡
✴️ደንበኛ በመሆናችን የምናስተላልፋቸዉ ዳታዎች ከመዳረሻዉ ኔትወርክ ከመድረሳቸዉ በፊት
#ይመሰጠራሉ፡፡
❇️ቪፒኤንን ለምን መጠቀም አስፈለገ?
✴️ማንኛዉንም የዌብ ተግባራት
#ኢንክሪፕትድ(የተመሰጠሩ) እንዲሆኑ ያደርጋል።
✴️የቀጥታ የበይነመረብ ግንኙነት (online) ተግባራችንን
#በመደበቅ ከሚከታተሉን የመረጃ መንታፊዎች ያድነናል፡፡
✴️መዳረሻችንን በግልፅ እንዳይታይ እንዲሁም በቦታ የተገደቡ ዌቦችና ይዘቶችን አገልግሎት ማግኘት እንድንችል ይረዳናል።
✴️በዌብ(በይነ-መረብ) ተግባር ላይ የማንነት መታዎቅ አጋጣሚን በእጅጉ ያጠባል።
✴️የህዝብ ዋይፋይ ሆትስፖቶችን በምንጠቀምበት ጊዜ ግንኙነቱ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ያደርግልናል፡፡
✴️በአጠቃላይ ደህንነቱ የተጠበቀ መረጃና የመረጃ ልዉዉጥ መንገድ ይፈጠርልናል ማለት ይቻላል፡፡©Elatech
@JOSIE_TECH ....የእናንተው✨
ادامه مطلب ...