የፍቅር ሰላምታ ከገብረክርስቶስ ደስታ ግጥም ተወስዶ የተዘፈነ
ግጥሙ ከስር ሙሉው ተቀምጧል
ጠጉርሽን ዳብሶ በጆሮሽ ያለፈው ነፋሱ ምን አለሽ በመስኮት ላይ ሆነሽ የፍቅሬን ሰላምታ ሲያስተጋቡ ሰምተው ተራሮች የላኩት በሩቅ የሚታዩት የሚወዛወዙት ቆመው በመስኮትሽ ዛፎቹ ምን ይላሉ ይንሾካሾካሉ አይተዋል ደብዳቤ ማታ ስጽፍልሽ ይግለጹ ምስጢሩን ልቤ መሸበሩን ልብሽን ስትለብሽ ወፎች የሚዘፍኑት የሚሉት ምንድነው ጡቶችሽን አየተው በፍቅርሽ ሰላምታ ልቤን እንዲያደክሙ ላኪያቸው ያምጡልኝ መድሃኒቱን ይስጡኝ ኮከቦች ከሰማይ ይጠቃቀሳሉ ውበትሽን አይተው በቅርጽሽ ተደንቀው በሰማዩ ባህር ጠልቀው ይዋኛሉ ፍቅርሽን ሊይዙ ወደኔ ሊጓዙ ምን አለች ጨረቃ በመስኮትሽ ገብታ ስትነካ ፊትሽን ተደግፋ አልጋሽን ልኬልሽ ነበረ የፍቅር ሰላምታ ጠይቂያት ውሰጂ መልሱንም ስደጂ የቤተ ክርስቲያን ደወሉ ዘመረ ምን ሆኖ ይጮሀል ሰው ይሰበሰባል ጉዳችንን አይቶ ገልጦ ተናገረ እባክሽ ለፍቅር ሞተን እንቀበር ምነው ምን ፈለገ ሲጨፍር ከበሮ ተነሳ የሚለኝ የሚቀሰቅሰኝ ፍቅርሽና ፍቅሬን በመሀረም አስሮ እንሂድ ተቃቅፈን ደብቆ ይውሰደን የበረረው ልቤ ካጠገቤ ጠፍቶ ምን ምስጢር አወራ ደንግጦ እየፈራ ስታንጎራጉሪ መኝታሽ ቤት ገብቶ የፍቅሬን ሰላምታ ይስጥሽ በቀስታ
👇👇👇
@old_musica
ሼር🙏
Ko'proq ko'rsatish ...