Best analytics service

Add your telegram channel for

  • get advanced analytics
  • get more advertisers
  • find out the gender of subscriber
Category
Channel location and language

all posts TIKVAH-ETHIOPIA

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።  @tikvahuniversity   @tikvahethAfaanOromoo   @tikvahethmagazine   @tikvahethsport   @tikvahethiopiatigrigna   #ኢትዮጵያ  
Show more
1 346 583-178
~253 514
~19
19.74%
Telegram general rating
Globally
250place
of 78 777
1place
of 396
In category
6place
of 2 347
Posts archive
59 419
46
#ትንሣኤ ለመላው በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ ! " በዚህ የለም ፤ እርሱ እንደተናገረው ተነሥቶአል "   በማቴዎስ ወንጌል ፥ " እነሆ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ ወርዶአልና ፤ ቀርቦም በመቃብሩ አፍ ላይ ድንጋይዋን አንከባሎ በላይዋ ተቀመጠ፡፡ መልኩም እንደ መብረቅ ፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበር፡፡ እርሱንም ከመፍራት የተነሣ መቃብሩን የሚጠብቁ ታወኩ ፤ እንደ በድንም ሆኑ፡፡ መልአኩ መልሶ ሴቶቹን እንዲህ አላቸው፥ ' እናንተስ ፤ የተሰቀለውን አውቃለሁና፡፡ በዚህ የለም ፤ እርሱ እንደ ተናገረው ተነሥቶአል ' " ተብሎ እንደተጻፈው ብርሃንን ተጎናጽፎ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን በክብር ፡፡ መልካም የትንሣዔ በዓል ! በዓሉ የሰላምና የፍቅር ይሆን ዘንድ እንመኛለን !
Show more ...
149 613
344
#ትንሣኤሎተሪ የ2016 የትንሳኤ ሎተሪ ዕጣ የወጣ ሲሆን 10 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የአንደኛ ዕጣ ቁጥር 1407747 ሆኖ ወጥቷል። 5 ሚሊዮን ብር የሚያስገኘው የሁለተኛው የዕጣ ቁጥር ደግሞ 0179265 ሆኖ ወጥቷል። የ2.5 ሚሊዮን ብሩ የሶስተኛው ዕጣ ቁጥር 2160591 እንዲሁም የ1.5 ሚሊዮን ብር የ4ኛ ዕጣ ቁጥር 0165786 ሆኖ ወጥቷል። (ተጨማሪ ዝርዝር የዕጣ ማውጫው ከላይ ተያይዟል)
134 926
444
1
0
ዲቪ 2025 ዛሬ ምሽት ይፋ ሆኗል። የአሜሪካ ዲቪ (Diversity Visa) ሎተሪ 2025 ዛሬ ምሽት ይፋ መደረጉን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት አሳውቋል። መ/ቤቱ፥ አመልካቾች መመረጥ አለመመረጣቸውን / ደርሷቸው እንደሆነ እና እንዳልሆነ ማየት የሚችሉት በ ላይ የማረጋገጫ ቁጥራቸውን በማስገባት መሆኑን አሳስቧል። ከዚህ ውጭ የዲቪ ውጤት የሚታይበት ምንም አይነት መንገድ የለም። N.B. ዲቪ የሚደርሳቸው ሰዎች የሚስጥር ቁጥሩን እስከ ቀጣይ አመት መስከረም መጨረሻ ቀናት መያዝ አለባቸው። ምናልባትም  " ዲቪ ደርሷችኃል ከአሜሪካ ኤምባሲ ነው የምንደውለው፣ ኢሜል / ቴክስት መልዕክት የሚንልከው " የሚሉ አጭበርባሪ ስለሚኖሩ ጥንቃቄ አድርጉ ተብሏል። እንደ አሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ፥ የዲቪ ተመራጭ መሆን ለቪዛ ወይም ለቃለመጠይቅ ዋስትና አይሆንም። የዲቪ ሎተሪ ተመራጭ መሆን የቪዛ ጥያቄ ለማቅረብ የመጀመሪያው መስፈርት ሲሆን በቀጥታ ለቪዛ ወይም ለቃለመጠይቅ ዋስትና አይሰጥም።
Show more ...
211 815
3 529
198 315
311
190 763
37
223 785
564
1
0
187 719
89
#LionInternationalBank አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ መጪውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን የሚያስገኙ የጥያቄና መልስ ውድድር ይዞላችሁ መጥቷል፡፡ እርስዎም የሽልማቱ ተሳታፊ ለመሆን ከታች ያሉትን የባንኩን ይፋዊ የቴሌግራም እና የፌስቡክ ገፆች በመቀላቀል እና ጥያቄውን ቀድመው በመመለስ ሽልማቶችን የራስዎ ያድርጉl ጥያቄው የሚካሄዳው እሁድ ሚያዚያ 27 ከቀኑ 5:00 ሰዓት ሲሆን ጥያቄውን ቀድመው ለመለሱ 3 ሰዎች ሊሸልም ዝግጅቱን ጨርሷል። 1ኛ ለሚወጣ ተሸላሚ የበግ ሽልማት 2ኛ ለሚወጣ  የ5000 ብር ሽልማት  3ኛ ለሚወጣ የ3000 ብር ሽልማት      ያበረክትላችኋል። እርስዎም ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የውድድሩ ተሳታፊ ይሁኑ!! አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ          የስኬትዎ አጋር!     
Show more ...
213 386
146
268 967
9 425
274 984
1 486
1
0
241 658
332
234 553
34
ከዘመናዊ የATM ማሽኖቻችን ብር ለማውጣት ካርድዎን ወደ ማሽኑ በማስጠጋት እና የሚስጥር ቁጥርዎን በማስገባት መገልገል ይችላሉ። አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
221 511
18
239 994
82
1
0
224 025
492
220 054
671
195 809
95
ኢትዮ ቴሌኮም ተናፋቂው የትንሳኤ በዓል ፋሲካ እንደ ሁልጊዜው ደምቆ እንዲፈካ በፍጥነት ግንኙነት የበዓል ድባቡን ለማቅለም ልዩ የትንሳኤ ጥቅል ከ ኢትዮ ቴሌኮም እስከ 25% ቅናሽ የተደረገባቸውን የትንሳኤ ጥቅል በተለያየ የጊዜ ገደብ አማራጮች ማቅረባችንን በደስታ እንገልጻለን! ጥቅሎቹን በቴሌብር ሱፐርአፕ ከተጨማሪ 10% ስጦታ ጋር እንዲሁም በማይ ኢትዮቴል፣ አርዲ ቻትቦት ወይም በ*999# ይግዙ፤ ለሚወዷቸውም በስጦታ እያበረከቱ መልካም ምኞትዎን ይግለጹ! መልካም የትንሳኤ በዓል ! ተጨማሪ መረጃ ፦
228 567
11
1
0
ተናፋቂው የትንሳኤ በዓል ፋሲካ እንደ ሁልጊዜው ደምቆ እንዲፈካ በፍጥነት ግንኙነት የበዓል ድባቡን ለማቅለም ልዩ የትንሳኤ ጥቅል ከ ኢትዮ ቴሌኮም እስከ 25% ቅናሽ የተደረገባቸውን የትንሳኤ ጥቅል በተለያየ የጊዜ ገደብ አማራጮች ማቅረባችንን በደስታ እንገልጻለን! ጥቅሎቹን በቴሌብር ሱፐርአፕ ከተጨማሪ 10% ስጦታ ጋር እንዲሁም በማይ ኢትዮቴል፣ አርዲ ቻትቦት ወይም በ*999# ይግዙ፤ ለሚወዷቸውም በስጦታ እያበረከቱ መልካም ምኞትዎን ይግለጹ! መልካም የትንሳኤ በዓል!
2
0
በአዲስ አበባ ከተማ የወጣው የመሬት ሊዝ  ጨረታ ተራዘመ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክፍለ ከተማ  ፤ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ በሌሎችም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል። በዚህም ከሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 24/2016 ዓ/ም ድረስ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ ሲከናወን ቆይቷል። ነገር ግን የጨረታ ሰነድ ሽያጩ ከ28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 09/09/2016 ዓ/ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት መራዘሙ ተነግሯል። ተጫራቾች ፦ - የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ፣ - ሲፒኦ፣ - የግንባታ አቅም ማሳያ ማስረጃ፣ - ሰነዱን ለመግዛት በቴሌ ብር የከፈሉበት ስሊፕ - ሌሎች መያያዝ ያለባቸዉ እና በተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን በመጨመር የጨረታ ሰነዶችን በኤንቨሎፕ በማሸግ ግንቦት 09/2016 ዓ/ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አከባቢ ኤም ኤ (MA) ህንፃ ላይ በሚገኘው የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ተብሏል። ጨረታው ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 12/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ ለተከታታይ 9 የስራ ቀናት በቦሌ ክ/ከተማ አስተደዳር አዳራሽ  እንደሚከፈት ተገልጿል። የጨረታው ዝርዝር👇
Show more ...
261 141
358
#Kenya በጎረቤት ኬንያ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 188 ደርሷል። ካለፈው መጋቢት ጀምሮ በደረሰው አውዳሚ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 188 መድረሱን የሀገር አስተዳደር ሚኒስቴር አሳውቋል። እስካሁን ያልተገኙ በርካታ ሰዎች መኖራቸውም ተገልጿል። በኬንያና ሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች በተከታታይ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ የብዙ ሰዎች ህይወት እየጠፋ ሲሆን የከፍታ ቦታዎች መናድም ነዋሪዎችን ካለመጠጊያ አስቀርቷል፡፡ መንገዶችን ድልድዮችን እና ሌላም የመሰረተ ልማት አውታሮችን ውድሟል።
254 806
88
234 763
96
" በየጊዜው ወጣቶች የምገብርበት የጦርነት ምዕራፍ መዘጋት አለበት " - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በኩል ዛሬ መልዕክት አሰራጭተው ነበር። በዚህም ፤ " የህዝባችን ሁለንተናዊ መብትና ጥቅም ከማረጋገጥና አስተማማኝ ከማድረግ የሚቀድም ሌላ አጀንዳ የለንም " ብለዋል። " የህዝባችን ጥቅምና መብት የሚያረጋግጥ መንገድ ሁሉ እንጓዘዋለን " ያሉት አቶ ጌታቸው " ጉዞው እንዲሳካ የህዝቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነው " ሲሉ አክለዋል። ፕሬዜዳንቱ ፤ " ከሚገባው በላይ ያበረከተ ህዝብ በቅንነትና ታማኝነት ማገለገል ይገባል " ሲሉም ገልጸዋል። " ህዝቡ ከጦርነትና ጦርነት ወለድ ችግሮች በማላቀቅ ወደ አስተማማኝ ሰላም እንዲሸጋገር መስራት ይገባል " ሲሉም አስገንዝበዋል። አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ " በየጊዜው ትኩስ ሃይል የሆኑትን ወጣቶች የምንገብርበት የጦርነት ምዕራፍ ተዘግቶ ፤ የልማትና የእድገት ፍላጎታችን እንዲሳካ መስራት አለብን " ብለዋል።
Show more ...
259 460
36
226 729
34
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር በዓሉን ምክንያት በማድረግ እስከ 25% ቅናሽ የተደረገባቸውን ማራኪና ውብ የመመገቢያ ጠረጴዛዎቻችንን በመግዛት ልዩ የአብሮነት ጊዜ ያሳልፉ! የዘመናዊነት ተምሳሌት! አድራሻችን፦ 1. ዊንጌት አደባባዩን ተሻግሮ: +251 995 27 2727 / +251 911 51 6843 2. ፒያሳ እሪ በከንቱ : +251 957 86 8686 3. ሲ ኤም ሲ አደባባዩን አለፍ ብሎ: +251 993 82 8282 👉 Telegram:  👉 Facebook:  👉 TikTok: 👉 Instagram:
214 149
31
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር በዓሉን ምክንያት በማድረግ እስከ 25% ቅናሽ የተደረገባቸውን ማራኪና ውብ የመመገቢያ ጠረጴዛዎቻችንን በመግዛት ልዩ የአብሮነት ጊዜ ያሳልፉ! የዘመናዊነት ተምሳሌት! አድራሻችን፦ 1. ዊንጌት አደባባዩን ተሻግሮ: +251 995 27 2727 / +251 911 51 6843 2. ፒያሳ እሪ በከንቱ : +251 957 86 8686 3. ሲ ኤም ሲ አደባባዩን አለፍ ብሎ: +251 993 82 8282 👉 Telegram:  👉 Facebook:  👉 TikTok: 👉 Instagram:
1
0
228 363
82
የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ  ሊቀ ማእምራን ብርሃኑ ተክለ ያሬድ በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 12:00 በፌዴራል ፖሊስ " " በሚል ከቤታቸው ተወስደው መታሠራቸውን ቤተሰቦቻቸው መናገራቸውን ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ዘግቧል። ቀደም ብሎ ፥ የሰንበት ት/ ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ የሆኑት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶክተር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ ከቤታቸው በጸጥታ ኃይል መወሰዳቸውና ቤታቸው ላክ ፍተሻ መደረጉን የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን መዝገቡ ይታወሳል።
223 804
111
208 951
88
215 580
199
226 304
647
218 588
57
#DStvEthiopia 🏆የዋንጫው ደረሰ🏆 በታላላቅ የዓለማችን እግር ኳስ ሊጎች ዋንጫ ለመሳም የሚደረጉትን ግስጋሴዎችን በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ቻናሎች በቀጥታ ይከታተሉ! አንድም ደቂቃ እዳያመልጦ አሁኑኑ ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ወርሃዊ ካፍያዎን ይፈፅሙ! 💥 የአውሮፓ ምርጥ ተጫዋቾችን ፍልሚያ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ቻናሎች ይከታተሉ! የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ1,999 ብር ከ1 ወር ነፃ የሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ። የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ! 👇
194 111
10
https://t.me/LionBankSC አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ መጪዎቹን የትንሳኤ እና ፋሲካ በዓላት ምክንያት በማድረግ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን የሚያስገኙ የጥያቄና መልስ ውድድር ይዞላችሁ መጥቷል፡፡ እርስዎም የሽልማቱ ተሳታፊ ለመሆን ከታች ያሉትን የባንኩን ይፋዊ የቴሌግራም እና የፌስቡክ ገፆች በመቀላቀል እና ጥያቄውን ቀድመው በመመለስ ሽልማቶችን የራስዎ ያድርጉl ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የውድድሩ ተሳታፊ ይሁኑ!! አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ       የስኬትዎ አጋር!     
227 427
23
#CAR የ77 ዓመቱ የቀድሞው የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ፍራንሷ ቦዚዜ ላይ የእስር ማዘዣ ትዕዛዝ ወጣ። ማዘዣው የወጣው ሠራዊታቸው ከእአአ 2009 እስከ 2013 ባለው ጊዜ ውስጥ በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል ፈጽሟል በሚል ነው። ማዘዣውን ያወጣው በባንጊ ላይ የተሰየመውና ከሃገር ውጪ ካሉ ፍርድ ቤቶች ጋራ የሚሠራው ልዩ የወንጀል ችሎት ነው። ይህ ችሎት በእ.አ.አ 2015 በተመድ እገዛ የተቋቋመ እንደሆነ ተገልጿል። የቀድሞ የሀገሪቱ መሪ ቦዚዜ ፦ - ግድያ፣ - አስገድዶ መሰወር፣ - ሰቆቃ፣ - መድፈር እና ሌሎች ኢሰብዓዊ ድርጊቶችን ፈፅመዋል በሚል ተከሰዋል። ቦዚዜ በመፈንቅለ መንግስት ወደ ስልጣን የመጡት በእ.አ.አ 2003 ሲሆን ከአስር (10) ዓመታት በኋላ ከወንበራቸው ተወግደዋል። ቦዚዜ ካለፈው ዓመት መጋቢት ወር ጀምሮ ጊኒ ቢሳዉ የሚገኙ ሲሆን፣ ከዛ ሆነው ዋናኛ የሚባል አማጺ ቡድን በመምራት ላይ ይገኛሉ። ጊኒ ቢሳዉ ተጠርጣሪውን ቦዚዜ እንድታስረክብ ተጠይቋል።
Show more ...
250 650
38
#CAR የ77 ዓመቱ የቀድሞው የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ፍራንሷ ቦዚዜ ላይ የእስር ማዘዣ ትዕዛዝ ወጣ። ማዘዣው የወጣው ሠራዊታቸው ከእአአ 2009 እስከ 2013 ባለው ጊዜ ውስጥ በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል ፈጽሟል በሚል ነው። ማዘዣውን ያወጣው በባንጊ ላይ የተሰየመውና ከሃገር ውጪ ካሉ ፍርድ ቤቶች ጋራ የሚሠራው ልዩ የወንጀል ችሎት ነው። ይህ ችሎት በእ.አ.አ 2015 በተመድ እገዛ የተቋቋመ እንደሆነ ተገልጿል። የቀድሞ የሀገሪቱ መሪ ቦዚዜ ፦ - ግድያ፣ - አስገድዶ መሰወር፣ - ሰቆቃ፣ - መድፈር እና ሌሎች ኢሰብዓዊ ድርጊቶችን ፈፅመዋል ሲል ከሷል። ቦዚዜ በመፈንቅለ መንግስት ወደ ስልጣን የመጡት በእ.አ.አ 2003 ሲሆን ከአስር (10) ዓመታት በኋላ ከወንበራቸው ተወግደዋል። ቦዚዜ ካለፈው ዓመት መጋቢት ወር ጀምሮ ጊኒ ቢሳዉ የሚገኙ ሲሆን፣ ከዛ ሆነው ዋናኛ የሚባል አማጺ ቡድን በመምራት ላይ ይገኛሉ። ጊኒ ቢሳዉ ተጠርጣሪውን ቦዚዜ እንድታስረክብ ተጠይቋል።
Show more ...
1
0
“ ማን እንደገደላቸው መረጃ የለኝም ፤  በተተኮሰባቸው ጠይት ተገድለዋል ዞሮ ዞሮ ” - ስሜ አይገለጽ ያሉ ባለስልጣን በአማራ ክልል፣ ሰሜን ወሎ የላስታ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው መልሴ እና የወረዳው ጤና ጽ/ ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን አፈወርቅ ትላንት በጥይት  መገደላቸውን ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋገጧል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ አንድ የሰሜን ወሎ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ባለስልጣን በሰጡት ቃል፤ “ ትላንት ከዞን ግምገማ ቆይተው ሲመለሱ ነው ግድያው የተፈጸመው። የሞቱት የወረዳው አስተዳዳሪ የወረዳው ጤና ኃላፊ ናቸው ” ብለዋል። “ ኩል መስክ የሚባል ቦታ ነው ግድያው የተፈጸመው ” ሲሉ ተናግረዋል። ሌላ የተጎዳ ሰው አለ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፣ “ ሌላ እዛው ኩል መስክ የቀበሌ ሊቀመንበር የተጎዳ አለ ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። “ አርብና ቅዳሜ ግምገማ ነበረ፤ እዚያ ተመልሰው ኩል መስክ ቆይተዋል ለሁለት ቀናት ” ሲሉም አክለዋል። ግድያውን የፈጸመው ማነው ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ “ እስካሁን መረጃው የለኝም፤ በተተኮሰባቸው ጠይት ተገድለዋል ዞሮ ዞሮ ” ብለው፣ የገዳዮቹን ማንነት ከመግለጽ ተቆጥበዋል። “ ዞሮ ዞሮ በግድያ የሚመለስ አንድም ጥያቄ የለም። እነዚህ (ሟቾቹ) የሕዝብ አስተዳዳሪዎች ናቸው። ሕዝብም ጥበቃ ሊያደርግላቸው ይገባል እንጂ መሞት አለባቸው ብዬ አላስብም ” ብለዋል።
Show more ...
242 651
41
" ወደቡ ዝግጁ ነው፤ መንገዱም ከሞላ ጎደል ዝግጁ ነው " - ሰዓድ አሊ ሽሬ ሶማሌላንድ የበርበራ ወደብ 30% ጭነት እንዲያስተናግድ ትፈልጋለች። ለዚህ ደግሞ አስፈላጊ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ገልጸለች። አሁን ላይ ስምምነት እንዲፈረም እየተሰራ ነው ተብሏል። የሶማሌላንድ የፋይናንስ ሚኒስትር ሰዓድ አሊ ሽሬ ምን አሉ ? " አካላዊ መሰረተ ልማትን በተመለከተ ወደቡን ገንበተናል። ☑ አንድ ኪሎሜትር የሚሰፋ የመርከብ ማቆሚያ፤ ☑ ኮንቴነሮችን መጫንና ማውረድ የሚችሉ ክሬኖች ያሉት ዓለም አቀፍ ወደብ አለ፤ ☑ ከበርበራ ወደብ ድንበር ላይ እስከምትገኘው ያለውን መንገድ ገንብተናል፤ ስለዚህ ወደቡ ዝግጁ ነው። መንገዱም ከሞላ ጎደል ዝግጁ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በበርበራ ነጻ የኢኮኖሚ ዞኖች አሉን። የነዳጅ ማጠራቀሚያ ጋኖች ከነዳጅ ጫኝ መርከቦች ማራገፊያ አዘጋጅተናል። አካላዊ ክፍል ከሞላ ጎደል አልቋል። ለምሳሌ በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል የወደብ አጠቃቀም ስምምነት (Transit Agreement) ሊኖረን ይገባል። የጉምሩክ ስርዓቶቻችን ማገናኘት ወይም ማስተሳሰር ይኖርብናል ይህ አሁንም በስራ ላይ ነው። የመጓጓዣ ስምምነትም ማባጀት አለብን ይሄም ሂደት ላይ ነው። ከስርዓት አኳያ በሂደት ላይ የሚገኙ የተወሰኑ ጉዳዮች አሉ " ብለዋል። እንደ ሶማሌላንድ የወደቦች አስተዳደር ዳይሬክተር ሰኢድ ሀሰን አብዱላሂ ማብራሪያ ደግሞ ፥ ➡ ህጋዊው ጉዳይ በመንግስታት መካከል የሚፈርም እንደሆነ ➡ ስምምነቱ እየተጠናቀቀ ስለመሆኑ ➡ በአንድ እና ሁለት ቀሪ ጉዳዮች ላይ ውይይት እየተደረገ መሆኑን ➡ በመጪው 60 ቀናት ስምምነቱ ሊጠናቀቅ እንደሚችልን ከ60 ቀናት በኃላ እንደሚፈረምና ኮሪደሩ ጥቅም መስጠት ይጀምራል። በተጨማሪ ፦ ° የUAE ዲፒ ወርልድ እና ሶማሌላንድ ከበርበራ ወደብ 15 ኪ/ሜ ርቀት ነጻ የኢኮኖሚ ቀጣራ ማበጀታቸውን ° ነጻው የኢኮኖሚ ቀጠና ከወደቡ ወደ ኢትዮጵያ በሚያመራው መንገድ ላይ እንደሚገኝ ° ነጻው የኢኮኖሚ ዞን 300 ሺህ ካሬ ጫማ የሚሰፋ ከማብሰያ ዘይት ማሸጊያ ፋብሪካ ጭምር አለው። ከ6 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ከሶማሌላድ እና ዲፒ ወርልድ ጋር በተፈራረመችው ስምምነት በበርበራ ወደብ ልማት 19% ድርሻ ነበራት ግን አልዘለቀችበትም። ግን አሁን ኢትዮጵያ ወደቡ ላይ ድርሻ እንዲኖራት ትፈልጋለች። የበርበራ ወደብ ያለበት ቀጠና ለዓለም አቀፍ የመርከብ እንቅስቃሴ ወሳኝ በመሆኑ ሶማሌላንድ እና ዲፒ ወርልድ አሁንም ማስፋታ ይፈልጋሉ። ግዙፍ የኮንቴነር ተርሚናል ለመገንባት ሙከራ እየተደረገ መሆኑ፣ ተጨማሪ 600 ሜትር የሚሰፋ የመርከብ ማቆሚያ ፣ 7 ግዙፍ የእቃ መጫኛና ማውረጃ ለመጨመር እቅድ እንዳለ ታውቋል። ይህን ተከትሎ የበርበራ ወደብ መርከብ መቆሚያ 1650 ሜርት እንደሚሆን 2 ሚሊዮን ኮንቴነርም ማስተናገድ እንደሚችል ለኢትዮጵያም ትልቅ አማራጭ መሆኑ በሶማሌላንድ ባለስልጣናት ተገልጿል። Credit - DW (Eshete Bekele)
Show more ...
228 065
138
261 447
79
263 256
132
#SafaricomEthiopia የሳምሰንግ ጋላክሲ S24 ስልኮችን በሳፋሪኮም ሱቆች መሸጥ ጀምረናል! በአቅራቢያዎ ወደሚገኙ የሳፋሪኮም ሱቆች በማቅናት  ምርጥና እጅግ ዘመናዊ የሆኑትን ስልኮችን ዛሬውኑ ይግዙ !  የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ትክክለኛ መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት ቀጥሎ በሚገኙት ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲከታተሉ  እንጋብዛለን። 👉Facebook: 👉Telegram: 👉Twitter: 👉Instagram: 👉 YouTube:
Show more ...
259 461
69
#ሜይዴይ “ ኑሮ ውድነቱን ሠራተኛው ሊቋቋመው አልቻለም ” - አቶ ካሳሁን ፎሎ ዛሬ የሜይዴይ በዓል እየተከበረ ነው። በዓሉ አስመልክቶ ትላንት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን በመግለጫው ላይ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ተገኝቶ ነበር። ኮንፌዴሬሽኑ ፤ በባለፈው ዓመት በተከለከለው ሰልፍ ሳቢያ ከመንግሥት ጋር የገጠማችሁ አለመግባባት ተፈታ ? የሠራተኞች ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ አሁንስ ምን እየተሰራ ነው ? የሚል ጥያቄ ቀርቦለታል። የኢሰማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ፣ “ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነው ክልከላው ደርሶን የነበረው። በመነጋገር መፍታት አልቻልንም በወቅቱ ” ብለዋል። “ ከዚያ በኋላ ግን ለምን እንደተከለከልን ከመንግሥት አካላት ጋር በየደረጃው ተወያይተናል። ክልከላው ሆን ተብሎ ሠራተኛው ያለውን ጥያቄ እንዳያቀርብ የተደረገ እንዳልነበር ተግባብተናል ” ሲሉ ገልጸዋል። “ ከዚያም ጥያቄያችንን አደራጅተን ለጠ / ሚኒስትሩ አቅርበን ግብር እንዲቀነስ፣ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ስኬል እንዲወሰን መጠየቃችን ይታወቃል። ጠ/ሚኒስትሩ በጥናት ላይ ተመስርቶ ምላሽ እንደሚሰጥ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ያኔ ” ሲሉ አስታውሰዋል። “ አቅጣጫ የተሰጠባቸውን ጉዳዮች እየተከታተልን ነው ” ያሉት አቶ ካሳሁን ፣ “ ነገር ግን አቅጣጫ የተሰጠባቸው የኑሮ ውድነቱን የተመለከቱ ጥያቄዎች ምላሽ አሁንም ዘግይቷል። ኑሮ ውድነቱን ሠራተኛውም ሊቋቋመው አልቻለም ” ብለዋል። አሁን ምን አዲስ ነገር አለ ? ለሚለው ፦ ➡️ ከሠራተኛው በነጻ መደራጀት ጋር በተያያዘ ለሁሉት ዓመታት ተቋርጦ የነበረው መንግስትና ሠራተኛ ቁጭ ብለው የሚወያዩበት የአሰሪና ሠራተኛ አማካሪ ቦርድ ዘንድሮ ሥራ ጀምሯል፡ ➡️ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሰብሳቢነት የሁሉም ክልሎች ሠራተኛ እና ማኀበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊዎች በሚገኙበት ስብሰባ ግምገማ ማካሄድ ተጀምሯል ጥያቄዎች በዚሁ አካሄድ ይፈታሉ ሲሉ አስረድተዋል።
Show more ...
240 112
48
#AmharaRegion በአማራ ክልል የሰሜን ወሎ ዞን ፤ የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና የወረዳው ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ በታጣቂዎች ጥቃት መገደላቸውን ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት ዘግቧል። የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው መልሴ እና የወረዳው የጤና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን አፈወርቅ ትላንት በተፈጸመ ጥቃት ነው የተገደሉት። ባለስልጣናቱ ተኩስ የተከፈተባቸው ወልዲያ ከተማ የነበራቸውን ስብሰባ አጠናቀው እየተመለሱ በነበረበት ወቅት እንደሆነ ተነግሯል። ጥቃቱ የተፈጸመው ከላሊበላ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ ከምትገኘው " ኩልመስክ ከተማ " አቅራቢያ ነው። ከሁለቱ ኃላፊዎች በተጨማሪም አንድ ሌላ ግለሰብ መገደላቸውን እና ሌሎችም መቁሰላቸውን ምንጮቹ ገልጸዋል። ጥቃቱ ሲፈጸም አብረው የነበሩ ሌሎች የመንግስት ኃላፊዎች ወደ ላሊበላ ከተማ የሚያደርጉትን ጉዞ አቋርጠው ወደ ኋላ በመመለስ ኩልመስክ ከተማ ማደራቸው ተነግሯል። አንድ የላሊበላ ከተማ ነዋሪ በሰጡት ቃል " ማታ በዋና አስተዳዳሪው መኖሪያ ቤት ሲለቀስ ነው ያመሸው። አሁንም የአካባቢው ነዋሪ ወደ ለቅሶ እየሄደ ነው " ብለዋል። የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪው አቶ ጌታቸው መልሴ የቀብር ስነ ስርዓት ጥቃቱ ከተፈጸመበት አካባቢ በምትገኘው የትውልድ ከተማቸው " ገነተ ማርያም " እንደሚፈጸም ተገልጿል። የጤና ፅ/ቤት ኃላፊው አቶ ሚሊዮን አፈወርቅ የቀብር ስነ ስርዓት በላሊበላ ከተማ እንደሚፈጸም የወረዳው አስተዳደር ውስጥ የሚሰሩ ኃላፊን ዋቢ በማድረግ ቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ዘግቧል።
Show more ...
240 259
73
#AmharaRegion በአማራ ክልል ፣ ሰሜን ወሎ ዞን ፣ የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና የወረዳው ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ በታጣቂዎች ጥቃት መገደላቸውን ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት ዘግቧል። የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው መልሴ እና የወረዳው የጤና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን አፈወርቅ ትላንት በተፈጸመ ጥቃት ነው የተገደሉት። ባለስልጣናቱ ተኩስ የተከፈተባቸው ወልዲያ ከተማ የነበራቸውን ስብሰባ አጠናቀው እየተመለሱ በነበረበት ወቅት እንደሆነ ተነግሯል። ጥቃቱ የተፈጸመው ከላሊበላ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ ከምትገኘው " ኩልመስክ ከተማ " አቅራቢያ ነው። ከሁለቱ ኃላፊዎች በተጨማሪም አንድ ሌላ ግለሰብ መገደላቸውን እና ሌሎችም መቁሰላቸውን ምንጮቹ ገልጸዋል። ጥቃቱ ሲፈጸም አብረው የነበሩ ሌሎች የመንግስት ኃላፊዎች ወደ ላሊበላ ከተማ የሚያደርጉትን ጉዞ አቋርጠው ወደ ኋላ በመመለስ ኩልመስክ ከተማ ማደራቸው ተነግሯል። አንድ የላሊበላ ከተማ ነዋሪ በሰጡት ቃል " ማታ በዋና አስተዳዳሪው መኖሪያ ቤት ሲለቀስ ነው ያመሸው። አሁንም የአካባቢው ነዋሪ ወደ ለቅሶ እየሄደ ነው " ብለዋል። የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪው አቶ ጌታቸው መልሴ የቀብር ስነ ስርዓት ጥቃቱ ከተፈጸመበት አካባቢ በምትገኘው የትውልድ ከተማቸው " ገነተ ማርያም " እንደሚፈጸም ተገልጿል። የጤና ፅ/ቤት ኃላፊው አቶ ሚሊዮን አፈወርቅ የቀብር ስነ ስርዓት በላሊበላ ከተማ እንደሚፈጸም የወረዳው አስተዳደር ውስጥ የሚሰሩ ኃላፊን ዋቢ በማድረግ ቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ዘግቧል።
Show more ...
2
0
1
0
216 952
61
214 960
59
2
0
Last updated: 11.07.23
Privacy Policy Telemetrio