#አቢሲንያ_ባንክ
አቢሲንያ ባንክ በአቢሲንያ አሚን በኩል ሲያዘጋጀው የነበረውና ለነገ ያልናቸውን ግቦች ዛሬ ማሳካት የምንችልበትን ወርቃማ ዕድል ይዞ ከአጓጊ ሽልማቶች ጋር የመጣው አሚን አዋርድ የሁለተኛ ዙር ውድድር ምዝገባ በበርካታ ተሳታፊዎች ጥያቄ መሠረት እስከ ጥቅምት 10/2016 መራዘሙን ሲያበስር በደስታ ነው።
በየደረጃው ለአሸናፊዎች ከብር 200,000 ሺህ እስከ ብር 1,000,000 ድረስ የሚያሸልመው አሚን አዋርድ በአዲስ አበባ፣ በደሴ እና በድሬዳዋ ከተሞች በድምቀት የሚከወን ሲሆን፤ መሳተፍ የሚፈልጉ የአዲስ አበባ አመልካቾች በምስራቅ ፣ በመካከለኛውና በምዕራብ አዲስ የዲስትሪክት ጽ/ቤቶች፤ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ውጭ የሚገኙ ተወዳዳሪዎች በአቅራቢያቸው በሚገኙ የአቢሲንያ ባንክ ቅርንጫፎች በአካል በመቅረብ የሥራ ፈጠራ ሐሳባቸውን በባንኩ ድረ-ገጽ ላይ በተቀመጠው ቅጽ መሠረት ሞልተው እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃ 8397 በመደወል አሊያም በባንኩ ድረ ገጽ መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል፡፡
ደንብና ሁኔታዎች ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል፡፡
አቢሲንያ አሚን
እሴትዎን ያከበረ!!
Show more ...