Best analytics service

Add your telegram channel for

  • get advanced analytics
  • get more advertisers
  • find out the gender of subscriber
Channel location and language

audience statistics Ethio Construction

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም 👷‍♂እናማክራለን 🏢ዲዛይን እናደርጋለን 📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን 🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን 📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም tiktok  https://www.tiktok.com/@ethiocons  ለሃሳብ እና ኣስተያየት  @Ethiocon143bot  ይጠቀሙ 
Show more
26 662+57
~3 574
~88
14.55%
Telegram general rating
Globally
34 213place
of 78 777
252place
of 396
In category
266place
of 546

Subscribers gender

Find out how many male and female subscibers you have on the channel.
?%
?%

Audience language

Find out the distribution of channel subscribers by language
Russian?%English?%Arabic?%
Subscribers count
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

User lifetime on the channel

Find out how long subscribers stay on the channel.
Up to a week?%Old Timers?%Up to a month?%
Subscribers gain
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

Since the beginning of the war, more than 2000 civilians have been killed by Russian missiles, according to official data. Help us protect Ukrainians from missiles - provide max military assisstance to Ukraine #Ukraine. #StandWithUkraine
"በሕንጻ ግንባታ ሥራ selective material ከመጠቅጠቁ (ከመረምረሙ) በፊት ውኃ የሚጠጣው ለምንድነው? የጎንዮሽ ተጽእኖስ አለው ይላሉ?" 🏷የአፈር መጠቅጠቅ ሂደት ቅንጣቶች በመካከላቸው ያለውን ክፍተት ለመቀነስ የሚደረግ የመጫን ጉልበት (compaction) ትግበራ ነው። 💫በጣም የታመቀ፣ የተጠቀጠቀ አፈር የቅንጣቶችን ክፍተት በመቀነስ አፈሩ በጣም ጥቂት ቦታን (ስፋትን) እንዲይዝ ያግዘዋል። ⭐️ነገር ግን ይህንን የመጠቅጠቅ (ጥግግት) ደረጃ  የምናገኘው ጥሩ የእርጥበት መጠን ካለው  ነው። አፈሩ በጣም ጥሩ እርጥበት የሌለው ከሆነ የአፈር ቅንጣት ጥግግት በሚፈለገው ልክ ሊከናወን ስለማይችል ውስጥ ውስጥ  ያሉትን ክፍተቶች በሙሉ ለመሙላት አስቸጋሪ ይሆናል።  የተደፋው አፈር (Back filled or selective material) ሁሉም አካሉ በቂ እርጥበት እንዲኖረው ቢያንስ ከአንድ ሌሊት በፊት ቀደም ብሎ  ውኃ መጠጣት አለበት። 🌟የተወሰነ ጊዜ ቀድሞ ማጠጣት (አንደኛ) በሰዓቱ መርዘም የተነሳ የውኃውን የስርገት ሂደት በመጨመር እና ሁሉንም አካል የማግኘት (የማዳረስ) ዕድሉን በማስፋት ሁሉም የአፈር ቅንጣት በቂ እርጥበት እንዲያገኝ ያደርገዋል። 🌟(ሁለተኛ) የአፈሩ የመጠቅጠቅ ሂደት አስቀድሞ በውኃው ስርገት የተነሳ እየተከናወነ እንዲቆይ ያድርጋል። ያ ማለት የመጠቅጠቂያ ጉልበትን ይቀንሳል። ⚡️ሆኖም ግን የተመረጠው አፈር በቂ የሆነ የኮረት፣ የጓል እና የደቃቅ አፈር መዋጮ የሌለበት ከሆነ ውኃ ሲጠጣ የባሰ የላመ አፈር (silty) የመሆን እድሉን ስለሚጨምር ከሚፈለገው አገልግሎት አንጻር ጉዳት እንዳይደርስበት የውኃውን መጠን እና የሚጠጣበትን የጊዜ ርዝማኔ እንደአፈሩ አይነት እና እንደአካባቢው አየር የመመጠን ሥራ ከአንድ መሐንዲስ የሚጠበቅ የውሳኔ አካል ነው።
Show more ...
3 382
22
የዓለማችን ድንቅ እስላማዊ የ ኮንስትራክሽን ስትራክቸሮች እንሆ 1. መስጂድ አል-ሀራም፡- መካ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ የሚገኝ መስጂድ አል-ሀራም የአለማችን ትልቁ መስጂድ ሲሆን በእስልምና እጅግ የተቀደሰ ቦታ የሆነውን ካባንን ይከብባል።  መስጂዱ በሀጅ ወቅት እስከ 4 ሚሊዮን ሰጋጆችን ማስተናገድ ይችላል። 2. መስጂድ አል-ነበዊ፡- በመዲና፣ ሳውዲ አረቢያ፣ መስጂድ አል-ነበዊ በእስልምና ሁለተኛው ቅዱስ መስጂድ ነው። የነብዩ መሐመድ መቃብር የሚገኝበት ሲሆን በግሩም አረንጓዴ ጉልላት እና በዓይነቱ ልዩ የሆነ የስነ-ህንፃ ጥበብ ይታወቃል። 3.ቡርጅ ካሊፋ፡ 828 ሜትር ላይ የቆመው ቡርጅ ካሊፋ በዱባይ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ በአለማችን ረጅሙ ህንፃ ነው ኢስላማዊ እና ዘመናዊ ኪነ-ህንፃዎች ቅልቅል ያለው እና ተወዳጅ የቱሪስት መስህብ ነው። 4. ሱልጣን አህመድ መስጂድ፡- በተለምዶ ሰማያዊ መስጂድ በመባል የሚታወቀው በቱርክ ኢስታንቡል የሚገኘው ሱልጣን አህመድ መስጂድ የውስጥ ግድግዳውን እና ስድስቱን ሚናራዎችን በሚያጌጡ ሰማያዊ ሰቆች ይታወቃል።  etconp የኦቶማን አርክቴክቸር ድንቅ ስራ ነው። 5. ሀሰን II መስጂድ፡ በሞሮኮ ካዛብላንካ ውስጥ የሚገኝ፣ ሀሰን 2 መስጂድ በአለም ላይ ካሉት ትልቁ መስጊዶች አንዱ ነው እና አስደናቂ የእብነበረድ ውስጠኛ ክፍል፣ ውስብስብ የጣር ስራ እና አስደናቂ የባህር ዳርቻ አቀማመጥ አለው። 6. አልሀምብራ፡ በግራናዳ፣ ስፔን ውስጥ የምትገኝ፣ አልሀምብራ መጎብኘት ያለበት የእስልምና አርክቴክቸር ድንቅ ነው። ይህ ቤተ መንግስት እና ምሽግ ውስብስብ የስቱኮ ማስዋቢያዎች፣ የፈረስ ጫማ ቅስቶች እና የተረጋጋ የአትክልት ስፍራዎችን ያሳያል። 7. የሼክ ዛይድ ታላቁ መስጊድ፡ በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አቡ ዳቢ የሚገኘው የሼክ ዛይድ ታላቁ መስጂድ የዘመናዊ ኢስላማዊ ኪነ-ህንፃ ድንቅ ስራ ነው።  etconp ነጭ የእብነበረድ ጉልላቶች፣ ውስብስብ ቅርጻ ቅርጾች እና አስደናቂ የአበባ ንድፎችን ይዟል። 8. ታላቁ የኮርዶባ መስጊድ፡ በ8ኛው ክፍለ ዘመን በኮርዶባ፣ ስፔን ውስጥ የተገነባው ታላቁ የኮርዶባ መስጊድ የሞሪሽ፣ የጎቲክ እና የህዳሴ ስነ-ህንፃ ቅጦች ድብልቅልቅ የሚያሳይ የባህል ሀብት ነው።  ውስጣዊ ክፍሎቹ ከ 850 በላይ አምዶች እና ውስብስብ ቢሞች ኣሉት። ❤️መልካም ዒድ😇
Show more ...
3 995
10
✅ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን እንኳን ለመውሊድ በዓል አደረሳችሁ፣ መልካም በዓል!
3 568
2
የቻይና መሃንዲሶች ለትራንስፖርት ተስማሚ የሆነ የመንገድ መሠረተ ልማት ለመገንባት የሚያግዳቸው ተራራማ፣ ኮረብታማ እና ጎበርባጣ መልከዓ ምድር የለም ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል።
4 550
7
🌼🌼🌼እንኳን አደረሳችሁ!🌼🌼🌼 🌻አዲሱ አመት የሰላም ፣ የደስታ ፣የፍቅር ፣ የመተሳሰብ፣ የስኬት አመት ይሁንላችሁ!!! 🌼🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት!🌼🌼🌼
6 101
21
ኮንስትራክሽን ክሌም           የኮንስትራክሽን ክሌም ለመስራት የውሉ የክፍያ መንገድ ላምፕ ሰም ወይስ አድሜዠርመንት የሚለውን መለየት ግድ ነው። የውሉ አይነትም ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(DBB) ወይም ዲዛይን ቢዩልድ(DB) ስለመሆኑ  መለየት ይገባል። DBB እና DB የተለያየ ጀኔራል ኮንዲሽን ይጠቀማሉ።ለምሳሌ FIDIC 2017 Red Book ለDBB እና Yellow Book ለDB መጠቀም ይቻላል። የክፍያ መንገዱ ላምፕ ሰም ወይም አድሜዠርመንት መሆኑ ግን የጀኔራል ኮንዲሽን እንድትቀይር አያስገድድም። ለምሳሌ ፒፒኤ 2011 ቨርሽን ለሁለቱም የክፍያ መንገዶች ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። ስፔሻል ኮንዲሽን ላይ የተለወጠ የጀኔራል ኮንዲሽን ክሎስ ያለ እንደሆነ ማረጋገጥም ቀዳሚ ተግባር መሆን አለበት። ከዚህ በኋላ ለክሌሙ አግባብነት ያለውን የውል ድንጋጌ፣የህግ ድንጋጌ እና የጀኔራልና ስፔሻል ኮንዲሽን ድንጋጌ መለየትና መስፈርቱን የሚያሟላ ክሌም ማዘጋጀት ይቻላል። ከዚያም ክሌሙ ለአማካሪ፣ለዲስፒውት ሪቪው ቦርድ፣ለአርቢትሬሽን ወይስ ለፍርድ ቤት መቅረብ እንደሚገባው ለመለየት ጀኔራል ኮንዲሽኑን እና በዋናነት ስፔሻል ኮንዲሽኑን ማየት ይገባል። በጉባዔ አሰፋ
Show more ...
7 348
21
ጥያቄ ✅በአንድ ተቋራጭ ሥር የሚሠሩ ምክትል ሥራ ተቋራጮች (Sub Contractors) የሠሩበትን የሥራ ክፍያ ዋናው ተቋራጭ አልከፍል ቢላቸው ክስ መስርተው በዋናው ተቋራጭ ውል ላይ የተመለከተውን የሥራ ዋጋ የማግኘት መብት አላቸው? መልስ በኢትዮጵያ የሕንጻ ነክ ሕጎች መሰረት በአንድ የሕንጻ ተቋራጭ ሥር የሚሰሩ ምክትል /ንዑስ/ ሥራ ተቋራጮች (Sub contractors) ወይም ሠራተኞች (labours) ዋናው ተቋራጭ ለሠሩበት ሥራ ሳይከፍላቸው ከቀረ እና ለሠሩበት ሥራ ዋጋ እንዲከፈላቸው ክስ ካቀረቡ ክሳቸውን ባቀረቡበት ጊዜ አሠሪው ለሥራ ተቋራጩ ሊከፍል በሚገባው ገንዘብ መጠን በቀጥታ ገንዘባቸውን የመጠየቅ መብት ስላላቸው ያንን ክፍያ የማግኘት መብት አላቸው። ለምሳሌ፦ አንድ ተቋራጭ በውል ሰነዱ ውስጥ የአንድ ካሬሜትር የፎርምወርክ ሥራን በ500 ብር ሂሳብ ተዋውሎ ለምክትል ሥራ ተቋራጮች  (Sub contractors) በ300 ብር ተነጋግሮ ካሠራቸው በኋላ ክፍያ ሳይከፍላቸው ቢቀር (ቢያዘገይባቸው) ክስ ማቅረብ ይችላሉ። ክስ ሲያቀርቡ ሥራውን ለመሥራታቸው ማረጋገጫ ካቀረቡ እና የሥራው ጥራት ታይቶ ተቀባይነት ካገኘ ዋናው ተቋራጭ የተዋዋለበትን 500ብር ሊከፈላቸው የሚችልበት አግባብ አለ ማለት ነው።
Show more ...
6 531
31
ይህ ግዙፍ የአፓርትመንት ኮምፕሌክስ መጠሪያ ስሙ Novy Okkervil ይባላል፤ በሩሲያ ነው የሚገኘው። 🏷እ.ኤ.አ በ2015 የተገነባው የመኖሪያ መንደር ከአለማችን ከሚገኙ ተመሳሳይ ግንባታዎች በቀዳሚነት እንደሚገኝ ይነግርለታል። 💫በዚህ መንደር ውስጥ ወደ 18 ሺህ የሚጠጋ ህዝብ ይኖርበታል። ⭐️እያንዳንዱ ሕንፃ ባለ 25 ወለል ሲሆን፣ በጠቅላላው ወደ ሕንፃው ለመግባትም ሆነ ለመውጣት 35 በሮች አሉት።
7 672
6
🌟Training (With Discount)           🌟Online Class (With Certificate) 1. ETABS Price = 2000birr 2. Ms Project Price = 2500birr 3. Quantity Survey Price = 2000birr 4. Civil 3D Price =2500birr 5. Etabs With Safe Price = 3000birr 6. Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000 7. Structural Design in ProtaStructure Software 8. Autocad Price = 2500birr 9. Sap2000 Price = 2500birr 10. Autodesk Revit Architecture 11. WatrGems 🫵 If u take More than 2 Course u will have Big Discount 🚧Prepared by Engineering Solution Abel Muluken 🫵For Registration - 0948552002 Or 0933575753 or 🚧Telegram Channel - 🚧YouTube Channel -
Show more ...
Engineering Solution
Youtube link - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2BA
6 071
10
5 085
15
አንድ ሰው ግንባታ እያከናወነ የጎረቤት ቤት ቢፈርስበት የጎረቤቱን ቤት እንዲያሰራ ይገደዳል ወይስ ሌላ የህግ እይታ አለ? አንድ ሰው ግንባታውን ሲያከናውን የጎረቤቱን ቤት ቢናድበት ወይም በግንባታ ሥራው የተነሳ የጎረቤቱን ቤት ቢያፈርስ ተጠያቂ ነው። 💫የመፍረስ አደጋ ባይገጥምም እንኳን በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2077 (1) እና (2) መሰረት  አንድ ሕንጻ በሌላው ይዞታ ላይ ያልታሰበ ድንገተኛ ሌላ አደጋ ቢያደርስ የሕንጻው ባለቤት ተጠያቂ (ካሳ ከፋይ) ይሆናል። ▶️ይህም ማለት እንዲፈርስ ያደረገውን ቤት በእራሱ ወጪ እንዲጠግን/እንዲሰራ ይገደዳል። ⏺ቢሆንም ግን በቁጥር 2079 መሰረት በግንባታ ወቅት (በተለይ ከቁፋሮ ጀምሮ ባሉት የመሰረት ሥራዎች ጊዜ) በሌላ የጎረቤት ሕንጻ ላይ የመፍረስ አደጋ ከመድረሱ በፊት አስቀድሞ ሥጋት ላይ ያለው ክፍል አስፈላጊውን ድጋፍ ወይም ጥንቃቄ እንዲደረግለት ማድረግ ይችላል። ▶️“ጎረቤት” የተባለው አካልም ይህ ስጋት ከተሰማው አስቀድሞ ጥንቃቄ እንዲደረግለት የመጠየቅ ሕጋዊ መብት አለው። 🚧ጠቅለል ሲደረግ፦ አንድ የሕንጻ ባለይዞታ በግንባታ ወቅት በጎረቤት ይዞታ ላይ የተገነባን ሕንጻ የመፍረስ ወይም የመሰንጠቅ ጉዳት ቢያደርስ እንዲሁም ሕንጻው በሚገነባበት ወቅትም ይሁን ከተጠናቀቀ በኋላ ከዚያ ሕንጻ ላይ እየወደቁ በሌላው ሕንጻ ወይም ይዞታ ላይ ለሚያደርሱት ጉዳት ተጠያቂ ነው (ፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2080)። ❇️የጎረቤት ሕንጻ ቢፈርስ ተጠያቂ የማይሆንበት አግባብ ▶️በጎረቤት ይዞታ ወይም ሕንጻ ላይ ጉዳት ቢደርስ የማይጠየቀው በሁለት ምክንያት ነው። 📜[አንደኛው] በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2078 (1)  መሰረት ጎረቤት የተባለው ባለይዞታ ይዞታውን ግንባታ ለሚያከናውነው ሰው የለቀቀለት እንደሆነ ወይም ግንባታ የሚያከናውነት አካል የራሱን ሕንጻ ለፈረሰበት ጎረቤቱ የሚለቅለት ከሆነ ነው። 📜[ሁለተኛው] “ጎረቤት” የተባለው አካል ሕንጻው የመፍረስ አደጋ እንዳይገጥመው ጥንቃቄ እንዲደረግለት የመጠየቅ መብት የሚኖረው ግን አስቀድሞ የገነባው ሕንጻ በመሬት ውስጥ፣ በመሬት ላይም ይሁን በአየር ላይ አዲስ የሚገነባውን ባለይዞታ የካርታ መስመር ያላለፈ ከሆነ ብቻ ነው። 🗂ለምሳሌ፦ አስቀድሞ የገነባው ጎረቤት የመሰረት ግንባታው ወይም ተንጠልጣይ የባልኮኒ ወለል ወደሰው ይዞታ አንድ ሳንቲሜትርም ቢሆን ካለፈ እንዲያስተካክል ወይም እንዲያፈርስ ይገደዳል። ⏹አዲስ ግንባታ የሚገነባውም ሰው ጎረቤቱ ወደይዞታው ገብቶ የሰራውን የሕንጻ አካል እንዲያፈርስና እንዲያስተካክል ሳያስጠነቅቅ ማፍረስ የለበትም፣ በፍርድ ቤት በተቆረጠ ቀነ ገደብ እንዲያስተካክል ማሳሰብ ሲኖርበት በዚያ ቀነገደብ ካላስተካከለ ግን ትእዛዝ አስወጥቶ ማስፈረስ/ማፍረስ/ ይችላል።
Show more ...
7 337
34
የግንባታ ውል ሰነድ በግልጽ ማስቀመጥ ያለበት ነጥቦች:- የፕሮጀክቱን ዲዛይን እና ዝርዝሮች: ➢የፕሮጀክት ባለድርሻ አካላትን ድርሻ፣ መብትና ግዴታ፣ ➢የሚጠበቀውን የግንባታ ጥራት የሚገልጹ ትንታኔዎች፣ ➢የፕሮጀክቱን ተጠባቂ የጊዜ ሰሌዳዎች፣ ➢የፕሮጀክቱን ዋጋ እና አከፋፈል ሁኔታዎች፣ ➢የደህንነት እና የጤና አጠባበቅ፣ መመሪያዎች፣ ➢ፕሮጀክቱን የሚመለከቱ የሕግ ማእቀፎች ➢የፕሮጀክቱ ባለድርሻ አካላትን ፊርማ እና ማኅተም ➢ፕሮጀክቱ የሚፈልገውን የሰው ኃይል ብቃትና ብዛት ➢ፕሮጀክቱ የሚፈልገው ማሺነሪ አይነትና ብዛት ➢የእያንዳንዱን የሥራ አይነት ዝርዝርና የግንባታ ስነዘዴ ➢የፕሮጀክቱን ባለድርሻ አካላት ዝርዝር መረጃ አንድ የግንባታ ውል ሰነድ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ዋና ዋና ጭብጥ ጉዳዮች በግልጽ እና በዝርዝር ማስቀመጥ ይኖርበታል። የተወሳሰበ፣ ያልተብራራ እና እርስ በእርሱ የሚጋጭ ሀሳብ ቢኖርበት ግን በሚኖረው የፍርድ ቤት ክርክር ባለድርሻ አካላትን በተናጠል አልያም በጋራ ኪሳራ ላይ ሊጥል ይችላል። ይህ ሁኔታ ደግሞ ፕሮጀክቱን በጤናማ ግንኝነት ለመፈጸም እክል ሊፈጥር ስለሚችል ለጥራት ችግር እና ለጊዜ ብክነት እንዲጋለጥ ያደርገዋል። 
Show more ...
7 164
34
🌟Training (With Discount)           🌟Online Class (With Certificate) 1. ETABS Price = 2000birr 2. Ms Project Price = 2500birr 3. Quantity Survey Price = 2000birr 4. Civil 3D Price =2500birr 5. Etabs With Safe Price = 3000birr 6. Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000 7. Structural Design in ProtaStructure Software 8. Autocad Price = 2500birr 9. Sap2000 Price = 2500birr 10. Autodesk Revit Architecture 11. WatrGems 🫵 If u take More than 2 Course u will have Big Discount 🚧Prepared by Engineering Solution Abel Muluken 🫵For Registration - 0948552002 Or 0933575753 or 🚧Telegram Channel - 🚧YouTube Channel -
Show more ...
Engineering Solution
Youtube link - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2BA
3 379
1
✅የግንባታ ቦታን ማስረከብ 🚧🏗 የግንባታ ባለቤት (Client) ለግንባታ ሥራ መሰናክል ከሆኑ ነገሮች (ለምሳሌ፦ የካሳ ጥያቄ ከሚያነሱ ሰዎች ቁጥጥር፣ ከመብራት፣ ከውሃ፣ ከቴሌ ግንባታዎችና መሣሪያዎች) በማጽዳት ወይም ነጻ በማድረግ ዝግጁ የሆነ የግንባታ ቦታን ለሥራ ተቋራጩ (Contractor) የማስረከብ ሕጋዊ ኃላፊነት አለበት። ባለቤቱ የግንባታ ቦታውን ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ውስጥ ለሥራ ተቋራጩ ካላስረከበ የግንባታ ማስረከቢያ ጊዜ መራዘም/መዘግየት/ ላይ ለሚያስከትለው ኪሳራ ወይም ወጪ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ የሕንጻ ግንባታ ደንቦች (Standard Building Contract with quantities) በአንቀጽ 2.4 እና 2.24 ስር የሰፈረ ድንጋጌ ነው።
5 405
17
5 964
3
🌟Training (With Discount)           🌟Online Class (With Certificate) 1. ETABS Price = 2000birr 2. Ms Project Price = 2500birr 3. Quantity Survey Price = 2000birr 4. Civil 3D Price =2500birr 5. Etabs With Safe Price = 3000birr 6. Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000 7. Structural Design in ProtaStructure Software 8. Autocad Price = 2500birr 9. Sap2000 Price = 2500birr 10. Autodesk Revit Architecture 11. WatrGems 🫵 If u take More than 2 Course u will have Big Discount 🚧Prepared by Engineering Solution Abel Muluken 🫵For Registration - NaN Or NaN or 🚧Telegram Channel - 🚧YouTube Channel -
Show more ...
Engineering Solution
Youtube link - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2BA
3 261
8
https://t.me/major/start?startapp=371415119 👑 Join me in game and earn $MAJOR token soon! ⭐️ 750 rating bonus for you. ⭐️ 1000 rating bonus if you are Premium.
Major
Welcome to @Major bot. Boost your rating by stars and completing tasks. Convert rating to $MAJOR token soon.
1 468
0
በሀገራችን ኢትዮጵያ በግንባታው ዘርፍ የሚታዩ ዋና ዋና ችግሮች:- ⚡️በኮንስትራክሽንፈ ኢንዱስትሪ የማጭበርበር አመለካከትና ተግባር የሚስተዋልበት ነባራዊ ሁኔታ መኖሩ ⚡️በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሰለጠነና የሙያ ብቃቱ የተረጋገጠ የሰው ኃይል እጥረት ያለ መሆኑ ⚡️የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ስራ አመራር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር የተሳለጠ ያለመሆኑ ⚡️በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የሚሠማሩ አማካሪዎችና ተቋራጮች መካከል ተወዳዳሪነት በሚፈለገው ደረጃ ማድረስ ያልተቻለ መሆኑ ⚡️ለኮንስትክሽን ኢንዱስትሪ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ቀጣይነት ያለው የአቅርቦት ሠንሠለት ያልተዘረጋ መሆኑ 🌟ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ መስፋፋትና መጠናከር የተመቻቸ ሁኔታ የሚፈጥር የፋይናንስና የማሽነሪ አቅርቦት ሥርዓት የተጠናከረ ያለመሆን 🌟የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዋና ዋና ባለሚናዎች በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ ለዘርፉ የተፋጠነ ዕድገት በጋራ የሚሰሩበት ሁኔታ ያለመፈጠሩ 🌟የህንፃ ግንባታና መጠቀሚያ ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር አገልግሎት የተጠናከረ ያለመሆን 🌟ፈርጀ ብዙ ሥራዎች ከኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ሥራዎች ጋር ተጣጥመው የሚታቀዱበትና የሚተገበሩበት ሥርዓት ያለመዘርጋቱ 🌟የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት ፕሮግራም ወይም ፓኬጅ አዘጋጅቶ በተሟላና በቀጣይነት ያለመተግበር 🌟ለባለሞያዎችና ስራተቋራጮች የሚደረግ የአቅም ግንባታ ድጋፍ እጅግ አናሳ መሆን
Show more ...
10 791
24
🌟Training (With Discount)           🌟Online Class (With Certificate) 1. ETABS Price = 2000birr 2. Ms Project Price = 2500birr 3. Quantity Survey Price = 2000birr 4. Civil 3D Price =2500birr 5. Etabs With Safe Price = 3000birr 6. Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000 7. Structural Design in ProtaStructure Software 8. Autocad Price = 2500birr 9. Sap2000 Price = 2500birr 10. Autodesk Revit Architecture 11. WatrGems 🫵 If u take More than 2 Course u will have Big Discount 🚧Prepared by Engineering Solution Abel Muluken 🫵For Registration - NaN Or NaN or 🚧Telegram Channel - 🚧YouTube Channel -
Show more ...
Engineering Solution
Youtube link - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2BA
6 026
26
የግንባታ ላይ ደህንነት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ትኩረት አንዱና ዋነኛው ትኩረት ማድረግ የሚገባው በሰው ልጆች ደህንነት ላይ መሆን ይኖርበታል፡፡ ግንባታዎች በሚገነቡበት በዋናነት ለሰውልጆች አገልግሎት ለመስጠት በመሆኑ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ስራዎች የስራ ላይ ደህንነት ሥጋት የሌለባቸው እንዲሁም ለአገልግሎት በሚውሉበት ጊዜ ለአካባቢ የተመቹ እና ደህንነታቸው  የተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል፡፡ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ትኩረት ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ውስጥ የደህንነት ጉዳይ አንዱ ነው፡፡ ደህንነቱ የተረጋገጠ የኮንስትራክሽን ስራ እንዲኖር ቁጥጥር በማድረግ ሂደት ትኩረት እንደሚሰጥ ቢነገርም ደህንነት በቁጥጥር ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ሁሉም የግንባታው ዘርፍ አካላት በየራሳቸው ትኩረት ሊያደርጉበት የሚገባ ነጥብ  ነው፡፡ 👷‍♀የግንባታ ሂደት ውስጥ የሰራተኞች ደህንነት እንዲጠበቅ በግንባታ ስራው ላይ የሚሰማሩት የመስክ ሰራተኞች በሙሉ ደህንነታቸው የተጠበቀ ሆኖ እንዲሰሩ የሚያስፈልጋቸውን የግል የአደጋ መከላከያዎችን  በማቅረብ ሰራተኞቹም የስራ ላይ ትጥቃቸውን በመጠቀም በስራ ወቅት የሚደርሱ አደጋዎችን መቀነስ ይቻላል፡፡ በህንጻ ግንባታ ሆነ በሌሎች ግንባታዎች ደህንነቱ የተጠበቀ በማድረግ በሰውም ሆነ በንብረት ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን መቀነስ ይቻላል፡፡ የህንጻ ግንባታዎች ላይ በተለይም የግንባታ ስራ የእቃ መስቀያ፣ መወጣጫዎች እንዲሁም ወደ መንገድ እና ወደ አጎራባች ህንጻዎች፤ መኖሪያዎች፣መተላለፊያዎች የሚወርዱ የግንባታ ተረፈ ምርቶች የግንባታ ግብዓቶች በሰው እና በንብረት ላይ ቀላል የማይባል አደጋ ያደርሳሉ፡፡ ሆኖም በእነዚህ አደጋዎች የሚፈጥሩትን ኪሳራ የግንባታ ጊዜ ማስታወቂያዎች መከላከያዎች በማድረግ እንዲቀነሱ ማድረግ ይቻላል፡፡ 🚧በግንባታ ስራ ላይ የተሰማሩ ሙያተኞች ወደስራ ቦታቸው ሲገቡ አስፈላጊውን የደህንነት መጠበቂያ ባለማድረጋቸው የሚደርሱ የአካል እና የመንፈስ ስብራቶች ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ የራስ (የአናት) መከላከያ ቆብ፣ ጓንት፣ አስፈላጊ የደህንነት ጫማዎች፣ የመለያ አልባሳት ወ.ዘ.ተ ለደህንነት ዓላማ የተዘጋጁ ቁሶች እንደመሆናቸው ቅድሚያ ለደህንነት በመስጠት መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ በቀላል የሚቀረፉ እና የሚስተካከሉ ጉዳዮች በብዙ ዋጋ የሚያስከፍሉ እንዳይሆኑ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ግንባታ ዘርፈ ብዙ የሆኑ ጥቅሞች ቢኖሩትም በግንባታ ወቅት የሚደርሱ ኪሳራዎች ደግሞ በግለሰብ በማህበረሰብና በሀገር ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ ቀላል የሚባል ባለመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ ታሳቢ ቢያደርገውና ቅድሚያ ለደህንነት በማለት የመጀመሪያውን እርምጃ ለደህንነት ማድረግ ይኖርበታል፡፡                                            (ኢኮባ)
Show more ...
11 680
12
የግንባታ ላይ አረንጓዴ ስፍራ ህግ በ100 ሜትር ካሬ ይዞታ ላይ 2 በ2 ሜትር ስፋት ያለው ከግንባታ ነጻ መሬት እንዲኖር የሚደነግገው ህግ ጽሁፍ ተያይዟል።
11 360
44
Ads❗❗ አንድ ቀን ብቻ ቀረው‼️ ቴሌግራም ወደ Business app እየተቀየረ ነው፣Dogs mining ሊያበቃ አንድ ቀን ብቻ ቀረው፣መጪው August 14 ቴሌግራም የተመሰረተበት እለት ነው፣ስለ Dogs airdrop አዲስ ነገር አለ ተብሏል፣ ከስር ባለው ሊንክ task ስሩ👇👇👇
3 955
2
👉August 14 የቴሌግራምን birthday ምክንያት በማድረግ ትልቅ ነገር እንዳለ በ official ገፃቸው ተናግረዋል። 🚨 በብዙ መረጃዎች ላይ 100,000 dogs እየተገመተ ያለው ከ300$ እስከ 500$ ነው 🥶 እንስካሁን ያልጀመራችሁ ጥቂት ቀናት አላቹ task ስሩ።
2 536
6
አስደሳች ዜና በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ ለተሰማራችሁ ባለሙያዎች፡፡ አዲስ ኮስት ኤስቲሜተር ይባላል፡፡ ዌብ ሳይቱ ይግንባታዎትን መረጃ ከእርስዎ በመዉሰድ ጥንቅቅ BOQ በኤክሴል አዘጋጅቶ ይሠጥዎታል፡፡ አጠቃቀሙ በጣም ቀላል ሲሆን አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጋችሁ፣ የኢሜል አድራሻ ብቻ ነዉ፡፡ አሁኑኑ በነጻ ይሞክሩት፡፡ ✨ጥቅሞቹ 📌የተሟላ የዋጋ ዝርዝር 📌ፈጣን እና ቀላል 📌ቶሎ ቶሎ የሚሻሻል የገበያ ዋጋ 💥ስራዎትን በጥራት እና በፍጥነት በማጠናቀቅ ደንበኛዎትን ያስደስቱ፡፡ For more information call NaN
8 693
48
Did you know? 💫The reasons for honeycomb in concrete: 1. Inappropriate workability of concrete. 2. Use of stiff concrete mix or the concrete is already set before placing. 3. Improper vibration of concrete in formwork. 4. Over reinforcement. 5. Use of larger size aggregates in excessive amounts. 6. Formwork is not rigid and watertight. 7. Concrete is poured from more than allowable height. 8. Congestion of steel is preventing the concrete to flow over all corners.
Show more ...
11 155
32
Watering the concrete with water after pouring: 👉 increases the strength of concrete and the durability of the building. 👉 reduces the permeability of concrete due to water evaporation. 👉 completes the cohesion and reaction of cement that continues for a period after pouring. ⚡️Watering the concrete with water after pouring is very important. It must be done for a period of at least one week, twice a day, to reach 70% of its resistance in a week.
8 393
26
አስደሳች ዜና በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ ለተሰማራችሁ ባለሙያዎች፡፡ አዲስ ኮስት ኤስቲሜተር ይባላል፡፡ ዌብ ሳይቱ ይግንባታዎትን መረጃ ከእርስዎ በመዉሰድ ጥንቅቅ BOQ በኤክሴል አዘጋጅቶ ይሠጥዎታል፡፡ አጠቃቀሙ በጣም ቀላል ሲሆን አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጋችሁ፣ የኢሜል አድራሻ ብቻ ነዉ፡፡ አሁኑኑ በነጻ ይሞክሩት፡፡ ✨ጥቅሞቹ 📌የተሟላ የዋጋ ዝርዝር 📌ፈጣን እና ቀላል 📌ቶሎ ቶሎ የሚሻሻል የገበያ ዋጋ 💥ስራዎትን በጥራት እና በፍጥነት በማጠናቀቅ ደንበኛዎትን ያስደስቱ፡፡ For more information call NaN
14 561
113
8 289
3
ዜና ዕረፍት! የዝነኛው ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ባለቤት ሲሞን ፔትሮ ሳሊኒ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ በአገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ብሔራዊ እና ግዙፍ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በማከናወን ዝናን ያተረፈው ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ባለቤት በ92 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። እኚህ ግለሰብ 1.5 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሀብት እንዳላቸው የፎርብስ መጽሔት መረጃ ያሳያል።
10 043
14
የቤት ዋጋ እንዴት ሊቀንስ ይችላል? "ቤት አትግዙ " የሚል የሶሻል ሚዲያ ቻሌንጅ የማከብረው ወዳጄ ልኮልኝ ተመለከትኩ። አላማው በደምሳሳው ቤት ውድ ስለሆነ እስኪቀንስ ድረስ አትግዙ የሚል ነው...ይሄ ብዙም ውጤታማ ሊሆን የማይችል ቻሌንጅ እንደሆነ ቢታወቅም ሀሳቡ ግን የሚበረታታ  አይደለም ምክንያቱም ስሁት ነው። የሪል እስቴት ዘርፍን በቅጡ ካለመገንዘብ የመጣ ቤት ተወዷል ብሎ ለውድነቱም አልሚዎችን ብቻ ተወቃሽና ተከሳሽ ለማድረግ የታሰበ የችግሩን መሰረት ያልተረዳ ነው።  እስኪ የዘርፉን አሰራርና ችግሩን እንድንረዳ ስለ ሪል እስቴት ኢንቨስትመንት ዋና ተዋናዮችና አስተዋጽኦዋቸው ጥቂት እንበል።  ሀ) ባለድርሻ አካላትና ድርሻዎቻቸው የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት አምስት ዋና ዋና ባለድርሻ አካላት አሉት። የሀገራችንን ሁኔታ ታሳቢ አድርገን ስናቀርበው ከዚህ በታች የተገለጸውን ሊመስል ይችላል:- ፩) አልሚ (Developer) :- ስራ ፈጣሪ ነው፣ መሬትን ወደ ውጤታማ የሆነ ተፈላጊ የመኖሪያ ስፍራ በመቀየር ትርፍን የሚያገኝ መላ ፈጣሪ ነው፣ የገንዘብ አምጪ፣ የኪሳራሃላፊነት ወሳጅ፣ ቀጣሪ ሲሆን ዓላማው የገንዘብ ትርፍ ማግኘት፣ የቤት ችግር መቅረፍ ቢዝነሱ ያደረገ፣ ዘላቂ ንብረት ማፍራት፣ ጥሩ ስም መገንባት ... ፪) መንግስት(public organization):- መንግስት ዜጎች ቤት እንዲያገኙ የተለያዩ ፖሊሲዎችንና መመሪያዎችን ያወጣል፣ ለቤት ልማት የሚሆን መሬት ያቀርባል፣ የግንባታ ሂደቱን ይከታተላል፣ የግብይት ሂደቱን ይቆጣጠራል.... በሪል እስቴት ልማት ውስጥ የመንግስት ዋና ፍላጎት  የልማቱ ሂደት በስኬት ተከናውኖ   ዜጎች ቤት እንዲያገኙ ማድረግ፣  የህዝብ ሃብት የሆነው መሬት በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ .... ፫) ካፒታል ማርኬት:- ይህ ለግንባታም ሆነ ለቤት ገዢዎች ብድር የሚሆን የገንዘብ አቅርቦትን የሚያቀርቡ ባንኮችንና ሌሎች ወደፊት የሚመጡ የገንዘብ አቅርቦት የሚሰሩ ተቋማት ሲሆኑ ተሳትፏቸውም ለልማቱና ለቤት ገዢዎች ገንዘብ ማቅረብና ከልማት ሂደቱ ማትረፍ ነው። ፍላጎታቸው ኢንቨስትመንቱ አዋጭ መሆኑን ማረጋገጥ ነው። ፬) የቤት ገዢዎች (ተከራዮች) (ደንበኞች):- ዋና ፍላጎታቸው ለመኖር በቂ የሆነ ፣ በጊዜው ተጠናቅቆ መረከብ፣ በቂ ስፋት ያላቸው መገልገያ ክፍሎች ፣ በተመጣጣኝ ዋጋ ቤት ማግኘት ሲሆን። የቤት አልሚው ይህንን የቤት ገዢዎችን አቅምና ፍላጎት በገበያ ጥናት አጥንቶ መገንባት ይጠበቅበታል። ፭) የተለያዩ ባለሙያዎች (Development Team ) :- የሪል እስቴት ዘርፍ ብዙ ሙያዎችን የሚጠቀም ዘርፍ ነው። ለምሳሌ አርክቴክቶች፣ መሃንዲሶች፣ ገንቢዎች፣ የግብይት ሂደት ውስጥ ያሉ ባለሙያዎች፣ የፋይናንስ፣ የባንኪንግ ፣ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ባለሙያዎች፣ IT ባለሙያዎች፣ የህግ ባለሙያዎች ወዘተ.... ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው ። ባለሙያዎቹ በግልም በህብረትም በየሙያቸው ያለውን ከፍተኛና ፈጠራ የተካተተበት የደንበኞችን  ፍላጎት መሰረት ያደረገ ውጤት እንዲመጣ የማድረግ ሃላፊነት አለባቸው። ለ) ቤት ዋጋ እንዲቀንስ የሚጠበቅባቸው አስተዋጽኦ የሪል እስቴት ልማትና ግብይት የተሳካ እንዲሆን ከላይ የተዘረዘሩት ባለድርሻ አካላት የሚጠብቃቸውን ያለማጓደል ሊያበረክቱ ይገባል። ለምሳሌ :- ፩) መንግስት ለአልሚዎች መሬት በቅናሽና በብዛት ካቀረበ፣  የዲዛይን ማጽደቅና ክትትል ስራውን ካሳለጠ፣ ግብይቱ የሚመራበት መመሪያና ግብይቱን የሚመራ  አካል ሰይሞ በስርዓት እንዲመራ ካደረገ፣ በርካታ ቤቶችን ለሚገነቡ አልሚዎች የግንባታ  ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ  ካደረገ። ፪) የገንዘብ አቅራቢ ተቋማት ለአልሚዎችና ለቤት ገዢዎች በቂ የሆነ የገንዘብ አቅርቦት ካደረጉ ፫) ቤት ገዢዎች ጠንክረው ሰርተው ቁጠባን ባህላቸው ቢያደርጉና እቅም ከፈጠሩ ፬) ባለሙያዎች ገበያውንና የቤት ገዢዎችን አቅምና ፍላጎት ያገናዘቡ ቤቶች የሚገነቡበትን ዲዛይን፣ ወጪ ቀናሽ የግንባታ ቴክኖሎጂ ፣ የአከፋፈል ስርዓት በጥናት ላይ በተመሰረተ ሁኔታ ካዘጋጁ ፭) አልሚዎች ዘርፉን በእውቀት በባለሙያዎች እንዲመራ ካደረጉ ሐ) መውጫ በምሳሌ ነገር ግን ከአምስቱ  አንዱ ሲያጎድል ዘርፉ ውጤታማ እንዳይሆን ሊያደርግ ይችላል በሌሎቹ አካላት ላይም ተጽዕኖን ያሳድራል ። ለምሳሌ :- ባለሙያዎች ገበያውን ያላገናዘበ ውድ ቤቶች ንድፍ ቢሰሩና የሰሩትም ቢገነባ  ቤት ገዢዎች ሊገዙት አይችሉም፣ ካልተሸጠ ባንኮች ያበደሩት ብር በወቅቱ አይመለሰም፣ የቤት ችግርን ስለማይቀረፍ መንግስት ላይ ተጽዕኖ ይፈጥራል ከልማቱ ማግኘት የነበረበትን ገቢ ያሳጣል፣ አልሚውም ይከስራል... ስናጠቃልለው የቤት ዋጋ ሊቀንስ የሚችለው በአልሚዎች ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ከላይ የተጠቀሱት አካላት የተናበበ የጋራ ተሳትፎ ሲኖር ብቻ ነው። በ ደሳለኝ ከበደ (አቶ ደሳለኝ ከበደ ሲቪል መሀንዲስ፣ ስራ ተቋራጭ፣ አሰልጣኝ እና ጸሀፊ ሲሆኑ በግንባታው ዘርፍ ላይ ሰፊ ተሞክሮ ያላቸው ባለሙያ ናቸው)
Show more ...
11 338
23
Last updated: 11.07.23
Privacy Policy Telemetrio