Best analytics service

Add your telegram channel for

  • get advanced analytics
  • get more advertisers
  • find out the gender of subscriber
Category
Channel location and language

audience statistics TIKVAH-SPORT

209 673+128
~41 032
~33
22.33%
Telegram general rating
Globally
5 015place
of 78 777
26place
of 396
In category
104place
of 1 121

Subscribers gender

Find out how many male and female subscibers you have on the channel.
?%
?%

Audience language

Find out the distribution of channel subscribers by language
Russian?%English?%Arabic?%
Subscribers count
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

User lifetime on the channel

Find out how long subscribers stay on the channel.
Up to a week?%Old Timers?%Up to a month?%
Subscribers gain
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

Since the beginning of the war, more than 2000 civilians have been killed by Russian missiles, according to official data. Help us protect Ukrainians from missiles - provide max military assisstance to Ukraine #Ukraine. #StandWithUkraine
#Update የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ከኔዘርላንዳዊው አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ጋር የፊኖርዱን ምክትል አሰልጣኝ ሲፕኬ ሁልሾፍ እና ፐርፎርማንስ ሀላፊውን ሩበን ፒተርስ እንደሚያስፈርሙ ተገልጿል። አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ብዙ የካሳ ክፍያ የተከፈለባቸው የምንግዜም ውዱ ኔዘርላንዳዊ አሰልጣኝ መሆን እንደቻሉም ተነግሯል። ሊቨርፑል ለአሰልጣኙ የውል ማፍረሻ ካሳ ከ 13-15 ሚልዮን ዩሮ ለፊኖርድ ለመክፈል መስማማታቸው ተገልጿል።     
1
0
ሊቨርፑል አሰልጣኝ ለመሾም ተስማማ ! የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ኔዘርላንዳዊውን አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በአሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ምትክ በሀላፊነት ለመሾም ከፊኖርድ ከስምምነት መድረሳቸው ይፋ ሆኗል። ሊቨርፑል ለአሰልጣኙ ውል ማፍረሻ ካሳ ያቀረበው ዘጠኝ ሚልዮን ዋጋ ውድቅ ሆኖበት እንደነበር የሚታወስ ሲሆን አሁን ላይ ክለቦቹ ሙሉ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል። የ 45ዓመቱ አሰልጣኝ አርኔ ስሎት አሁን የኔዘርላንድ ሊግ ሲጠናቀቅ ሊቨርፑል መቀላቀል እንደሚችል ተገልጿል።     
7 052
15
አል ሂላል መሪነቱን አጠናክሯል ! በሳውዲ አረቢያ ሮሸን ሊግ የሀያ ስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የሊጉ መሪ አል ሂላል አል ፋቴህን 3ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነቱን ማጠናከር ችሏል። ለሊጉ መሪ አል ሂላል የማሸነፊያ ግቦችን ሚሼል ፣ ኔቬስ እና አል ቡላሂ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል። አል ሂላል በአንድ የውድድር አመት ሀያ ስድስት ጨዋታዎችን በማሸነፍ ብዙ ጨዋታዎች ያሸነፈው ክለብ መሆን ችሏል። አል ሂላል በሳውዲ አረቢያ ሊግ ታሪክ በአንድ የውድድር አመት ሰማንያ ነጥቦችን መሰብሰብ የቻለ ቀዳሚው ክለብ ሆኗል። ሩበን ኔቬስ በውድድር አመቱ በሁሉም ውድድሮች ለአል ሂላል ባደረጋቸው አርባ ሰባት ጨዋታዎች ሀያ አንድ የግብ አስተዋጽኦ ማድረግ ችሏል። የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 1️⃣ አል ሂላል :- 80 ነጥብ 2️⃣ አል ናስር :- 68 ነጥብ 3️⃣ አል አህሊ :- 52 ነጥብ 4️⃣ አል ታዎን :- 51 ነጥብ     
Show more ...
25 457
3
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ማደጉን አረጋገጠ ! የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ አንድን እየመራ የሚገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወደ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል። ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ኦሮሚያ ፖሊስ ነጥብ መጣሉን ተከትሎ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አምስት ጨዋታዎች እየቀሩት ከወዲሁ ወደ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ማደግ ችሏል። ባለፈው አመት ወደ ታችኛው ሊግ የወረደው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከአንድ አመት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገሪቱ ትልቅ ሊግ መመለሱን ማረጋገጥ ችሏል። ምንጭ :- የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን     
33 305
3
ፖቼቲኖ ከክለቡ ባለቤቶች ጋር መነጋገር እንዳቆሙ ገለፁ ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋና አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ባለፉት የተወሰኑ ወራት ከክለቡ ባለቤቶች ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተው እንደማያውቁ በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል። የክለቡ ባለቤቶች ለመጨረሻ ጊዜ አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖን ያናገሯቸው ከሊቨርፑል ጋር በዌምብሌይ በነበራቸው የካራባኦ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ ወቅት መሆኑ ተገልጿል። " ከባለቤቶቹ ጋር ባለፉት ወራት መልዕክት ተለዋውጬ አላውቅም ፣ የምንገናኘው በስፖርቲንግ ዳይሬክተሩ በኩል ነው ነገርግን ምንም የተቀየረ ነገር የለም።"ሲሉ ፖቼቲኖ ተናግረዋል።     
32 379
0
ኤሪክ ቴንሀግ ደጋፊዎች ራሽፎርድን እንዲደግፉ ጠየቁ ! የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የቡድኑ የፊት መስመር አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ ወደ አቋሙ እንዲመልስ ደጋፊዎች ከጎኑ እንዲቆሙ ጥሪ አቀርበዋል። " ራሽፎርድ እርዳታ ያስፈልገዋል " ያሉት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ እሱ ባለፈው አመት ድንቅ ነበር እሱን ሁሉም ሰው መርዳት አለበት ባለፈው አመት የነበረበት ደረጃ ላይ እስኪመለስ ማገዝ አለብን።ሲሉ አሳስበዋል። ማርኮስ ራሽፎርድ በዚህ አመት እያሳየ በሚገኘው ጥሩ ያልሆነ የውድድር አመት ምክንያት ትችቶች እየደረሱበት የሚገኙ ሲሆን ዛሬ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ቅሬታውንም ገልጿል። ራሽፎርድ በዚህ አመት ባደረጋቸው አርባ ጨዋታዎች ስምንት ግቦች አስቆጥሮ አምስት አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።     
33 158
5
" ወደ ጨዋታ ስሄድ የዳኛውን ማንነት አላውቅም " ጋርዲዮላ የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ለሚያደርጓቸው ጨዋታዎች የሚመደቡ ዳኞችን የሚያውቁት ሜዳ ላይ መሆኑን ገልጸዋል። " ወደ ጨዋታ ሴሄድ ዳኛው ማን እንደሆነ በጭራሽ አላውቅም ይህንን በማጣራት ጊዜዬን ማቃጠል አልፈልግም ስለ ዳኞች ምንም ጊዜዬን አላጠፋም።"ሲሉ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል። የእሁድ ተጋጣሚያቸው ኖቲንግሃም ፎረስት ጋር " ሁልጊዜም የሚደንቅ ድባብ አለ " የሚሉት ፔፕ ጋርዲዮላ እነሱ ላለመውረድ ሲፎካከሩ ደግሞ ከፍተኛ ይሆናል በማለት ተናግረዋል። ቢሆንም እኛ እንደዚህ አይነት ድባቦችን ለምደናል የሚሉት ፔፕ ጋርዲዮላ " ደጋፊያቸውን እና ስታዲየሙን ለመጠቀም ይሞክራሉ እኛም ለማሸነፍ ነው የምንገባው " ሲሉ ተደምጠዋል።     
31 713
0
" ትልቁ ተቀናቃኛችን እንዲያሸንፈን አንፈቅድም " ፖስቴኮግሉ የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ዋና አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ ስለ ሰሜን ለንደን ደርቢ አስፈላጊነት ጠንቅቀን እናውቃለን በማለት ከጨዋታው በፊት በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል። " ትልቁ ተቀናቃኛችን እንዲያሸንፈን አንፈቅድም " የሚሉት አንሄ ፖስቴኮግሉ የሰሜን ለንደን ደርቢን አስፈላጊነት በደንብ ተገንዝበናል በማለት ተናግረዋል።     
30 761
4
የሲቲ ክስ ጉዳይ በቅርቡ ይታያል ተባለ ! ማንችስተር ሲቲ የፕርሚየር ሊጉን የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ህግ ጥሰዋል በሚል ከዚህ በፊት ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ይታወቃል። አሁን ላይ የማንችስተር ሲቲ የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ህግ ጥሰት ክስ ጉዳይ የሚታይበት ቀን መቃረቡን የፕርሚየር ሊጉ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሪቻርድ ማስተርስ አሳውቀዋል። ዋና ስራ አስፈፃሚው የተቆረጠው ቀን ይህ ነው ባይሉም " ማንችስተር ሲቲ ላይ የቀረቡት 115 ክሶች በቅርቡ መታየት ይጀምራሉ።"ሲሉ ተናግረዋል።     
33 215
17
" የዋንጫ ፉክክሩ ውስጥ ነን " አርቴታ የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው አሁንም በዋንጫ ፉክክሩ ውስጥ መኖሩን በመግለፅ ቡድኑ ሙሉ ትኩረቱን ቀሪ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ላይ እንዲያደርግ አሳስበዋል። " እኛ አሁንም ፉክክሩ ውስጥ እንገኛለን " ያሉት ሚኬል አርቴታ ራሳችን ላይ ትኩረት ማድረግ እና አስፈላጊውን ነገር አድርገን ቀሪ ጨዋታዎችን ማሸነፍ አለብን በማለት ተናግረዋል። " ማንችስተር ሲቲ ትላንት ምሽት አሳማኝ በሆነ መንገድ ማሸነፍ እንደሚችሉ ያስመሰከሩበት ሌላ ጨዋታ ነበር ይህንን እኛ መቆጣጠር አንችልም።" አርቴታ ከረጅም ጉዳት የተመለሰው ተከላካዩ ጁሪያን ቲምበር የእሁዱ ጨዋታ እንደሚፈጥንበት የገለፁት አርቴታ በጨዋታው መሰለፉ ነገ እንወስናለን ብለዋል።     
33 978
3
ቴንሀግ ጋዜጠኞች እንዳይጠይቋቸው ከለከሉ ! የማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በነገው የበርንሌይ ጨዋታ ዙሪያ በአሁን ሰዓት እየሰጡ በሚገኘው ጋዜጣዊ መግለጫ የተወሰኑ ሚዲያዎች ጥያቄ እንዳያቀርቡ መከልከላቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ጥያቄ እንዳይጠይቋቸው የከለከሏቸው " MEN " ፣ " THE SUN " እና " Mirror " የተባሉት መገናኛ ብዙሃን መሆናቸው ተገልጿል። ማንችስተር ዩናይትድ ከዚህ በፊት የተወሰኑ መገናኛ ብዙሃን የክለቡን ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይከታተሉ አግዶ እንደነበር አይዘነጋም።     
34 019
3
ቶተንሀም ተጨዋቾቹ ወደ ሜዳ ይመለሳሉ ! ቶተንሀም እሁድ ከአርሰናል ጋር በሚያደርገው የሰሜን ለንደን ደርቢ ጨዋታ በጉዳት ላይ የነበሩ ተጨዋቾቹ እንደሚመለሱለት አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ አረጋግጠዋል። ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሪቻርልሰን እና ፔድሮ ፖሮ ለጨዋታው ዝግጁ መሆናቸውን አሰልጣኙ አስታውቀዋል።     
34 369
5
ኮል ፓልመር ወደ ቡድኑ ይመለሳል ! የሰማያዊዎቹ የፊት መስመር ተጨዋች ኮል ፓልመር ካጋጠመው ህመም በማገገም ወደ ልምምድ መመለሱን አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ አሳውቀዋል። ቼልሲ ነገ ምሽት ከአስቶን ቪላ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ወደ ሜዳ ይመለሳል ብለው እንደሚጠብቁ አሰልጣኙ አረጋግጠዋል። " ፓልመር ቀልፍ ተጨዋቻችን ነው " ያሉት ፖቼቲኖ ያለ እሱ ጥሩ እንዳልሆንን እና እንደምንቸገር አሳይቶናል ይህ ልንደብቀው የማንችለው እውነታ ነው ብለዋል። በሌላ በኩል ራሂም ስተርሊንግ እና ካርኔይ ቹኩሜካ ጉዳት እንዳጋጠማቸው እና የህክምና ምርመራ እንደሚደረግላቸው ክለቡ አሳውቋል።     
33 363
3
ባየር ሙኒክ ተጨዋቹ ወደ ሜዳ ይመለሳል ! የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ ቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ ከሪያል ማድሪድ ጋር በሚያደርገው የሻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የወሳኝ ተጫዋቹን ግልጋሎት እንደሚያገኝ አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ገልጸዋል። በጨዋታው ጀርመናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ስርጅ ግናብሪ ዝግጁ እንደሚሆን የገለፁት አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል " ተጫውቶ ግብ እንደሚያስቆጥር እርግጠኛ ነኝ " ብለዋል። በሌላ በኩል ሌሮይ ሳኔ ለማክሰኞው ተጠባቂ ፍልሚያ መድረሱን እየተከታተሉ እንደሚገኙ የገለጹት አሰልጣኙ ለጨዋታው መድረሱ አጠራጣሪ ነው በማለት ተናግረዋል።     
33 755
2
" የሊጉ ፉክክር በሲቲ አርሰናል መካከል ነው " ክሎፕ የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በነገው ዕለት ከዌስትሀም ዩናይትድ ጋር ከሚያደርጉት ጨዋታ በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገው ነበር። አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በቆይታቸው ምን አሉ ? - " ከኤቨርተን ሽንፈት በኋላ አይነት የተበሳጨሁበትን ጊዜ አላስታውስም ጥሩ ጨዋታ አልነበረም የተጫወትነው ራሴን እወቀሳለሁ። - የፕርሚየር ሊጉ የዋንጫ ፉክክር በአርሰናል እና ማንችስተር ዩናይትድ መካከል እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ እነሱ ሁለት ጨዋታ ይሸነፋሉ ብዬ አልጠብቅም። - የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ቦታን ለማረጋገጥ አሁንም ነጥቦች ያስፈልጉናል ሁሉም ሰው እዚህ ደስተኛ አይደለም። - አሰልጣኝ ምርጫ ውስጥ አልገባም ነገርግን የአርኔ ስሎትን ብዙ ነገሮች እወዳለሁ ትክክለኛው ሰው ከሆነ ጥሩ ነው ቡድኑ የሚጫወትበትን መንገድ አደንቃለሁ ጥሩ ሰው ነው። - ሊቨርፑልን ማሰልጠን የአለም ምርጡ ስራ ነው ይህ የአለም ምርጡ ክለብ ነው ምርጥ ቡድን እና ምርጥ ሰዎች እዚህ አሉ።" ሲሉ ተደምጠዋል።     
Show more ...
33 430
2
✝🎁እንኳን አደረሳችሁ✝🎁 📲 ስልክዎትን ለመቀየር ወይም አዲስ ለመግዛት አስበዋል 🤔?   🆕 አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል📱ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ 📌 📞  NaN 📩 inbox 📍አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ 📨 ክፍለ ሀገር ላላቸሁ ደንበኞችቻችንም በ DHL መላክ ጀምረናል
31 252
2
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የለንደን ደርቢ ጨዋታ💥 ⚽️ 4 ጨዋታዎች ብቻ የቀሩት አርሰናል ለዓመቱ ለመጨረሻ ጊዜ የለንደን ደርቢውን ቶተንሃም እሁድ ከሰዓት 10፡00 ሰዓት ይገጥማል! ይህንን አጓጊ ፍልሚያ በቀጥታ በSS Liyu በአማርኛ ኮሜንትሪ በሜዳ ፓኬጅ ይመልከቱ! 🤔 አርሰናል እያሳየ የለውን ብቃት መቀጠል ይችላል? የእናንተን ግምት ያጋሩን   👉 ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ለመከታተል ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ! 👉 የዲኤስቲቪን ዲኮደር በ1,999 ብር ከ1 ወር ነፃ የሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ። የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ! 👇
33 220
1
" በአርሰናል ጨዋታ ወደ አቋማችን እንመለሳለን " ሰን የቶተንሀሙ የፊት መስመር ተጨዋች ሰን ሁንግ ሚን ቡድናቸው በቅርቡ ካጋጠመው ከባድ ሽንፈት በእሁድ የአርሰናል ጨዋታ ለማገገም ጠንካራ ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል። ከሳምንት በፊት በኒውካስል ዩናይትድ 4ለ0 የተሸነፉት ቶተንሀሞች ከሁለት ሳምንት እረፍት በኋላ እሁድ የአመቱን ትልቅ ጨዋታ ከምንግዜም ተቀናቃኛቸው አርሰናል ጋር ያደርጋሉ። ቡድኑ ምላሽ ለመስጠት ጥሩ እድል ማግኘቱን የሚገልጸው ሰን " በኒውካስል ጨዋታ ተቀባይነት የሌለው ውጤት እና እንቅስቃሴ ነበረን አሁን ለማገገም ዝግጁ መሆን አለብን። ብሏል። ሰን በሊጉ አርሰናል ላይ ስድስት ግቦችን ማስቆጠር የቻለ ሲሆን አሁንም ይህንን ማስቀጠል እንደሚችል ሙሉ እምነት እንዳለው ገልጿል።     
38 588
13
የሙኒክ ደጋፊዎች ቱሄል እንዲቀጥል ድምፅ አሰባሰቡ ! የባየር ሙኒክ ደጋፊዎች ጀርመናዊው አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል በሚቀጥለው የውድድር አመት በክለቡ አሰልጣኝነቱ እንዲቀጥል ድምፅ እያሰባሰቡ እንደሚገኙ ተገልጿል። " አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል እንዲቆይ እንፈልጋለን ራልፍ ራግኒክ እንዲመጣ አንፈልግም " በሚል ርዕሰ በቀረበው የድምፅ ማሰባሰቢያ አቤቱታ ላይ 10,000 የክለቡ ደጋፊዎች ድምጽ መስጠታቸው ተገልጿል። የኦስትሪያ ብሔራዊ ቡድንን በማሰልጠን ላይ የሚገኙት ጀርመናዊው አሰልጣኝ ራልፍ ራግኒክ ከቀናት በፊት ከባየር ሙኒክ ጋር ድርድር ላይ መሆናቸውን ተናግረው ነበር።     
39 473
5
ማርታ ከብሔራዊ ቡድኑ ራሷን ልታገል ነው ! ብራዚላዊቷ ታሪካዊ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማርታ በዚህ አመት ከብራዚል ብሔራዊ ቡድን ራሷን ለማግለል መወሰኗን በይፋ አሳውቃለች። " ከብራዚል ጋር የመጨረሻ አመቴ እንደሆነ አረጋግጣለሁ ጊዜው እንደደረሰ መረዳት አለብን " ያለችው ማርታ ውሳኔዋ ለብሔራዊ ቡድኑ ወጣት ተጨዋቾች እድል ለመስጠት ያለመ እንደሆነም ገልፃለች። ማርታባሳለፈቻቸው ወርቃማ የእግርኳስ ታሪክ ውስጥ በአምስት የኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ ሀገሯን የወከለች ሲሆን እ.ኤ.አ 2004 እና 2008 የብር ሜዳልያ ማሳካት ችላለች። ለሀያ አመታት ለእግርኳስ በሰጠችው ድንቅ ግልጋሎት ምክንያት ፊፋ ልዩ ሽልማት ያበረከተላት ማርታ በተጨማሪም ከ2025 ጀምሮ " ማርታ አዋርድ "የሚል የሴቶች ምርጥ ግብ የሚሸልም ዘርፍ እንደሚያካትት አሳውቋል።     
Show more ...
40 762
1
" በዋንጫ ፉክክሩ ሁሉም ነገር ሊፈጠር ይችላል " ጋርዲዮላ የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋር በዋንጫ ፉክክሩ ውስጥ የሚገኙት ማንችስተር ሲቲ እና አርሰናል እንደ ሊቨርፑል ሊገጥማቸው እንደሚችል ገልጸዋል። " በዋንጫ ፉክክሩ ሁሉም ነገር ሊፈጠር ይችላል ሊቨርፑል መመልከት ይቻላል ሁለት ጨዋታ ተሸንፈዋል ይህ በእኛ እና አርሰናል ላይም ሊደርስ ይችላል ማንም እርግጠኛ የሆነ የለም።"በማለት ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል። አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ በበኩላቸው ከምሽቱ ሽንፈት በኋላ " ማንችስተር ሲቲ ከአለማችን ምርጥ ቡድኖች አንዱ ነው ፣ ሽንፈቱ ይገባናል ስህተቶች ዋጋ አስከፍለውናል።"ብለዋል።     
39 425
0
iPhone 15 Promax •256GB = 147,000 Birr •512GB = 173,000 Birr Samsung 24 Ultra •256GB = 127GB Birr •512GB = 143,000 Birr Contact us : NaN NaN
8 709
1
📢 #አስደሳች ዜና ከዋናው! ዋናው ስፖርት ከዘመን ባስ ጋር በመተባበር በሀገራችን የተለያዩ ክፍለ ሀገራት ለሚገኙ ደንበኞቹ እስከ #ሚያዝያ ወር መጨረሻ የሚቆይ የስፖርት አልባሳት #ነፃ_የዴሊቨሪ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ሊያበስር ይወዳል። 📍 የመዳረሻ ከተሞች፦ 👉🏾 ድሬዳዋና ሀረር 👉🏾 ጅማና ቦንጋ 👉🏾 ሻሸመኔ፣ ሆሳዕናና ሀዋሳ 👉🏾 አርባምንጭና ወላይታ 👉🏾 ደሴ፣ ባህርዳርና ጎንደር 👉🏾 ደብረታቦር፣ ኮሶበር፣ ፍኖተሰላም 🚀 በሚቀርቦት የሀገራችን ክፍል ሆነው የሚፈልጉትን ዓይነት የስፖርት አልባሳትን በተለይም ከ #600_ብር ጀምሮ የሚሸጡ ማሊያዎቻችንን #በቀላሉ_ይዘዙን፣ ይህን ልዩ ዕድል ይጠቀሙ! 📍አድራሻችን:- ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት፣ አለም ገብሬ ህንፃ፣ 2ተኛ ፎቅ። 📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ። 👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WANAWSbot በኩል ይዘዙን። Instagram |Facebook | TikTok 🏅 ዋናው ወደፊት... @wanawsportwear
Show more ...
39 443
1
ማንችስተር ሲቲ ወሳኝ ድል አሳክቷል ! በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ተስተካካይ መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ከብራይተን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል። የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ፊል ፎደን 2x ፣ ኬቨን ዴብሮይን እና ጁሊያን አልቫሬዝ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል። እንግሊዛዊው ተጨዋች ፊል ፎደን በውድድር ዘመኑ ያስቆጠራቸውን የሊግ ግቦች አስራ ስድስት ማድረስ ችሏል። ፊል ፎደን በዘንድሮው የውድድር አመት ለማንችስተር ሲቲ በሁሉም ውድድሮች ባደረጋቸው ጨዋታዎች በሰላሳ አራት ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል። በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ? 2️⃣ ማንችስተር ሲቲ:- 76 ነጥብ 1️⃣1️⃣ ብራይተኖ :- 44 ነጥብ ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ? እሁድ - በርንማውዝ ከ ብራይተን እሁድ - ኖቲንግሃም ከ ማንችስተር ሲቲ     
Show more ...
51 648
9
90 '  ብራይተን 0 - 4 ማንችስተር ሲቲ                         ⚽ ዴብሮይን                         ⚽⚽ ፎደን                         ⚽ አልቫሬዝ     
16 507
2
75 '  ብራይተን 0 - 4 ማንችስተር ሲቲ                         ⚽ ዴብሮይን                         ⚽⚽ ፎደን                         ⚽ አልቫሬዝ     
16 886
3
57 '  ብራይተን 0 - 4 ማንችስተር ሲቲ                         ⚽ ዴብሮይን                         ⚽⚽ ፎደን     
49 289
4
57 ' ብራይተን 0 - 3 ማንችስተር ሲቲ                         ⚽ ዴብሮይን                         ⚽⚽ ፎደን     
16 383
0
እረፍት | ብራይተን 0 - 3 ማንችስተር ሲቲ                         ⚽ ዴብሮይን                         ⚽⚽ ፎደን     
47 523
20
33 ' ብራይተን 0 - 3 ማንችስተር ሲቲ                         ⚽ ዴብሮይን                         ⚽ ፎደን     
46 603
30
Last updated: 11.07.23
Privacy Policy Telemetrio