https://youtu.be/u5mFjeYJZqE?si=6PViluviN3kfWtVY
🔴አዲስ ዝማሬ‼️👉ሊስትሮዋ ዘማሪት ጽጌ ማርያም 🔸''እንዴት ልደብቀው?''🔸በእምባ የሚደመጥ🔸Zemarit Tsigemaryam Baye
🆂🆄🅱🆂🅲🆁🅸🅱🅴
በሊስትሮ ሥራ ለዘመናት እናቷን፣ እህቶቿንና ወንድሞቿን እያስተዳደረች በክራር በበገና ደግሞ ፈጣሪዋን ታመሰግነዋለች።የሊስትሮ ቦታዋ ክራር ይሰቀልባታል፤ዝማሬ ይዘመርበታል። ወዲህ የሰዎችን ጫማ እየሰፋች እያሳመረችም ወዲህ ለፈጣሪዋ በባህርዳር ጎዳና ክራሯን ስትደረድር ትደመጣለች። ተመስገን ተመስገን እያለችው ትውላለች። ዘማሪት ጽጌማርያም ባየ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ እግዚአብሔርን ማመስገን እንደሚገባ ማሳያ ናት።በሊስትሮ ቦታ ያልተወሰነው አገልግልቷ አሁን ደግሞ በራማ ቲዩብ ስፖንሰርነት ሙሉ ገቢው ለእርሷ መበርቻ እንዲውል አዲስ ዝማሬ ይዛ ቀርባለች።
''
እንዴት ልደብቀው
እንዴት ልደብቀው ጌታዬ አንተ ያረክልኝን
ቤቴ እንጀራ ባይኖር ሸሽገህ የምታጎርሰኝን
ባለቅስ እንኳን እንባ ባፈስ ዛሬ ፊትህ ቆሜ
የሃዘን አይደል የደስታ ነው ተሳክቶልኝ ሕልሜ
ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች ደግሞም ትሁን በምድር
የእለት እንጀራዬን አትንፈገኝ መጋቢዬ እግዚአብሔር
በከንቱ ነው የምጨነቀው
ላይቀር ሊሆን (መሆኑ አይቀር) ጌታዬ ያልከው
የሰማዩን ስሻ መንግስቱን
ይጨመራል የምድሩ ነገር
በለስ ባታፈራ ዘይት ባይኖር ከጎጆዬ አንዳች ነገር
ኤልሻዳዩ ጌታ ሁሉ ያለህ አንተ አለኸኝ አልቸገር
አባክኜ ያላዘንክብኝ
በጥፋቴ ያልጨከንክብኝ
ከኔ በላይ የምታስብ ለኔ
ምን አጉድለህ ያማሃል ልሳኔ
ማጎንበስ ማንባቴን ማቀርቀሬን ዝቅ ብዬ መራመዴን
ከሰው ጋር እየዋልኩ ሰው አላየው የተጎዳው ስሱን ልቤን
ከላይ ሆነህ ምትመለከት
የማትረሳ የእጅህን ፍጥረት
ያልተለየህ ያልራክ ከነፍሴ
አንተ አየኸኝ ሳትንቀኝ ሥላሴ
አንገቴን ሰብሬ በእግሬ መሃል ሳለቅስብህ እንደ ህጻን
ከኔ ጋራ ሆነህ አጠገቤ በኔ ሐዘን አንተ አዝነሃል
መቼ ይሆን መቼ ነው ስልህ
ለእምባዬ ጌታዬ መልስህ
በማለዳ ልከህ መልክተኛ
አዘመርከኝ ሆንክልኝ መጽናኛ
ግጥምና ዜማ
ዘማሪ ኢንጂነር ታዴዎስ አውግቸው
ድምጽ ቀረጻ እና ማስተሪንግ
ዘጎላ ዲጂታል ስቱዲዮ
ዘማሪ ዲያቆን ዘላለም ታከለ
ክራር: አንተነህ ተክለማርያም
መሰንቆ: አሮን በረከት
ዋሽንት:ዮናስ አስራት
ካሜራ: በረከት
ዘማሪ እንጂነር ታዴዎስ አውግቸው
ኤዲቲንግና ግራፊክስ
ዲያቆን መዝሙር ኤርሚያስ
አዘጋጅ: ራማ ቲዩብ
0928311773
Rama Production©2016
#mezmur #mezmurorthodox #ramatube
Contact us via telegram --@rama1621/0928311773
______________/Connect With Me On Social Media\_____________
► Telegram:➜@rama23
► Tiktok:➜@tadewos7
► Facebook:➜https://www.facebook.com/Rama-Tube-ll...
► Instagram:➜@tadewosawugchew
=========================================
Zemarit Tsige Maryam Baye songs are uploaded here with the singer’s full consent and all songs are produced by Rama Tube. © @tadewos23 has all exclusive rights for all materials in this video. All materials in this video are copyright protected. Unauthorized use, distribution and re-upload of this content are strictly prohibited.
All rights reserved to @tadewos23
Copyright ©2023: @tadewos23